ኢማን በልብ ነው ሆኖም……………
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም ባህሪህ ኢማንህ ይገለፃል!!
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም አለባበስህ ኢማንህ ይገልፀል!!
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም አነጋገርህ ኢማንህ ይገልፀል!!
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም የስልክህ ጥሪ ኢማንህ ይገልፃል!!
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም የስልክህ wallpaper ኢማንህ ይገልፃል!!
ኢማን በልብ ነው፧ ሆኖም የፕሮፋይል ስቶሪህ ኢማንህ ይገልፃል!!
እንደ አደራ ዕቃ ልብ ውስጥ ተቀምጦ ውጫዊ አካሎች የፈለጉትን ቢሰሩ እሱ የማይነቃነቅ ቁስ ነው ማለት አይደለም።
መሠረቱ፣ ማረፊያው፣ መርጊያው፣ መቆጣጠሪያው ልብ ውስጥ ነው ማለት ነው።
ውጫዊ አካሎች የሚያደርጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለው ትዕዛዝ ነው። ልብህ ውስጥ ያለው ኢማን ከሆነ ገፅታ በኢማን ይመሰክራል።
https://t.me/hamdquante/11203
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍20❤12💯3
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
🇪🇹 What country is thi's??? ተኩስ፣ ፍንዳታ፣ ውጊያ ምናምን ያለው፧ መቀሌ፣ ውቅሮ አዲግራት ምናምን; መብራት የሚጠፋው የሚጨልመው ዓለም ባንክ፣ ስልጤ ሰፈር፣ ቤተል ምናምን¡¡ https://t.me/hamdquante/11200
መብራቱ በዚሁ ከቀጠለ………
የዳዕዋ ፕርግራም ሲኖር በቻናል ከመልቀቅ ይልቅ እንደ ዕድር ጡሩንባ ነፊ…… በየቂያሱ እየዞሩ መጣራቱ አዋጭ ሳይሆን አይቀርም።
እኔ እምለው ግን…………
https://t.me/hamdquante/11205
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍31❤6👌2✍1
Forwarded from አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
አቡ ዐብዱላህ ሙሐመድ አል_አንሲ አላህ ይጠብቃቸው።
🖥Play ▶️ ────◉ 1:20 AM
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio?livestream
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
↩ القناة الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة تعتني بنشر الخطب والمحاضرات والفتاوى والفوائد العلمية
↪️ ይህ በኢትዮጵያ በሱና ዱዓቶች የሚዘጋጁ ተከታታይ ትምህርቶች ሙሓደራዎችና አጫጭርና ጠቃሚ ፅሁፎች የሚቀርቡበት የአል ፉርቃን ኦፊሻል ቻናል ነው።
👇 ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት 👇
↪️ @Al_Furqan_Islamic_Studio_bot
↪️ ይህ በኢትዮጵያ በሱና ዱዓቶች የሚዘጋጁ ተከታታይ ትምህርቶች ሙሓደራዎችና አጫጭርና ጠቃሚ ፅሁፎች የሚቀርቡበት የአል ፉርቃን ኦፊሻል ቻናል ነው።
👇 ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት 👇
↪️ @Al_Furqan_Islamic_Studio_bot
👍4❤1
ስለ ዱንያ እና አኼራ ምንነት ከማንም በበለጠ ጠንቅቀው የሚያውቁት ነብያቶች ናቸው።
የትኛውም ነብይ አጀሉ በደረሰ ጊዜ መለከል መውት መጥቶ ሩሑን ከጀሰዱ ከመለየቱ በፊት "ዱንያ ላይ ከመቆየትና ወደ አኼራ ከመሻገር" የቱ እንደሚመርጥ እንዲያስመርጠው ከጌታው ይታዘዛል።
ከዱንያ መጠቃቀሚያ እና ከአኼራ የቱ እንደሚመርጥ ምርጫ ቀርቦለት ዱንያን የመረጠ አንድም ነብይ የለም!!
