Hasen Injamo
15.1K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
391 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
-> መኪና ተፈብርኮ ዘግይቶም ቢሆን በአባቶቻችን ኢትዮጵያ ሲገባ መቅደም ቢያቅተን እንኳ መኮረጅ ትተን የሰይጣን ሥራ ወደማለት ሄድን:: የጋሪ መዘውር እንኳ መሥራት ሳንችል የኤሌክትሪክ መኪና መጣብን::

-> በእኛው ዘመን ሞባይል ተመርቶ ኢትዮጵያ ሲገባ ማምረት ትተን ትላልቅ ቀረጥ, ኮንት^ሮባንድ ጋር መሯሯጥ እና ስክሪን ሴቨር የሚሆን ፎቶ ላይ አተኮርን::

-> በልጆቻችን ዘመን Ai ሲመጣ ምርትን ማቀላጠፍ ትተን የማምረቻ ቦታዎችን የው^ጊያ ምሽግ, የሰው መኖሪያና መሥሪያ ቦታዎችን ፓርክ አድርገናቸዋል:: ገና ከጫካ የሚመጣ ቡድን ያሻሽለናል ብለን እንጠብቃለን::
_
ወቀሳ ብቻ ሆነ እንዴ?
ይሁና!
❤49
የንግድ ፈቃድ ካፒታል ስንት ቢሆን ይመከራል?

-> በምትንቀሳቀሱበት ልክ አድርጉት:: ካነሰም መከራ ነው:: ከበዛም የባሰ መከራ ነው:: በ10 ሚሊዮን ብር እንቅስቃሴ የምታደርጉ ከሆነ በ1 ሚሊዮን ብር ካፒታል ንግድ ፈቃድ ብታወጡ ቀሪው ዘጠኙ ከየት መጣ የሚል ጥያቄ ያመጣል:: ከባንክ ብድር ከተሟላ መረጃ እስካለ ድረስ ችግር የለም:: ብድሩ ከግለሰብ ወይም ከራሳችሁ ከሆነ በውልና ማስረጃ የብድር ውል ብታካሂዱም ቅሉ ገቢዎች still ምንጩን ይጠይቃሉ:: ብድሩ ከራሳችሁ ከሆነ ድብቅ እንቅስቃሴ ወይም አደን^ዛዥ ዕ^ፅ እየሸጣችሁ ነው አይደለም በሚል ወደ ልዩ እና ሙሉ የባንክ አካውንት ኦዲት ይከታችሗል:: የቢዝነስ እና የግል የባንክ አካውንታችሁ ተለይቶ እየተንቀሳቀሳችሁ ቢሆን እንኳ ገቢዎች ድንበር ጥሶ ወደ ግል ሒሳብ ማጣሪያ ይገባል:: ብድሩ ከሌላ ሰው ከሆነ ከአራ^ጣ አበዳሪዎች ያመጣችሁት መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሌላ ገተት ውስጥ ትገባላችሁ:: የአበዳሪው ሒሳብ ወደ ማጣራት ይገባሉ:: ፈቃድ ስትጀምሩ ካበጠም ሌላ ችግር ነው:: ምክንያቱም ብሩን ማውጣት ይቸግራል:: ስለዚህ ፈቃድ ከማውጣታችሁ በፊት የእንቅስቃሴያችሁን ተመጣጣኝ ካፒታል ላይ አድርጉት::
❤31
የመኖሪያ ቤት ችግር በሞርጌጅ ባንክ ይፈታል የሚል እምነት የለኝም:: መሬቱ እንዳይታረስም ቤት እንዳይሠራበትም ጾሙን ውሎ እያደረ ባንክ ብቻውን ሊፈታው ቀርቶ ይብስ ይቆጣጥረዋል:: ምእመኑ በጊዜ ገደብ በጭቃ እንኳ ሠርቶ እንዲኖር አልተደረገም:: መሬቱ እንዳይሰምጥ ይሁን ወይም ጭቃው እንዳያስጠላ እንደሆነ ግልጽ አይደለም:: ከድህነትና እፍግ ብሎ ከመኖር በላይ ምን አስቀያሚ ነገር አለ? ያለፈው 20 ዓመት ያልተሠራበት ቦታ ዛሬም ሌጣ ሜዳ ነው:: ኑሮ እየተሻሻለ ሲመጣ ምእመኑ በራሱ እያሻሻለ ይሄዳል:: በእርግጥ በተለጠጠ ቁጥር መሠረተ ልማት ማሟላት አዳጋች ነው:: መንገድ ቀርቶ የውኃ መስመር መዘርጋት ፈታኝ ስለሆነ ፎቅ ላይ ማጠራቀም ዋጋ ይቀንሳል:: ፎቁስ የታለ? የምእመኑ ኢኮኖሚ ይፈቅዳል? ችግሩ ይህ ብቻ አይመስለኝም:: ገና የብሔ^ር ብሔ^ረሰብ ወሰን መች ተወሰነ? አዲስ አበባ ላይ ገና እየተጣላንማዴል!

