Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
✔
70.2K subscribers
1.86K photos
128 videos
26 files
1.36K links
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Download Telegram
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia pinned «🚨 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት❗️ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስም ከሚፈጸም ማጭበርበር ራስዎን ይጠብቁ! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ስም፣ አርማ፣ የከፍተኛ አመራሮችን ፎቶና ፊርማ በመጠቀም ሐሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጩ ይገኛሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች በተለያዩ ሀገራት የሥራ ዕድል እንደሚያመቻቹ የሚገልፁ፣ ሂደቱን ለማስጨረስ ቀስ በቀስ ገንዘብ…»
የአርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የብቃትና የጥራት ማረጋገጫ ISO-21001:2025 ሠርተፍኬት አገኘ!

የአርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት አመራር ስርዓትን የሚያረጋግጠውን ISO 21001:2025 (EOMS - Educational Organizations Management System) የዕውቅና ሠርተፍኬት ከኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት በይፋ ተረክቧል!

የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የማርኬቲንግ፣ቢዝነስና ልማት ዳይሬክተር እና የዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ተኬ ብርሃነ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ አርዳይታ ኮሌጅ ያገኘው የISO 21001:2025 ዕውቅና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙሉ ተቀባይነት ያለው መሆኑን አረጋግጠዋል።
አያይዘውም ይህ ዕውቅና የመጨረሻ ግብ ሳይሆን የላቀ ስኬት መነሻ በመሆኑ ኮሌጁ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በእስታንዳርዱ መሠረት አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በመቀጠል የኮሌጁ ዲን ተወካይ እና የሥልጠና ዘርፍ ም/ዲን ወ/ት ነጅሀ ረዲም በበኩላቸው ይህ ታሪካዊ ስኬት በርካታ ውጣ ውረዶችን በማለፍ የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ውጤት ትልቅ አስተዋፅዖ ላበረከቱት የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት፣ የISO TASK FORCE ቡድን አባላት፣የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች፣ መምህራን እና ባለድርሻ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበው "እንኳን ደስ አላችሁ!" ብለዋል።

አያይዘውም የሠርተፍኬቱ ስኬት የጠንካራ ሥራ ውጤት እና የተጨማሪ ኃላፊነት አደራ በመሆኑ በየዕለቱ በዓለም አቀፍ መስፈርቱ መሠረት የላቀ አገልግሎት በመስጠት፤ ተማሪዎቻችን ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንሰራለን ሲሉ ገልጸዋል።

ምንጭ፡- የአርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤46👍2🎉2
ኢንስቲትዩቱ በታዳሽ ሃይል የስልጠና ፕሮግራሞችን ለማስጀመር የስርዓተ-ስልጠና ግምገማ አካሄደ

የኢትዮጵያ ቴክኒክ ልህቀት ኢንስቲትዩት ስድስት አዳዲስ ስልጠናዎችን በታዳሽ ሃይል ለማስጀመር ያለመ የስርዓተ-ስልጠና ግምገማ አካሂዷል።

ግምገማውን ያስጀመሩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢንስቲትዩቱ ባለፈው ዓመት ነባር ስልጠናዎችን በመከለስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን አስጀምሯል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው ሰፊውን የኢንዱስትሪ ፍላጎት መነሻ በማድረግ ሲሆን በታዳሽ ሃይል ዘርፍ የበቃና የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ የታዳሽ ሃይል አቅም ቢኖራትም እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው ግን ጥቂቱ ብቻ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ብሩክ፣ ከውሃ ሃይል በተጨማሪ ሌሎችንም የሃይል አማራጮች በመጠቀም ኢንዱስትሪዎችን ማንቀሳቀስ የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት የስርዓተ-ስልጠናው ዝግጅት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል።

በግምገማው ወቅት የቀረቡት ስርዓተ-ስልጠናዎች በደረጃ 6 (BSc) የሚሰጠውን Power and Renewable Energy ጨምሮ Solar Energy፣ Wind Energy፣ Geothermal Energy፣ Hydropower Energy እና Waste Energy በተሰኙ አጫጭር የጊዜ ስልጠናዎች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

