Hasen Injamo
15K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
393 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
ሁለት ዓይነት የኢምፖርት cost 💲💲 ስሌት አለ:: አንደኛው የኢምፖርተሩ ሲሆን ይህም በደቂቃዎች ውስጥ ትርፍና ኪሳራ ለማስላት የሚያስችል Lazy-man calculation 🧮 ነው:: ስልጠናም ላይ እዚህኛው ላይ ነው የምናተኩረው:: ይህ በእጅ, በእርሳስ, በሞባይል, አለፍ ሲልም በ Excel ሊሰላ የሚችል ነው:: በምንም አስላው ሲስተሙ ያው ነው:: ሁለተኛው ከጉምሩክ ጀምሮ እስከ ገቢዎች ኦዲት, ከአካውንታንት እስከ ባንክ ሪፖርቶች የሚመለከቱት እና ሰነዱ እስከ 10 ዓመት አርካይቭ መገኘት ያለበት ነው:: ይህ ለነጋዴው ትእግስት አይሆንም:: ቢሆንም ግን ሁለቱም ሳይጋጩ መናበብ አለባቸው:: በዌብ ፖርታል ሠርተነዋል:: ግን ለነጋዴው አይመችም:: ስለዚህ ሁለቱንም ያጠቃለለ Excel ነበር የምንሰጠው:: አሁን በጣም አዘምኘዋለሁ:: ስለዚህ ከፊታችን የኢምፖርት ስልጠና ቀን ጀምሮ ይለቀቃል:: ቀድማችሁ የሰለጠናችሁም በተቻለ መጠን ለመላክ እሞክራለሁ:: አብሽሩ ለሰልጣኝ ክፍያ የለውም:: ብችል ደግሞ ለቀድሞ ሰልጣኞች በዙም ባብራራላችሁና ደስ ባለኝ:: ያው ልትጭኑ ስትመጡ የከበዳችሁ ፓርት ካለ እናየዋለን::