ንብረት የማፍራት ዋስትና ቢከበር ኖሮ ብዙ ችግር ይቀረፍ ነበር:: አሁን ማን ደፍሮ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ንብረት የሚያፈራው? ቤት ከመሥራት መከራየት ባስመረጠበት ወቅት ... መከራየትም ነፍስ ውጪ ነፍ ግቢ በሆነበት በዚህ ጊዜ የቤት ችግር በቀላሉ ይፈታል ማለት አይቻልም:: የቱ ጋር መች እንደሚፈርስ መንግሥት ያውቀዋል? እልፍ ሲል ከደበረው በዚህ በኩል ቅደዱት, በዚህ በኩል እረሱት, በዚያ በኩል ይታደስ የሚባል ነው እኮ የሚመስለው:: የሆነ ሕጋዊ ቦታቸው ላይ ቤት በተገጣጣሚ ላሜራ የሠሩ ጎረቤቶቼ አሉ:: ድንገት ተነሱ አፍርሱ ከተባሉ እንዳይጨነቁ::
❤26
ከ500 ዓመታት በሗላ ዓለም የአፍሪካን "ትክክለኛ ካርታ" እንዲጠቀም UN መወሰኑ, ለምን አሁን ተወሰነ የሚለውን ትንታኔ የራሱ ጉዳይ:: ግን ይህንን ሁሉ ዓመታት መምህሩም ተማሪውም ውሸት መማርና ማስተማሩ ነው የሚገርመው:: ከወር በፊት የሆነ መምህር ይህንን ትክክለኛ የተባለውን አዲሱን ካርታ ቢያስተምር ኖሮ ከሥራ ሊባረር ይችል ነበር:: የፋይናንስ ሲስተሙ ደግሞ ከዚህ የባሰ ወጭበሬ ነው:: በብሩ ኒውዮርክ ውስጥ ምንም ዓይነት ዕቃ መግዛት የማይችል ምእመን በዶላር ግን አዲስ አበባ ውስጥ ሲገበያይ ለምን እንደማይጠይቅ አይታወቅም:: ይህንን ትክክለኛ የገንዘብ ምንነት ስናገር ስንቱ እንዳፈላብኝ እኔ ነኝ የማውቀው:: አንድ "ግድንግድ ኡስታዝ" የአሜሪካ ዶላር በኢትዮጵያ ብርም ይሁን በስዑዲ ሪያል መመንዘሩ ከሸሪዓ ጋር አይጋጭም:: ትክክለኛ ሥራ ነው:: ምክንያቱም ከለራቸው የተለያየ ስለሆነ እንደ ወርቅና እንደ ብር ቆጥረን መጠቀም እንችላለን ብሎ እኔን ለመቃወም መጽሓፍ ሁላ ጽፏል:: አሃሃሃሃሃሃ! ደረሶቹም አዎ ሸይኻችን ረጅም ዕድሜ ሲሉ ነበር:: ያው ሲስተሙ ሲሸከሽካቸው ግልብጥ ብለው መጡ እንጂ!
❤29
የዚህን ያህል መሴጅ ተከምሮ አያውቅም:: SMS ሁሌ ባዶ ነው:: ሁሌ ይነበባል ወይም ይደለታል:: ይህኛው ግን የመ-ገንዘብ መሴጅ ነው:: መጽሓፍ ሲደርስ ለእኔም መሴጅ ይደርሳል:: ደስስስስ ይለኛል:: ከፍሎ የማይደርሰው አንድም ሰው አይኖርም:: አንዳንዴ ሰዎች ያግዙኛል:: ስህተት አገኛለሁ:: ለማረም ትንሽ ጊዜ ይወስዳል:: እኔው ነኝ የምይዘው::

-> ፖስታ ቤት የተሸኘ, የእኔ ማስታወሻ ነው የሚል የቴሌግራም መሴጅ በፍጹም የመጽሓፍ መቀበያ አይደለም:: እርሱን ይዛችሁ ፖስታ ቤት እንዳትሄዱ::

-> መቀበያው በስልክ SMS ላይ RD ብሎ የሚጀምር 13 ዲጂት ቁጥር ሲደርሳችሁ ነው:: እርሱን በፖስታ ቤት ዌብሳይት Tracking ላይ በማስገባት የት እንዳለ ይነግራችሗል::
_

ለመጽሓፍ ክፍያ ቆሟል:: አትክፈሉ:: እጅግ በጣም አመሰግናለሁ::
❤30
ያ ጾታ ከbad ነው:: ሁሌ ልክ ስለሆነ አደም ተሳሳች ነው ብለህ ኑር::
🤣60
ማፍላት እና መብረድ
(ድጌ)
=============
የሆነ ጊዜ ቴኳንዶ ገብቼ ደህና መወራጨት ጀመርኩ:: ሒሳብ ከምሠራለት የሕንጻ መሳሪያ የሚያምር ጉርድ Safety-shoes ገዛሁ:: ጫማው ከፊት ብረት ስላለው በቴኳንዶኛ ስንዘራ ማንንም ብትመታበት ይወድቃል:: ይህንን ፍላቴን በማን እንደማበርደው ግራ ገባኝ:: የሚለክፈኝ አጣሁ:: ዝም ብለው የቆሙ የስልክ እንጨቶችን በሴፍቲሹ (ጫማ) እቺን ለቁመትህ ... ይህንን ለገመድህ እያልኩኝ ወዝውዤው ሥራ እሄዳለሁ:: ሥራም ላይ ሲያወሩ ንግግሩ የነገር ነው ወይስ አይደለም እላለሁ:: ብቻ ወበራሁ:: አፈላሁ:: ችግር ግን አላደረስኩም::

