Hasen Injamo
15.1K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
391 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
👇🏼👇🏼👇🏼
👆🏾👆🏾👆🏾
ታክስ እንዴት ተጀመረ?
ንጹሕ የብር ሳንቲሞች በሕዝቦች መካከል ተሰራጭተው ነበርና አምጡት ቢባሉ በጀ አይሉም:: ስለዚህ ንጉሡ የታክስ ሲስተም ፈጠሩና ሰዎች እንዲገብሩ አደረጉ:: የተሰበሰቡ ንጹሕ ብሮች ላይ የንጉሡ ፎቶ የታተመባቸውና መጠነኛ መዳብ እየተቀላቀለባቸው ሳንቲሞች መለቀቅ ጀመሩ:: ሕዝቡ ብሮቹን አስረክቦ ሲጨርስ የመዳብ ቀላጩ እየተጨመረ ሄደው::

ኢትዮጵያም ውስጥ በ1980ዎቹና በ1990ዎች ገበያ ውስጥ የተበተኑ የመዳብና ኒኬል ሳንቲሞች የተሰበሰቡት በኢትዮ ቴሌኮም የግድግዳ ስልኮች አማካይነት ነው:: በወቅቱ የብረት ሳንቲም እየተተዋወቀ ስለነበር የተሻለ ዋጋ ያላቸው ሳንቲሞች በስልክ ማስደወያ ተሰብስበው ሲያልቁ ስልኩም ከአገልግሎት ውጭ ሆነ:: ለገሃር ጋር የኒኬልና መዳብ ሁለት 50 ሳንቲሞች በብር ከ20 ይሸጡ ነበር:: ስልኮቹ የሚሠሩት በአዲሱ የብረት ሳንቲም ሳይሆን በአሮጌዎቹ ሳንቲሞች ስለሆነ በመታሸት ብዛ ጽሑፋቸው የደበዘዙ ሳንቲሞች ላይ ሁላ እየሠራ በአዲሱ የብረት ሳንቲም ግን አለመሥራቱ ገርሞኝ ወዲያው በራልኝ:: ያኔ ነው የፋይናንስ ሲስተሙ ከጀርባ ቁ^ማር እንዳለው የገባኝ::

ታክስም ልክ እንደዚሁ ነው:: መንግሥት አዳዲስ እና እንደ ምላጭ ስል የሆኑ ብሮችን እያተመ/እያሳተመ ከምእመኑ ላይ አሮጌ ብር ይሰበስባል ተብሎ አይታሰብም:: የሚሰበስበው ሌላ ነገር ነው:: የመግዛት ኃይልን ነው የሚቀንሰው:: ሳር ወይም ጽድ ወይም ጸጉር የሚከረከመው ወጣ ወጣ ያለውን እንደሆነው ሁሉ ከገቢም ወጣ ወጣ ያለውን በታክስ እየተከረከመ ይስተካከላል:: የ100 ብር ምግብ ልትበላ ገበያ ስትወጣ የ70 ብር ብቻ እንድትበላ ስትደረግ የሠላሳ ብር ምግብ ለሌላ ሰው ይተርፋል:: ነጋዴ ሁሌ የታክስ ቢሮ ወኪል እንጂ የታክስ ከፋይ አይደለም:: ከበላተኛ ይሰበስብና ወደ መንግሥት ካዝና ይወረውራል:: እርሱ የሚከፍለው ከትርፉ ላይ ነው:: ትርፉ ብር ሌላ ቦታ ችግር እንዳይፈጥር ይከረከምበታል:: ባንተ ሶላት እና ጾም ሰማይ እንደማይቆመው ሁሉ ባንተ ታክስም መንግሥት አይቆምም:: ያገር ውስጥ ብር አይቸግረውም:: አታካብድ::
👍30
የሸይኽ ዐዲል አባት ሸይኽ አሕመድ ዐብዱልቃዲር ሸሪፍ ወደ አኼራ ተሻግረዋል:: በያለንበት ፋቲሃ:: ቀብር ኮልፌ ነው ተብሏል::
❤73
በዚህ ወቅት ስለቢዝነስ ወይም የሆነ ሌላ ነገር ስንፖስት እየሆነ ባለው ነገር ሳይሰማን ቀርቶ አይደለም:: ስለምን እንደሚጻፍ ግራ ያጋባና በቃ ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል እንኳ ሞክረን አይቻልም:: በእርስበእርስ ግጭት ላይ ተሸናፊ እንጂ አሸናፊ አይገኝለትም:: ሁላችንም ነን ተሸናፊው:: አሸናፊም ካለም የውጭ ጠላት ነው የሚሆነው:: እንደ ሀገር የተራዘመና የሚራዘም ግጭ^ት ውስጥ መሆናችንን ሲታሰብ ይሸክካል::