(ፎቶ:- የኢምፖርት ዋጋ ማስሊያ ዝርዝር ገጽ መግቢያ)
❤8
ቲክቶክ ግን ሲጨንቅ ወላሂ:: ስክሮል እያደረግህ ሳትፈልግ መጦዝ ነው:: ፌስቡክ እኮ አይንቀዠቀዥም:: ዓይንን አይወሰውስም:: በቀልምና በምስል ተንቀልቅሎ ልብህን አያስገድድብህም:: ቲክቶክ የግድ የሆነ መልእክት ያላችሁ ሰዎች እንደ ካካ ጣል አድርጋችሁና ውኃ ደፍታችሁ ማለቴ logout ተጭናችሁ መጥፋት ነው:: ኮሜንትና ኢንቦክስ ዘግቸዋለሁ:: ስክሮል ስታደርግ ውለህ ምን እንደተማርክ የት እንደዋልክ ይጠፋብሃል::
😢62
የምትሸጡትን እቃ
ቀድማችሁ ለዩ
=======
ኢምፖርት ቢዝነስ ቀላል እንዳይመስላችሁ:: ከፍተኛ ውድድር እና ከፍተኛ መጭ^በርበር ያለበት ሰፈር ነው:: በየትኛውም stages ላይ ገንዘብ ከመክፈላችሁ በፊት የሰዎቹን ማንነት አጣሩ:: ለማንም ሰው ይህንን ያህል ብር አለኝ ምን ልሥራ ባትሉ ይመከራል:: አትመካከሩ እያልኩ አይደለም:: ብር ጋር ሲደርስ ጠንቀቅ ማለት ነው:: ገራሚ ትርፍ ካሳዩዋችሁ ችግር አለ:: በዚህ ብር ምን ልጫን? ተብዬ በተደጋጋሚ እጠየቃለሁ:: እንዲህ ለሚለኝ ሰው "ሲጀመር ይህ ያህል ብር እንዴት እዚህ ጋር ደረሰ? ምን ሠርተህ ነው ያመጣኸው?" ነው ልለው የምችለው:: ምክንያቱም ሥራን የሚያውቅ ሰው ምን ልጫን አይልም:: ቢልም ዋነኛ ሥራ መጫን ሳይሆን መሸጥ መቻል ነው:: የማትሸጠውን ዕቃ እንዴት ልትጭነው ነው? ንግድ ፈቃድ ከማውጣት ጀምሮ መዘጋጀት ይፈልጋል:: ዛሬ የጫንከው እቃ ሰነድ እስከ 10 ዓመት ማስቀመጥ አለብህ:: ይህንን ለመሸሽ በሌላ ሰው ማለትም በኪራይ ንግድ ፈቃድ መጫን የራሱ ሪስክ አለው:: ሁሌ መጠያየቅ ሁሌ መረጃ ማነፍነፍ የግድ ይላል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርተህ ከቆምክማ አበቃልህ:: ገብተህ መታገል ነው:: የባሕሩን ጥልቀት በአንድ እግርህ ለካ::
❤37
ኢምፖርተር የሚሆነው እቃውን መሸጥ የሚችል ሰው ብቻ ነው:: <<ብቻ>> የሚለው ቃል ስጠቀም እርግጠኛ ሆኜ ነው:: ከመርካቶ ሳሪስ ወስደህ ለመሸጥ ትልቁ ልፋት ከመርካቶ ማምጣቱ ሳይሆን ላልታወቁ ለወደፊት ዓመታት ሳሪስ ላይ ከደንብ, ከደንበኛና ከተወዳዳሪ ጋር ታግለህ አትርፈህ ሽጠህ ቅርንጫፍ ለመክፈት መቻል ማለት ነው:: ኢምፖርተር ከመሆንህ በፊት የግድ ኮንሲዩመሮችህን ማለትም እቃህን የሚገዙህ ተጠቃሚዎችህን ማወቅ አለብህ:: ዘው ብለህ ገብተህ እቃ ካመጣህ "አሕያ ያረጀበት ሰው" ትሆናለህ:: አሕያህን አታ^ርደው, አትጭነው, አትጥለው ነገር ይሆንብሃል:: ላስፈራራችሁ ሳይሆን ትልቁ ሥራ ያለው ቻይና ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው:: መሸጥ ከቻልክ ሌላው ቀላል ባይባልም ከባድ አይደለም:: ካልኩለሱ እዚሁ እኛው ሀገር ነው:: እዚያ እኮ የእቃ ውቅያኖስ ነው ያለው:: ከውቅያኖሶች ወይም ወንዞች ጨልፈህ መምጣቱን አያሳስብህ:: እኛ አለን:: ካንተ ግን ሁለት ነገር እንፈልጋለን:: መሸጥ መቻል እና መነሻ ካፒታል:: ከካፒታልህ ጋር ንክኪ አይኖረንም:: በስንት እንደምትሸጠው አናውቅም:: ያንተ ምስጢር እና ሀጃ ነው::

(ምሥጢርህን መጠበቅ ዋነኛ ካፒታላችን መሆኑንም ማስታወስ ያስፈልጋል)
👏16
Live stream scheduled for
ዛሬ ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ? በሚል ርዕስ Live ይኖረናል:: ቀጣይ ሲስተሙ በዚህ እየከፈለን ስለሆነ ጎራችንን ለመለየት ይረዳናል:: ሲስተሙ እየቆለፈና እያጠበበ ነው::
🔥20
Live stream started
Live stream finished (55 minutes)
ዛሬ የነበረው የ Live ፕሮግራም አንኳር ነጥቦች
🫡9
Audio
የግብርና ባንክ በኢትዮ FM 📻 107 በዓብዱልቃዲር ኑረዲን ከእስከዳር ጋር
❤21
የባንክ ሒሳባችሁ ከታገደ ከንግድ ፈቃድ ጋር የተያያዘ ሊሆን ስለሚችል TIN እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ይዛችሁ የከፈታችሁበት ባንክ ሄዳችሁ ማስለቀቅ ትችላላችሁ:: ምክንያቱም ከንግድ ፈቃድ ጋር ያልተያያዙ የባንክ አካውንቶች ላይ ብሮች ሲዘዋወሩ ሲስተሙ እየዘጋ ነው::