ከዕለታት ባንዱ የተባረከ ቀን ይመስለኛል እንደ ልማዴ አዳራሽ ገባሁ:: ሳቦም ገበየሁ አረፈደ:: እኛ አሟሙቀን እስኪመጣ ካገኘነው ጋር ፋይት ጀመርን:: እኔ ከቀጫጫዋ ሶፊያ ጋር ልሞክራት አልኩ:: በቤልት ደረጃ እንራራቃለን:: ያው ቀጫጫ ስለሆነች በዚያውም ነገር ለመፈለግም ለመተዋወቅም ሰበብ ይሆናል በሚል ፋይት ጋበዝኳት:: ወንድሜ ምናለ ውጪ ክትፎ ብጋብዛት! እግሯ ከላይ በግሮሊጊ ሲወርድ እኔ ደግሞ ከስር ሰላም ለማውረድ አሰላሙዓለይኩም አልኳት:: እሷም ስቃ ዋዓለይኩሙሰላም ብላ በቦክሲኛ ይሁን በቴኪኛ አስተቃቀፍ ዓይነት ተቃቀፍን:: አጋጣሚውን ለመጠቀም እንተዋወቅ ስላት ዘወር ብላ ጠፋች:: ብዞር አጣሗት:: ከፍራክሽን ሰከንዶች እረፍት ግን እግሯ ከሗላ በዲቻጊ አገኘኝ:: ቦታው የፋይት በመሆኑ ጋባዥም እኔ ስለሆንኩ የሞት ሽረት ከአታክ ወደ ብሎክ ዞርኩ::

በዚሁ መሃል የቀበሌው ሰፊ አዳራሽ ሲከፈት ሳቦም ገበየሁ የመጣ መሰለኝ:: ግን ተለቅ ኮስመን ያለ ሰውዬ ገባ:: አብረውን ሕጻናትም ነበሩ:: እየሄዱ ተጠመጠሙበት (ባቸው):: እኔ ደግሞ ምን የሰው ፍቅር ያላቸው የቀበሌው ዘበኛ ናቸው ብዬ ወደ ሶፊ ፋይት ልመለስ ስል ወደ ፊት ወደ ብላክ ቤልት ረድፍ ሄዳ ተሰለፈች:: ሳቦም ገበየሁን ባየው የለም:: እኔ መሃል ረድፌ ላይ በቤልቴ ገባሁ:: የቅድሙ ኮስማና ሰውዬ መድረክ ላይ ሆኖ "ቺሪዮት" ሲሉ ምእመኑ ጸጥ አለ:: ዛሬ ደግሞ እዚሁ ስልጠናው ባደመጡ ዘበኛ ነው የምንሠራው ብዬ እስቲ ልያቸው አልኩና ምእመኑ ጋር አብሬ ኩኔ ገባሁ:: እዚያው መድረክ ላይ ያለች ትንሽዬ ግርዶሽ ገብቶ ለብሶ ቤልቱን ታጥቆ ወጣ:: ኢላሂ በሗላ ስሰማ ዋናው ማስተር ብርሃኑ ነው::

ቀጫጫዋ ሶፊ እንዲህ እንደ ሐረር ቃሪቦ ከጨለጠችኝ ... የማናቸው ሽሜ ያልኩትም ሰው እንዲህ ባለብዙ ዳን ሆኖ እንዲህ ከተገለባበጠ .. መንገድ ላይ ካለው ሰው ማን ነው የሚታመነው? ብዬ ማፍላቴ በርዶ በአደቤ ስልጠናዬን ቀጠልኩ:: እንደውም በሗላማ ፋይት ላይ ሳቦም "የእርሱን እግር ተጠንቀቁት, አንተም ቀንስ" ይለኝ ነበር:: ሳኮ-ፓድ ስንመታ ሲይዝልን የስንዘራ ፓወር ይለያል:: ብቻ ከዚያ ቀን በሗላ መንገድ ላይ ኮስማና ሰው ሳይ ባለስንት ዳን ይሆን? ቀጫጫ ሴት ሳይ ባለስንት ዳን ትሆን እያልኩ በአደብ አለሁ:: አንዳንዴ እረሳና እግሬ ይቀድመኛል እንጂ በብዙ ተሻሽያለሁ:: ሴዶ ስለሚባል ልጅ ሲወራ ማነው ብዬ ወደሗላ አንዳንድ ነገሩን ሳይ እኔም አንድ ሰሞን እንደዚያ አድርጎኝ ነበር አልኩ:: ይሁን:: ምን አገባኝ!

