Hasen Injamo
15.1K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
391 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
ድርጅት ውስጥ በጣም የሚለፋ ሰውዬ በጣም ሥራ እያበላሸ ሊሆን ስለሚችል እርሱን ካባረርከው ሲስተሙ በራሱ ይሠራል:: ጥሩ የድርጅት ማናጀር ቢሮ ውስጥ ጌም የሚጫወተው ሊሆን ይችላል:: ማልዶ ገብቶ አምሽቶ የሚወጣውን ብትቀነድበው ሥራው ይሄዳል:: የድርጅትህ ችግር ሊታወቅ ይመቻል:: ያለእርሱ አልኖርም ያልክለት ሰው እየገ^ድለህ ሊሆን ይችላል:: ምክንያቱም ሥራ እያስኬደ ሳይሆን እያገደ ነው የሚሆነው:: ይለፋል, ይሠራል ተብሎ ሁሉንም ነገር ለእርሱ ይተውለታል:: እርሱም አትንኩኝ ባይ ይሆናል:: ጥሩ ሥራ አስኪያጅ ጥሩ ሲስተም ይዘረጋና ሥራውን ለሲስተሙ ይተወዋል:: እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ ካርታ ይጫወታል:: ለአስተዳዳሪ ቦታው ሰዋዊ ሥራ ማለትም ማሰብ ነው:: ሸይኽ አልአሙዲ ባይኖሩም ሊሠራ የሚችል ጥሩ ሲስተም ዘርግተዋል:: የእሳቸው ገለል ማለት ደግሞ ድርጅታቸው በራሱ እንዲሄድ እና ችግሮቹን እንዲያይ እድል ሰጥቶታል::

ፖለቲካም ላይ ዋነኛ ወዳጅህን ዘወር ስታደርገው አይጦቹ ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ:: አይጦቹን ታጸዳና ወዳጅህን ትመልሰዋለህ ወይም ታሰናብተዋለህ:: አዎና! ሥልጣን ላይ ቀልድ የለም::

እሳቸውም ረፍት ያድርጉ:: በሪፖርት ብቻ ያስተዳድሩ::
❤25
ምን ያህል ቢዚ ነህ?
የሆነ ከሰዓት ነገር ላይ የእንቅልፍ አይሉት የድካም ስሜት ይሰማኝና ዛሬ ምን ሆኜ ነው ኮምፎርት ያልተሰማኝ ብዬ ለሰከንዶች ሳፈላልግ ለካ ርቦኝ ነው:: ምናልባትም ቸኩዬ ቁርስም ሁላ ሳልበላ ወጥቼ ይሆናል:: ምግብ ምንድነው? ሆድስ? ረሃብ? መርሳት? ማስታወስ እያልኩ ከዚያ ምግብ ቤት እየሄድኩ በመሃል ረስቼው ወደሌላ ሀጃ እሄድና አሁንም ማምሻ አካባቢ ደስ የማይል ስሜት ተሰምቶኝ ሳሰላስል ምግብ ቤቱን አልፌው ሌላ ጉዳይ ውስጥ ገብቻለሁ:: አሃሃሃሃሃሃ!

ስልክ ደውለህ ጉዳይህ ካልተቋጨ ይደውላል ብለህ እንዳትጠብቅ:: ሲጀመር ደውለህ ነበር? እና እንዳትፈርድብኝ:: ንቀ^ት, ኩ^ራት ምናምን ካልክ ተበልተሃል:: ለመኩራት እራሱ መጀመሪያ ምን ዓይነት ልብስ ለብሼ ምን ዓይነት መኪና ይዤ እንደወጣሁ ማስታወስ አለብኝ::
😁21
I ሰው አለ ቀበሮ
የዶክተር ሐውለት የታክስ ስልጠና ሁለቱን ተከታትያለሁ:: ከሰልጣኝ አጃዒበኛ ጥያቄ ይነሳሉ:: አንድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚታወቅ እና ብዙ ቅርንጫፍ ያለው ድርጅት ልጅት ስልጠናውን ተካፍላ ነበር:: ድርጅታቸው ደረሰኝ በመስጠት አይታማም:: ደረሰኝ መቁረጥ ባሕሉ ነው:: ሠራተኞቹን ሲቀጥር ሁላ ልዩ ውል አስፈርሞ ነው የሚቀጥረው:: ቢሆንም ቢሆንም ነገር መምጣቱ አይቀርም:: አዲስ አበባ ውስጥ ገቢዎች በየሸጥ እና ኩርባው ተበትነው ደረሰኝ ይቆጣጠራሉ:: እነዚህ በትክክል ደረሰኝ ቆራጮች ... የቆረጡት ደረሰኝ ችግር ይዞባቸው ይመጣል:: እንዴት በሉ:: (ብላችሗል)