ቀጣይ አቅጣጫ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መቀጠር የሚል ነው:: የቀጣሪነት ወይም የተቀጣሪነት እድላችሁን እራሳችሁ ናችሁ የምትወስኑት:: መቼለት ቴሌግራም "ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ?" Live ፕሮግራሜ ይህንን የተመለከተ ነበር:: የባንኩንም አንስቼዋለሁ:: ወይ ድርጅት ከፍተህ ቀጣሪ ትሆንና እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ በደረሰኝ ይሆናል ወይ ተቀጣሪ ሆነህ ገቢህ በፔይሮል ይሆናል:: (መ-ገንዘብ 2 ስለዚህ ጉዳይ ነው የሚያወራው)::
❤23
በግል ሴቪንግ የሚንቀሳቀስ ምንጩ ያልታወቀ እንቅስቃሴ የባንክ ሲስተም Block እና Lock 🔒 እያደረገ ነው:: በዚህ ወቅት የገቢህ ምንጭ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ እየሆነ ነው::

1ኛ) ንግድ ፈቃድ አውጥቶ በደረሰኝ የገቡ ገቢዎች
2ኛ) ተቀጥሮ በደመወዝ እና አክሲዮን ገዝቶ በዲቪደንድ መልክ ነው የሚሆኑት
ሌሎች ገቢዎች እንኳ ቋሚ ስላልሆኑ ብዙ ምድብ አናወጣላቸውም::
_____
በችርቻሮም ይሁን ጅምላ ንግድ ተሠማርታችሁ ግን ከኢምፖርተር የምትረከቡ ምእመናን የኢምፖርት ስልጠናው ይመለከታችሗል:: በ Less than Container Load (LCL) ሞድ ለምሳሌ 2 ሜትር ኪዩብ (CBM) መጫን ብጀምሩ ሲስተሙን ትለማመዱበታላችሁ:: (የተለያዩ መጠኖች ያሉዋቸው የመርከብ 🚢 ኮንቴይነሮች አሉ:: መደበኛዎቹን ብንወስድ ቮሊዩም ላላቸው እቃዎች ባለ68 ሜት ኪዩብ እና ለባለክብደት እቃ 28 ሜትር ኪዩብ በሚል ያዙት):: ስለዚህ በጣምራ አንዱን ሞልቶ ማምጣት ይቻላል:: ታዲያ አሁን ላይ ንግድ ፈቃድ የግድ ብሏል:: ባላችሁ ፈቃድ ላይ ኢምፖርት ታክሉበታላችሁ ከሌላችሁም ታወጣላችሁ:: ያው የራሱ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት:: እንዴት እንደሚቀናጅ እና ፈቃድ እንዴት እንደሚወጣ ስልጠናዎቻችን ላይ አለ:: ሁሉንም በባለ ሙያ ነው:: Almost ሞልቶ ሊዘጋ ስለሆነ ግቡለት:: ዝርዝር በኮሜንት አለ:: ዊዝሆልድ የምትቆርጡ ተመዝጋቢዎች ቆርጣችሁ አስገቡና የዊዝሆልድ ደረሰኙን አምጡልን::
❤12
የኢትዮጵያ ባንኮችን ብድር ሢሦ የሚበደሩት አስር ሰዎች ናቸው:: የዓለም 75% ሀብት የተያዘው አስር ፐርሰንት በማይሞሉ ሰዎች ነው:: ይህ ለምን እንደሆነ በመ-ገንዘብ መጽሓፍ በደንብ ተብራርቷል:: እኔ ሲስተሙ ምን እንደሚመስል ከእነመፍትሔው ጽፌያለሁ:: ብዙ ጸሓፍትም ጽፈዋል:: ከየትኞቹ እንደምንሆን ውሳኔው የየግላችን ነው::
👍17
ሀጂ የደመወዝ መዳረሻ ከቴሌብር ብበደር ሀራም ይሆናል ወይ?