ቢዝነስ ላይ ስለትርፋማ ቢዝነስ ጤፍ ሲቆላ ካያችሁት አፍልቶ ነው:: ወይም ሿሿ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ ቢዝነስና ትርፋማነት ደፍረህ መናገር አትችልም:: እራስህ እየሠራኸው ስላለው ቢዝነስ እንኳ ደፍረህ በእርግጠኝነት መናገር አትችልም:: ዛሬ ላይ ስላለው ነገር ልታወራ ትችላለህ:: ከወር በሗላ ግን ብዙ ነገር ተቀይሯል:: ስለዚህ Main principles ከ A እስከ Z ይዘህ ግን ሁልጊዜ update መሆን ያስፈልጋል:: (ኢምፖርት ስለጠና እየሞላ ነው)::
❤33
ኢምፖርት ስልጠና አለ:: HAB እና DINAR እያሳለጡት ነው:: A እስከ Z ይኬድበታል:: የታክሱን በታክስ ባለሙያ, የትራንዚቱን በትራንዚት ባለሙያ ተሸንሽኖና ተከሽኖ ይቀርባል:: ትኩረቱ ቻይና ላይ ነው:: ከቪዛ እስከ ጭነት ድረስ የማይዳሰስ ዘርፍ የለም:: ይመቻችሁ:: መመዝገቢያ በኮሜንት::

በተለይ በድርጅት የተመዘገባችሁ የድርጅታችሁ ስም እና TIN የግድ ነው:: ከስክሪንሹቱ ጋር ጻፉት:: ዊዝሆልድ የምታደርጉም አድርጋችሁ ላኩ::

ኢምፖርት A to Z ለ 3 ቀናት ጠዋት ጠዋት ጥቅምት 3,4,5/2019 ቦታ: አፍሪካ ኅብረት አካባቢ ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register
ወይም 2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
ስልክ: +251990555599
ስልጠናው የሚሰጠው በአማርኛ ቋንቋ ነው።
❤9
ሀብታም መሆን ከፈለግህ ሰው ጋር ስትገናኝ አምልጦህ እንኳ ብር እንደሌለህ ወይም ሽግር እንደገጠመህ ወይም ግራ እንደገባህ እንዳታወራ:: ሥራ ሊያሠራህ የነበረውን ሞራሉን ክሽክሽ ነው የሚያደርገው:: ሁሉም ሰው ለትርፍ ነው የሚወጣው:: ብር እንደተቸገርክ ወይም ስተክ (stuck) እንዳደረግህ ከነገርከውማ ላክስርህ, አብረን እንክሰር እያልከው ነው:: ከዚያች ቅጽበት በሗላ ካንተ ጋር የሚያደርገው ንግግር ድራማዊ ይሆናል:: የሌለህን ጎርር እያልኩ ሳይሆን ለትርፍ የሚወጣ ሰው በምንም ፎርሙላ ከሰው ልጅ መከጀል የለበትም:: ከከጀለ immediately ወደ ተመጽዋችነት ነው የሚዞረው:: ሴትም ሆና የብር ክጃሎት ምልክት ካሳየችው ወንዱ ወዲያው ሌላ ነገርዋን ይከጅላል:: የሰው ልጅ በሙሉ ፈላጊ ነው:: ብድር የሚያበድርህ ባእድ ሰው ወይ ነገ የሚያገኝብህን ትርፍ አስልቶብህ ነው ... ወይ ጀነት አስቦብህ ነው:: ከሁለቱ አይወጣም:: ሦስተኛ የለውም:: ስለዚህ ለሥራ ከወጣህ ምድብህን እወቅ:: ያኛው ሰው ካንተ የሚያገኝብህ ነገር እንደሌለ ከገለጽክለት አበላሸኸው:: ድህነት ወይም ተመጽዋችነት ጎራ ገባህ:: ስለዚህ ሲጠቃ-ለል ሀብታም መሆን የፈለገ ብር እንደቸገረው አይግለጽ::
❤24
ወደ ጥቅምት የወሰድነው የልጆች ትምህርት ቤት, እንቁጣጣሽ, ኢሬቻ, መስቀል ተደራራቢ በዓላት ስላሉ ነው:: መመዝገቢያ ቀኑን ያስቀደምነው ምእመኑ ብሩ አልቆበት እንዳያልፈው በማሰብ ነው::

ቻይና ከትራምፕ ታሪፍ በሗላ በተለይ ኤክስፖርት ታክስ እና የክፍያ ግልጽነት ጨምረዋል:: አዳዲስ ነገር face እያደረገ ነው::

-> 13,800 ብር ትከፍሉና ስክሪንሹት በቴሌ ግራም ትልካላችሁ
-> አወራራጆች TIN እና የድርጅት ስም እንዳትረሱ
-> ዊዝሆልድ አድራጊዎች ቀንሳችሁ አስገቡ

CBE
ACC. No. 1000762139646
HAB MANAGEMENT AND TECHNOLOGIES PLC

ስክሪንሹት 👇🏼👇🏼
t.me/hab_management
❤2
ፌስቡክ ላይ የራሴን የሥራ ማስታወቂያ የምንለጥፈው ፌስቡክን ላለመተው ጭምር ነው:: ከ14 ዓመታት በሗላ ነው ማስታወቂያ የጀመርኩት:: ብዙ ጠቅሞኛል:: ክሶኛል:: ዋና ዓላማዬ ብር ማግኘት ብቻ አይደለም:: በፍጹም! ብር መሸጋገርያ (means) ነው:: ሶሻል ሚዲያ ላይ ትልቁ ዓላማዬ ተሻጋሪ ዕውቀት ለግሶ መታወስ ነው የምፈልገው:: ምክንያቱም ዛሬ ላይ active ፖሳች ሰው እንደቤተሰብ ነው የምናውቀው:: መች? ፖስት ማድረግ እስካልተወ ድረስ:: ልክ ፖስት ማድረግ ሲተው እስከነመፈጠሩ እንረሳዋለን:: ይህ የፕላትፎርሙ ጸባይ ነው:: ስለዚህ መቼም ቢሆን የማይረሳ ነገር ቋሚ ዕውቀት እና ቋሚ ፎርሙላ በመጽሓፉ መልክ ሲቀመጥ ይሸጋገራል::

