Ethiopian News Agency
✔
22.3K subscribers
8.51K photos
1.06K videos
6 files
20.5K links
Ethiopian News Agency official telegram channel
Download Telegram
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት፡-

“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ። የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው።
‎
‎በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው። ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል።
‎
‎በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች።
‎
‎ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል!
❤2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር  ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፦‎በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል ብለዋል።
❤4👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ
#PMOEthiopia