ʜᴀᴍɪᴅ ᴛᴇᴄʜ ™
3.97K subscribers
3.78K photos
134 videos
213 files
1.61K links
Creator || @hamidleo16

🌏ሰላም የHamid tech ቻናል ቤተሰቦች

ይህንን የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል👇👇

►አዳዲስ የቴክኖሎጅ ጥቆማዎችን
►airdrop/web
►የአፕሊኬሽን ማውረጃ ሊንኮችን ያገኙበታል

◈◈SOCIAL MEDIA LINK ◈◈
▻TIKTOK◍►hamid_tech1
▻YOUTUBE◍►hamidtech10

Buy ads: https://telega.io/c/Hamidtech10
Download Telegram
"የዋትሳፕ አካውንታችን እንዳይጠለፍ ማድረግ የሚገቡን ጥንቃቄዎች"

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ዋትሳፕ
#WhatsApp ለስራ፣ ለቤተሰብ ግንኙነት እና ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች እጅግ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል።

ሆኖም ግን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያውያንን የዋትሳፕ አካውንት ለመጥለፍ የሚሞክሩ የመረጃ መንታፊዎች የግል መረጃዎቻችን እና ሚስጥራዊ ንግግሮቻችን እንዳይመነተፉና እንዳንጭበረበር የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥንቃቄዎች መተግበር ያስፈልጋል።

👉ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ
#Two_Step_Verification) ፡
በዋትሳፕ Settings > Account ውስጥ ገብተው ባለ 6 ድጂት ሚስጥር ቁጥር
#PIN ይቆልፉ። ይህ በጣም አስፈላጊው መከላከያ ነው።

👉ዋትሳፕ የሚልክልዎትን ኮድ ለማንም አለመስጠት፡
በኤስኤምኤስ
#SMS የሚመጣላችሁን የዋትሳፕ መክፈቻ ኮድ ወደ "ግሩፕ ማስገቢያ ነው" ወይም "ለሽልማት ነው" ለሚሉ አጭበርባሪዎች በፍጹም አይስጡ።

👉ሊንኮችን አለመክፈት፡
"ነፃ የካርድ ስጦታ" ወይም "የስራ እድል" በሚል የሚመጡ አጠራጣሪ ሊንኮችን አይክፈቱ መረጃዎን ሊሰርቁ ይችላሉ።

👉የግላዊነት
#Privacy ቅንብር ማስተካከል፡
Settings > Privacy ገብተው ፕሮፋይልዎን እና ግሩፕ ውስጥ እርስዎን ማስገባት የሚችሉ ሰዎችን "My Contacts" ብቻ ያድርጉ።

👉የተገናኙ መሳሪያዎችን
#Linked_Devices መፈተሽ፤
አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ሳያውቁ ስልክዎን ለጥቂት ደቂቃ ያገኘ ሰው የዋትሳፕ ዌብ
#WhatsApp_Web በራሱ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ ከፍቶ መልእክትዎን ሊከታተል ይችላል።


መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ለወዳጅ ዘመድዎ #Share ያድርጉ!