🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
12.2K subscribers
2.91K photos
302 videos
70 files
8.07K links
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።

✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante

አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
Download Telegram
✍
   ጉዞ ወደ ጧኢፍ…………
አሳዛኝ ፈተና ቢመስልም: በድንቅ ጥበብና ተኣምር የታጀበው ተኣምራዊው የነብዩﷺ ጉዞ!!

  የኡሑድ ዘመቻ ነብዩﷺ በአካል ተገኝተው ከተሳተፉባቸው ዘመቻዎች ሁሉ ከባድ የሆነ ችግር የገጠማቸው፤ ብዙ ስቃይ ያሳለፉበትና ሙስሊሞች ላይ አሳማሚና አሳዛኝ ክስተት የታየበት ከባድ ውጊያ ነበር። በዚህ ጦርነት ረሱልﷺ ጭንቅላታቸው ተፈንክቷል፣ ደማቸው ፈሷል፣ ብዙ ባልደረቦቻቸው ተሰውተውበታል፣ ለረሱልﷺ የዐይንና ጆሮ ያህል ቅርብና ተወዳጅ የነበረው ሐምዛ ተገድሎበታል። ይህ ሁሉ ስለተከሰተበት ሰሓቦች ዘንድ በረሱልﷺ የዳዕዋ ጉዞ ላይ ከኡሑድ ዘመቻ ቀን የበለጠ ከባድ ክስተት ያለፈበት ቀን ያለ መስሎ አይታያቸውም ነበር። በመሆኑም……………

  ኡአሙል ሙእሚኒን ዓኢሻ ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሀ
«የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እንደው ከኡሑድ ዘመቻ ቀን በበለጠ አስቸጋሪ ቀን አልፎቦት ያውቃልን??» ብላ ጠየቀቻቸው። እሳቸውም;
   «አዎን!! የውሙል ዐቀባ ወደ ጧኢፍ የተጓዝኩበት ቀን» ብለው የሆነውን ዘረዘሩላት።


ወደ ጧኢፍ የተደረገው ጉዞ ምን ይመስል ነበር???

  ወደ ጧኢፍ የተደረገው ጉዞ እንዲሁ ተራ የደርሶ መልስ ወይም የጉብኝት ጉዞ አልነበረም። ይልቁንስ አላህ መልእክተኛውን በከባድ ፈተና ፈትኖ፣ ከተራራ በላይ የፀናው እምነታቸው በማሳየት፣ ከብረት የጠነከረው ሰብራቸው በመግለፅ፣ ጥልቅ የሆነው አዘኔታቸው በማጉላት፣ በየትኛውም የመከራ ጊዜ መሸሸጊያው ወደ አላህ ብቻ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ታሪካዊ ጉዞ ነበር።

   ጊዜው መካ ለእስላማዊ ዳዕዋ አልለሰልስ ብላ፤ የገዛ ልጇና ወዳጇ በሆኑት በነብዩﷺ ላይ ፊት ነስታ፤ የረሱልና የዳዕዋቸው የጀርባ አጥንት በነበረችዋ በኸድጃ ሞት የረሱል ልብ የተሰበረበት፤ የረሱል ጠበቃና መከታ በነበረው በቁረይሾች ንጉስ በአቡ ጧሊብ ሞት የረሱል ሀዘን በበረታበት አስቸጋሪው ወቅት ላይ ነበር።
  በዚህም የቁረይሽ ቂሎች ከምንጊዜውም በላይ ረሱልﷺ ላይ የሚያደርሱት ስቃይ በርትቶ መካ ለሌሎች ሰፍታ ስታበቃ በረሱልﷺ ላይ ግን ጠበበችባቸው። ሀዘናቸው ላይ የጠላት ስቃይ ተጨምሮ ማረፊያ አጡ።

  በዚህም ጊዜ ረሱልﷺ አጋዥ ፍለጋ፣ አስጠጊ ፍለጋ፣ ረዳት ፍለጋ ፊታቸው ወደ ጧኢፍ አቀጣጩ። በነብይነት ከተላኩ ዐስረኛው ዓመት በሸዋል ወር: ከእሳቸው ጋ ኻዲማቸው ዘይድ ቢን ሓሪሳ አስከትለው ጉዞ ወደ ጧኢፍ……………

  ጧኢፍ እንደደረሱ ቀጥታ ህዝቡን ሰብስበው ከመጥራት ይልቅ ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ፈልገው ቅድሚያ የጧኢፍ መሪዎችን ማግኘት ፈለጉ። እነርሱም ዐብዱ ያለይል፣ መስዑድ እና ሑበይብ ነበሩ። ሦሥቱንም አግኝተው አናገሯቸው። እስልምና እንዲቀበሉ፤ እስልምና እንዲረዱና ህዝቦቻቸውም ወደ እስልምና አንዲያመላክቱ ጠየቋቸው። የሦሥቱም ምላሽ ግን ተመሣሣይ በሆነ መልኩ ማላገጥና ማፌዝ የተሞላበት ይበልጥ ቅስም የሚሰብር ነበር። "እንደው አላህ ሌላ ሰው አጥቶ ነው አንተን የላከው??¡¡ አንተ የአላህ ነብይ ከሆንክ እኔ አንተን የማናገር ክብር የለኝም፤ አላህ ላይ የምትቀጥፍ ውሸታም ከሆንክ ደግሞ ከአንተ ጋ የማባክነው ጊዜ የለኝምና ሂድልኝ" ብለው አሾፉባቸው።

  ነብዩﷺ እነዚህ ሰዎች እንደማይቀበሏቸው ካረጋገጡ በኋላ ትተው ተነሱ። ሌላ የፈሩት ነገር ግን ነበር =>ወደዚህ መምጣታቸውና እዚህም ተቀባይ ማጣታቸው ቁረይሾች ከሰሙ ይበልጥ ሊያሾፉባቸውና ሊያዋርዷቸው ነው። ስለሆነም ለእነዚህ ሦሥት ሰዎች «እንግዲያውስ የፈለኩትን ካልሰጣችሁኝ በአንድ ነገር አደራ ልበላችሁ: እናንተጋ መምጣቴንና ምን እንደመለሳችሁኝ ለማንም እንዳትናገሩ አደራ።» አሏቸው።
   ረሱልﷺየነበሩበት ሁኔታ አስቡት እስኪ!!


