ያደረ ታክስ እና የጸባይ ሽልማት
አንድ አዲስ የመፍትሔ ጥቆማ
(ርዕሱ ነው)
=======
ገቢዎች ወደ ሗላ ሄደው ኦዲት እያደረጉ እና የባንክ አካውንት እያዩ ምእመኑ ሰምቶት የማያውቀው ግብር እየጫኑ ናቸው:: ጉዳዩ በግለሰብ ወይም በውሱን ቢሮ ደረጃ ይሁን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ደረጃ አቅጣጫ ተይዞ ይሁን እርግጠኛ አይደለሁም:: በችርቻሮ የሚተዳደር እና መኪናም ይሁን ቤት እንኳ ያልገዛ ዘመድ 185 ሚሊዮን ብር ክፈል ተብሎ ሰምቶ ዝም ብሏል:: ምን ያድርገው? ጆሮው ሰምቷል:: ያለው አማራጭ ከት ብሎ መሳቅ, ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ, ዝም ብሎ መቃም, ወደ ጫካ መቀላቀል ነው የሚሆነው:: ፈጠራ ሳይሆን አሁን የሆነ እና እየሆነ ያለ ነው::
ግብር እየተጠየቀ ያለው ዓመታት እኮ ኮቪድ የነበረበት, በጦ^ርነት ሥራ የተበላሸበት, ንብረቶች የወደሙበት ዓመታትን ይጨምራል:: አንድ ነገር ገመትኩ:: ዲጂታል ሥርዓቱ ለገቢዎች ሙሰኞች አልተመቸም:: ምክንያቱም ሁሉም ነገር ይታወቃል:: ጉ^ቦ መብሊያ ክፍተት ሲጠፋ የድሮ ፋይል እየጎረጎሩ መደራደር ይመስለኛል:: ይህም አልበቃ ካለ "አያትህ ነጋዴ ነበሩ:: በል አምጣ" መባል ሊጀመር ይችላል::
እንደ መፍትሔ:- በሥርዓት መጓዝ ማንም አይጠላም ብዬ አልጎዘጎዝም:: ግልጽ ነው:: ለሥርዓት ማስከበሪያው ግን ሥርዓት ይበጅለት:: Cutoff ይሰጠው:: ያለፉ የለውጡ ወቅት እና እየቀጠሉ ያሉ ምስቅልቅሎች ከግምት ይግቡ:: ከዚያ አንድ አዲስ መፍትሔ ልጠቁም::
ቸርቻሪ ነጋዴው የወንጀል ሪከርዱ ይታይ:: ምንም ዓይነት የግልም ይሁን የቡድን ወንጀል ውስጥ ካልተሳተፈ ይህንን ጸባዩን እንደ እሴት ይያዝለት:: Score ይመደብለት:: በዚያ ይካካስ:: ለቀጣይ ንግዱን በሥርዓት እንዲመራ ተሃድሶ ገብቶ ሰልጥኖ ሥራውን ይቀጥል:: ይህ መፍትሔ ሌሎች potential ወንጀለኞችንም ያስታግሳል:: ለሰላም አስተዋጽኦ ይኖረዋል:: የግብር አንዱ ዓላማ ለጸጥታ አካላት የሚከፈል መዋጮ ማዋጣት ነው:: ሥራ ሳይሠሩ, ለጸጥታ አካላት መዋጮ (ግብር) ሳያዋጡ ወንጀል ላይ የሚዘወትሩ እና ወንጀል ላይ ሳይሳተፉ ግን የተወሰነ እያዋጡ ለሥራ ተፍ ተፍ የሚሉት እኩል መታየት የለባቸውም:: ሪከርዱ ታይቶ Score ይደረግ:: ምንም ዓይነት ወንጀል ላይ ካልተሳተፈ ምሳሌ Triple AAA ይይዛል:: አንገቱን ደፍቶ እንዲሠራ ላስቻለው ሰላም ታክስ ያዋጣል:: በሥራ ተጠምዶ ወንጀል ባለማሰቡ ደግሞ የግብር ጫና ሊቀነስለት አልፎ ተርፎም ነጻ ሊባል ሁላ ይችላል:: ሥራ ሲፈጥር ወንጀለኛን በሥራ በሥራ በመጥመዱ በፈጠረው የሥራ እድል ልክ ማካካሻ (incentive) ሊሰጠው ይመቻል::

👍27