-> መድረስ ከቻልክ ችግር የለውም:: ዋናው ትደርሳለህ ወይ ነው ነጥቡ:: ከ10 ዓመታት በላይ ስናገር ኖሬያለሁ:: ይህኛው የፋይናንስ ሲስተም ሲበዛ ጨካኝ ነው:: ከወለድ ነጻ ይመጣል ብለህ አትጠብቅ:: መቼም አይመጣም:: ትናንትና እንደማይመጣው:: ከመደበኛው ቢብስ እንጂ አይሻልም:: ስለዚህ ከደመወዝ መበደሩን እርሳው:: ጉዳዩ ቤት አስይዘህ ከንግድ ብትበደርም አትደርስበትም:: በዚህ ሦስት ዓመት እኔም አንተም ፈጥነን ንብረት እንያዝ:: የማይፈራ ዑለማእ ቢኖር ጥሩ ነበር:: አንዳንዶቹ ካንተ የባሰ ቸግሯቸው ጺም እና አማማ ለባንክ እያከራዩ ናቸው:: ጭራሽ ባንተ ድህነት ላይ ፎቅ ይገነባሉ:: ፑ! ደህና የምትላቸው ዑለሞች ደግሞ ትንሽ ትንፍሽ ቢሉ በጺም አከራዮቹ ይሰ^ደባሉ:: ስ^ድቡን አይችሉትም:: እኔም ቆዳዬ አደንድኜ ሰ^ዳቢዎችን ቦልኬ ነው የተቋቋምኩት:: በዚያኛው ፌስቡክ አካውንቴ እኮ 5K የሚደርስ ተቦላኪ አለ::

መቸም ደመወዝ መዳረሻ ጠየቅኸኝም አይደል? መንግሥት እያለልህ ከመሥሪያ ቤት ጓደኛም ይሁን ከዘመድ አትበደር:: ለግለሰቦች ነውርህን ትዘከዝካለህ:: ኢማን እና ታማኝነትህን አስይዘህ ነው የምትበደረው:: ደመወዝተኛ በነበርኩ ወቅት እንዴት እንደሚጨንቅ አውቀዋለሁ:: ቴሌብር ስለኢማንህ አያገባውም:: በሰከንዶች ያበድርሃል:: ነውርህን ይሸፍንልሃል:: ከዚህ አዙሪት ግን ቶሎ ውጣ:: ጊዜ የለንም:: ሲስተሙ እየቆለፈ እየመጣ ነው::
❤60
ፌስቡክ ላይ ሂዱበት:: በነጻ ማስተዋወቅ ማለቴን ነው::

https://www.facebook.com/share/19cJ6SeifV/?mibextid=wwXIfr
❤3
ኢምፖርት በዚህኛውም ዙር ወዲያው ሞልቷል:: የሚገርመኝ የሪፈራል ሰው ይበዛል:: ማለትም በጥቆማ የሚመጣ ... ከሌላ ስልጠናችን ዞሮ የሚገባ:: አቦ ሀብታም ያድርጋችሁ:: ከዚህ በፊት የሰለጠናችሁ ደግሞ የምንገናኝባቸው መድረኮች ይኖሩናል::

የኢምፖርት ሒሳብ ማስሊያ Microsoft Excel አሪፍ አድርጌ ሠርቸዋለሁ:: ትንሽ ማስተካከያ ይፈልግ ስለነበር ሰሞኑን እሱ ላይ ነበርኩ:: አስተካክዬ ጨረስኩ:: ምክንያቱም በሁሉም ሴናሪዮ ቼክ መደረግ እና ቀለል ማድረግ ይጠይቃል:: ለአንድ ኢምፖርት የሦስት ሀገራት መገበያዎች እና ሁለት ዓይነት ክፍያዎችን በቀላል አገላለጽ ማቀናጀት ቀላል አይደለም:: ደረሰኝ ያላቸው እና የሌላቸው ክፍያዎች አሉ:: ሁሌም ይኖራሉ:: እነዚህ ሁለቱም ወጪዎች ቴክኒካሊ የዕቃው አካል ናቸው:: ደረሰኝ ኖሮኣቸው እንኳ የማይያዙልን አሉ:: ከአየር መንገድ የበረራ ደረሰኝ ይዘህ ገቢዎች "የሄድከው ልትዝናና ቢሆንስ?" ሊልህ ይችላል:: ሁሉም ነጋዴ ደግሞ ወጪውን ሸፍኖ ማትረፍ ይፈልጋል:: አንድ አፕልኬሽን ሲዘጋጅ ሙሉ መስመሩን የሚያውቀው መሆን አለበት:: እራሴ ኢምፖርት ስለማደርግ, ድሮ የኢምፖርተሮችን ሒሳብ እስከ ኦዲት ክርክር ስለሄድኩበት አውቀዋለሁ:: እንዲህም ሆኖ የሚያመልጡኝ recent ጉዳዮች ስለሚኖሩ ለሌላ ታማኝ ባለሙያ አሻግራለሁ::