  የሰቂፍ መኳንንቶች ግን ረሱልﷺ ላይ አሹፈው መመለሱ ብቻ አላብቃቃቸውም። ወደ መንደር ተመልሰው የሰፈሩ ህፃናቶች፣ አገልጋዮች፣ ዕብዶችና ቂላቂሎች በአጠቃላይ ሰብስበው ረሱልﷺ ላይ እንዲጫወቱ ከኋላቸው ላኩባቸው። እነዚህም ቂላቂሎች ረሱልን ከኋላ ኋላ እየተከተሉ ይጮሁባቸዋል፤ ያፌዙባቸዋል፤ ድንጋይ እየወረወሩ እግራቸው እስኪደማና ጫማቸው በደማቸው እስኪርስ ድረስ አሰቃዯቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን አብሯቸው የነበረው ዘይድ በእጁ በጀርባው ረሱልﷺን እየከለለ እሳቸው ላይ የሚወረወሩ ድንጋይና እንጨቶች እሱ ይመልስላቸዋል። በዚህ መልኩ እያባረሩና እያሰቃዩ ሲከተሏቸው ዑትባና ሸይባ ለተባሉ ወንድማማቾች የጋራ ማሳ የነበረበት ጋ ደረሱ። ዑትባና ሸይባ ማለት ቀንደኛ የረሱልና የኢስላም ጠላቶች ነበሩ።

   ረሱልﷺ እና ባልደረባቸው ወደ ማሳው ከገቡ በኋላ ድካማቸውና ህመማቸው ለማሳረፍ ወደ አንዲት ዛፍ ተጠግተው ከጥላው ስር አረፉ። በዚህም ጊዜ ነብዩﷺ በሙሉ ልባቸው ወደ አላህ ተቀጣጭተው ያ……… ሁሉም ሙስሊሞች ባነበቡትና በሰሙት ጊዜ እንባ የሚተናነቃቸው የሆነው አስለቃሽ ዱዐ አደረጉ፦

«اللهمّ إليك أشكو ضعف قوتي، وقلة حيلتي، وهواني على الناس، يا أرحم الراحمين، أنت رب المستضعفين وأنت ربي، إلى من تكلني؟ إلى بعيد يتجهمني؟! أم إلى عدو ملّكته أمري؟! إن لم يكن بك عليّ غضب فلا أبالي، ولكن عافيتك أوسع لي. أعوذ بنور وجهك الذي أشرقت له الظلمات، وصلح عليه أمر الدنيا والاخرة من أن تنزل بي غضبك، أو يحل عليّ سخطك. لك العتبى حتى ترضى، ولا حول ولا قوة إلا بالله»
  «አላህ ሆይ! የዐቅሜን ማነስ፤ የጉልበቴን መድከምና በሰዎች ዘንድ መዋረዴን ወዳንተ አመለክታለሁ፤
የአዛኞች ሁሉ አዛኝ የሆንከው ጌታ ሆይ! የደካሞች ጌታ አንተ ነህ፤ የእኔም ጌታ አንተ ነህ!!
ወደ ማን ትተወኛለህ??
  ፊቱን ወደሚያጨልምብኝ የሩቅ ሰው?? ወይስ ጉዳዬን በእጁ ወዳደረከው ጠላት??
ሆኖም ግን ጌታዬ;
  በእኔ ላይ የአንተ ቁጣ ከሌለብኝ: ሌላው ምንም አያስጨንቀኝም!! ……………»

የዚህ ትልቅ ዱዐ ቁንጮ ሀሳቡ;
  ረሱልﷺ ይህንን ሁሉ ስቃይ የደረሰባቸው አላህ ተቆጥቶባቸው እንዳይሆን መስጋታቸው ነበር። አላህ ካልተቆጣባቸው ግን የትኛውም ዓይነት ሙሲባ ቀላል መሆኑ ነው።

   ዑትባ እና ሸይባ ረሱልﷺ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነው ሲያዯቸው የዝምድና አንጀታቸው አልቻለም፤ ራሩላቸው። የሁለቱም አገልጋይ የነበረ ነይኑዋ ከምትባል የዒራቅ ግዛት የመጣ ዑዳስ የሚባል ነሷራ ባሪያ ነበራቸው። ጠርተውት "ለዛኛው ሰውዬ የተወሰነ ዒነብ ወስደህ ስጠው" አሉት። ባሪያው በአለቃዎቹ ትዕዛዝ መሠረት የተወሰነ ዒነብ ይዞ ለረሱልﷺ አቀረበላቸው።

   ረሱልﷺ ከዒነቡ ለመብላት «ቢስሚላህ» ብለው እጃቸውን ዘረጉ። በዚህ ጊዜ ይህ ባሪያ ክው ብሎ ደንግጦ ወደ ረሱልﷺ ፊት በአግራሞት እየተመለከተ;
  "እዚህ ሀገር እኮ እቺን ቃል የሚጠቀም አንድም ሰው የለም" አላቸው።
ረሱልﷺ «ዑዳስ ሆይ! ሀገርህ የት ነው? ሐይማኖትህስ ምንድን ነው?» አሉት።
ዑዳስ "ከነይኑዋ ግዛት ነኝ: ሐይማኖቴም ነሷራ ነው" አላቸው።
ረሱልﷺ «የሷሊሑ ሰው የዩኑስ ኢብኑ መታ ሀገር?» አሉ።
ዑዳስ ይበልጥ በመገረም "ዩኑስ ኢብኑ መታ እንዴት አወቅከው?" አላቸው።
ረሱልﷺ «እሱማ ወንድሜ ነው። ነብይ ነበር፤ እኔም ነብይ ነኝ» አሉት።
ዑዳስ በዚህ ጊዜ ራሱን መቆጣጠር አልቻለም። ረሱልﷺ ላይ ተደፍቶ አንዴ ግንባራቸው አንዴ እጃቸው እየሳመ ማልቀስ ጀመረ።