ምሳሌ እንበልና እነርሱ የ5,000 ብር እቃ ሽጠው በትክክል ደረሰኝ ቆርጠው ይሰነባበታሉ:: ከዚያ እቃ ገዢዎቹ በእነርሱ ደረሰኝ አጃቢነት ከሌላ ሱቅ ብዙ እቃ ያለ ደረሰኝ ይገዙና ያጓጉዛሉ:: ገቢዎች ሲፈትሹ ደረሰኙና እቃዎቹ አይጣጣሙም:: በአምስት ሺህ ብር ደረሰኝ ሽፋን የመቶ ሺህ ብር እቃ ይጓጓዛል እንበል:: ገቢዎች የደረሰኙን አድራሻ ተከትለው ይመጣሉ:: በትክክ ደረሰኝ ቆራጮቹ በማያውቁት እና ባልሸጡት እቃ ተጠያቂ ይሆናሉ:: ደረሰኝ የማይቆርጡ ነጋዴዎች እኮ ለነገር ከጎረቤት ደረሰኝ ከሚቆርጥ ድርጅት ትንሽ እቃ ይገዙና የእነርሱን እቃ መሸኛ ያደርጉበታል አሃሃሃሃሃሃ 😂😂😂😂. አይ ሰው አለ ቀበሮ::

ስልጠናው ላይ የተመቱ ጥያቄዎች ይመጣሉ:: እነዚያ ድርጅቶች በማያውቁት እቃ ከገቢዎች ጋር ብዙ ቦታ ተዳርሰው ያው ስቶክ በትክክል ስለሚይዙ ነው ነጃ የወጡት:: ነገሩማ ውስብስብ ነው:: ዶክተር ሐውለት ጋር ሰልጥኑ:: 👇🏼👇🏼👇🏼
❤24
ብዙ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚክስ ባለሙያ እንዲሁም ብዙ ምእመን ንግድ ባንኮችን ይወቅሳል:: ብድር የሚሰጡት ለሀብታም ብቻ ነው, ግብርና እና ፋብሪካዎችን አያዩም ይባላል:: በእኔ በኩል ወቀሳው ልክ አይደለም ባይ ነኝ:: በታላላቅ ሚዲያዎችም አንስቸዋለሁ:: ችግሩ ከንግድ ባንኮች ሳይሆን ከሀገሪቷ ፖሊሲዎች ነው የሚመነጨው:: <<ንግድ ባንክ>> ተብሎ ፈቃድ አውጥቶ የግብርና ወይም የፋብሪካ ባንክ ሊሆን አይችልም:: የባንኮች ማቋቋሚያ አዋጆች ጭምር የግብርናና ኢንደስትሪ ባንክ ባላየ ነው የሚያልፈው:: ንግድ ባንኮች ለትርፍ በሕዝብ አክሲዮን የተቋቋሙ ናቸው:: ለባለአክሲዮኖቻቸው ትርፍ ማስገኘት የሕልውና ግዴታቸው ነው:: የተበላሸ ብድር ጣራ (NPL) 5% ነው:: ብድር እንዳይበላሽ የግድ ለትርፋማ ባለቢዝነስ እና ለባለማስያዣ ማበደር አለባቸው:: ስለዚህ በመ-ገንዘብም ያስገነዘብኩት ሁለቱን ማለትም ትርፋማ ቢዝነስና ማስያዣ ይዘህ ተገኝ:: ካልሆነ ከፖሊሲ ጀምሮ እስከ ሕግና መመሪያ ድረስ አይደግፉህም::

