SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
💥የሕንጻ ምድብ አወሳሰን

🚧በ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሰረተ ልማት ቅንጅት እና ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሰራር መመሪያ 1/2011 ክፍል 1፣ አንቀጽ ሁለት ሥር ባስቀመጠው መሰረት ሕንጻዎች በሦስት ምድብ ማለትም "ምድብ ሀ" ፣ "ምድብ ለ" እና "ምድብ ሐ" ተብለው ሊወሰኑ ይችላሉ።

🚧ምድብ "ሀ" ሕንፃ

▶️በሁለት የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ርቀት ከ7 ሜትር ወይም ከዚያ በታች የሆነ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ወይም ማናቸውም ከሁለት ፎቅ በታች የሆነ የግል መኖሪያ ቤት ነው።  

🚧ምድብ "ለ" ሕንፃ

▶️የኮንክሪት ወይም የብረት ወይም ሌሎች ስትራክቸራል ውቅሮች መካከል ያለው ከ7ሜትር  በላይ የሆነ ወይም ባለሁለት ፎቅና ከሁለት ፎቅ በላይ የሆነና በምድብ "ሐ" የማይሸፈን ሕንፃ ወይም "ምድብ "ሀ" የተመደበ እንደሪል እስቴት ያሉ የቤቶች ልማት ነው።

🚧ምድብ "ሐ" ሕንፃ

▶️የሕዝብ መገልገያ ወይም ተቋም ነክ ሕንፃ ፣የፋብሪካ ወይም የወርክ ሾፕ ሕንፃ ወይም ከመሬት እስከ መጨረሻው ወለል ከፍታ ከ12 ሜትር በላይ የሆነ ማናቸውም ሕንፃ ሲሆን፣ በዚህ መመሪያ የተካተቱትን ማስተካከያዎች ያካትታል።

🖱ይህ የሕንጻዎች ምድብ አንድ የመሬት ባለቤት በቦታው ላይ ያለውን የግንባታ ሁኔታ (የሕንጻ አይነት፣ ከመንገድ ወደቦታው ሊገባ የሚችል የመንግሥት መሰረተ ልማትን እና የመሳሰሉትን ለማየት ስለሚጠቅም ዲዛይን የሚሰሩ አማካሪዎች ይህንን መረጃ የሚያሳይ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ ከሦስት ወይም ስድስት ወር በላይ ጊዜ ያላለፈው የፕላን ስምምነት ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል።

https://t.me/ethioengineers1
👍20❤1
💥እየተገነባ ባለው ህንጻ የአፈር ክምር ተደርምሶ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሸዋ ሱፐርማርኬት አካባቢ    በመገንባት ላይ ባለ ህንጻ የአፈር ክምር ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል፡፡

ህይወቱ ያለፈዉና ጉዳት የደረሰበት ሰዉ  በዚሁ የህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የሟቹ ዕድሜ 37 ዓመት የተገመተ ሲሆን አስከሬኑን ከተጫነበት አፈር ለማዉጣት 1:30 ሰዓት ፈጅቷል ።
ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አደጋ የተከሰተበት የህንጻ ግንባታ ስራ የደህንነት መስፈርቶችን ያልጠበቀና አሁንም ለአደጋ ስጋት በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም  የሚመለከታቸዉ  አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ እሳስበዋል፡፡

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ከሶስት ቀናት በፊት በህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉ ይታወሳል።

የኮንትራክሽን ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ አስሪዎችም ሆነ ሙያተኞች አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎች ባለመከተል መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት ቢተላለፍም ተግባራዊ በአለመሆኑ  አደጋዉ እየተደጋገመ ይገኛል ብለዋል፡፡

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም


https://t.me/ethioengineers1
👍9🤔6❤3
✍️ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው  ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ:-

🚧አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው። 

✍️The reasons a building collapses can be due to
✔️poor structural design,
✔️poor compliance with specifications
✔️poor quality control
✔️faulty construction methodology foundation failure
✔️extraordinary loads and corruption. Natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