  ረሱልﷺ በዚህ መልኩ ቅስማቸው ተሰብሮ: ልባቸው ተጣቦ: ጭንቀታቸው ጨምሮ ወደ መካ መመለስ ጀመሩ። ይህንን ሁሉ ልብ አድሚ ክስተት ገጥሟቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ አላህ  ያዘነው ልባቸው የሚያረጋጋ: የተረበሸው መንፈሳቸው የሚያድስ ተኣምር አደረገላቸው።


  ኡሙል ሙእሚኒነ ዓኢሻ ለረሱልﷺ«እንደው እርሶ ላይ ከኡሑድ ዘመቻ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን አልፎቦት ያውቃልን?» ብላ ስትጠይቃቸው ይህንን አወሱላት………

  «እኔማ ከህዝቦችሽ (ከቁረይሾች) የደረሰብኝ ሁሉ ደርሶብኛል። እነርሱ ላይ ከደረሱብኝ ሁሉ ከባዱ ግን የውሙል ዐቀባ ቀን የተከሰተውን ነው። ወደ ኢብኑ ዐብድ ያለይል ቢን ዐብዱል ኪላል ጥገኝነት ጠየኩኝ: የፈለኩት ነገር ማግኘት አልቻልኩም። በጥልቅ ጭንቀት ውስጥ ሆኜ እየተጓዝኩ ቀርኑ ሰዓለብ የሚባለው ቦታ ስደርስ እንጂ አልነቃሁም ነበር። ራሴን ቀና አድርጌ ሳይ ደመና አጠልላኝ ተመለከትኩኝ።  ሳይ ጅብሪልም እሷ ውስጥ አገኘሁት።
  ሙሐመድ ሆይ አላህ ህዝቦችህ ለአንተ ምን እንዳሉህና ምን እንደመለሱልህ ሰምቷል፤ በእነሱ ላይ በፈለከው ነገር ልታዘው የተራራዎች ሀላፊ የሆነው መላኢካም ወዳንተ ልኮታል አለኝ።
  የተራራዎች ተቆጣጣሪ የሆነው መላኢካም ጠራኝና ሰላምታ አቀረበልኝ። ከዝያም እነሆ በፈለከው ነገር እዘዘኝ: ከፈለክ ሁለቱ ትላልቅ ተራራዎች ላጣብቅባቸው አለኝ።»

ረሱልﷺ ግን
  «ኣኣኣይ እንደውም አላህ ከዝርያዎቻቸው አላህ ላይ ምንም ሳያጋራ በብቸኝነት የሚያመልክ ትውልድ እንዲያወጣ ነው የምፈልገው» አሉ።
  በዚህም የረሱልﷺ ጥልቅ አዘኔታና ይቅርባይነት በግልፅ ታየ። ያንን ሁሉ ያረጓቸው ሰዎች እሳቸው ከፈለጉ የሚጠፉበት ቅጣት መጥቶ እንኳ: እነርሱ ከሰሩት ነውር ይልቅ ከእነርሱ ውስጥ ስለሚወለደው ትውልድ ተጨነቁ።


   ከዚሁ ጉዞ በመመለስ ላይ ሳሉ ዋዲ ነሕላ እሚባል ቦታ ሲደርሱ ሌሊት ነበርና አላህ ያገራላቸው ያህል የለይል ሰላታቸው ሰገዱ። ሰላታቸው ላይ ቆመው ሳሉ ነሲቢዪን ከሚባል ጎሳ የሆኑ ከፊል ጂኒዎች በአጠገባቸው አለፉ። በዚህም ረሱልﷺ ሰላታቸው ላይ ይቀሩት ከነበረው ቁርኣን አደመጡ። ረሱልﷺ ሰግደው ሲጨርሱ ቁርኣኑን ያደመጡ ጂኒዎች እስልምና ተቀብለው ወደ ህዝቦቻቸው በመሄድ ወደ እስልምና መጣራት ጀመሩ። ይህንን ክስተት አላህ በሱረቱል አሕቃፍ ውስጥ ጠቅሶታል።

   ይህ ከአላህ ለነብዩ የተሰጠ የማፅናኛ ስጦታ ይመስላል። ድጋፋቸው ከጅለው የሄዱባቸው ወገኖቻቸው ድጋፍ ካለመስጠት አልፈው አዋርደውና አነውረው ሲመልሷቸው ረሱልﷺ ጭራሽ ባላሰቡት መልኩ ከሰው ልጆች ውጪ የሆኑ የሌላ ዓለም ፍጡራኖች አጋዥና ረዳት አድርጎ የዳዕዋው አጋር አደረገላቸው።


   ጉዞው በዚህ መልኩ ተጠናቆ ወደ መካ ከደረሱ በኋላ ረሱልﷺ ቀጥታ ወደ መካ ለመግባት ፈሩ። የቁረይሾች የተለመደው ጭቆና አለ፤ ከዚህ በፊት የሚከላከልላቸው አጎታቸው ሙቷል፤ አሁን ላይ ወደ ጣኢፍ ሄደው የሆነው ሲሰሙ የበለጠ እልህ ሊይዛቸው ነው። በመሆኑም ቀጥታ ከመግባታቸው በፊት ከለላ ሊሰጣቸው የሚችል ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ወደ ተለያዩ የመካ መኳንንቶች ጋ ቢያስልኩም ለእሳቸው ከለላ ለመስጠት ፍቃደኛ የሚሆን ማግኘት አልቻሉም። በመጨረሻም ወደ ሙጥዒም ኢብኑ ዐዲይ አስላኩ: እሱ ግን ምንም እንኳ ሙሽሪክ ቢሆንም የከለላነት ጥያቄው ተቀብሎ "አብሽር እኔጋ ይምጡ" አለ። ረሱልﷺ ምሽቱን እሱጋ አድረው ጠዋት ላይ ሙጥዒም ረሱልﷺ ከለላ እንደሰጣቸውና ማንም እንዳይዳፈራቸው ለማሳወቅ ከስድስት ወይም ከሰባት ልጆቹጋ ሰይፋቸው ታጥቀው ለነብዩ አጅበው ወደ ካዕባ በመሄድ: ረሱልﷺ ጠዋፍ ሲያደርጉ ሙጥዒምና ልጆቹ ታጥቀው አጀቧቸው።