በዚህ የምክክርና ግምገማ መድረክ ላይ ከጀርመን አገር፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና ከሌሎችም አጋር ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መረጃው የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልህቀት ኢንስቲትዩት ነው፤
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤43👍5
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ከዘርፉ አመራሮች ጋር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግመዋል።

በመድረኩ የሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት፣ የሙያ ደህንነትና ጤና እንዲሁም የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫዎች በዝርዝር ተመልክተዋል።

ያሉ ጥንካሬዎች በማላቅ እና ክፍተቶችን በማረም፣ በቀጣይ ጊዜያት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠይቅ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት አሳስበዋል፡፡

ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRETelegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficialWhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤22🎉5👍2
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ከክልሎች ጋር ገመገመ

ሀገራችንን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘው ሀገራዊ ራዕይ በሚጠበቀው መጠን ለማሳካት ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል የማቅረብ ድርሻ ያለው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የላቀ ሚና አለው፡፡

ዘርፉ ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የሚስችል ዓቅም እንዲላበስ ለማስቻል ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የለውጥና የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊ እመርታ ተመዝግቧል፡፡

ይህንኑ መነሻ በማድረግ በተቀረፀው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ፣ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ የሁሉም ክልሎች የሚመለከታቸው የዘርፍ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ግምገማ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ፣ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ ዘርፉን አስመልክቶ ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃሳብ ግልፅነትና የጋራ መግባባት መፈጠሩን በውይይቱ ላይ አመልክተዋል፡፡

በቀጣዮቹ ጊዜያት የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂን በዝርዝር በመፈፀም ስልጠናውን በሥፋትና በጥራት ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በእያንዳንዱ የስልጠና መስክ የበቃ የሰው ኃይል ከማፍራት ተልዕኳቸው ጎን ለጎን አምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ፣ የአርሶ አደሩን ችግር የሚፈቱ፣ ምርታማነትን የሚያጎለብቱና ገቢ ምርቶችን የሚተኩ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ማምረት እንደሚጠበቅባቸውም ተብራርቷል፡፡

ዘመኑን በሚመጥን መልኩ ተቋማትን ተወዳዳሪ ለማድረግ ለዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎች ተገቢውን ትኩረት መስጠትና ተቋማት ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን በማሟላት የጥራት ሥራ አመራር (ISO) ሰርተፍኬት ባለቤት መሆን እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል፡፡

የአሰልጣኝ መምህራንን ብቃት በማሳደግ፣ የስልጠና ተቋማትን በግብዓት በማጠናከርና፣የሥልጠና ሥርዓቱን ውጤታማነት በማረጋገጥና ሰልጣኞችን በቋሚነት በማስመዘን የመደበኛና የአጫጭር ስልጠና አጠናቃቂዎች የመብቃት ምጣኔ ማሳደግ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑም በአፅንኦት ተመላክቷል፡፡

ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤47👏6👍5🎉4
የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ ተጠቆመ

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ላይ ተወያየ።

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሚድ ዱላ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት በመሆኑ፣ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት ከ38 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቀው በተያዘው በጀት ዓመትም ከ40 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ዜጎችን ወደ ሥራ ለማስገባት መታቀዱን አብራርተዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ አስመልክቶ በተካሄደው በውይይት የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅሞችን በአግባቡ ለመጠቀምና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