ለምሳሌ:-
የመ-ገንዘብ ሦስቱ የለውጥ መመሪያዎች
1) ሲስተሙን መረዳት
2) ግብ ማስቀመጥ
3) ወደ ግብ መሄጃ መንገዱን ማወቅ የሚሉ መመሪያዎች አሉ:: እነዚህ ለብዙ ዓመታት ያገለግላሉ::

-> ግብ አስቀምጠህ ካልተጫወትክበት ለምን አይሆንም::
-> ሲስተሙ እንዴት እየሠራ እንደሆነ ሳታውቅ ለመጫወት ብትወጣ ከንቱ ልፋት ነው:: ሲስተሙ ገልብጦ ይጫወትብሃል::
-> አካሄዱንና መተጣጠፉን ሳትረዳ ጨዋታ ብትጀምር ባወቁ ሰዎች ባርነት ስር ትሆናለህ::

ሦስቱን ካቀናጀህ ለስኬት አለመድረስ አትችልም::

ግብ ላይ SMART ትሆናለህ (ይህኛው ከሌላ ጸሓፊ የተወሰደ ነው):: 👇🏼

S: Specific (ግልጽ ብሎ ምልክት ያለው)
M: Measurable (ተለኪ)
A: Achievable (ሊፈጸም የሚችል)
R: Relevant (አስፈላጊ)
T: Time based (መፈጸሚያ ጊዜ የተቀመጠለት)
❤22
በዚህ ዘመን የሚያምር የቢዝነስ ፕሮፖዛል ትርጉሙ እምብዛም ነው:: ድሮም ቢሆን ብዙም አይነበብም:: ልክ ሶፍትዌር ስትጭኑ ሳታነቡ Accept ብላችሁ እንደምታልፉት ዓይነት አየት አየት አድርገው ይወረውሩታል:: ስንት ተጨንቃችሁ የሠራችሁት የመመረቂያ ፔፐር የት እንዳለ እናንተም አታውቁም:: ፕሮፖዛል የሚያዩ ጥቂት መሥሪያ ቤቶች አሉ:: አብዛኞቹ የራሳቸው ፎርማት አላቸው:: ፕሮፖዛል ማጥናትና መተንተን አይፈልጉም:: በዚህ ዘመን የቢዝነስ ፕሮፖዛል ተራ ነገር ነው:: የማንም ሰው እጅ ላይ ያለ ስልክ በራሱ ቋንቋ ጥንቅቅ አድርጎ ይሠራዋል:: ሞባይሌ በአማርኛ ወይም አፋን ኦሮሞ እንዲገባኝ አድርጎ እየሠራ በእንግሊዝኛ ቢራቀቅ ምንም አይደንቅ::
ሲጠቃለል:- አሁንም ድሮም አሸናፊ ጎል ያገባ ነው:: አሁንም ድሮም አሸናፊው ወንበሩን የያዘ ነው:: አሁንም ድሮም አሸናፊው ብር ይዞ የተገኘ ነው:: መቶ ብር ከእጃችሁ ላይ ወድቆ እያያችሁት ሌላ ሰው ቢያነሳው የትኛውንም ፍርድ ቤት ብትሄዱ ባለ ብሩ ያነሳው ሰው ነው:: ጠንካራ መረጃና ማስረጃ እስካላመጣችሁ ድረስ:: እንደውም በዘረ^ፋ ወንጀል ሊጠይቃችሁ ይችላል:: ባራዳም በፋራም መያዝ ብቻ ነው:: ይህንን የምላችሁ እኔ ሳልሆን ገዢያችን ካፒታሊዝም ነው:: ለእኔ እንኳ ካፒታሊዝም ብዙም አይመቸኝም::
❤26
መ-ገንዘብ እኔ ጋር ከፍላችሁ ያልወሰዳችሁ ምእመናን በሙሉ በፖስታ ቤት እየተካሄደ ነው:: የፖስታ ቤቱ አሠራር በጣም ዘመናዊ መሆኑ ጥርጥር የለውም:: ተመችቶኛል:: ግን አሁንም በዚያ መንገድ ብቻ ማዳረስ አልተቻለም:: ተጨማሪ ባሕላዊው አማራጭ አሁንም በደንብ ይሠራል:: እያሰብንበት ነው:: ምክንያቱም መዳረስ አለበት:: ስለገንዘብና ሀብታም መሆኛ መንገድ በደንብ ይገባን ዘንድ ውይይቱ ይፏፏም:: ሲስተሙ ጠንክሮ የሠራና ጎብዞ የተማረን የሚያደኸይበት ምክንያት ማወቅ የግድ ይላል:: መ-ገንዘብ መጽሓፍ ያስገነዝባል:: ለልጅም ላዋቂም ተዘጋጅቷል::
👍8
ስለሕዋ ብዙ ባነበብክ ቁጥር ኩራ^ትህ እብስ ብሎ ይጠፋል:: ትቀየራለህ:: ከእኛ ጋላክሲ እስከ አንድሮሜዳ ጋላክሲ በሰከንድ 300 ሺህ ኪሎሜትር ብትወነጨፍ 2 ሚሊዮን ዓመት እንደሚፈጅብህ ስታነብ እንዴት ልትኮራ ትችላለህ? የፈጣሪ አቃጣ^ሪነት እንደማያዋጣ ገብቶህ በራስህ ነውር ማጽዳት ቢዚ ትሆናለህ::
👍19
ፎቶው ለጨዋታ ድምቀት
ነው እንጂ የእኔ አይደለም
========
የዓለም የገንዘብ ሥርዓት እንዴት እንደሚሠራና ሳይንስ እንጂ ምትሃት እንዳልሆነ በደንብ አውቃለሁ:: የሀገራችን የፋይናንስ ሥርዓት እንዴት እንደሚሠራና እንዴት እንደማይሠራ እንዲሁም የተሻለ መፍትሔ ምን እንደሆነ አውቃለሁ::