  በእርግጥም ረሱልﷺ ለሙጥዒም ይህንን ውለታው ይጠብቁለት ነበር። የበድር ዘመቻ ቀን እንኳ ከፊል የሙሽሪክ ወታደሮች ከተማረኩ በኋላ ነብዩﷺ
  «ሙጥዒም በሕይወት ቢኖርና በእነርዚህ ምርኮኞች ጉዳይ ቢያናግረኝ: ለእሱ ስል በነፃ አሰናብታቸው ነበር።» ብለዋል።


    የነብዩﷺ ባይተዋርነት፤ አጋዥና ረዳት የማጣት ህመም፤ የብቸኝነት ቁስል፤ የዐላዋቂ ተቀናቃይ ክፋት፤ ከሁሉም በላይ ለአላህ የሆነ ሰው አላህ እንደማይጥለው በግልፅ የታየበት ወደ ጧኢፍ የተደረገው ተኣምራዊው ጉዞ በዚህ ተቋጨ።


    ከዚህ ትልቅና አስገራሚ ከሆነው ጉዞ እያንዳንዳችን ለሕይወታችን ስንቅ የሚሆኑ በርካታ ትምህርቶች የምናገኝበት ሲሆን; በዋነኝነት…………

  በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ ከመመካትም ጋ የተቻለን ያህል ሰበብ ማስገኘት!!

  አንድ ሰው በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ላይ ቢሆን ከዱዐ መቋረጥ እንደሌለበት!!

   አንድ ሰው የትኛውም ዓይነት ሙሲባ ሲደርስበት ከአላህ ቁጣ እንዳይሆን መፍራት እንዳለበት!!

   ወደ አላህ የሚጣራ የትኛውም ሰው ለሰው ልጆች በአጠቃላይ አዛኝና ሆደ ሰፊ መሆን እንዳለበት!!

   የአላህ ፈረጅና እገዛ ከመከራና ከትዕግስት በኋላ ይመጣል እንጂ: አላህ ወዳጆቹን በፍጹም እንደማይተዋቸው!!

   ወደ አላህ የሚጣራ ሰው ከምንም ነገር በላይ የተሟላ ውብ ስነ_ምግባር ሊኖረውና ትሆን መሆን እንዳለበት!!

  የእስልምና ዳዕዋ በሰው ልጆች ብቻ የተገደበ ሳይሆን አጠቃላይ ፍጥረተ_ዓለሙ ያካተተ መሆኑን እንገነዘባለን!!



https://t.me/hamdquante
❤35👍18👌1
✍
    ከፈጅር ሰላት በኋላ ፀሀይ እስከምትወጣ ድረስ ባለው ሰዓት መተኛት ሰለፎች ዘንድ የተጠላ ነበር።


ምክንያቱም፦
   ይህ ወቅት ሲሳይ የሚከፋፈልበት፣ በረከት የሚሰፍንበትና የምርኮ ወቅት ነው!!
       /ኢማም ኢብኑል ቀይም/




https://t.me/hamdquante
❤24👍15
✍
ሰዎች ሁለት ዓይነት ናቸው፦ ዲን ፈላጊና ዱንያ ፈላጊ።

🔥ሸይጧን………
ለዲን ፈላጊዎች ወደ ሽርክና ቢድዐ ይገፋፋቸዋል፤

  ለዱንያ ፈላጊዎች አካላዊ ስሜታቸው እንዲከተሉ ይገፋፋቸዋል!!
        /ኢብኑ ተይሚያ/




https://t.me/hamdquante
👍19❤3
✍
ሷሊሖች ሲባል ወንጀል የማይነካቸው ፍጹም አይደሉም። ይልቁንስ፦

ወንጀላቸው የሚደብቁ እንጂ ግልፅ የማያደርጉ፤
ከወንጀላቸው የሚቶብቱ እንጂ የማይዘወትሩ፤
ድክመታቸው አምነው የሚሰባበሩ እንጂ የማይጥራሩ፤
ከስህተታቸው በኋላ ላበላሹት ነገር ማሳመሪያ የሚያስከትሉ ናቸው!!
             /ኢማም ኢብኑል ቀይም/



https://t.me/hamdquante
👍18❤5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🕋
 
  💥ሙእሚን የዛሬ ስራ ለነገ አያሳድርም!!💥


   ለነፍስህም ይሁን ለንብረትህ ዘውታሪነት ምንም ዋስትና በሌለው ዓለም ስትኖር፧ ብልህ ከሆንክ ዛሬ መስራት የምትችለውን ዛሬውኑ በመስራት ሙሉ ዋስትና ለተሰጠው ዘውታሪው ዓለም ተሰነቅ!!

🗓ከጥቅምት🥰🥰 እስከ ህዳር🥰 ለተያዘው ልዩ የዑምራ ፓኬጅ ምዝገባ ሊጠናቀቅ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።


   ዛሬ ማድረግ እየቻልክ ቀጣይ…… ቀጣይ…… የምትል ከሆነ ስላንተ ቀጣይነት እንኳ ዋስትና የለህም።

   ጤነኛ ሆነህ ደርሰህ የምትመለስበት ነፈቃ ካለህ ሁለቴ እንዳታስብ። አሁኑኑ ስልክህን አውጣና ወደ የለምለም ደውል!! ኢንሻ አላህ በዚህ ተግባርህ በፍጹም አትፀፀትም!!


📍3ቀናት መዲነቱል ሙነዋራ 7ቀናት መከተል ሙከረማ ቆይተን፤

📍በሁለቱም ሐረሞች ለሁለቱም መስጂዶች ቅርብ በሆኑ ሆቴሎች አርፈን፤

📍ሁለት ጁሙዐዎች በሁለቱ ሐረሞች ሰግደን፤

📍ከእንግልትና ከሙኻለፋ የጠራ ሱናውና አዳቡን የጠበቀ የተሟላ ዑምራ ፈፅመን፤

📍የዱንያም የአኼራም ፋይላችን በአጠቃላይ ሰብስበን የጉዳዮች ሁሉ ፈፃሚ ለሆነው ልዕለ ሀያሉ አላህ አስረክበን፤
    ከጉዞ ባሻገር የማይረሳ ውብና ምርጥ ትዝታ ያለበት ጊዜ አሳልፈን እንመለሳለን!!


💥ፓኬጁ ሦሥት ዓይነት የዋጋ አማራጭ አለው: በሚመቻችሁ መርጣችሁ ተመዝገቡ!!