✍️በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል
☑️ poor structural design
☑️faulty construction
☑️poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

👉አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

#⃣ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1,በ Fatigue ና
2, Creep ነው

1,Fatigue
✔️ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
✔️አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

@ethioengineers1
👍18❤6🙏1
💥በስምንት ሰዓት ውስጥ 47 ሺህ ብሎኬት የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

በዱከም ከተማ በአንድ ፈረቃ ወይም በስምንት ሰዓት ውስጥ ብቻ 47 ሺህ የተለያዩ መጠን ያላቸውን ብሎኬቶችን የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ ተሰማ።

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/ተ/ግ/ማ በዱከም ከተማ ያቋቋመው ፋብሪካ በከፍተኛ ጥራት የሚያመርታቸውን የብሎኬት እና ቴራዞ ምርቶች ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ታውቋል።

የፋብሪካው ባለድርሻና ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ወንደሰን መንግሥቱ እንደገለጹት፣ ፋብሪካው  34 ሺህ ባለ (40*15*20 ሳ.ሜ)፣  እና 25 ሺህ ባለ (40*20*20 ሳ.ሜ)፣ ውፍረት/ስፋት ያላቸውን ብሎኬቶች የማምረት አቅም አለው፡፡

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ 99 በመቶ የአገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን
በመጠቀም ጥራት ያለው ምርት ማምረት የሚችል የግንባታ ግብአት አቅራቢ ፋብሪካ ነው።

የፋብሪካ ግምባታ እና ማሽን ተከላ 18 ወራትን ወራትን የፈጀ ሲሆን፣  ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይወጣበታል ተብሏል።

እንደ ፕሮጀክት ማናጀሩ ገለጻ፣ ፍላጎትን መሠረት አድርገን በተጨማሪ ፈረቃ ምርት ማምረት እንችላለን ብለዋል።

በተመሳሳይ የቴራዞ ማምረቻው በተለያየ ሞልድ በቀን ከ 2500 ካ.ሜ በላይ የሚሸፍን ከፍተኛ ጭነት መቋቋም የሚችሉ የወለል ንጣፎችን ማምረት እንደሚችል ታውቋል።

ፋብሪካው  ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ150 በላይ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።


https://t.me/ethioengineers1
👍25❤2👏1🤔1
💥ስለንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract)

-ንኡስ ተቋራጭነት(sub-contract) በፍትሀብሄር ህጉ አገላለጽ ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ ይባላል፡፡ ይሄውም ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በከፊል ለማስፈጸም ከአንድ ሶስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(2)) 
-ውሎችን ለሌላ መልቀቅ(Assignment) ደግሞ ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3201(1))
-ስለዚህ ንኡስ ተቋራጭነት የግንባታ ስራ ተቋራጮች ከአሰሪው ጋር ሊገነቡት ግዴታ የገቡበትን የግንባታ ስራ በከፊል ለሌላ ተቋራጭ በውል በሚያሰሩበት ጊዜ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ውሎችን ለሌላ መልቀቅ የሚባለውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡
-ንኡስ ተቋራጭነት ሁለት አይነት ነው፡፡በአሰሪው የሚታወቅ(Nominated sub-contracting) እና በአሰሪው የማይታወቅ(Non nominated sub-contracting)::ከውጤት አንጻር ተመሳሳይ ቢሆኑም ንኡስ ተቋራጭነቱን አሰሪው የፈቀደውና ያወቀው የሆነ እንደሆነ ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ከመዘግየት ቅጣት ነጻ ይሆናል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 3206)   
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩበት ክፍያ ከማን መጠየቅ ይችላሉ?
-ንኡስ ተቋራጮች ለሰሩት ስራ በውላቸው መሰረት ከዋናው ተቋራጭ ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡(የፍ/ህ/ቁ 1755፣1756) ምክንያቱም ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ህግ ነው፡፡(የፍ/ህ/ቁ1731)
-በተጨማሪም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3040 በአንድ የህንጻ ስራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ወይም ሰራተኞች የሰሩበትን ስራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሰሪው ለስራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሰሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን ለመጠየቅ መብት አላቸው በሚል ይደነግጋል፡፡ስለዚህ ከዋናው አሰሪ ላይም በቀጥታ ክፍያ ለመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡

https://t.me/ethioengineers1
👍19❤1
🦺በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ❗️❗️