ዘገባው የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው

ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤48👍21
‎በክልሉ የሥራ አጥነት ምጣኔን በመቀነስ ወጣቶችን የቋሚ ሼል ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
‎
‎በሐረሪ ክልል በ«ብቃት» የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች የፕሮጀክቱን ፋይዳ አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
‎
‎በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሐረሪ ክልል ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰሚር አብዱላሂ፤ በክልሉ በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር 1 ሺህ 365 ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
‎
‎ፕሮጀክቱ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 29 ዓመት የሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራና ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አብራርተዋል።
‎
‎ወጣቶቹ በሚያደርጉት የ6 ወራት የሥራ ላይ ልምምድ በሥነ-ልቦና፣ በክህሎትና በእውቀት ራሳቸውን እንደሚያዳብሩ የጠቆሙት አቶ ሰሚር፤ ይህም ብቁና የሠለጠነ የሰው ኃይል በመፍጠር ለአመርቂ የሥራ ባህልና ለኢንዱስትሪዎች ዕድገት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
‎
‎አቶ ሰሚር አክለውም፤ ፕሮጀክቱ በመደበኛ የሥራ ዕድል ውስጥ ያልተካተቱ ዜጎች ከተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ ሥልጠና እንዲወስዱና በቋሚነት የሙያና የሥራ ባለቤት የሚሆኑበትን ሰፊ ዕድል የሚያመቻች መሆኑን ገልጸዋል።
‎
‎ለፕሮጀክቱ ውጤታማነትና ስኬት ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ የጠቆሙት አቶ ሰሚር፤ ወጣቶችም የተሰጣቸውን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲጠቅሙ ጥሪ አቅርበዋል።
‎
‎የቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ግርማ መኮንን በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ ከንድፈ-ሀሳብ ሥልጠና ባለፈ ወጣቶች በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በተግባር ተሰማርተው ልምድ እንዲቀስሙ የሚያስችል በመሆኑ በክልሉ የሚታየውን የሥራ አጥነት ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
‎
‎ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ ስድስቱም የከተማ ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለፁት አቶ ግርማ፤ ተግባራዊ እንቅስቃሴውም ከፊታችን ሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀመር አመልክተዋል።
‎
‎በዚሁም በመጀመሪያው ምዕራፍ ለሐኪም፣ ለአቦከርና ለአሚርኑር ወረዳ ተጠቃሚዎች በሐረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ12 ቀናት የሥነ-ልቦና እና የክህሎት ማበልጸጊያ ሥልጠና የሚሰጥ ሲሆን፤ በመቀጠልም ለጂንኤላ፣ ለአባድርና ለሸንኮር ወረዳዎች ተመሳሳይ ሥልጠና ተደራሽ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
‎
‎ሰልጣኞቹ የ12 ቀናት የቅድመ-ዝግጅት ሥልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለ6 ወራት ያህል በየተመደቡበት ተቋም የሥራ ላይ ልምምዳቸውን እንደሚያካሂዱም አስታውቀዋል።
‎
‎በመድረኩ ላይ በክልሉ የመጀመርያው ዙር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
‎
‎ምንጭ ሀረሬ መገናኛ ብዙሀን
‎
❤104🙏6
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችሮችንለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ፣ የዜጎችን እንግልት ከመቀነስና ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያ የሚነሱ ጥያቄዎች በዝርዝር ተመልክተዋል።

በዘርፉ አሰራሮችን ለማዘመን የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም ማሻሻያ በሕግና በመመሪያ መሠረት መፈጸምና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አስገንዝበው፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአሰራር ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ገልፀዋል።

ጥቅምት  18/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤50👍14👏11
"የክልሉ መንግሥት ዋነኛ ትኩረት በክህሎትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በማተኮር የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ነው" ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በመቶ ቀን ዕቅድ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ የምክክር መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የመሠረተ ልማት እጥረቶችንና ማነቆዎችን በመቅረፍ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የክህሎት ማሻሻያ፣ የገበያ ትስስርና የፋይናንስ ተደራሽነትን ማጠናከር ለስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማነት የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር በበኩላቸው፣ የክልሉን የተፈጥሮ ጸጋዎችና የሰው ኃይል አቅም ወደ ምርታማነት በመቀየር ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ወጣቶችና ሴቶች ያላቸውን አቅም እንዲጠቀሙ በክህሎት ሥልጠና ማብቃት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምስ አድማሱ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኢንዱስትሪ ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሥራና ክህሎት ተግባራት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል ባደረገ መልኩ እንዲስፋፉና የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚገድቡ ተቋማዊ ችግሮች እንዲፈቱ ጥረቶች እንደሚደረጉም ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ከ214 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸው ከእነዚህም 35 ሺህ 400 ዜጎች የሥራ ውላቸው ፀድቆ የውጭ አገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የመቶ ቀናት ዕቅድና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ሰነድ እየቀረበ ሲሆን ውይይት የሚካሄድ ይሆናል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ነው

ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤40👍6
ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚያስቀር ጥገና በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እየተሰራ ነው።

የኢትዮጵያ ቴክኒክ ልህቀት ኢንስቲትዩት የወርክሾፕ፣ የላብራቶሪ እና የቢሮ አገልግሎት መስጫ ማሽኖች ጥገናና ተከላ የሚያከናውን የባለሙያዎች ቡድን ጥገና ማከናወን ጀምሯል።