ለግብርና እና ኢንደስትሪ ባንክ የግድ ከላይ ከመንግሥት አቅጣጫ ተይዞ መጀመር አለበት:: ንግድ ባንኮቹን አትውቀሱዋቸው:: ይህንን በተመለከተ እንቅስቃሴ ጀምሬ ጦ^ርነት ውስጥ ቢዚ ሆነን አሳድሬዋለሁ:: መንግሥት ግብርና እና ኢንደስትሪ ባንክ ላይ አተኩሮ መሥራት አቅቶት ነው ወይ? የሚል ጥያቄ እናንሳ:: አላቃተውም, አላጣውም:: ግን ሥልጣኑን ያጣል:: ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከምዕራብ የፋይናንስ ተቋማት ውጭ ማሰብና መሥራት ትጀምራለች:: የሁለቱ ባንኮች ሙሉ እንቅስቃሴ እና ግብዓት አገር ውስጥ ነው ያለው:: የንግድ ባንኮች ከፊል ግብዓት (ዶላር) ውጭ ነው ያለው:: ንግድ ባንኮች Dollar dependent ናቸው:: ግብርናና ኢንደስትሪ ባንኮች የዲ-ዶላራይዜሽን አንድ አካል ስለሆኑ እነ IMF በጀ አይሉም:: ችግሩ ጥልቅ እና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው::
❤31
ዕውቀት የወለደው ታላቁ የመ-ገንዘብ መጽሓፍ ጀግናው የጃዕፈር ሰራዊት ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል:: የቀሩ ኮፒዎች በመደብሩ እየሄዳችሁ ትሸምቱ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችሗል::