#Ethiopia | ትላንት ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ዉሀ ታንከር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በመገንባት ላይ ያለ ባለሦስት ወለል የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ተደርምሶ የሰዉ ህይወት አልፏል።

አደጋዉ የደረሰዉ ትላንት ጥር 27 ቀን ከቀኑ 9:35 ሰዓት ሲሆን አደጋዉ ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ በተደረገ ፍለጋ ዛሬ ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ማምሻዉን የአንድ ሰዉ አስከሬን የተገኘ ሲሆን በአካባቢዉ የነበሩ ሰዎች የሰጡት መረጃ መነሻ በማድረግ የቀሪ የአንድ ሰዉ አስከሬን እየተፈለገ ይገኛል።

አደጋዉ የደረሰበት ቦታ የመኖሪያ ቤቶች ተጠጋግተዉ እየተገነቡ ያሉበት በመሆኑና የቦታዉ ሁኔታ ብረትና ፍርስራሾቹን ለማንሳት አስቸጋሪ ሁኔታ በመፈጠሩ አስከሬን በፍጥነት ለማግኘት አልተቻለም።

በአስከሬን ፍለጋዉ ሂደት የክፍለ-ከተማዉ አስተዳደርና የጸጥታ ሀይል አመራሮች እንዲሁም የአካባቢዉ ማህበረሰብ ከእሳት አደጋ ሰራተኞች ጋር በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

በሌላ በኩልም በከፍተኛ መጠን የሚገኘዉን ፍርስራሾቹን ለማንሳት የሚያስችል ሶስት ማሽነሪዎችን በድርጅቶች ትብብር ተደርጎ ፍለጋዉን እያገዙ ይገኛሉ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋዉ ከደረሰበት ከትላንት ከቀኑ 9:35 ሰዓት ጀምሮ በፍለጋ ላይ ናቸዉ።

አስከሬኑ የተገኘዉ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን አደጋዉ በደረሰበት ሰዓት በህንጻዉ ስር በስራ ላይ ነበረ።

በአዲስ አበባ በመሰል የኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ የዛሬዉን ሳይጨምር በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል።


https://t.me/ethioengineers1
👍10🤔8❤2
🪡 Post tension 

ከቃሉ ስንነሳ post - ድህረ ማለት ነው። concrete ከተሞላ በኋላ ብረቱን ስንወጥር post tension (ድህረ መወጠር) concrete ከመሞላቱ በፊት ደግሞ ሲወጠር pre-tension ይባላል።   ዛሬ ስለ post tension እናውጋ!

Post tension እዛው መስክ(site) ላይ የምናከናውነው የግንባታ ዘዬ ነው pretension ግን  በ precast ማምረቻ warehouseኦች ላይ ሚተገበር ነው።

በpost tension ጊዜ መጀመሪያ ብረት እናነጥፋለን(bottom bar) ኮለኖች አካባቢ lower reinforcement እናበጃለን ከዛም ኮለኖች አካባቢ punching shear reinforcement እናበጃለን (drop panel in exceptional case ካልሆነ አንጠቀምም) ከዛም chair bar (“ከበሌቶ”) ካረግን በኋላ strand እንዘረጋለን ከዛም በ side formwork በኩል  መወጠሪያ ብረቶቻችንን ካወጣን በኋላ anchorage እና grout vent እንዘረጋለን ከዛም እናጠብቃቸዋለን ከዛም top reinforcement (minimum reinforcement ለ shrinkage እና ለ temperature) ከዛም ኮንክሪት መሙላት ከዛም ያወጣነውን ቴንደን መወጠር ከዛም የተመዘዘውን መጠን መለካት ( measuring elongation) ከዛም የወጡትን የ strand ጫፎች መለካት ከዛም ክፍተቱን (void) በሲሚንቶ (cement screed) መሙላት።


https://t.me/ethioengineers1
👍32❤12👏1😍1
💥በመሀል አዲስ አበባ (ፒያሳ) የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አሁናዊ ገፅታ

https://t.me/ethioengineers1
👍11❤1
💥ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/