በኢንስቲትዩቱ የብየዳ ማዕከሉን ጨምሮ ከሁሉም ዲፓርትመንቶች በተለያየ ደረጃ ብልሽት ገጥሟቸው አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የስልጠና ማሽኖች ጥገና እየተደረገ ይገኛል።

በዚህም ከ250 በላይ የተበላሹ የስልጠና እና አገልግሎት መስጫ ማሽኖች የተለዩ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና ባለሙያዎች ጥገና እያደረጉላቸው ይገኛሉ።

ማሽኖቹ ተጠግነው አገልግሎት ሲጀምሩ ከ10ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወጪ እንደሚያስቀሩ በባለሙያዎች የተጠና ሲሆን ከሁሉ በላይ ኢንስቲትዩቱ የተግባር ስልጠናዎችን በስፋት ለመስጠት ያግዛሉ ተብሏል።

መረጃው የኢትዮጵያ የቴክኒክ ልህቀት ኢኒስቲትዩት ነው፡፡
ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤45👍11👌3🎉2
የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ለማሻሻልና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

ክቡር አቶ አወሉ አብዲ – የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከሚኒስቴሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ላይ በተስተዋሉ ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በውይይቱ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውንና የመፍትሔ አማራጮችን የሚያብራራ ሰነድ ቀርቦ ዝርዝር ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ለሀገር ትልቅ ሀብት መሆኑን ጠቁመው ሥርዓቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካትም ትልቅ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

በሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በጥልቀት መለየትና በቅድሚያ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸውን ችግሮች መለየት እንደሚገባም ገልጸዋል። ችግሮቹ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በተዘጋጀ አቅጣጫ መፍትሔ እንዲያገኙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ከቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር፣ ከሰው ኃይልና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ከሕግና አሠራር ጋር የተያያዙ ችግሮች በአስቸኳይ ተለይተው እንዲቀርቡም አሳስበዋል።

እነዚህን ችግሮች በየደረጃው በመፍታት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ችግሮቹ እስኪፈቱ ድረስ አገልግሎቶች መቋረጥ የለበትም ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ክፍተቶቹን እየፈቱ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ አብራርተዋል።

በውይይቱ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ መካከለኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤59👍8🙏8🎉1
የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት  በማሳደግ ላይ ያተኮረ ሥልጠና

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት(GIZ) ጋር በመተባበር በቴክኒክና ሙያ ስልጠናና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ  ስልጠና  ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ላይ  መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሼል አስፈጻሚ ፣  ወ/ሎ እምዬ ቢተው በሚኒስቴሩ በሶስቱም ዘርፎች በአካቶ ትግበራው ዘርፍ ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው እያንዳንዱ የሥራ ክፍልም በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ እቅድ ይዞ እንዲሠራ ድጋፍና ክትትል እተደረገ ይገኛል፡፡

በየዘርፉ የሚዘጋጁ ፕሮግራሞች  የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉና ተናበቡ እንዲሆኑ  ለማስቻል በጋይድላይኑ ላይ ተመሳሳይ አረዳድ እዲኖር ስልጠናው  ሁሉም የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ ተወካዮች መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የ GIZ ተወካይ የሆኑት ሚሲስ ሜሎና ባስተላለፉት መልዕክት በአካል ጉዳተኞች አካቶ ትግበራ ላይ  ግንዛቤ ለመፍጠር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሰጠው ትኩረት  አድናቆታቸውን ገልጸው ጋይድላይኑንም  አካታችነትን በማስፈን ረገድ ጉልህ ለውጥ ይዞ የመጣ ስለሆነ በአግባቡ መረዳትና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤33
የሥራ ዕድል ፈጠራ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት የልማት አጋሮች ጠንካራ ትብብር ወሳኝ ነው።

ክቡር አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

የልማት አጋር ድርጅቶች የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተያዙ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ድጋፋቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው ከአውሮፓ ሕብረት ልዑክ እና ከጀርመን የልማት ትብብር (GIZ) ተወካዮች ጋር በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ወደፊት በትኩረት ተጠናክረው መቀጠል በሚገባቸው የትብብር መስኮች ላይ አተኩረው ተወያይተዋል።