የጦ^ርነቱ ዘላቂ መፍትሔ መሠረታዊ ፍላጎቶች እና ኢንፍራስትራክቸር ግንባታ ላይ ማተኮር ነው::

ይህንን እያስብኩ የነበርኩት 2ኛው ልጄን ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ግቢ እያስጎበኘሁት ነበር:: እየዞርን ወደ ምክር ገባሁ:: ግቢው የአጼ ኃይለ ሥላሴ ቤተመንግሥት እንደነበርና ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደቀየሩት አስረዳሁት:: ምን ዋጋ አለው:: አመጹ ከዚሁ ግቢ ተቀጣጠለና በአሰቃቂ ሁኔታ ወረዱ:: እነሆ አለቆቻችን ጎረምሶች ሆነው ፍዳችንን እየከፈልን ነው::

ጃንሆይ ሽማግሌ ነበሩ:: ትውልዱ ስህተታቸውን ትቶ በጎ ነገራቸውን ወስዶ አክብሮ ቢያሰናብታቸው ኖሮ ይከበር ነበር:: ታላቅን ማክበር ክብርን ይጨምራል:: ይህ የኤኮሲስተሙ ሚዛን ነው:: ያኔ የጀመረ .. ጎረምሶች ሽማግሌዎችን ያሳድዳሉ:: ከዚያም እርስበእርስ ይሳደዳሉ:: ወጣቶች እርስበርስ ነው የተላለቁት:: የትም ሀገርና ባሕል አባት አያጠፋም:: ከእኛ ከልጆች ትክክል የእነርሱ የአባቶች ስህተት ይሻላል:: ታላቅ ሰው የተሳሳተ ሥራ እየሠራ መስሎ ካየኸው ሽሽ:: አምልጥ:: ፈተና ውስጥ ወድቀሃል:: ነገ አንተም ዕድሜህ እዚያ ጋር መድረሱና ሆርሞንህ መቀየሩ አይቀርም:: ምናልባትም ምላሹ ከጊዜ ታገኘዋለህ:: ታላቅ ተሳሳተ ብለህ እንዳትሳሳት:: እርሱ አንተ ያላገኘኸው ሌክቸረር ማለትም ጊዜ አስተምሮታል:: ሕጻን በነበርክ ወቅት የምታለቅስለት ነገር አሁን ያስቅሃል:: እናልህ ባልተማርከው አድቫንስድ ኮርስ ላይ ምላሽ እንዳትሰጥ እያልኩ እየመከርኩት ክፍለጊዜው ደርሶ ክላስ ገባ:: እኔም ወደ ቤት ሄድኩኝ::