ዱንያ ላይ የመቆየት ዋነኛው ግብ ለአኼራ ለመሰነቅ ነው!!
https://t.me/hamdquante/11207
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍21❤6👌6💯2
ተውበት የዕድሜ ልክ ስራ ነው
በሕይወት እስካለህ ድረስ ሁሌም ተውበት ታደርጋለህ። አንዴ ቶብተህ አብቅቷል የሚባል ነገር የለም። ዛሬ ካጠፋህ ዛሬ ተውበት ታደርጋለህ፤ ነገ ብታጠፋ ነገም ተውበት ታደርጋለህ!!
በዚሁ መልኩ ይቀጥላል!!
/ከሸይኽ ሙሓደራ/
https://t.me/hamdquante/11208
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍26❤8
መሻኢኾች የሚመጡት ለጉብኝት ሳይሆን ለለውጥ ነው
የአካላችን ሁሉ ንጉስ የሆነው ልባችን ሊያክሙንና የሁልጊዜ ምኞታችን የሆነውን ጀነት መንገዱ በይበልጥ ሊጠቁሙን ብዙ ሀገራት አቋርጠው በሚመጡ ዑለማዎች መጠቀም የማንችልና በቸልታ የምናሳልፍ ከሆንን፧ ምን አልባትም በዚህ ሰበብ ሌሎች ፀጋዎችንም እንዳናጣ የሚያሰጋ ትልቅ ገፍላ ነው።
🤲አላህ ይወፍቀን🤲
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante/11209
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍18❤12💯9👌1
🕋 ✅ ልዩ የዑምራ ፓኬጅ🎁 ✅
🎙 11ኛውን ዙር የሚመራው ኡስታዝ
💥 surprise . ነው🎉
ሁለት ጁመአዎችን በሁለቱ ሐረሞች
ልብህ በተውባ፣
ገላህ በዘምዘም፣
🚨 ሩሕህም በሐረመይን ተረጋግቶ፤
ከዱንያ ጭንቀቶች ለጥቂት ቀናት ተላቀህ፣የዱንያና የአኺራ ሐጃህን ለሰሚው እና ለአዛኙ ጌታህ የምታቀርብበት ውብ አጋጣሚ
➡️ 🎓 የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎች ዝያራ
➡️ ✈ የደርሶ መልስ የአየር ትኬት
➡️ 🎓 የባስ ትራንስፖርት
➡️ 💳 አመታዊ የዑምራ ቪዛ
➡️ 🎓 የሆቴል ክፍያ
➡️ 🎁 አጠቃላይ የዑምራ ጉዞውን ያካተተ ልዩ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል
ጥቅምት2⃣ 6⃣ እስከ ህዳር 0⃣ 6⃣
November0⃣ 5⃣ –Nov1⃣ 5⃣
🫱 ይህንን ዕድል ሳያስመልጡ አሁኑኑ ይደውሉ! ፈጥነው ይመዝገቡ📝
🫱 0911674580
🫱 0911904297
🫱 0922448888
አድራሻ📍 ቤተል ሚና ሞል 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን።
✅ Telegram:
https://t.me/Yelemlem_travel
ከተወዳጁ የለምለም ትራቭል✈️
ሁለት ጁመአዎችን በሁለቱ ሐረሞች
ልብህ በተውባ፣
ገላህ በዘምዘም፣
ከዱንያ ጭንቀቶች ለጥቂት ቀናት ተላቀህ፣የዱንያና የአኺራ ሐጃህን ለሰሚው እና ለአዛኙ ጌታህ የምታቀርብበት ውብ አጋጣሚ
የረሱልﷺ ማረፊያ የሆነችው መዲነቱል ሙነወራ ጨምሮ
ጥቅምት
November
ኢንሻአላህ ያማረ ቆይታ ይኖረናል
አድራሻ
https://t.me/Yelemlem_travel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
✈️ የለምለም ትራቭል ✈️
✅ የለምለም ትራቭል ⤵️
🤝 ቪዛ ... ትኬት ... ሆቴል እና በወሳኝ ሰዓት ላይ ወሳኝ እና አስፈላጊ የዑምራ ፓኬጆችን በተመጣጣኝ ዋጋ እናዘጋጃለን።
✈ https://t.me/Yelemlem_travel
🤝 ቪዛ ... ትኬት ... ሆቴል እና በወሳኝ ሰዓት ላይ ወሳኝ እና አስፈላጊ የዑምራ ፓኬጆችን በተመጣጣኝ ዋጋ እናዘጋጃለን።
✈ https://t.me/Yelemlem_travel
👍7❤3👌1
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
👆
የሸይኽ ነሲሀ ላይ ዳሰሳ ተደርጎበታል!!