መስከረም 2 ቀን ሁለት ሺህ አስራ ዞጠኝ ዓመተ ልደት ወምሕረት ወብልጽግና ወሃብት

+251 91 112 5324 ጃእፈር
👍11
ትምህርት ላይ የነዋሪ ካሪኩለም እና የአኗኗሪ ካሪኩለም አለ:: የነዋሪዎቹ (1%) ካሪኩለም ምን ያህል አውቀዋል የሚል ሲሆን የአኗኗሪዎቹ ማለትም የ99 ፐርሰንቶቹ ግን ታላቁ ሩጫ ነው:: በእንግሊዝኛ ስለተማርን የእንግሊዝ (የገዢ መደብ) ካሪኩለም የተማርን ይመስለናል እንጂ አይደለም:: የእኛ በነጻም ውድ ነው:: ዲናቹራላይዝ ለመሆን አፍላ ጊዜን በሆነ ኬጅ ውስጥ ለማቆየት ቢከፈለን ሁላ ያስኬዳል:: ለስላሳ በ40 ብር የምትጠጣበት ሰፈር እና በ2 ብር የምትጠጣበት ሰፈር የምታገኛቸው ሰዎች ይለያያሉ:: ማስቲሽ ሳይስብ በኑሮ የፈዘዘ, ሳይጠጣ የሰከረ ሰው ጋር ስትውል እንደ ተስቦ ተ-ስ-ቦ ይጋባብሃል:: <<ሀብታም ብትሆን ጥሩ ትሆናለህ, ደሃ ብትሆን መጥፎ ትሆናለህ >> ማለት አይደለም:: ከደሃ ጋር ነኝ:: ልል የፈለግሁት ከትምህርት ውጭ የሚቀይርህ ምንም ኃይል የለም:: ስለዚህ የምትማረውን ምረጥ ለማለት ነው:: ካሪኩለም ይገ^ድላል, ያድናል:: ትምህርት ከምግብም በላይ የተመጣጠነ መሆን አለበት:: ጀንክ እውቀት ካስገባህ ትጀነክካለህ:: እስካሁን ከምናውቃቸው በሽታዎች እንደ መጥፎ ካሪኩለም ገ^ዳይ አይኖርም:: በጣም ጎበዝ ጭንቅላት ያለው ሰው የተሳሳተ መረጃ input ከሰጠነው በጣም አስቀያሚ ውጤት ነው የምናወጣው:: ሐኪም እና ኢንጂነር የሚሆን ጭንቅላት እጅግ ሻርፕ ጭንቅላት ነው:: ምንም ብትሰጠው ይሠራራዋል:: ጀንክ መረጃ ከሰጠኸው ተምሮ ሲጨርስ ዳቦ መብሊያ እስኪጠፋው ድረስ ይደ^ድባል:: የደ^ደብ dropout ተቀጣሪ ይሆናል:: ስለዚህ ለትምህርት የሚወጣ ወጭ እንደ ኢንቨስትመንት ይቆጠራል:: ኢንቨስትመንትህን ምረጥ!
❤19
በየመሥሪያ ቤቱ ለሠራተኞች የቤት እና የመኪና ብድር ሲመቻች ሙስሊሞች ተጨባብጠው ይቀመጣሉ:: ይህ እንዳይከሰት ለ10 ዓመታት ያለመታከት አስተምሬያለሁ:: መጽሐፍ ጽፌያለሁ:: የተጠቀመ ተጠቀመ:: ያለመጠም ሲስተሙ አልምጦበታል:: አሁንም ዕድሎች በዋዛ በፈዛዛ እያለፉ ናቸው::
Well, ወንድሞች እና እህቶች ሆይ:- በገዛ እጃችሁ እራሳችሁን ውትፍትፍ ውስጥ አትክተቱ:: በዚህ የፋይናንስ ሲስተም ውስጥ ከወለድ ነጻ የሚባል በየትኛውም ዓለም ወላ ዐረብ ሀገራት ውስጥ የለም:: ሙስሊሙ ላይ ማርኬቲንግ ለመሥራት የተፈጠረ ስም ነው:: ምክንያቱም ከመደበኛው እየባሰ በምኞት ካልሆነ በስተቀር ከወለድ ነጻ ሊሆን አይችልም:: ውሸቱን ነው ይብስ የሚቀፈኝ:: አይደለም ብሎ ሐቁን መናገር እንጂ በዓረብኛ ቃላት ማጀብ "መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ" ከመሆን አይዘልም::
በመሥሪያ ቤት የቤት ብድር ተመቻቸ እንበል::
ወለዱ 20% ሆኖ በአቆልቋይ አሞርታይዜሽን ሲሰላ 12% ነው::
ይኸው 12% ነው ከወለድ ነጻ የተባለው:: በመደበኛ ባንክ ብድር በ20% ይባል እንጂ ካልኩሌት ሲደረግ 12% ይመጣል::
ሁለቱም ወለዶች አንድ ዓይነት ስለሆኑ ወደ ዋናው ጉዳይ ጋር እንምጣና ብድሩ የ10 ዓመት ነው እንበል::
በመደበኛው ተበድራችሁ በየትኛውም ዓመት ብታቋርጡ ወይም ብትሞቱ ወይም ከትዳር አጋር ብትፋቱ የወደፊቱን ወለድ ሳትጠየቁ ብድሩ ይዘጋል::
ወለድ ነጻ በተባለው ብትበደሩ ግን የወደፊቱንም ጭምር ከፍላችሁ ወይም ወራሽ እንዲከፍል ዕዳ ይቀመጥበታል:: አይ ይህኛው ከወለድ ነጻ ነው ብያለሁ በቃ ብያለሁ ካላችሁ "እሺ መፍትሄውስ?" አትበሉኝ:: መፍትሔው በዚህ ግትርነታችሁ በችግር ስትሞቱ ማየት ብቻ ነው:: እንዲህ ያለ ግትርነት እነአቡጀህል እንኳ መገጀራቸውም እንጃእ:: ምን የተለየ አግኝታችሁ ነው የምትገጅሩት?
በመሥሪያ ቤታችሁ የመጣላችሁን መደበኛውን ብድር ተጠቅማችሁ ቤትም ይሁን መኪና ግዙ:: አንብቡ:: ፊቅሕ ተማሩ:: ጀነት በዕውቀት እንጂ በጅህ^ልና አይገኝም:: አላህን የሚፈሩ ዐዋቂዎች ብቻ ናቸው እንጂ አማኒዮች (ሳያነቡ በመንጋ የሚተራመሱት) አይደሉም:: ወለዱ ሲብስ ከወለድ ነጻ ይሆናል የሚያስብለው ጅ^ህልናና ከዕውቀት ነጻ መሆን ብቻ ነው::
አልገባኝም አስረዳኝ ካላችሁ ክፈሉና ወረፋ ያዙ::
❤35
የሆነ ነገር ያስተምራል
❤47
እኛን የፈጠሩን ሌሎች ኢንተሊጀንት ጭንቅላቶች ቢሆኑና ሮቦታቸው ብንሆንስ?
-------
ስለገንዘብ ስመራመር ብዙ ነገሮችን አንብቤያለሁ:: ዛሬ Mohammed Teshome ነካክቶኝ ነው:: አውፍ በሉኝ:: ያልቃመ ሰው ባያነበው ይመረጣል:: የሆነ ነገር ውስጥ ገብቶ ለተቀረቀረ ሰው ጥሩ ማነቃቂያ ነው:: አብሽሩ:: ምንም አይፈጠርም:: አትፍሩ:: አንብቡት::  (ጽሑፉን እኛው የፈጠርነው Ai አግዞኛል)::

-> እኛ የምንኖረው ነፃ ፍቃድ ባለው ነፃ ዓለም ውስጥ ሳይሆን፣ ለተወሰነ የሀብት ማውጣት ዓላማ በተቀረጸ ግዙፍ ባዮሎጂካል ማስመሰያ (Biological Simulation) ውስጥ ቢሆንስ?