አንተዬ ትምህርት መቀጠል ግን አምሮኛል:: ተማሪ መሆን እኮ ሕይወት ነው:: ደስ የሚል::
❤59
ልጅህን አጎብዘህ አስተምረህ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አግኝቶ ያለው ፈተና ... ከእስካሁኑ ማለትም ከመጣኸው መንገድ ይበልጣል:: በዙሪያዬ ያሉ የብዙ ሰዎችን ልጆች በዩኒቨርሲቲ ተበላሽተውባቸው አስተውያለሁ:: አንዲት ጎረቤታችን አለች:: አንድ ልጇን እንዴት ሆና እንዳሳደገችው እና በትምህርት ለውጥ እንዴት እንደጠበቀች ዛሬ ላይ እንዴት ተስፋ እንደቆረጠች ማየት ያማል:: ምንም ስላልተማረች ልጇን ማስጠናትም ይሁን ለአስጠኚ መክፈል ስለማትችል ትክክል ሲሠሩ ✔️ሲሳሳቱ ደግሞ ❌ እንደሚሰጣቸው ጠየቀች:: ምልክቶቹን አስጽፋ ይዛ ለየቻቸው:: ከዚያ የልጇን ደብተር እያወረደች ❌ ያመጣባቸውን እየጠየቀችው እና ትምህርት ቤት ሄዳ ከመምህራን ጋር እየተወያየች ማትሪክ ጥሩ ውጤት አመጣላት:: ከዚያ ክፍለሃገር ዩኒቨርሲቲ ተመደበ:: ከ1ኛ ዓመት ግን ማለፍ አልቻለም:: በሚገርም ፍጥነት ጢጥ (ዕፀ-ሲዖል) እንደ ሚግ ሳበ:: High እበራለሁ ሲል ሕይወቱን Flight mode ላይ አድርጎ ለሃጭ በለሃጭ ሆኖ ተዝረክርኮ ቀረ::

ልጆቻችሁን ዩኒቨርሲቲ የምትልኩ ልጆ ከፍተኛ ክትትል አድርጉ:: ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በአጥራቸው ዙሪያ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማየት የግድ ይላቸዋል:: ትምህርቱ እንደሆን Gemini እና GPT እየሠሩት ስለሆነ የወጣቱ ጤናና ስነምግባር ላይ ያተኩሩ:: Gemini እና GPT የማይተኩት ይህንን ነው:: የብልሽት መሠረቱ ሀይስኩል ላይ ነው የሚጣለው:: በዚህ ዘመን ትዳሮች አይረጉም:: ብቸኛ የዓይን ማረፊያ ልጆች ናቸው:: በእኛ ዘመን ጎረቤትም ይሁን የጓደኛ ወላጅ እንደራስ ወላጅ ይፈራ ነበር:: ጎረቤቶች ቢኮረኩሙን ወላጆች እሰይ ነበር የሚሉት:: አንዱ ያንዱን ልጅ እየተቆጣጠረ አሳድጎኣል:: ሀሺ^ሻም ትውልድ እየበዛ ስለሆነ በያቅጣጫው ርብርብ ይፈልጋል:: ጭራሽ በኢለመንተሪ ደረጃ በጀላቲን (በረዶ) ይነጅሱዋቸዋል የሚባልም ሰምቼ ገርሞኛል:: ዩኒቨርስቲዎች ግቢዎቻቸውን ዘወትር መፈተሽ አለባቸው:: ዩኒቨርሲቲዎች ግቢዎቻቸው ሰፋፊ ስለሆኑ የሚተክሉ ተማሪዎች እንዳሉ ሁላ ትናንትና ሰምቻለሁ::
👍47
አማርኛው ታክስ እና ግብርን ይለያቸዋል::
=====
ግብር ማለት አንድ ገባሪ በግልም ይሁን በድርጅት ካተረፈው ላይ ቀጥታ እራሱ ገባሪው የሚገብረው ነው:: ታክስ ግን አንድ ድርጅት የመንግሥት ወኪል ሆኖ ከመጨረሻ ተጠቃሚ ላይ ሰብ-ስቦ ለመንግሥት የሚያስገባው ነው:: ታክስን ማጭ^በርበር በምንም አይማርም:: በኃይማኖት እና በብሔ^ር ልደበቅ ብትል ማንም አይሠማህም:: አደራ ሰብስብ የተባልከውን ሰብስበህ ማስረከብ ብቻነው:: ወደ ግብር ስመለስ አንድ በላተኛ ካተረፈው ላይ ብዙ እንዳይበላ በውዴታ ወይም በትምምን ወይም በሙግት ከሥጋው ላይ ቀንሶ የሚያስገባው ነው::