ግን ግን
ትንሹ ኑሮዬን ማሸነፍ እና ለልጆቼ የሚሆን ውርስ ንብረት የማልይዝ ከሆነ ከቱሪናፋነት አልዘልም:: ቱልቱላ ቀዳዳ::

(ሥራ ደከም ስል አካውንቴ ሲጎድል በዚህ ሰውዬ ባሕላዊ ስድ^ብ እበረታለሁ)
❤11
ሁለት ነጋዴዎች ከተጣሉ ወይም ብር ከተበላሉ የሚሸመግላቸው የኃይማኖት አባት ሳይሆን የሚበልጣቸው ነጋዴ ብቻ ነው:: ምክንያቱም ሥራ ይበላሽብኛል ብለው ይፈራሉ እንጂ የዚያኛው ዓለም ሥራ ለጭንቅላታቸው መልስ በመስጠት እራሳቸውን ሸውደው ጊዜ ይገፋሉ::
❤29
Forwarded from Hawlet Ahmed
በ2019 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ወስደዋል።

ብዙ ሰው እየደወለ ስለሚጠይቀኝ እና ትንሽ ግር የመሰኘት ነገር ስላየሁ እኔ ልጄን በማስመዝገብ ሒደት ካለኝ ልምድ እና ጠይቄ በተረዳሁት መሠረት ዝርዝሩ ሊያግዛችሁ ስለሚችል አንብቡት።

(✍️ በሐውለት አህመድ, ፒኤች ዲ)

📌 የመጀመሪያው ዙር የተፈተናችሁ

📍 የመጀመሪያው ዙር ፈተና በዋናነት በመንግሥት ስፖንሰር የሚደረጉና በግል ከፍለው የሚማሩት ይ'ለዩበታል። ስለዚህ ለፈተናው ሲመዘገቡ ''Government Sponsorship'' ብለው የሞሉ የመቁረጫ (cut-off) ነጥብ ሲቆረጥ ያንን ነጥብ እና ከዚያ በላይ ካመጡ ዩኒቨርሲቲውን join ያደርጋሉ።

📍 የመቁረጫ ነጥቡን ካላመጡ በመደበኛው መርኃ-ግብር (Regular) በአ.አ.ዩ. ባይቀጥሉም ስማቸው ለትምህርት ሚ/ር ተላልፎ በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ።

📍የአንድ ተማሪ ነጥብ የሚሰላው 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያመጣው ውጤት ከ50 እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ቅድመ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (UAT) ከ50 ተይዞ ከ100 በሚያመጡት መሰረት የሚቆረጠው (cut-off) ነጥብ ነው።

📍ለመንግሥት ስፖንሰርሺፕ ተመዝግበው ያልተመረጡ በቀጥታ ወደ ግል (self-sponsorship) ይገባሉ የሚባለው ስህተት ነው።

📍 Self-sponsored ሆኖ ለመማር መጀመሪያውኑ ለፈተና ሲመዘገቡ ''Self-sponsorship'' ብለው የሞሉት ብቻ ናቸው።

📍በግል ከፍለው የሚማሩ (self-sponsored) የፈለጉት ዲፓርትመንት ይገባሉ ማለት አይደለም። በተለይ በጣም ተፈላጊ የሆኑ የትምህርት ክፍሎች የሚያወጡትን የማለፊያ ነጥብ ማምጣት አለባቸው።

📍 Self-sponsored የሆኑ ተማሪዎች የዲፓርትመንቱን የመግቢያ ነጥብ ካመጡ በዚያው ዲፓርትመንት ይቀጥላሉ። እንደ መንግሥት sponsored የመጀመሪያና ሁለተኛ ሴሜስተር ውጤታቸው የመታየት ግዴታ የለባቸውም።