ክቡር አምባሳደር የልማት አጋሮች በዘርፉ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው፣ በተለይም የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በሚቀይሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ላይ የጋራ ጥረትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ለመፍጠር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የልማት አጋሮች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመው የሚፈጠረው የሥራ ዕድል በቁጥር የሚለካ ብቻ ሳይሆን ዜጎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው፣ ኢኮኖሚያዊ ነፃነታቸውን እንዲያጎለብቱና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያስችል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የGIZ ተወካዮች በበኩላቸው በኢኮኖሚ ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎትና ትምህርት ልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በስደተኞች ማኅበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማጠናከር ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcY
❤22
የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡

ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ትብብር በሥስት ዙሮች በተለያዩ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው የፋውንዴሽን ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉን ለማሻሻልና ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውን ከማሻሻል ጀምሮ አዲስ ስትራቴጂ ተቀርጾ በእነሱም ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማወያየት ስራዎች መሰራታቸውን አውስተዋል፡፡

የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶችን በመለየት በተሰጡ ስልጠናዎችም ለውጥ ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ የተገኘው ክፍተት የልል ክህሎት (soft skills) በመሆኑ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድ ዜጋ ቴክኒካል ክህሎት ስላለው ብቻ ተወዳዳሪ መሆን ስለማይችል ዜጎች ለሁሉም ነገር ዝግጁ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሰልጣኖች ይህንን የልል ክህሎት ስልጠና በትምህርታቸው ተካቶ እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም አሰራር ግዴታ በመሆኑ ሰልጣኞች የማስፈጸም ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ስልጠናውን ከላይኛው መዋቅር ጀምሮ እስከ ክላስተር ደረጃ ማስፋፋት እንደሚጠበቅ በመግለጽ፣ በእስካሁኑ ሂደት አበርክቶ ለነበራቸው አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደ/ር ሐሰን ሁሴን በበኩላቸው፤ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡም አርአያ የሚሆን ዜጋ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

ልጣኞችም በሙያቸው ለተማሪዎችና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እንዲሁም ዜጎችን መለወጥ የሚችሉ እንዲሆኑ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላት ትልቁ ሀብት ወጣት በመሆኑ እነሱን ለአለም ተወዳዳሪ አድርጎ የማውጣት እና የነገውን የኢንተርፕራይዝ ማስፋፊያ አሻራ የማሳረፉ ኃላፊነት በእጃቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን መሰል ስልጠና በማዘጋጀቱ ደስታቸውን ገልጸው የተሰጣቸው ኃላፊነት ትልቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
❤53🤩3
በሥራና ተግባር ትምህርት ብቁና ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የሥራና ተግባር ትምህርት አተገባበር የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለፁት፤ በክልሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውን የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ ኢንሼቲቮችን በመንደፍ ወደ ተግባር ተገብቷል።

ዘርፉ እንደ ሀገር በሥራ እድል ፈጠራ ረገድ የተቀመጠለትን ግብ ያሳካ ዘንድ ትምህርት ቤቶች ላይ ክህሎትን ከማስረጽ ባለፈ በሙያ የተደገፈ ትምህርትን መስጠት ይገባል ብለዋል።

በዚሁ መሰረት በክልሉ በአንደኛ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ግንዛቤውን በማስረጽ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቂ የሆነ የሥራና ተግባር ትምህርት በማቅረብ ብቁና ሥራ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ባለፉት ሁለት አመታት ከ24ሺ በላይ ተማሪዎች የሥራና ተግባር ትምህርት ወስደው መመረቃቸውንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ይህ ተግባር ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው በደረጃ ሁለት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ያሉት አቶ አንተነህ በቀጣይም ይህን በማጠናከር ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ትምህርት ቤቶች ከቴክኒክና ሙያ፣ ከጤናና ከግብርና መዋቅሮች ጋር ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩልም አቶ አንተነህ እንደገለጹት የተማሪዎችን መጠነ ማለፍ ለማሻሻል «ኢጁኬሽናል ዴቨሎፕመንት ትረስት» ከሚባል ሀገራዊ ኢንሼቲቭ ጋር በመቀናጀት ወደ ዩኒቨርስቲ፣ ወደ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ወደ ሌሎች የሥራ መስኮች የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢንሼቲቩ ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በማድረግ፣ ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ የማጠቃሻ መጽሃፍት ድጋፍ በማድረግና የአይሲቲ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት በኩል ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው

ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤22👍4🎉1
የክህሎት ሥነ-ምህዳርን ማዘመን ለዘላቂ ሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ ከፍተኛ የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ተሳትፈዋል።

በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በተነሳሽነት፣ በቁርጠኝነትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡ የመፍጠን፣ የመፍጠር እንዲሁም የመስፈንጠር ስልቶችን መከተልና ለጋራ ግብ የየዘርፎቹ መስተጋብር መቀናጀትና መጠናከር እንዳለበትም በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፤ ሀገራዊ እና ክልላዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ጥራቱን የጠበቀ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ እና አምራች የሆነ የሰለጠነ የሰው ሃይል ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

አቶ ሙስጠፋ አያይዘውም ከድህነት እና ከሥራ አጥነት ለመላቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀና አዲስ አስተሳሰብን የተከተለ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ የንቅናቄ መድረክ የክልሉን የሥራ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥነ-ምህዳር በማዘመን ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን ከመድረኩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ቀርበው የዳበረ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡

ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤26👏2🎉2
በክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገመገመ፡፡
በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆች የሚሰጡት የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ከተቋሙ ጋር በቅንጅት የሚተገበር በመሆኑ በእያንዳንዱ አፈጻጸም ላይ ተናቦና ተባብሮ መስራት እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።

በዚህም ረገድ የተቋማቱን እቅድና አፈጻጸም በጋራ መገምገም እና እንደአስፈላጊነቱ ተደጋግፎ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

አክለውም የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁና ለሌሎች ተቋማት ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ እቅዶችን መከለስና ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር አብሮ መለወጥ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አመላክተዋል።

የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተመስገን ሀይሉ የኮሌጁን የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፤ እንደዝግጅት ምዕራፍ በመደበኛ እና በማታው እንዲሁም በተለያየ ደረጃ በአጫጭር ስልጠናዎች ሰልጣኞች እየሰለጠኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በሩብ ዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት የነበረው የተመዛኞችን ውጤታማነት የማሻሻል ስራም በሚጠበቀው ልክ ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ኮሌጁ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን ማስተዋወቁን፣ ሰልጣኞች ወደ ተቋሙ እንዲመጡ በተለያየ ደረጃ የንቅናቄ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከስልጠና ባሻገር ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመድረስና በማህበራዊ እና ሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ላይ በመሳተፍ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዲኑ አክለውም ተቋሙ የውስጥ አሰራሩን ከማዘመንና ለሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የምርትና አገልግሎት አቅሙን በማሻሻል በሩብ ዓመቱ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የውስጥ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አብራርተዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ኮሌጁ እንደተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣበት ያለው መንገድ ለሌሎች አርአያ እንደሚሆንና በማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

ከምንም በላይ ተቋሙ የተቀናጀ አመራር በመስጠት ብቁ የሰው ሀይል ከማፍራት ባሻገር የውስጥ ገቢውን በአስደናቂ ሁኔታ ማሳደግ መቻሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

መረጃው -የቤ/ጉ/ክ/መ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤17👍4
መሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ማሳደግና አስተዳደሩን ማጠናከር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነው

የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትና አስተዳደርን ማሻሻል የኢንተርፕራይዞችን ዘላቂ ዕድገት ከማረጋገጥ ባለፈ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

ለዚህም የመሥሪያ ቦታዎችን በበቂ መጠን ከማቅረብ ባሻገር በፍትሐዊነትና በግልጽ የአስተዳደር ሥርዓት መምራት ይጠይቃል።

በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ ውስጥ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንደ ወሳኝ ግብዓት ተቀምጧል።