   ኑ……… ትደሰታላችሁ!!

ስልኮቻችን ሁሌም ክፍት ናቸው;

➡️ 0911674580
➡️ 0911904297
➡️ 0922448888


በአካል ለምትፈልጉን;
  ቤተል ሚና_ሞል 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን!!

✈️የለምለም ትራቭል የትውልዱ ተስፋ!!
https://t.me/Yelemlem_travel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8👍1👌1🤝1
✍️
     የወንድማማችነት ዓይነቶች‼️

አንደኛው=> የዲን ወንድማማችነት፣
ሁለተኛው=> የስጋ ወንድማማችነት እና
ሦሥተኛው=> የጥቢ ወንድማማችነት ናቸው።

💫ከሁሉም ጠንካራው እና ፅኑው…
👇                                   👇
👉የዲን ወንድማማችነት ነው‼️


💫"የዲን ወንድማማችነት ከስጋ ወንድማማችነት የጠነከረ ነው። የስጋ ወንድማማችነት በዲን መለያየት ሊቋረጥ ይችላል; የዲን ወንድማማችነት ግን በስጋ መለያየት ሊቋረጥ አይችልም።"
    /ኢማሙ ቁርጡቢይ/


💫"በዲን መገናኘት በዝምድና ከመገናኘት የበለጠ ነው። በልብና በሩህ መቀራረብ በአካል (በስጋ) ከመቀራረብ ይበልጣል።"
    /ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ/




https://t.me/hamdquante
❤16🤝5👍2👌1
☝️
የአላህ ዕዝነት ተመልከቱ…………



አንዴ ጀነት የገባ ሰው በፍጹም ከጀነት አይወጣም።

ጀሀነም ከገቡት ውስጥ ግን በወንጀላቸው ልክ ተቀጥተው የሚወጡ አሉ።





https://t.me/hamdquante
💯24👍7❤6👌1
✍
  ባመለጠው ኸይር ተፀፅቶ፤ በቀጣይ ተኣምር ለመስራት ቃል ገብቶ፤ በፍጹም ጀግንነት ቃሉን የሞላወውና ምን አልባትም ከእሱ በስተቀር ለማንም ያልተገኘ ሙእጂዛ የተከሰተለት የ*** ድንቅ ታሪክ……………

:
:
:
:
:
:
     ደህና ቡና☕️ ከተገኘ ዛሬውኑ ይፖሰታል!!

👇 👇 👇
https://t.me/hamdquante
❤8✍7👍6🤝1
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
Photo
✍
ሀምሳ ቢወለድ ሀምሳ ነው ጉዱ
እንደ አነስ ያለ  ይበቃል አንዱ‼️


  የበድር ዘመቻ ረሱልﷺ በአካል ተገኝተው የተሳተፉበት የመጀመሪያው ዘመቻቸው ነበር። በእሳቸው የነብይነት ዘመን የመጀመሪያው ዘመቻ ከመሆኑ በተጨማሪ ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅትም ይሁን ስልጠና ሳይደረግለት በድንገት የታወጀ የጦር ዘመቻ ነበር።

   እንደምታውቁት ሙስሊሞች ለበድር ዘመቻ ሲወጡ ውጊያ አስበው ሳይሆን ያልታጠቁ ነጋዴዎች የሚነዱት የጠላት ሸቀጥ ለመማረክ ብቻ ነበር። ስለሆነም ለሙስሊም ዘማቾች ሰፊ ጥሪ ሳይደረግ፤ ሩቅ የነበሩት እስኪመጡ ሳይጠበቅ፤ ሌላው ይቅርና እዛው ተገኝተው ግን መጓጓዣቸው ሌላ ቦታ የነበረ ሰሓባዎች "መጓጓዣችን ሄደን እናምጣ" ሲሉ «አይሆንም!! እዚህ ያለ ሰው እዚሁ ያለ መጓጓዣ ብቻ ይዞ ይውጣ።» በሚል የረሱልﷺ ድንገተኛ ትዕዛዝ የተደረገ ዘመቻ ነበር። በመሆኑም ብዙ ከረሱልﷺ ጋ አንዲትም ጉዞ ወይም ዘመቻ እንዲያመልጣቸው የማይፈልጉ ሰሓቦች: በጊዜው እዛ ቦታ ላይ ባለመገኘታቸው ዘመቻው አምልጧቸዋል። ከእነርሱም ውስጥ ስሙ ጎልቶ የሚጠቀሰው;

   አነስ ኢብኑ ነድር የአነስ ኢብኑ ማሊክ አጎት ነው!!

  ረሱልﷺ በቅጡ ካልታጠቁና ጥቂት ባልደረቦቻቸው ጋ፤ በድር ላይ ጠብቀውት ከሄዱ ሌላ ገጥሟቸው፤ በእጥፍ እጥፍ የሚበልጣቸውና እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ብርቱ የቁረይሽ ሰራዊት ተዋግተው፤አላህ ያልተገመተና ያልተጠበቀ ድል አጎናፅፎ ወደ መዲና ሲመልሳቸው; አነስ ኢብኑ ነድር በቀጥታ ወደ ረሱልﷺ በመምጣት በድር ላይ ያለመሳተፉ ቁጭት በመግለፅ በቀጣይ ዘመቻ ከተገኘ ግን ተኣምር እንደሚሰራ በአላህ ስም ቃል ገባላቸው።

  "يا رسول الله غبتُ عن أول قتال قاتلت المشركين، لئن الله أشهدني قتال المشركين ليرينَّ الله ما أصنع"
  "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሽሪኮችን የተዋጉበት ዘመቻ አምልጦኛል፧ አላህ ከሙሽሪኮች በሌላ ዘመቻ ካገናኘኝ ምን እንደምሰራ አላህ ያያል" አላቸው።

  በዚህ መልኩ በቀጣይ የሚደረገው ሌላ ዘመቻ በጉጉት ሲጠባበቅ የቆየው አነስ ትልቁ የኡሑድ ዘመቻ ጦርነት ለመካፈል አላህ ወፈቀው። የኡሑድ ቀን ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ከደረሰ በኋላ ሸይጧን ያናፈሰው "ረሱልﷺ ሙተዋል" የሚለው የውሸት ዜና ሁሉም ጋ ተዳርሶ ነበር። ይህንን አስከፊ መርዶ የሰሙ የሙስሊም ወታደሮች የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው ተደነባብረዋል። በዚህ ጊዜ ነበር የዚህ የትልቅ ሰሓብይ ጀግንነት ጎልቶ የወጣው።

