በርካታ ፊልሞች ላይ የምናውቀው ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ) ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።ለቤተሠቡና ለአድናቂዎቹ መፅናናቱት ይሰጥልን።
❤2
የዚ ሁሉ ጠንሳሽ አሜሪካ....
ከዚ ቀደም ፓቭል በኢንተርቪዉ ወደ አሜሪካ ሲያቀና በተደጋጋሚ FBI ሳይቀር ጫና ያደርግበት እንደነበር ገልፆ ነበር
አሜሪካውያኖቹ ቴሌግራምን መሰለል ይፈልጋሉ እያንዳንዱ ሶሻል ሚዲያ የተጠቃሚዎች መረጃ መሰለል ቢፈልጉም በተደጋጋሚ ጫና ቢያደርጉም ፓቭል ግን ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ጫናዎችንም በመቋቋም አሳልፏል ።
በተጨማሪም በቅርቡ አንድ የእስራኤል ተቃራኒ የሆነ ሃከር ከፍተኛ መጠን ያለው በእስራኤል ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ፋይሎችን ቴሌግራም ላይ አስቀምጦ ነበር ፤ ታዲያ የእስራኤል መንግስት ቴሌግራምን ያንን መረጃ ደርሳበት ማጣራት ወይም ስለላ ላድርግ ስትል ቴሌግራም የግለሰብ ዳታን አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ውድቅ አድርጎባታል ።
ቴሌግራም ለሁሉም ሀገራቶች ተመሳሳይ አካሄድ ነው ያለኝ የተጠቃሚዎች መረጃ አሳልፌ አልሰጥም ለረጅም አመታት ብሏል ። ነገር ግን በመጨረሻም ያው አሜሪካ አሜሪካም አይደለች ማታ ይዛዋለች.....አሁን ለፓቭል ሁለት ምርጫዎች እንዳሉት እየተነገረ ይገኛል ።
ያም ወይ ቴሌግራምን የአሜሪካ መንግስት ልክ በሌሎቹ ሶሻል ሚዲያዎች በተመሳሳይ መሰለል እንዲችሉ ሙሉ ፍቃዱን መስጠት ፤ አልያም ደግሞ ለአመታት በእስርቤት መቆየት !
ጥያቄያቸውን የማይቀበል ከሆነ ቴሌግራምን እስከማጣት ሊደርስ ይችላል ተብሏል ። ከዚ ሁሉ ጀርባ ያለው የአሜሪካ መንግስት እና ኔቶ ነው !!
#FreeDurov

❤5👍2
የጃኖ ኤፍኤምን የ24 ሰዓት ስርጭትን በቀጥታ ያድምጡ
https://www.zemaradio.com/station/jano-fm

ZemaRadio
Jano FM - Zema Radio
Jano FM is an Ethiopian entertainment radio station based in Addis Ababa, Ethiopia. The station provides music, talk shows, and cultural programming for listeners in Ethiopia and around the world through live online streaming.
Broadcasting and Content…
Broadcasting and Content…
የዜማ ራዲዮን ኦፊሻል የፌስቡክ ገጽ ላይክ ያድርጉ https://www.facebook.com/ZemaRadios
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
''ኤርትራ ሰራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቴ አሰብ ታስወጣ!'' የኢትዮጵያ መንግስት
የኤርትራ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት በመጣስ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ግልጽ ወረራ ፈጽሞብኛል ሲል የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የተጻፈውና ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ በተላከው በዚህ ደብዳቤ፣ የኤርትራ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት በመጣስ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ግልጽ ወረራ መፈጸሙንና እዛ ከሚገኙ በደብዳቤው ላይ በስም ካልተጠቀሱ ታጣቂዎች ጋር ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ በደብዳቤው ጠቅሷል።
"የሁለቱን ሀገራት የጋራ ብሔራዊ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ በላቀ የመከባበር ስሜት ለመመካከር ዝግጁ ነን" ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ፣ አሁን በኤርትራ በኩል የተከፈተው ትንኮሳ ግን በምንም መመዘኛ ቅቡልነት የሌለው መሆኑን በማብራራት "ኤርትራ ሰራዊቷን በአስቸኳይ እንድታስወጣና ለሰላማዊ ድርድር ዝግጁ እንድትሆን በይፋ እንጠይቃለን" ሲል በአጽንኦት ይጠይቃል።
ለግማሽ ምዕተ አመት ያህል ሁለቱም አገራት በማያባራ ግጭት ላይ እንደኖሩ የሚያብራራው ደብዳቤው ይህ አይነቱ የግጭት አዙሪት በውይይትና በዲፕሎማሲያዊ ጥረት እልባት ሊያገኝ የሚችልበት እድል እንዳለ በመግለጽ በኤርትራ በኩል በጎ ምላሽ ከተገኘ የኢትዮጵያ መንግስት ልዩነቶችን በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ያብራራል።
በኤርትራ መንግስት በኩል እስካሁን ለዚህ ደብዳቤ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

''በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም ተሰይሞ የነበረውን ትምህርት ቤት ስሙ ተቀየረ!''
በወላይታ ዞን የቦዲቲ መለስ ዜናዊ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተብሎ የተሰየመዉንና ለዓመታት ሲጠራበት የነበረዉን በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም በመሠረዝ የአካባቢዉ ተወላጅና የሀገር ባለውለታ ናቸዉ ባሏቸዉ በብርጋዲየር ጀነራል ጋጋ ኦልጁ(ዶ/ር) የሚል የስም ለውጥ ማድረጋቸዉን የቦዲቲ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት መሪ አላት ተብሏል'' ነገ መሪዎች ሲቀየሩም እንዲሁ እንደማይሆን ምን ዋስትና አለ አስብሏል፣ ምናልባትም ዛሬ በሕይወት የሌሉት የቀድሞዉ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሥልጣን ባይሆኑና ግን በሕይወት ቢኖሩ ይህ ይደረግ ነበር ወይ ተብሏል?

❤1
''ሰበር❗️ መንግስት ተጨማሪ ታክሶችን ሊጥል እንደሆነ ተሰማ!'' መንግስት የራሱን ወጪ ለመሸፈን ከድሀው ሕዝብ ላይ ለመቁረጥ የዘየደውም ነው ተብሏል።
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከደረጋቸው ለውጦች አንዱና በተፅዕኖው የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የሚነካው የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ነው።
የአለም የገንዘብ ድርጅትን ቅድመ ሁኔታዎች የተከተለውንና መንግስት “ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ” ሲል የጠራው ፕሮግራም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2019 ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በትግራዩ ጦርነት ሳቢያ ተጓትቶ የሁለተኛውና “የተሟላ” ነው የተባለው መርሀ ግብር በ2024 (ሐምሌ 2016) ተጀምሯል።
ይህን ማሻሻያ በተመለከተ የአለም የገንዘብ ድርጅት(IMF) ከሰሞኑ በሂደቱ ላይ ጥልቅ ግምገማ አድርጓል። ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በዝግ ባደረገው ውይይት የተነሱ ፍሬ ሐሳቦች፣ የተወሰዱ እርምጃዎችና ወደፊት የተያዙ ዕቅዶች ተዘርዝረዋል። የግምገማውንም ሪፖርት ዘለግ አድርጎ ፅፏል።
ዋዜማ ራድዮ ተመለከትኩት ባለው የIMF ሪፖርት መሰረት መንግሥት አዳዲስ ታክሶችን ለመጣል ተዘጋጅቷል። የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ ለIMF ዋና ዳይሬክተር ባለፈው ወር የጻፉት ደብዳቤም በዚህ የIMF ሰነድ ውስጥ ተካቷል፡፡
ደብዳቤው እንደሚለው መንግሥት ብዙ ዓይነት ታክሶችን ለመጣል እያሰበ ነው፡፡ ከእነዚህም አንዱ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ግብር ሪፎርም ነው፡፡ ክልሎችና ፌደራል መንግስት ይኼን ግብር በሚሰበስቡበት ሁኔታ ላይ በቅርቡ በፓርላማ ምክክር እንደሚደረግም ሰነዱ ይገልጻል፡፡ ይህም 0.2 ከመቶ ጂዲፒ ሊሸፍን ይችላል፡፡
የመንግሥት ገቢ ማሰባሰብን በተመለከተ፣ IMF ባዘዘው መሠረት መንግሥት ድጐማዎችን በማጠፍ፣ መሠረታዊ የአገልግሎት ታሪፎችን በሒደት ከፍ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት መንግሥት በነዳጅ፣ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌ፣ ማዳበሪያና ሌሎች የሚያደርገውን ድጐማ በማንሳት የመንግሥት ገቢን ሲያሳብጥ የሕዝቡን ኑሮ ግን አጐሳቁሏል፡፡
በዚህም በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ከድህነት ወለል በታች የወደቁ ዜጐች ቁጥርና በሴፍቲኔት የሚታቀፉ ዜጐች ቁጥር በከተማና በገጠር በእጥፍ ጨምሯል፡፡
መንግሥት የራሱን ወጪ ለመሸፈን ከሌለው ሕዝብ ለመቁረጥ የዘየደው ከፍተኛ የግብር ምጣኔዎችና አዳዲስ የታክስ አይነቶች የሕዝቡን ገቢ ከማዳከም ባለፈ የንግዱን ማኅበረሰብ ከድጡ ወደ ማጡ አድርሰዋል፡፡
Via:- ዋዜማ