📍በመንግሥት sponsor የሚደረጉ ተማሪዎች እንደ self-sponsored ከመጀመሪያው ዲፓርትመንት የመምረጥ ዕድል አይሰጣቸውም። ሁለት ሴሜስተር (የመጀመሪያው ዓመት) ተምረው ነው ዲፓርትመንት መምረጥ የሚችሉት። ይሁንና ከፍተኛ ፉክክር ስለሚኖር በጣም ተፈላጊ ዲፓርትመንት such as Software Engineering ወይም ሕክምና ትምህርት ቤት ለመግባት CGPA እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት በሁለቱ ሴሜስተሮች ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ያ ካልሆነ ወደሌሎች ዲፓርትመንቶች ይመደባሉ።

📍በማታው መርኃ-ግብር ለመማር የተመዘገቡ እና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲውን ማለፊያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች በሚወጣላቸው ስኬጁል መሠረት ይመዘገባሉ።

📍 ፎርም ላይ Government Sponsorship ሞልቶ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ ነጥብ ከ50% በላይ አምጥቶ ነገር ግን ለsponsorship የማያበቃ ነጥብ ያለው ተማሪ ድጋሚ መፈተን ሳያስፈልገው በማታው መርኃ-ግብር ተመዝግቦ (በግሉ እየከፈለ) መማር ይችላል።

📍 በማታው መርኃ-ግብር ለመማርም UAT መፈተን ግድ ነው።

📍በመንግሥት sponsorship ለመታቀፍ መቁረጫ ነጥብ በጣም በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። (ይህንን መልዕክት እስከምጽፍ ድረስ አልተገለጸም)።

📍 የመቁረጫ ነጥብ የሚወጣው ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ሶሻል ሳይንስ በሚል ለሁለት ተከፍሎ ነው። የወንዶችና የሴት ተማሪዎች መጠነኛ ልዩነት አለው።

📍በመጀመሪያው ሴሜስተር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ወደ ሶሻል ሳይንስ ፊልዶች መቀየር አይችልም። የመጀመሪያውን ዓመት ካጠናቀቀ በኋላ transfer መጠየቅ ይችላል። ይሁንና በዩኒቨርሲቲው በኩል እንደ አጠቃላይ ማሟላት የሚጠበቅበት መስፈርት እንዳለ ሆኖ ዲፓርትመንቶች የራሳቸው ጥብቅ መስፈርት ስላላቸው ትራንስፈር ቀላል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። እንደ የዲፓርትመንቱ የመግቢያ ነጥባቸውን ማሟላት እንዲሁም ቦታ ክፍት መኖሩ መታየቱ እንዳለ ሆኖ።

📌 ሁለተኛ ዙር ፈተና

🔺 ከዚህ በፊት ሁለተኛ ዙር ፈተና አልነበረም። ወደፊትም የሚኖር አይመስለኝም። ይሁንና በመጀመሪያው ዙር ፈተና ምዝገባ ወቅት የሲስተም መጨናነቅ በመፈጠሩ ሳቢያ የመጨረሻ የምዝገባ ቀን ችግር በመፈጠሩ ሁለተኛ ዙር ምዝገባ እየተከናወነ ነው። አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል። ፈተናው መስከረም 4/2019 ይሰጣል።

🔺 ይህ ፈተና በግል ከፍለው ለሚማሩ (self-sponsored) እና ለማታው መርኃ-ግብር ብቻ ነው። የመንግሥት sponsorship ውድድር በመጀመሪያው ዙር ተጠናቅቋል።

🔺 የመመዝገቢያ ሊንክ እንዲሁም ስለፈተናው የምትከታተሉበት ቴሌግራም ገጽ ከታች ተቀምጧል።

------------------------------
‼️ ማሳሰቢያ ይህ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው እንደመጣ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት አ.አ.ዩ ሬጅስትራር ጽ/ቤት (6 ኪሎ) በመገኘት መጠየቅ ትችላላችሁ።