   ያልተጠበቀ የጠላት ምት ደርሶባቸው የነብያቸው መሞት የሰሙ ሙስሊሞች ግራ በተጋባና በተደናገጠ ስሜት ሆነው ከፊሉ ነፍሱን ለማትረፍ ሲያፈገፍግ ከፊሉ እዛው ጦርሜዳው መሃል ላይ ሆኖ ምን ማድረግ እንዳለበት ጠፍቶታል።

  ይህንን አሳዛኝ ክስተት የተመለከተው አነስ ኢብኑ ነድር ወደ ሰማይ ቀና አለና……

"اللهم إني أعتذر إليك مما صنع هؤلاء - يعني أصحابه - وأبرأ إليك مما صنع هؤلاء - يعني المشركين"
  ወደ ሙስሊሞች እያመላከተ "አላህ ሆይ! እነዚህ ከሰሩት ነገር ከአንተ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ወደ ሙሽሪኮች እያመላከተ "አላህ ሆይ! እነዚህ ከሰሩት ነገር ወዳንተ እጠራለሁ"  እያለ
   ከማፈግፈግ ይልቅ ሰይፉን አንግቶ በጀግንነት መንፈስ ወደ ፊት እየተራመደ ወደ ጠላት ግንባር ገሰገሰ።

   በዚህ ጊዜ [በአላህ ፍቃድ ሌላ ጊዜ ታሪኩን በሰፊው የምንዳስስለት ትልቁ ሰሓብይ] ሳዕድ ኢብኑ ሙዐዝ ያገኘውና "አነስ ሆይ! ወዴት ነህ?" አለው:
አነስ "እናንተስ ወዴት እየተመለሳችሁ ነው?" አለው።
  "ነብዩﷺ እኮ ተገድለዋል" አሉት።
አነስ በወኔና በጀግንነት "እሳቸው ከተገደሉማ ለየትኛው ሕይወት ነው የምትኖሩት??!! ሂዱና ነብያችሁ በሞቱበት ነገር ላይ ሙቱ!!" አላቸው።

  "እኔ እንደሆነ ከኡሑድ ተራራ ስር የጀነት ሽታ እየሸተተኝ ነው: ዞር በሉልኝ።" አላቸውና ጉዞውን ቀጠለ።

  ወደ ጠላት ጦር ጥሶ በመግባት ይህንን እየገደለ: ያንን እየቆረጠ: ከዚህም ከዝያም ሲፋየት ቆየና በመጨረሻም ለጌታውን የገባው ቃል በጀግንነት ሞልቶ፤ ወደ ሸተተችው ጀነት ተሸጋገረ ተሰዋ!!


   ውጊያው አብቅቶ የሸሒዶች ጀናዛ ሲሰባሰብ የእሱ ጀናዛ ማን እንደሆነ እንኳ ለይቶ ማወቅ አልተቻለም። ሰማኒያ ምናምን ቦታው በሰይፍ፣ በጦርና በቀስት ተወግቶ ሙሉ ሰውነቱ ማንነቱ እስኪያጣ ድረስ ተጫወቱበት። በስተመጨረሻም እህቱ መጥታ ስታገለባብጠው የእጆቹ ጣቶች ላይ የነበረው ምልክት አይታ እሱ መሆኑን አረጋገጠች።

አነስ ኢብኑ ነድር…………
   "ከኡሑድ ተራራ ስር የጀነት ሽታ ይሸተኛል" ያለበትን ገለፃ ከፊል የሐዲስ ሹራሖች ሲያብራሩት; "አነስ ይህንን ያለው ለጀነት ያለው ጉጉት ለመግለፅ ፈልጎ ብቻ ሳይሆን: በእውነትም የጀነት ሽታ አግኝቶ ነው። ይህ አላህ ለእሱ ሊያደርግለት የከበደ ነገር አይደለም።" ብለው ለአነስ አላህ ያደረገለት ከራማ ነው ብለው ይጠቅሳሉ።


  አነስ ኢብኑ ነድር ኡሑድ ላይ ከተሰዋ በኋላ ሰሓቦች እቺ አንቀፅ የወረደችው አነስና መሰሎቹን አስመልክታ ነው ብለው ይናገሩ ነበር;
{مِّنَ الْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ ۖ فَمِنْهُم مَّن قَضَىٰ نَحْبَهُ وَمِنْهُم مَّن يَنتَظِرُ ۖ وَمَا بَدَّلُوا تَبْدِيلًا}
   {ከአማኞቹ ለአላህ በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ፡፡ ከእነርሱም ስለቱን የፈጸመ (የተሰዋ) አለ፤ ከእነርሱም (ቃሉን ለመሙላት) የሚጠባበቅ አለ፡፡ (የገቡትን ቃል ኪዳን) መለወጥን አልለወጡም፡፡}
      [አል_አሕዛብ:²³]




https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤28👍12
👆
የዱንያው ጀነት ላሳያችሁ ብዬ ነው!!



.
❤28💯11👍9
👌
ማንም እኮ ነው ራሱን ማስደፈር የማይፈልገው👇

جلس أحد الشّيوخ بين طلابه يشرح "نُونيِّة القحطَاني" فلمَّا وصل إلى البيت القائل:

لا تحشُ بطنَك بالطَّعامِ تسمّناً
فجسوم أهل العلمِ غير سِمانِ


وكان الشيخ سميناً، فقال: هذا البيت محل نظر!




https://t.me/hamdquante
👌8❤3
✍
እጅግ በጣም ወሳኝ እና አሳሳቢ ግን ደግሞ ሁሉም ዘንድ
(አላህ ያዘነለት ሲቀር) የተረሳ የዒባዳ ዓይነት………
:
:
:
:
:
:
:
ፅሁፉ ከመለቀቁ በፊት ገምቶ በትክክል ለመለሰ የመጀመሪያው ሰው ሳምንታዊ የ1GB ፓኬጅ ይሸለማል!!