ገቢዎች በቲዎሪ ደረጃ ቀረጥ የሚያሰሉት በ CIF (Cost insurance freight) ቢሆንም ግን ትግበራው ላይ ግን ሌሎች ወጪዎችም አሉ:: ደረሰኙ አንድ ሆኖ ግን ለገቢዎች ኮስት እና ለጉምሩክ ቀረጥ ተብለው ለሁለት የሚሰነጠቁ ወጪዎች አሉ:: ለማንኛውም ለሰልጣኞቻችን ለድሮዎችም ጭምር እንልከዋለን:: ያልገባችሁ ምእመናን አንዴ እንገርበዋለን::
❤6
መ-ገንዘብ 2 የአዋቂዎቹ ማለት መ-ገንዘብ 1ን ያጠቃልላል:: የታዳጊዎቹ የተዘጋጀው ሌሎቹ ከበድ ስለሚሉ ነው:: ጃእፈር ጋር የገባው ሳያልቅ አይቀርም:: መኖሩን ቀድማችሁ ብትደውሉ መልካም ይመስለኛል:: ተጨማሪ ይታተም አይታተም ሲወሰን አሳውቃለሁ::
ስልኩ
+251 91 112 5324
❤1
ጊዜ ኖሮኝ በፋይናንስ ጉዳይ ስንትና ስንት የሚብራሩ ነገሮች ነበሩ:: የወረቀት ፊያትን ማስረዳት ስጀምር ያለመጡ ነበሩ:: ያ ዘመን አልፎ የዲጂታል ሜታዳታ ተረከበ:: አሁን ቀጣዩ አንተ የማታዘው እርሱ ግን የሚያዝህ ሥርዓት እየተተከለ ነው:: እስከ 2030 ብዙ ነገር መጠናቀቅ አለበት ተብሎ aggressively እየተሠራ ነው:: ያኔ ገንዘቡ እኛ አናዘውም:: ያዘናል እንጂ:: ንብረት የያዘ ይመነዝራል:: ያልያዘ ያለው አማራጭ ሁለት ሦስት ቦታ እየተቀጠረ በክሬዲት ካርድ ዕድሜውን ቀጥሎ ለልጆቹ ተመሳሳይ ሕይወት ያወርሳል:: እንደ ግለሰብ ንብረት መያዣ ጥቂት ጊዜ ነው ያለው:: አንዳንድ እስላሞችና ሙስሊሞች እንድንከራከር ይፈልጉ ነበር:: የደላው ሙቅ ያኝካል ነው ነገሩ:: የሆነ ጊዜ የሙስሊሞች ቴሌዢዥኖች ፕሮግራም እንድናዘጋጅ ሲደውሉ ... ጉዳዩ ፕሮግራም የማሳመር ... ክፍተት የመሙላት ... ወይም አጉል የመወያየት አይደለም:: የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው:: አንዳንድ የዋሆች የዓብዱልቃዲር አመለካከት ይመስላቸዋል:: አዲስ ነገር እያወራሁ አይደለም:: ያለ እና እየኖርነው ያለነው ግን የተዘናጋንበት መሠረታዊ ጉዳይ ነው:: መዓት እያወራሁ, እየቃዠሁ, እያስጨነቅሁ አይደለም:: በቂ ጭንቀት ይዞናል:: ሮጠን የማንደርስበት ነገር ውስጥ ሳንገባ አንዘናጋ ለማለት ነው:: በእንጥልጥል የቀረ ንብረት ካለ ቶሎ አስከብር:: ልቀማ ብሎ የሚመጣ ካለም ፋ^ስህን ስለህ ጠብቅ:: አንዳንድ ጅ^ል የምር ፋ^ስ ሊስል ይችላል እኮ::
❤15