1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate)

• ከ 20% እስከ 30%  ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡

• ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡

• አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤ ዋስትናውን በሁኔታ ላይ የተመሠረተ ዋስትና ተአማኒነት ካለው ኢንሹራንስ ድርጅት እንዲያሲዝ ፈቅደው፤ ገንዘቡ በጋራ በተከፈተ ሂሣብ(አሠሪና ተቋራጭ) እንዲቀመሥ ተደርጎ በጋራ ፊርማ እንዲወጣ ያደርጋሉ፡፡

• የቅድሚያ ክፍያው ለሚሠራ ሥራ ከሚዘጋጅ ተከታታይ ክፍያዎች በሂደት ተቀንሶ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

2. ጊዜያዊ ክፍያ (Interim Payment Certificate)

• ለተሠራ ሥራ በየወቅቱ የሚዘጋጅና በአማካሪው ተረጋግጦ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡

• ይህ ክፍያ ስሙም እንደሚያመለክተው ጊዜአዊና ወደፊት የሚወራረድ ሂሣብ ነው፡፡

• አንድ ክፍያ ሲፈጸም የሂሣብ ስህተት ቢያጋጥም የሚቀጥለው ላይ ለማስተካክል የሚያስችል መንገድ አለው፡፡

3. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment)

• በሕጉ የአንድ ፕሮጀክት ክፍያ የሚባለው የመጨረሻ ክፍያ ነው፡፡

• በዚህ ግዜ አማካሪው ከመጀመሪያ ጀምሮ በተከታታይ የተፈጸመውን ጊዜአዊ ክፍያ ከመስክ በሚወስደው ስፍረ መሠረት አገናዝቦና መርምሮ የሚያጸድቀው ክፍያ ነው፡፡

• ክፍያው ከጸደቀ በኋላ ለመያዣ ከተያዘው ግማሹን ጨምሮ ለተቋራጩ እንዲከፈል ያዛል፡፡

• ግማሹ የመያዣ ገንዘብ ከአንድ ዓመት የዋስትና እና የጥገና ግዜ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ ሲፈጸም ይለቀቃል፡፡ በዚህ ግዜ የፕሮጀክቱም ሂሣብ ይዘጋል ማለት ነው፡፡

• የመያዣ ገንዘብ ሚባለው በመንግስት ሥራ ግዢ ደንብ መሠረት የተሠራው ሥራ 5% ሲሆን ጊዜአዊ ርክክብ ከተፈተመ በኋላ እስከ መጨረሻ ርክክብ የሚቆየው እና በመጨረሻ የሚለቀቀው ግማሹ 2.5% ነው፡፡

በክፍያ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ችግሮች

1. ወጥነት የሌለው የክፍያ መፈጸሚያ ምስክር ወረቀት ቅጽ
• ይህ ቅጽ በሐገር አቀፍ ደረጃ አንድ አይነት ቢሆን ተቋራጮች በሠሩበት ሁሉ አንድ አይነት ግንዛቤ ስለሚኖራቸው መደናገር አይኖርም፤ የሂሣብ ምርመራ ሥራንም ቢሆን ያቀላል፡፡
2. በባለቤት እና/ወይም አማካሪ ምክንያት የሚዘገይ ክፍያ
• የተቋራጩን የግዢ ዑደት ስለሚያሰናክል የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ይታወካል
• በጀት አጠቃቀም ላይ ችግር ይፈጥራል
• የሥራ ጥራት ያበላሻል
• ዋጋ ያንራል


https://t.me/ethioengineers1
👍26🙏4❤3