ፈተናዎችን በተመለከተ 👇
https://t.me/aauGAT

ሁለተኛው ዙር UAT መመዝገቢያ 👇
https://admission.aau.edu.et

ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው። 🙏🙏
❤14
❤2
👆🏾👆🏾
ለሚስት የውጭ ሥራን እንደመዝናኛ የቤት ወጭን እንደ ውዴታ
ጋዜጠኛ ናፍቆት የቤት ወጭ በሙሉ በባል መከናወን አለበት ያለችው ነገር በዚህ ወቅት መሰማቱ በዕውነቱ ሴቶች አሉ .. ወንዶችም አሉ ማለት ነው አስብሎኛል:: ጋዜጠኛ ናፍቆት ሴት ነኝ ብላ በሴትነቷ ኮራ ብላ እንዳወራች ነው የምቆጥረው:: ተባረኪ:: በሰማነው መሠረት ከሆነ ባሏም ወንድ ነው:: አይለያችሁ:: ትዳራችሁ የተባረከ ይሁን:: (አደራ የተደበላለቀባቸው ሰዎችን አስተያየትና ስ^ድብ ከብዷችሁ ወይም ለእይታ አድርጋችሁት ሗላ ፕራንክ ነበር እንዳትሉን)
እንደዚህ ወቅት ሚና የተደበላለቀበት ወቅት ያለ አይመስልም:: ዶክተር ወይም ኢንጂነር ነኝ ማለት አሳፍሮ ቲክቶከርነት የሚኮራበትና የሚሸቀልበት, ከመማር ይልቅ መሰገጥና መደ^ደብ የሚሞገስበት, ፖለቲካውንም በሉት ፋይናንሱ, ኃይማኖቱም በሉት ፊዚክሱ በማይመለከተው ሰው የሚቦካበት, ወንድነትና ሴትነት የተደበላለቀበት, ሀይ ባዮች ሳይቀሩ ሆይ ሆይታ ውስጥ የገቡበት ወቅት ላይ ነን::
ዘመኑን መር^ገም ትክክል አይደለም:: እኛው ነን የምንሠራው:: ያው ሚና ተደበላልቋል:: ትምህርታችን የኢንደስትሪ ዘመን ካሪኩለም ስለሆነ ማኅበረሰቡም የዚያ ውጤት ነው:: አባት ሴት ልጁን .. ባል ደግሞ ሚስቱን ዐረብ ሀገራት እያሰደደ እንድታኖረው የሚያደርግ ወንድ በርክቷል:: መንግሥትም ለእነዚህ ሴቶች የርቀት ትምህርትም ይሁን ሲመጡ የሚያርፉበት ጎጆ መሥሪያ እንኳ ሳያመቻች በምንዛሪያቸው የሚተዳደርበት የሚና መደበላለቅ ውስጥ ነን:: ጋዜጠኛ ናፍቆት የምትለው ዕውነት ከሆነ አልተደበላለቀባትም::
ሚስት ውጭ ሠርታ እንደገና ቤትም ሠርታ ... ዋናው የተፈጥሮ ኃላፊነትዋ ልጅ ወልዳ ማጥባትን ተሸክማ ሌላ ኃላፊነት ... ግፍ ነው:: እሺ ባል ተፈጥሯዊ ግዴታ ላይኖርበት ነው? ይህማ ወደል አሕያ ወይም ወደል ኮርማ ሆነ:: ታዲያ አሁን ላይ ያለው የወንዶች ይህ ሁሉ ሥራና ልፋት ለማን ነው? ለአልፎ ኺያጅ ለመንገደኛ?
ለሚስት ሥራ ማለት እንደ መዝናኛ ነው መሆን ያለበት:: ወጪን የተመለከተ በሙሉ የባል ነው:: ሚስት ሥራ ይኑራት:: ደስ እያላት ትሥራ:: የሆነ ችግር የገጠማት ወቅት, ፍቺን ይመስል, የባል ሥራ ማጣት ወይም መታመም ወይም መሞት ሲከሰት አትደናበርም:: በችግር ምክንያት የማትፈልገውን ሌላ ባል እንድታገባ አትገደድም:: ማለፊያ ይሆናታል:: ብር ካላት ባሏ እየተነሳ ለፍቺ አይሮጥም:: ሌላ ሚስት ድረባም አይቸኩልም::
ሙሉ ወጭ የባል ነው ሲባል ... ሚስት ብትሠራ የትም አትወስደውም:: ለቤቷ ነው:: ልጅ የመውለድና የማጥባት ግዴታ ኃላፊነት አለባት:: ስለዚህ ባልም የቤት ወጭ የማምጣት ግዴታ ኃላፊነት መውሰድ አለበት:: ለወንድ ልጅ እዚህ ምድር ላይ ከሚያስደስት ነገር ሁሉ ሸቅሎ አምጥቶ ቤተሰቦቹ ሲበሉ ማየትን የሚያህል ምን ይኖራል? ከሁሉ የሚቀርቡት ደግሞ ልጅና ሚስት እንዲሁም ወላጆች ናቸው::
ባል ወጭ ይቻል ሚስት ግን እንደፍላጎቷ ሲባል ስ^ድ አደግ ወይም ሴ^ሰኛ ሆና ለውሽማ የምታውል ዐይነቷ ማለት አይደለም:: ይህችማ ሲጀመር ቤት ውስጥ ምን ትሠራለች? ሄዳለች እኮ:: ከምድር ባያሰናብታት እንኳ ከቤት ማሰናበት ነው:: (እርሱም ከተወሳ^ለተ በተመሳሳይ):: እያወራን ያለው ስለሌ^ቦችና ወስ^ላቶች አይደለም:: ወንድ ስለሆኑ ባሎችና አባወራወች እና ሚስት ስለሆኑ ሴቶችና እመወራዎችን ነው:: እንጂ በሴት ትከሻ ስለሚያድሩና ሚናቸውን ስለዘነጉ ባሎችና አባቶች አይደለም:: ወንድ ማርገዝ እና መውለድ አለበት ቢባል እንደማይዋጥልን ሁሉ ሴትም የቤት ወጭ ኃላፊነት አለባት የሚለውን ሊዋጥል አይገባም::
❤52
ሀብታም ከመሆኛ አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮች ውስጥ ለሥራ ጉዳይ ስትገናኙ ስልክ እና አፍንጫ አለመጎርጎር ይካተታሉ:: ስልክህን ካልጎረጎርክ የሶሻል ሚዲያ አካውንትህና የስልክ ጥሪዎችህ ጭምር በሠራተኛና በአድሚን የምታከናውን ይመስላል:: አፍንጫ ካልጎረጎርክ ስነሥርዓት ያለህ ነህ ተብሎ ይወሰዳል::
😁59