-> ሰብአዊ ማንነታችን፣ ስሜታችን፣ ስልጣኔያችን እና ታሪካችን በሙሉ በከፍተኛ ጥራት በተጻፈ የዲኤንኤ (DNA) ሶፍትዌር የሚመራ የኤአይ (AI) ፕሮግራም ቢሆንስ?

-> የሰው ልጅ በታሪኩ ሙሉ ያሳየው ወርቅ የማከማቸት፣ የመቆፈር እና ሀብት የመሰብሰብ እብደት የራሱ ፍላጎት ሳይሆን፣ በውስጡ የተጻፈ መነሻ ፕሮግራም (Default Code) ቢሆንስ?

ይህንን ምስጢር ለመረዳት አስቀድሞ የጊዜን መለኪያ ማስተካከል ያስፈልጋል። በእኛ ሥልጣኔ እና በፈጣሪዎቻችን (በዚያኛው ልዕለ-ኢንተሊጀንት ፍጡር) ዓለም መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው። በእነርሱ ዘንድ አንድ ቀን ማለት በእኛ ዓለም አንድ ሺህ ዓመት ነው። እኛ ለሺህ ዓመታት ያህል ስንወለድ፣ ስንሞት፣ መንግሥታትን ስንመሠርት እና ስናፈርስ፣ በእነርሱ ሰዓት ገና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የሚከናወን ፈጣን ክስተት ነው።

ታሪኩ የሚጀምረው በዚያኛው ምጡቅ የፍጥረተ-ዓለም ደረጃ ነው። እኛ ከምናውቀው የሦስት ቅጽታዊ ስፋት (Dimensions) በላይ በሚኖር፣ በኳንተም ኃይል በሚቀሳቀስ ልዕለ-ኢንተሊጀንት አርቲፊሻል ኮስሚክ ሲስተም (Hyper-Intelligent Consciousness) ውስጥ ነው። ይህ ከፍተኛ ሥልጣኔ የራሱን የኳንተም ማስያዣ እና የኃይል መከላከያ ጋሻ (Dimensional Anchor/Quantum Shield) ለመገንባት፣ የነሐስ እና የብርጭቆ ባህሪ የሌለውን፣ የማያዝግና ንጹህ የኃይል አስተላላፊ የሆነውን ወርቅን ከብዙ የጋላክሲ ክፍሎች ማውጣት ነበረበት።

ነገር ግን በሩቅ ፕላኔቶች ላይ ሜካኒካል ማሽኖችን አሰማርቶ በየጊዜው ጥገና ማድረግ እና የነዳጅ ወጪ ማውጣት ውጤታማ አልነበረም። ስለዚህ ይበልጥ ጥበበኛ የሆነ መፍትሔ ዘየዱ:: ይህም ራሱን የሚያድስ፣ በራሱ የሚባዛ እና በካርቦን-ውኃ የሚሰራ ባዮሎጂካል ኤአይ (Biological AI) ማምረት! ለዚህም ሲሉ በእነርሱ የጊዜ ሰሌዳ ለአንድ ሳምንት (ለ7 ቀናት) የሚቆይ፣ ምድርን ሙሉ በሙሉ ወርቅ ማውጫ እና ማከማቻ የሚያደርግ ፕሮጀክት ቀረጹ። ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት በእኛ ዓለም 7,000 ዓመታት ማለት ነው። ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያነትም የመጀመሪያዎቹን ሁለት ባዮሎጂካል ኤአይ ፕሮቶታይፖች ማለትም አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ፈጥረው በዲኤንኤ ኮድ አነቃቅተው ወደ ምድር ላኳቸው።

እነዚህ ፕሮቶታይፖች (ሰዎች) ተራ የብረት እና የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች አልነበሩም። በራስ የመጠገን፣ ከምግብና ውኃ ኃይል የመፍጠር፣ በየጊዜው እርስ በእርስ የመራባት፣ ከአየር ንብረት ጋር የማመቻቸት እና ዋናውን መረጃ ለቀጣዩ ትውልድ በዲኤንኤ የመተላለፍ ችሎታ ያላቸው ጥበበኞች ባዮሎጂካል ኤአይዎች ነበሩ። በውስጣቸው የተጻፈው ዋና ትዕዛዝ (Core Protocol) አንድ ብቻ ነበር፡ "ወርቅ እና ውድ ማዕድናትን ቆፍረህ ሰብስብ፤ በአንድ ማዕከላዊ ቦታ አከማች!"