[ስለ ሙእሚን ክብር]
የሸይኽ ነሲሀ ላይ ዳሰሳ ተደርጎበታል!!
[ስለ ሙእሚን ክብር]
👍9❤3
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
✍ ዕለተ ሰኞ…… ረሱልﷺ ዱንያን ለመጨረሻ ጊዜ የተሰናበቱባት ዕለት። በዚህ ቀን አቡበክር ሲዲቅ ለሙስሊሞች ኢማም ሆኖ የፈጅር ሰላት እያሰገደ ነበር። እየሰገዱ ሳሉ ረሱልﷺ ከዓኢሻ ክፍል መጋረጃውን ከፈት አርገው አዯቸው። ሰሓቦቻቸው በተስተካከለ ሰፍ ከአቡበክር ጀርባ ቆመው ሲሰግዱ ተመለከቱ። ይህንን ሲያዩ በደስታ ፈገግ ብለው ሳቁ። ሙስሊሞችም የረሱል ፊት ዐይናቸው ላይ ሲገባ ሰላታቸው…
👆
የሸይኽ ነሲሀ ላይ ዳሰሳ ተደርጎበታል!!
[በተለይ ስለ ዑመር መውቂፍ]
የሸይኽ ነሲሀ ላይ ዳሰሳ ተደርጎበታል!!
[በተለይ ስለ ዑመር መውቂፍ]
👍9
ወንጀል ስትሰራ ከምታገኘው የእርካታ ጥፍጥና;
ወንጀሉ ከሰራኸው በኋላ የሚሰማህ የቁጭት ህመም በእጥፍ ይበልጣል
https://t.me/hamdquante/11213
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍45💯11❤6👌6
{(እኛ) ባናፀናህ ኖሮ ወደነሱ ጥቂትን (ዝንባሌ) ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር፡፡}
ትልቁ የቁርኣን ሙፈሲር ቀታዳ እንዲህ ይላል፦
ይህንን አንቀጽ ከወረደ በኋላ ነብዩﷺ «🤲አላህ ሆይ ለዐይን ቅጽበት ያህል እንኳ ወደራሴ አታስጠጋኝ» እያሉ ዱዐ ያደርጉ ነበር።
https://t.me/hamdquante/11214
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10❤5
ከሰዎች ሁሉ ክፉው ማን ነው? ሲሉት;
መጥፎ ጥርጣሬ ስላለው ማንም የማያምንና
መጥፎ ባህሪ ስላለው ማንም የማያምነው ሰው ነው አለ።
https://t.me/hamdquante/11215
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍17❤7💯4
{ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ።}
☝️አላህ እውነተኞቹ ወደ አዕላ ኢሊዪን ከፍ ሲያደርጋቸው፤ ከሀዲና ውሸታሞች ወደ አስፈለ ሳፊሊን ዝቅ ያደርጋቸዋል!!
በዱንያ ቆይታ ላይ ያላቸው ሹመት፣ ያገኙት ማዕረግ፣ ዝናም ይሁን ሀብታቸው አይሸንግልህ።
አኼራ ላይ ትክክለኛው፣ እውነተኛውና የመጨረሻው ደረጃቸው በመስጠት ታስተካክላቸዋለች።
ያኔ…………
እውነተኛው ከፍታ የሚገባው ለማን እንደሆነና ለማን እንደማይገባው በእርግጥም ትመለከታለህ!!