በዚህ መሠረት በ2019 በጀት ዓመት 11,487 ሼዶችን በመገንባት፣ ሼድ ለሚፈልጉና ለማይፈልጉ የሥራ መስኮች 126,300 ሄክታር የለማ መሬት በማዘጋጀት 49,500 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ መላኩ ወልደዮሐንስ እንዳብራሩት፣ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች የሥራ መጀመሪያ መሠረት ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ዕድገታቸውና ለሽግግር ሂደታቸው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሼድ እጥረት እንዲባባስና አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ወደ ሥራ እንዳይገቡ እንቅፋት እንደሚሆንም አመልክተዋል።

በመሆኑም የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማስፋፋትና አስተዳደሩን ለማሻሻል በተለይ የግሉን ዘርፍ በሼድ ግንባታና አቅርቦት ማሳተፍ፣ ክፍት የሆኑ የመንግሥትና የወል ቦታዎችን ለመሥሪያ ቦታነት ማዋል እንዲሁም የሼድ አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው።

በተለይም የሼድ ማኔጅመንት ሲስተምን በመጠቀም ያሉትን ሼዶች በሙሉ ወደ ሲስተሙ ማስገባት፣ የመሥሪያ ቦታ ምደባን በግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከናወንና ዜጎች በእኩል ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከአሠራር ሥርዓት ውጪ የተያዙ ሼዶችን ማስመለስም የሼድ አቅርቦትን ለማሳደግና የተሻለ የቦታ አጠቃቀም ለመፍጠር አስፈላጊ ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢንተርፕራይዞች የሽግግር ጊዜ በአግባቡ መምራት ይገባል። የሽግግር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገሩና የለቀቁት ሼድ ለሌሎች አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገር በተገቢው ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል። ይህም ውስን የመሥሪያ ቦታዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀምና ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል።

በአጠቃላይ የመሥሪያ ቦታ ጉዳይ የሼድ ግንባታና ምደባ ብቻ ሳይሆን የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ጉዞ የሚወስን ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው።

ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት የሼድ አስተዳደር ሥርዓቱን በተግባር በማዋል፣ የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎችን በቁርጠኝነት በመፈጸምና የመሥሪያ ቦታዎችን በፍትሐዊነት በማስተዳደር ለኢንተርፕራይዞች ዘላቂ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ በማዋል የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል።

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤28
በ22 ቀናት ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጠሩ

የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ22 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ ዕቅድ አፈጻጸምን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ጋር ገምግሟል።

በግምገማው በንቅናቄው ወቅት 25,944 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸው፣ ከ406.6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱና 746 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም 29,409 ሥራ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ56 ሺህ በላይ ዜጎች በለስላሳና ቴክኒክ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሳትፈዋል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮው የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣ ከመጀመሪያው ዙር ንቅናቄ የተገኙ ልምዶችንና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተቀናጀና ውጤትን ያማከለ አፈጻጸም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአንድ ዕቅድና የሪፖርት ሥርዓት በመመራት፣ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤40🤩5
ሥልጠናን ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሰራ ነው፡፡

ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱን ከሥራ ገበያውና ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህን የገለጹት የSTEP IV – Horti-Skills የሆርቲካልቸር ክህሎት ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያና የትግበራ ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው።

የክህሎት ልማት ስኬት የሚለካው በሚሰለጥኑ ዜጎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ሠልጣኞች በሥራ ገበያው በሚኖራቸው ተሳትፎ፣ በሚያገኙት የሥራ ዕድል፣ በሚፈጥሩት የራስ ሥራና ለኢኮኖሚው በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በሥልጠና ተቋማትና በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በማጠናከር ላይ ያተኩራል።

ሆርቲካልቸር የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማጠናከርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም ያለው ዘርፍ ነው።

ይህንን አቅም ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኒካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ዲጂታልና የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች የተላበሰ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ ነው።

ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ በክህሎት ፍላጎት መለየትና በሙያ ደረጃዎች ዝግጅት ላይ በማሳተፍ፣ ተግባራዊ ሥልጠናንና የሥልጠና ጥራትን በማሻሻል፣ የተቋማትን ባለቤትነትና የውጤቶችን ዘላቂነት በማጠናከር ላይ ያተኩራል። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ የሥራ ቅጥርና የሥራ ፈጠራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል።

ፕሮጀክቱ በጀርመንና በኔዘርላንድስ መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ፣ በGIZ ትግበራና ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የሚከናወን ነው፡፡

ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
❤2👏2🤩2🥰1