Ethiopian News 24 ኢትዮጵያ ዜና 24
Photo
ሰበር
የኤርትራ ጦር በወልቃይት አቅጣጫ እየተጠጋ ነው!
የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ በስፋት መግባታቸውን አለምአቀፉ ተቋም ይፋ አደረገ።
ሻዕቢያ እና ህወሓት ጦራቸውን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ውጊያ ግንባሮች እያስጠጉ መሆኑን ክሪቲካል ትሪት የተሰኘ የግጭት ሁኔታዎችን የሚተነትን ተቋም አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጦርነት ለመክፈት የተስማሙት ሁለቱ ኃይሎች በዋናነት በሁለት አቅጣጫዎች ጦሯቸውን ወደ ድንበር አንቀሳቅሰዋል ተብሏል፡፡ ህወሓት ወደ አማራ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች ኃይሉን አስጠግቷል።
በሌላ በኩል ሻዕቢያ ጦሩን ያስጠጋበት አንደኛው ግንባር ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሱዳን በሚዋሳኑበት በወልቃይት በኩል መሆኑን የክሪቲካል ትሪት ሪፖርት ያመላክታል፡፡ የኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር በወልቃይት በኩል ከተከዜ በቅርብ ርቅት ላይ ማስፈሩን የተቋሙ ሪፖርት ያመላከተ ሲሆን፣ በዚያው አቅራቢያ የህወሓቱ አርሚ 70 ታንክ ጭምር ታጥቆ ሸረሪና ላይ በተጠንቀቅ ቆሟል፡፡
ሁለተኛው ግንባር ደግሞ በባድመ ድንበር በኩል ሲሆን፣ ሻዕቢያ ጦሩን እስከመቀሌ ድረስ ያስገባው በዚያው አቅጣጫ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡ ከህወሓት ጀርባ ሆኖ ጦርነቱን ወደ ማኸል ሀገር ለመግፋት ከባድመ እሰከ አዲግራት ጦር ያስገባው ሻዕቢያ፣ ወታደራዊ ሎጀስቲክሱን በትግራይ መዲና መቀሌ ከተማ አስገብቷል ተብሏል፡፡
የሻዕቢያ ጦር መቀሌ መድረሱን አዲስ ይፋ ባደረገው መረጃ ያረጋገጠው ክሪቲካል ትሪት፣ በአካባቢው ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል፡፡ ህወሓት ወደ አማራ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች ያለ የሌለ ኃይሉን ሰብስቦ ሲያስጠጋ፣ ሻዕቢያ ከጀርባ በታንክ የታጀበ ጦር ከባድመ እስከ አዲግራት እያስገባ ነው ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል እንቅስቃሴ ወደ ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እየገባ መሆኑን ተቋሙ ጠቁሟል፡፡ ከፋኖ አማጺዎች ጋር ውጊያ ላይ የነበረው መከላከያ ሰራዊት ከሰሞኑ ከአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለቆ ወደ ትግራይ አወሳኝ ቦታወች እና ወደ ኤርትራ ደበር እየተጠጋ መሆኑ ይሰማል።
በአንድ ጎራ በተሰለፉት ሻዕቢያና ህወሓት በኩል የጦርነት ዝግጅቱ እየተደረገ ያለው በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ ከህወሓት ጋር የተቀናጀው ሻዕቢያ አይቀሬ ነው ለተባለለት ጦርነት እየተዘጋጀ የሚገኘው በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሆኑን፣ ተቋሙ በካርታ አስደግፎ ያወጣው ሪፖርት ያመላክታል፡፡