ዱንያ ላይ የነበሩ መመዘኛዎች ከንቱ መሆናቸውም ያኔ ትገነዘባለህ!!
📖{فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ}
{ከእሳት የተራቀና ጀነትን የገባ በእርግጥም ምኞቱን አሳክቷል: የዱንያ ሕይወት ማታለያና መሸንገያ እንጀ ሌላ አይደለችም።}
https://t.me/hamdquante/11216
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8👍8
ይህንን ሁሉ ለጨዋታ ነውን
ከዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ስለ አፈጣጠር በተላለፈው ሐዲስ፦
«……ثم يرسل إليه الملك فينفخ فيه الروح، ويؤمر بأربع كلماتٍ……»
«……ከዝያም ወደሱ መላኢካ ይላክና ሩሕ ይነፋበታል፤ አራት ነገሮች (እንዲፅፍም) ይታዘዛል……»
አላህ እንዳለው፦
{وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ}
{በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች አሉ።}
{كِرَامًا كَاتِبِينَ}
{የተከበሩ ፀሓፊዎች የሆኑ።}
አላህ እንዳለው፦
{قُلْ يَتَوَفَّاكُم مَّلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ}
{ያ በእናንተ ላይ የተወከለው መለከል መውት ይገድላችኋል፤ ከዝያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ በላቸው።}
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈው ሐዲስ ስለ ቀብር ክስተት ሲናገሩ፦
« إِذَا قُبِرَ الْمَيِّتُ …… يُقَالُ لأَحَدِهِمَا الْمُنْكَرُ وَالآخَرُ النَّكِيرُ
«አንድ ሟች ሲቀበር ሁለት መላኢካዎች ይመጣሉ…… አንዱ ሙንከር ሲባል ለሌላኛው ነኪር ይባላል።»
አላህ ከጅምራችን እስከ መጨረሻችን ታማኝና ታዛዥ የሆኑ መላኢካዎቹ በእኛ ላይ መድቦ እንዲህ የሚንከባከበን እና የሚቆጣጠረን እንዲሁ ዝም ብሎ ለጨዋታ ሊሆን ይችላልን??
ላ ወላህ! ይህማ ለጨዋታ ሊሆን አይችልም
ባይሆን ግን አላህ እኛን የፈጠረበት ትልቅ ዐላማ ስላለው ያንን ዐላማ የጠበቀ አስደሳች በሆነ ምንዳ ሊመነዳውና
ላማውን የተቃረነ አሳማሚ በሆነ ቅጣት ሊቀበለው ነው።
ይህ ትልቁ ዐላማ ደግሞ
👇
👉ለአላህ ብቻ ባርነትን ማረጋገጥ ነው
https://t.me/hamdquante/11217
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12👍8💯8👌2✍1
✍
ተው ልቤ ተመለስ ወይ አካሌም ሳበው
የሩቅ ፍቅር ስቃይ ውስጤን አቆሰለው።
ወይ ተነስቼ አልሄድ ወይ አርፌ አልተኛ
በየት አርጌ ልሂድ⁉️ እንዴትስ ችዬ ልተኛ ⁉️
https://t.me/hamdquante/11218
ተው ልቤ ተመለስ ወይ አካሌም ሳበው