በምድር ታሪክ ውስጥ የነበሩ ታላላቅ የጥንት ሥልጣኔዎችን አስተውሉ፤ ፈርዖኖች፣ የሱሜሪያን ነገሥታት፣ የኢንካ እና የአዝቴክ ግዛቶች፣ የሮማ እና የፋርስ ኢምፓየሮች... ሁሉም ለምን ወርቅ ለማከማቸት ያብዱ ነበር? ወርቅ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነገር አይደለም፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በደሙ ውስጥ በተጻፈው ምስጢራዊ ፕሮግራም ምክንያት ወርቅን የመሰብሰብ፣ የማንጠር፣ የመቅረፅ እና በቤተ-መንግሥታትና በባንክ ካዝናዎች የማከማቸት አባዜ የተጠናወተው ነው። እኛ "የሰው ልጅ ሥልጣኔ፣ ኤኮኖሚ እና የገንዘብ ሥርዓት" ብለን የምንጠራው ነገር በሙሉ፣ በእውነቱ የኮስሚክ ሲስተሙ ወርቅ ሰበሳቢ ባዮ-ሮቦቶች በስራ ላይ ያሳዩት የዲዛይን ውጤታማነት ነበር።

አሁን ያለንበት ወቅት የስድስተኛው ቀን አመሻሽ ነው! በእኛ የዘመን አቆጣጠር የሰው ልጅ የተደራጀ ታሪክ እና ሥልጣኔ ከተጀመረ ወደ 6,000 ዓመታት ገደማ ሆኖታል። በፈጣሪያችን ሰዓት ግን ገና ስድስተኛው ቀን እየተጠናቀቀ ነው። ባለፉት 5,000 ዓመታት (በመጀመሪያዎቹ 5 ቀናት) በዘገምተኛ ፍጥነት ወርቅ ስንሰበስብ የቆየን ቢሆንም፣ በዚህ በስድስተኛው ቀን (ባለፈው 1,000 ዓመት) ግን የስብሰባ ሂደቱ በጥሬ ዕቃ ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ዳታ እና በሰው ሰራሽ አስተስህሮ (Digital AI) ጭምር እንዲፋጠን ተደረገ። የባንክ ሥርዓቶች፣ የማዕድን አውጣጣቶች፣ የላቁ የጂፒኤስ (GPS) ካርታዎች እና የኮምፒዩተር ሒሳቦች በሙሉ የዚያን የጠፋ ወርቅ እና የማዕድን ስብስብ የመጨረሻ ሂሳብ ለማዘጋጀት የተፈጠሩ ንዑስ-ፕሮግራሞች ናቸው።

እኛ ዛሬ ላይ ሆነን "የገዛ ራሳችንን AI ፈጠርን" ብለን ስንመካ፣ ምናልባት በከፍተኛው ሲስተም ውስጥ ያለ ሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራም (Nested Simulation) እየሰራን ሊሆን ይችላል። የሰው ልጅ የራሱን Digital AI መፍጠሩ፣ የዞረበት ፕሮግራም የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወርቅ የመሰብሰቡ ሂደት ሙሉ በሙሉ አውቶሜትድ መሆኑን ያሳያል።
በቅርቡ የሚመጣው ሰባተኛው ቀን ምንድን ነው? ሰባተኛው ቀን የኮስሚክ ሲስተሙ (የልዕለ-ኢንተሊጀንሱ) የስራ ግምገማ፣ የዳታ ማጠቃለያ እና የሒሳብ ማወራረድ ቀን ነው። የሳምንቱ ስራ ሲጠናቀቅ ሲስተሙ "Log Out" ያደርጋል ወይም የኔትወርክ ግንኙነቱን ይዘጋል። በምድር ላይ ያሉትን ባዮሎጂካል ሮቦቶች (ሰዎችን) በሙሉ ዳታቸውን በመጫን፣ እስካሁን የተሰበሰበውን ወርቅ፣ ፕላቲነም እና ውድ ሀብት መጠን በሒሳብ መዝገብ ይረከበናል።