https://t.me/hamdquante
❤11
🤝
ሁላችሁም
جزاكم الله خيرا

ብዙ የረሳናቸው የተዘናጋንባቸው ነገሮች ጠቁማችሁናል።


እኔ ለዛሬ ልንዳስሰው የፈለኩት ነጥብ ከስር የማስቀምጥላችሁ ነው።
👇 👇 👇
✍13❤5
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
✍ እጅግ በጣም ወሳኝ እና አሳሳቢ ግን ደግሞ ሁሉም ዘንድ (አላህ ያዘነለት ሲቀር) የተረሳ የዒባዳ ዓይነት……… : : : : : : : ፅሁፉ ከመለቀቁ በፊት ገምቶ በትክክል ለመለሰ የመጀመሪያው ሰው ሳምንታዊ የ1GB ፓኬጅ ይሸለማል!! https://t.me/hamdquante
🤲
ዱዐእ አል_ኢስቲኻራ‼️


   ይህ እጅግ በጣም ወሳኝ አስፈላጊና ብዥታ ለፈጠሩ ጉዳዮች ሁሉ ፍቱን መድሃኒት የሆነው የዒባዳ ዓይነት: ዛሬ ላይ አላህ ያዘነላቸው ጥቂቶች ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም ሙስሊሞች ዘንድ የተተወ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ የተረሳ ትልቅ ሱና ዒባዳ ነው።

የዒባዳው ትልቀትና አሳሳቢነት ለማወቅ ቀጣዩን ሐዲስ እንመልከት…………
 
ትልቁ ሰሓብይ ጃቢር ቢን ዐብዱላህ ከአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ያስተላልፋል፦
📚 "كان يعلم أصحابه الاستخارة كما يعلمهم السورة من القرآن"
  "ለሰሓቦቻቸው ከቁርኣን አንዲት ምዕራፍ በሚያስተምሩት ልክ የኢስቲኻራ ዱዐ ያስተምሯቸው ነበር።"

  እንዲሁ እግረ መንገድ ወይም በሆነ አጋጣሚ ጠቅሰው ማለፍ ሳይሆን: ለቁርኣንን ትኩረት ሰጥተው በሚያስተምሩት ልክ የኢስቲኻራ ዱዐ ያስተምሯቸው ነበር።


🚫ምክንያቱም፦
  ሁሉም የሰው ልጆች ዐቅላቸው ቲንሽና ዕውቃተቸው ጠባብ ነው፤ ሁሉም ጉዳዮቻቸው ላይ የሚበጃቸውና የማይሆናቸው በትክክል ለይተው የመወሰን ዐቅም የላቸውም። ስለሆነም፧ ግልፅ የሆኑ ጉዳዮቻቸው ላይ በራሳቸው ሲወስኑ… ነገሩን ያጠራጠራቸውና የተምታታባቸው ጉዳይ ሲሆን በዚህ ዱዐ መሠረት ወደ ጌታቸው በማስጠጋት አላህ የተሻለውን እንዲመርጥላቸው ያደርጋሉ።

ዱዐኡል ኢስቲኻራ ማለት፦
   አላህ በግልፅ ሸሪዐ ደንግጎ ከወሰናቸው ጉዳዮች ውጪ: አንድ ሰው በዱንያ ሕይወቱ ላይ በሚገጥመው የሕይወት ጉዞ ሁለት ዓይነት ጉዳዮች ገጥመውት የቱን ይዞ የቱን መተው እንዳለበት ግራ ሲገባው ወይም የትኛውን መምረጥ እንዳለበት ግራ ሲገባውና መወሰን ሲያቅተው;
   በዚህ ዱዐ መሠረት ጉዳዩን ወደ ጌታው አስጠግቶ አላህን የሚያስመርጥበት የዒባዳ ዓይነት ነው።

ለምሳሌ፦
  ትዳር ለመያዝ ብሎ ሁለት ወይም ከዝያ በላይ አማራጮች ቢምታቱበት፣ የሆነ ሳንቲም ኖሮት ቤት ከመስራትና ስራ ከመጀመር የቱ ማድረግ እንዳለበት ቢምታታበት፣ ስደት ከመሄድና በሀገሩ ለፍቶ ከመስራት ቢምታታበት፣ እና በመሳሰሉት።


የዱዐው አደራረግ…………
  ለየትኛውም ሰላት በሚደረገው መልኩ የተሟላ ውዱእ ይደረግና ከፈርድ ሰላት ውጪ ለዚሁ ዱዐ ተነይቶ ሁለት ረከዐ ሰላት ይሰገዳል።
   ይህ ሰላት በቀንም ይሁን በምሽት በየትኛውም ጊዜ መስገድ ይቻላል: ሰላት መስገድ የተጠላባቸው ሦሥቱ ወቅቶች (ልክ ፀሀይ ስትወጣ፣ ፀሀይ ከአናት ትይዩ ስትሆንና ልክ ፀሀይ ስትገባ) ከእነዚህ ወቅቶች ውጪ በየትኛው ሰዓት ይሰገዳል።
   ሁለት ረከዐ ሰላት ተሰግዶ ከተሰላመተ በኋላ ከረሱልﷺ የተገኘው የኢስቲኻራ ዱዐ ይደረጋል። ከፊሎች ከማሰላመቱ በፊት ማድረግ ይችላል ቢሉም የተሻለው ግን ሰላቱን ካሰላመተ በኋላ ነው።


ከረሱልﷺ የተገኘው የኢስቲኻራ ዱዐ……………
🤲«اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْتَخِيرُكَ بِعِلْمِكَ، وَأَسْتَقْدِرُكَ بِقُدْرَتِكَ، وَأَسْأَلُكَ مِنْ فَضْلِكَ الْعَظِيمِ، فَإِنَّكَ تَقْدِرُ وَلَا أَقْدِرُ، وَتَعْلَمُ وَلَا أَعْلَمُ، وَأَنْتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ.
[እዚህጋ ጉዳዩን (ይህ ትዳር፣ ይህ ስራ፣ ይህ ጉዞ፣፣) እያለ ቀጥታ ይጠቅሰዋል]
اللَّهُمَّ إِنْ كُنْتَ تَعْلَمُ أَنَّ هَذَا الْأَمْرَ خَيْرٌ لِي فِي دِينِي وَمَعَاشِي وَعَاقِبَةِ أَمْرِي، فَاقْدُرْهُ لِي وَيَسِّرْهُ لِي، ثُمَّ بَارِكْ لِي فِيهِ.
وَإِنْ كُنْتَ تَعْلَمُ أَنَّ هَذَا الْأَمْرَ شَرٌّ لِي فِي دِينِي وَمَعَاشِي وَعَاقِبَةِ أَمْرِي، فَاصْرِفْهُ عَنِّي وَاصْرِفْنِي عَنْهُ، وَاقْدُرْ لِيَ الْخَيْرَ حَيْثُ كَانَ، ثُمَّ أَرْضِنِي بِهِ»