የሩቅ ፍቅር ስቃይ ውስጤን አቆሰለው።
ወይ ተነስቼ አልሄድ ወይ አርፌ አልተኛ
በየት አርጌ ልሂድ
https://t.me/hamdquante/11218
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤34👌1
Forwarded from 🕋 ኢቅራእ የኡምራ ትራቭል ኤጀንሲ 🕋
🔶 ነይቻለው ጌታዬ 🔶
---------------------------
🕋 🕋 🕋 🕋 🕋 🕋
ነፍሴን ላሳርፍ ከዱንያ ጣጣ
ነይቻለው ቤትህ ልመጣ
ለብሼ የኢህራም ፎጣ
ይሁን በለኝ ኒያዬ ይሙላ
ወፍቀኝ ሁንልኝ ጋሻ ከለላ
ለቤትህ ክቡር እንግዳ አርገኸኝ
ለክብርህ ሱጁድ መውረድ ናፈቀኝ
ቀይ ባህርን በአየር ቀዝፌ
ለሶስት ቀን መዲና አርፌ
ዙል ሑለይፋ ላይ ለብሼ ፎጣ
ናፍቆኛል ሀረም ዘምዘም ልጠጣ
መኪናው በተልቢያ ሲናጥ
ሸይጧን ሲቆስል ሲላጥ
ዛፍ ቅጠሉ ሳይቀር አብሮ
ወዱድ ሲወሳ ተከብሮ
በቀኝም ያለው በግራ
ካንተ ጋር ይላል ተክቢራ
ለበይክ እያሉ ነሽጦ
መንገዱን በባስ አቋርጦ
ከሀረም ክልል ሲደረስ
እርግት ስትል ያቺ ነፍስ
ለጠዋፍ ሀረም ስትገባ
አይንህ ሲሞላ በእምባ
አክብረህ ቤትህ ጠራከኝ
ያረሒም ባክህ ታረቀኝ
እስተው ሲባል ለሰላት
ሀረም ላይ በፊት መደፋት
ምን አለ ክብር እልቅና
የሚሻል ከዚህ ጎዳና
ከሪም ነው ጌታዬ ሶመድ
መቶ ሺ አንዴ ሲሰገድ
ሊሰጥህ አጅር አጣጥፎ
ቃል ገብቷል አለ ተፅፎ
አስተውል ሞትን አትርሳ
ነወይቱ በል ነሽጥ ተነሳ
በኢቅራእ ትራቭል
ወደ ኡምራ እንኮብልል !!
✍️ አቡ ዘይድ ዐሚር ሙሀመድ
-----======-------=====-----
https://t.me/iQRA_TOUR_AND_TRAVEL
---------------------------
🕋 🕋 🕋 🕋 🕋 🕋
ነፍሴን ላሳርፍ ከዱንያ ጣጣ
ነይቻለው ቤትህ ልመጣ
ለብሼ የኢህራም ፎጣ
ይሁን በለኝ ኒያዬ ይሙላ
ወፍቀኝ ሁንልኝ ጋሻ ከለላ
ለቤትህ ክቡር እንግዳ አርገኸኝ
ለክብርህ ሱጁድ መውረድ ናፈቀኝ
ቀይ ባህርን በአየር ቀዝፌ
ለሶስት ቀን መዲና አርፌ
ዙል ሑለይፋ ላይ ለብሼ ፎጣ
ናፍቆኛል ሀረም ዘምዘም ልጠጣ
መኪናው በተልቢያ ሲናጥ
ሸይጧን ሲቆስል ሲላጥ
ዛፍ ቅጠሉ ሳይቀር አብሮ
ወዱድ ሲወሳ ተከብሮ
በቀኝም ያለው በግራ
ካንተ ጋር ይላል ተክቢራ
ለበይክ እያሉ ነሽጦ
መንገዱን በባስ አቋርጦ
ከሀረም ክልል ሲደረስ
እርግት ስትል ያቺ ነፍስ
ለጠዋፍ ሀረም ስትገባ
አይንህ ሲሞላ በእምባ
አክብረህ ቤትህ ጠራከኝ
ያረሒም ባክህ ታረቀኝ
እስተው ሲባል ለሰላት
ሀረም ላይ በፊት መደፋት
ምን አለ ክብር እልቅና
የሚሻል ከዚህ ጎዳና
ከሪም ነው ጌታዬ ሶመድ
መቶ ሺ አንዴ ሲሰገድ
ሊሰጥህ አጅር አጣጥፎ
ቃል ገብቷል አለ ተፅፎ
አስተውል ሞትን አትርሳ
ነወይቱ በል ነሽጥ ተነሳ
በኢቅራእ ትራቭል
ወደ ኡምራ እንኮብልል !!
✍️ አቡ ዘይድ ዐሚር ሙሀመድ
-----======-------=====-----
https://t.me/iQRA_TOUR_AND_TRAVEL
❤16🤝4👌1