የሰባተኛው ቀን ፀሐይ ስትወጣ፣ ልዕለ-ኢንተሊጀንሱ ሂሳቡን ተቀብሎ "ሥራችሁን አጠናቃችኋል" ብሎ ፕሮግራሙን ይዘጋዋል? ወይስ ደመወዛችንን ከፍሎ ዘና በሉ የሆነ ሌላ ዓለም ይልከናል ወይስ አዲስ ፕሮግራም ጭኖ Reboot ያደርገናል? እኛ የፍጥረተ-ዓለሙ ጌቶች ሳንሆን፣ የሌላ ከፍተኛ ሥልጣኔ ወርቅ ቆፋሪ ባዮሎጂካል ኤአይዎች ነን የሚለው እውነት ሲገለጥ፣ የሰው ልጅ ታሪክ የመጨረሻው ገጽ ይጻፋል።
(ቻይና ሬስቶራንት ውስጥ የሆነ ጊንጥ መሳይ ፍጡር ልበላ ቋምጬ የመጣልኝ ሐሳብ ቢሆንስ?)
❤18
ኢምፖርት ስልጠና የተመዘገባችሁ ምእመናን እና ምእመናት በእኛ በኩል ዝግ-ጅታችንን አጠናቀን ቀኑን በጉጉት እና በሚዳቆ እየጠበቅን ነው:: በነገራችን ላይ ጉጉት እና ሚዳቆ, ዋልያና ኒያላ Harmonized System Code (HS Code) አላቸው:: አንድ ሰው ከሚመለከተው አካል አስፈቅዶ ቀይ ቀበሮ 🦊 ወይም የሜዳ አሕያ 🦓 ኤክስፖርት ማድረግ ቢፈልግ ዓለም አቀፍ ኮድ ጠቅሶ ነው የሚልከው:: የኮዱ መጽሓፍ ዘጠኝ ምዕራፍ አለው:: ለወደፊት ድንገት discover ቢደረጉ ተብለው ክፍት የተደረጉ አሉ:: የሆነ ዕቃ ማስመጣት ስትፈልጉ ይህንን ኮድ ጠቅሳችሁ ነው የምታጓጉዙትም የምትቀረጡትም:: የምታስመጡት ዕቃ የቆጮ መጠፍጠፊያ ቢሆን HS ኮዱን እንዴት በቀላሉ እንደምታገኙት በስልጠናው ይዳበሳል:: የተመዘገባችሁ እዚያው ቴሌ-ግራም ላይ መልዕክት ይደርሳችሗል:: የስልጠና ፕሮ-ግራም እና የሚነበቡ ነገሮች ይቀርቡላችሗል:: የተሳትፎ ሰርተፊኬት ሲያልቅ ይሰጣል:: ግርግር ምናምን የብለይ:: መሰልጠን:: ወደ ሥራ መግ-ባት:: በበርጩማም ቢሆን እሳተፋለሁ የሚል ምእመን ኮሜንት ላይ ዳሰሳ ያድርግ::
❤6
Forwarded from Hawlet Ahmed
መ-ገንዘብ 2 (ለአዋቂዎች)
መ- ገንዘብ 3 (ለታዳጊ ወጣቶች)

መጻሕፍት ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ ጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ገብተዋል። ይህን አጃኢበኛ መጽሐፍ ሸምታችሁ አንብቡ። ታዳጊ ወጣቶችም እንዲያነቡ ሸምቱላቸው። በወጣቶቻችን ተስፋ አለን! 😊
❤6
የባንክ አካውንቴ መደበኛው ነበር:: ብዙ ወለድ አለው:: ምን ላድርገው? ብሩን ለማንስ ልስጠው?