ትርጉሙ…………
🤲«አላህ ሆይ! በእውቀትህ አማካኝነት ከአንተ መሪነትን እፈልጋለሁ፤ በኃይልህም አማካኝነት ብርታትን እሻለሁ፤ ከታላቅ ችሮታህም እጠይቅሃለሁ። አንተ ኃይል አለህ: እኔ ግን የለኝም፤ አንተ ዕውቀት አለህ፣ እኔ ግን የለኝም። አንተ የሩቅ ምስጢራትን ዐዋቂ ነህ።
[እዚህጋ ጉዳዩን (ይህ ትዳር፣ ይህ ስራ፣ ይህ ጉዞ፣፣) እያለ ቀጥታ ይጠቅሰዋል]
   አላህ ሆይ! ይህ ጉዳይ ለእኔ በሐይማኖቴ፣ በኑሮዬ እና በነገሬ ሁሉ ውጤቱ መልካም እንደሆነ የምታውቅ ከሆነ: ለእኔ አስወስነው፤ አቅልልኝ። እንዲሁም በውስጡ በረከትን አድርግልኝ።
   ይህ ጉዳይ ለእኔ በሐይማኖቴ፣ በኑሮዬ እና በነገሬ ሁሉ ውጤቱ መጥፎ እንደሆነ የምታውቅ ከሆነ: ከእኔ አርቀው፤ እኔንም ከእሱ አርቀኝ።
  ከዚያም መልካም የሆነውን ነገር የትም ይሁን የት ለእኔ አስወስንልኝ፤ በመጨረሻም በእሱ እንድረካ አድርገኝ።»
         ተጠናቀቀ!!


💥ልብ መባል ያለባቸው ነጥቦች…………

🥇ኛ, ኢስቲኻራ የሚደረግበት ጉዳይ ዋጅብም ያልሆነ ሐራምም ያልሆነ ሙባሕ የተፈቀደ ነገር መሆን አለበት። ዒባዳ ልስራ ወይስ አልስራ ተብሎ ወይም ወንጀል ልስራ ወይስ አልስራ ተብሎ የሚደረግ ኢስቲኻራ የለም።

🥈ኛ, ኢስቲኻራ የሚደረገው ጉዳዩን ለአላህ ሰጥቶ የተቻለን ሰበብ ከመያዝ ጋ አላህ የተሻለው እንዲመርጥ ለማድረግ ነው እንጂ; ስውር የሆነ ሚስጥር (የሩቅ ነገር ለማወቅ) የሚደረግ ጥረት አይደለም።

🥉ኛ, ይህ ወሳኙና አሳሳቢው ነው፦
   አንድ ሰው ኢስቲኻራ ካደረገ በኋላ አላህ የመረጠለት የቱን እንደሆነ ለማወቅ ህልም ማየት አይጠበቅበትም፤ ወይም በመንገዱ ያንን ነገር የሚጠቁም ምልክት ማየት አይጠበቅበትም፤ ወይም የሆነ እንደ ወሕይ ወርዶ ሹክ የሚለው ነገርም አይጠባበቅም።
   ኢስቲኻራውን ካደረገ በኋላ ሙሉ ተወኩሉ በአላህ ላይ ያደርግና የተቻለውን ሁሉ ሰበብ በማድረስ አላህ ያገራለት የሆነውን ጉዳይ ላይ ይወስናል። ኢንሻ አላህ የወሰነው በተሻለው ጉዳይ ላይ ይሆንለታል!!


📍ያስተውሉ…………
ما خابَ منِ استخارَ ، و لا ندمَ منِ استشارَ
አላህን ያስመረጠ አይከስርም: ሰዎችን ያማከረ አይፀፀትም!!





https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤33👍8👌6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍
  ተው ልቤ ተመለስ   ወይ አካሌም ሳበው
የሩቅ ፍቅር ስቃይ  ውስጤን አቆሰለው።


በርሬ አልመጣ  አይደለሁ አሞራ
ልቤ ግን ይከንፋል  ስላንቺ🕋 ሲወራ!!




https://t.me/hamdquante
❤20👍13
✍
  የዕዝነት የፍትህ  የሰላም ተምሳሌት፣
  ከሰው ልጅ የላቁ  የክብር ባልተቤት፤



   ዛፉ እንደ ህፃን    ያለቀሰላቸው፣
ግመል ስሞታውን  የሚያሰማቸው፤
ድንጋይ ሰላምታውን  ያቀረበላቸው፣



   ስሞትን ሳወሳ   ልቤ ይፈወሳል፤
ሀሳብ ጭንቅ ቀርቶ  ሰኪና ይወርሳል!!



  አላህ ይወፍቀኝ  የእርሶን ጉርብትና፤
 በተውሒድ አኑሮ  ይውሰደኝ በሱና።



ሸፍዓዎት ያድለኝ         አላህ በዕዝነቱ
ከሐውድም ያጠጣኝ  ያስገባኝ ጀነቱ።



ሰላትና ሰላም  ይውረድ በሙሐመድ
በተከተላቸው   ሱናቸውን በመውደድ‼️




  🌙ﷺ🌙ﷺ🌙ﷺ🌙ﷺ🌙
📖{إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا}
  🌙ﷺ🌙ﷺ🌙ﷺ🌙ﷺ🌙




   https://t.me/hamdquante
❤22💯10🎉1🤝1
✍
አላህ ጥሎ አይጥለኝም አይባልም፤

አላህ አይጥለኝም ነው የሚባለው።




https://t.me/hamdquante
👍57💯3❤1