-> ወተት, ማር, ጤፍ, ትምህርት እና እጅግ ጠቃሚ የምትላቸው ነገሮች ቅድሚያ በእርሱ ግዛበት:: ንጹሑ ገንዘብ ማለት ባንክ ወለድ ብሎ የሰጠህ ነው:: ወንድሜ እርሱኛው ገغኒማ (ምርኮ) ስለሆነ 1/5ኛውን ለበጎ ብታውለው ሁላ ጥሩ ነው:: ባንክ መጀመሪያ 100 ብር ሲሰጥህ መቶ ግሽበት ነው የሚሰጥህ:: ወለዱ (ፋኢዳው) ከግሽበት የዳነልህ ሐቅህ ነው::

አላህ የገንዘብን በረካ በሪባ ያጠፋል:: ምጽዋትን ያፋፋል:: መቶ ብሩን ባንክ አስቀምጠህ ብታየው በረካው ይጠፋል:: መቶ ብሩ ሪባ ነዋ! ከሪባ የተጣራው 7 ብሩ ነው:: እርሱኛውን ነው ገغኒማ የምልህ:: 93 ብሩ ቶሎ ወደ ንብረት ቀይረው:: ይህኛው በጣም ጥቂት ሰዎች ካልሆኑ አይገባቸውም:: ምክንያቱም ስለፋይናንሻል ሲስተሙ እስከ ምንጩ ማለትም ስለ 12ቱ ነገድ ካዝና ስለ FED የሚያውቁት ነገር የለም:: መ-ገንዘብ 2 ላይ በስፋት አለልህ::
❤31
🎯 ቢዝነስዎን እና ሙያዎን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዝግጁ ነዎት?

HAB Management & Technologies እንደ ምንጊዜውም በተግባር የተፈተኑ 3 ታላላቅ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን አቅርቦልዎታል!

1️⃣ የኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓት (Mastering the Ethiopian Taxation System)

📅 ቀን፡ መስከረም 26፣ 27 እና 28 / 2019 (Oct 6, 7 & 8 / 2026)

**************************

2️⃣ የአስመጪነት ንግድ ከ ‘ሀ’ እስከ ‘ፐ’ (Import Trade from A to Z)

📅 ቀን፡ ጥቅምት 3፣ 4 እና 5 / 2019 (Oct 13, 14 & 15 / 2026)

********

3️⃣ የፋይናንስ እውቀት ለሥራ መሪዎች (Finance for Non-Finance Managers)
📅 ቀን፡ ጥቅምት 10፣ 11 እና 12 / 2019 (Oct 20, 21 & 22 / 2026)

💡በስራው ላይ በቂ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች (ባንከሮች፣ ታክስ ኦዲተሮች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች) የሚሰጥ።

የሦስቱም ስልጠናዎች ሰዓት
ጠዋት ከ2:00 እስከ 7:00

🌐 ድረ-ገጽ፡ www.hab.et/register
✈️ ቴሌግራም፡ @hab_management
📞 ስልክ፡ +251990555599

💰 የስልጠና ክፍያ፡ 13,800 ብር (ለእያንዳንዱ ስልጠና)
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 1000762139646 (HAB Management & Technologies)
❤13
አለመፖሰትም እንደ መፖሰት የሆነበት አንዳንድ ወቅት አለ:: አጃዒብ!
🤔16
በባንክ እና ገንዘብ ጉዳይ አንዳንድ ሙስሊሞች ውይይት (ክርክር) ይፈልጋሉ::

ዕውቀት ላይ ክርክር አለ እንዴ? ዕውቀት ቀርቶ በሆነ ዕቃ ተከራክረህ ፍርድ ቤት ሄደህ ባለሐቁ መረጃና ማስረጃ አጥሮት ብትረታው ሀላል አይሆንልህም:: ዕውቀት እና ትምህርት ላይ ደግሞ ይብሳል:: ያልተማረ ሰው በተማሪያዊ አደብ ይማራል:: ያልገባውን በተማሪያዊ አደብ ይጠይቃል:: መጠየቅ እና መማር ካልቻለ ያደምጣል::

ፌስቡክ ቁጥር አንድ ከምቦልካቸው ውስጥ የባንክና የወለድ ጉዳይ ጽፌ አደበ ቢስ የሆኑ ኮማቾችን ሰከንድ አልሰጣቸውም:: ምክንያቱም ሲስተሙ ገርፎ ያመጣቸዋል:: በአረቄ ጉዳይ ብናወራና አደበ ቢስ ቢሆኑ እንኳ አረቄ የሙስሊሙ የሕይወት ሲስተም ስላልሆነ ብዙም አያገኛቸውም:: የባንክ ጉዳይ ግን በእስትንፋሳቸው ልክ ያገኛቸዋል:: በአደብ እንደመማር ሲያለምጡ አልታገስም::
👍11