ትናንትና መንጃ ፈቃድ ላድስ እግረ ጎማዬ ወዳንዱ አዲስ መሶብ ገባሁ:: ወደ ፎቁ ደረጃ ስለሚያደክምህ እዚሁ ግቢ ውስጥ ወዳለው አውቶቡስ ግባ ብለውኝ ይህንን በምጽፍበት ፍጥነት ጨርሰውና አትመው ሰጡኝ:: እንዲህ ሲሆን ግብር እና ታክስ ደስስስ እያለህ ትከፍለዋለህ:: ከጎኑ ሳጥን ብፈልግ አጣሁ:: የአስተያየት ሳይሆን የግብር ማስገቢያ ሳጥን ቢኖር ቦጨቅ አድርጌ አስገባ ነበር:: ያም ሆነ ይህ መብት እና ግዴታን በደንብ የሚያስጨብጥ ስልጠና ዘወትር ያስፈልጋል::
(የመዠመሪያው ኮሜንት ላይ ፈልጉት)
❤30
Hasen Injamo
አማርኛው ታክስ እና ግብርን ይለያቸዋል:: ===== ግብር ማለት አንድ ገባሪ በግልም ይሁን በድርጅት ካተረፈው ላይ ቀጥታ እራሱ ገባሪው የሚገብረው ነው:: ታክስ ግን አንድ ድርጅት የመንግሥት ወኪል ሆኖ ከመጨረሻ ተጠቃሚ ላይ ሰብ-ስቦ ለመንግሥት የሚያስገባው ነው:: ታክስን ማጭ^በርበር በምንም አይማርም:: በኃይማኖት እና በብሔ^ር ልደበቅ ብትል ማንም አይሠማህም:: አደራ ሰብስብ የተባልከውን ሰብስበህ…
👉🏼''Mastering the Ethiopian Taxation System''

ለ 3 ቀናት
መስከረም 26፣ 27 እና 28 ጠዋት

(ምዝገባ አርብ መስከረም 22 11:00 ላይ ይጠናቀቃል)

👉🏼''Finance for Non-finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት

ለአንድ ስልጠና ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register
ወይም 2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
🤳 +251990555599
የስልጠና ቦታ: አዲስ አበባ ሳርቤት አካባቢ
❤14
በቀደም ዘመናት መሪው የተፈጥሮ ሲስተም ስለነበር ሁሉም ወይም አብዛኛው ሰው ዙሪያውን ከሞላ ጎደል ያውቅ ነበር:: ማቀድም አይቸገርም:: ከዚያ እጅግ ውሱን ሰዎች ብቻ የሚገነዘቡት አርተፊሻል የፋይናንስ እና የፖለቲካ ሲስተም መጣ:: ወደ አልታወቀ future መልፋት ብቻ ሆነ:: የፋይናንስ ሲስተሙ አዘዋወር ከገባህ ጭንቀቶች በብዙ ይቀንሳሉ:: አሁን Ai ባንኮች እንኳ ሊቆጣጠሩት ወደማይችሉት ሲስተም እየከተተው ነው:: አዳዲስ ፋይናንሻል ፕሮዳክቶች እየመጡ ናቸው:: የፊያት ሲስተም ሳይገባህ የሜታዳታ ሲስተ አልፎ የ Ai ፋይናንሻል ፕሮዳክት እየተካው ነው:: ዛሬ ላይ ሀብታም እና ደሃ የሚባሉት ሊገላበጡ ይችላሉ:: ዛሬ ብዙ ፍየል እና እህል ያለው ሰው ደሃ ገበሬ ሲሆን ምንም የሌለው የከተማ ፖለቲከኛ ሀብታም ይባላል:: ይህንን ሁኔታ Ai ሊገለብጠው ይችላል:: አንዳንድ ሀብታሞች ግብርናና ማዕድን ላይ ለምን ያተኮሩ ይመስላችሗል?
❤26
Copy paste
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ ማስተናገጃ መመሪያ ይፋ አደረገ።

• ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 የበጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ ወቅት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታቸውን መወጣት ላልቻሉ የተወሰኑ የንግድና አገልግሎት ዘርፎች የተዘጋጀውን ዝርዝር የማስተናገጃ የአሰራር ስርዓት ይፋ አፍርጓል።

ቢሮው መስከረም 2019 ዓ.ም ባወጣው የክንውን መመሪያ እንዳብራራው፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 እንዲሁም በነባሮቹ አዋጆች ቁጥር 979/2008 እና 983/2008 መሰረት የደረጃ «ሀ» እና «ለ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብና መግለጫ መያዝ ህጋዊ ግዴታቸው ቢሆንም፣ በርካታ ከፋዮች የስራ ባህሪያቸውን ጠቅሰው ቅሬታ በማቅረባቸው ፍትሃዊ የታክስ አሰባሰብን ለማረጋገጥ የመጨረሻ የሽግግር አሰራር ዘርግቷል።

​በመመሪያው ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው፣ ስራዎችን ከመንግስት ጋር በተገባ ውል ብቻ የሚያከናውኑ እና የተለየ ድጋፍ የሚሹ ግብር ከፋዮች ማለትም:-

- በትምህርት ቤቶችና በምግብ ማዕከላት ውስጥ በምግብ አቅራቢነት የተደራጁ መጋቢ እናቶች፣

- በከተማ ፅዳትና ውበት፣

- በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እና በገፀ-ምድር ማስዋብ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ከመንግስት ተቋማት የተከፈላቸውን ዓመታዊ ክፍያ የሚያሳይ ሰነድ ሲያቀርቡ፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ «ሐ» መሠረት ግብራቸው ተሰልቶ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

ከዚህም በተጨማሪ የሸገር ዳቦ የሚሸጡ ማህበራት በተጓዳኝ የሚያከናውኑት ተጨማሪ ንግድ መኖሩ በመስክ ምልከታ ከተረጋገጠ ተጨማሪው ስራ ብቻ ተለይቶ ግብር እንዲጣልበት ይደረጋል።

• የጫኝና አውራጅ፣

• የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኤሌክትሪክ ምሰሶ ጉድጓድ ቆፋሪዎች፣

• በጥበቃ ስራ የተደራጁ ማህበራት እንዲሁም የታክሲ ታራ አስከባሪዎች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ሲኖርባቸው ያልያዙ ግብር ከፋዮች ለዘርፉ በተቀመጠው የትርፍ ህዳግ መሰረት ግብራቸው ይሰላል።

​በሌላ በኩል፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና በአዋጁ የተዘረዘሩ ሌሎች 8ቱ ዘርፎች የሂሳብ መዝገብ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ወጪን በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ እስካላወጣ ድረስ ቀደም ሲል በተጠኑ ጥናቶች መሰረት ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ እንዲያዝላቸው፣ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚሰላበት የተጣራ ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ «ሐ» እንዲስተናገዱ ይደረጋል።

በግምት ግብር አዋሳኝ አዋጅ ቁጥር 138/2010 መሰረት የደረጃ «ሀ» የንግድና የመኖሪያ ኪራይ ገቢ ያላቸው አካላትም መዝገብ ካላቀረቡ በተመሳሳይ መልኩ 35 በመቶ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ በ65 በመቶ ገቢያቸው ላይ ግብሩ ይሰላል።
​
መመሪያው የትራንስፖርት ዘርፉን እና የአነስተኛ ግብር ከፋዮችን እድገት በተመለከተም ዝርዝር መፍትሔዎችን አስቀምጧል።

በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች በ2016 ወይም በ2017 የበጀት ዓመት የ57 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ተደርጎላቸው በደረጃ «ለ» ቀመር መሰረት ግብራቸውን እንዲያሳውቁ ይደረጋል።

በአዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት በደረጃ «ለ» እና «ሐ» ስር ቆይተው በአዲሱ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ወደ ደረጃ «ሀ» ያደጉ ግብር ከፋዮችም የ2017 ዓመታዊ የንግድ ስራ ግብር እና የትርፍ ድርሻ ክፍያቸው ተወስዶ በደረጃ «ለ» አሰራር እንዲሰላ ተወስኗል።

በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 23 አማራጭ አነስተኛ ግብር ለደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የተደነገገውም ከ2 ሚሊዮን ብር አማራጭ አነስተኛ ግብር 2.5 በመቶ ጋር ተነጻጽሮ የተሻለው ተወስዶ ግብር ይወሰናል።

​ቢሮው በመሪሪያው ላይ እንዳመለከተው ፣ ይህ ሁሉን አቀፍ የማስተናገጃ አሰራር ተግባራዊ የሚሆነው ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ነው።

በዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ለቀጣዩ የበጀት ዓመት የሂሳብ መዝገብ ይዘው ለመቅረብ ህጋዊ የቃል-መሐላ እንዲፈፅሙ የሚደረግ ሲሆን፣ የሰነድ አለመያዝ አስተዳደራዊ ቅጣትም አብሮ ተግባራዊ እንደሚሆንባቸው ተመላክቷል።

ከቲክቫህ
መስከረም 23 ቀን 2019
❤11
ከድህነት መውጣት ከምትፈልግበት ጉጉት በላይ ጊዜህን ለንባብ ስጥ:: የሚያመረቅን (ሞቲቬት) የሚያደርግ ጽሑፍም ብታነብ አይከፋም:: ድሮ ንግድ በማንበብ የምናገኘው አይመስለኝም ነበር:: ምክንያቱም እኔ የቢዝነስ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ምሩቅ ሆኜ ግን ድህነት የሌለ አላገ^ጠብኝ:: ለምን እንደተፈጠርን, ፀሓይ ምናባቷ ልትሠራ እንደምትወጣ ግራ የሚያጋባ የገንዘብ እጦ^ት ጭንቅ ውስጥ ነበርን:: ሚሊዮኖች አሁንም እዚሁ ጭንቀት ውስጥ ናቸው:: ጸሎቱና ዱዓው ምንም ዋጋ የሌለውና ጭራሽ ወደ ጭንቀት እና አምላክን ወደ መሸሽ የሚወስድ ነው:: ይብስ ብሎ ለኃይማኖት ሰፈር ስካመሮች ከማጋለጥ ውጭ ረብ ያጣ ... እንደውም ዱር^ዬ የተሻለ ስብእና የሚታይበት አውድ ውስጥ ነን:: ችግሩ ከኃይማኖትና ከዱዓው እንዳልሆነ የገባኝ ስለገንዘብ ሲስተም ሲገባኝ ነው:: አንዳንድ ሀብታም መሆኛ መንገዶች በትምህርት ካሪኩለም የሉም:: የአፍሪካን ካርታ አጥብበው የሳሉ ሰዎች ያንተን ኑሮ ላያጠቡት ነበር?

መኪና እንዴት እንደሚሠራ ወይም መስተዋት እንዴት እንደሚመረት ስታውቅ ብዙ ግርዶሽ ይለቅሃል:: የገንዘብ ሲስተሞችን ማወቅ ከድህነት መውጫውን ካርታ ማግኘት ነው:: ሪሲፒውን ታውቃለህ:: አንድ ሽሮ ወጥ ምን ምን ሲካተትበት ለመብል እንደሚበቃ ማወቅ ማለት ነው:: ድስት, ውኃ, እሳት, ጨው, ዘይት, ቅመም, ምድጃ, ማማሰያ, ሽሮ, በርበሬ/እ^ርድ የመሳሰሉት ያስፈልጉታል:: እነዚህን ነው ስቴፓቸው ጠብቀህ የምታዋቅረው::

ሀብት እንደዚሁ ሪሲፒ አለው:: በሌላ ምሳሌ ሀብት እንደ ሰው ሁለት እግሮች አሉት:: አንዱ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው አትራፊ ድርጅት እና ለኮላተራል የሚሆን ሕጋዊ ዲጂታል ካርታ ያለው ቤት ናቸው:: ከሁለቱ አንዱ ከጎደለ በክራንች ከመዝለልም የባሰ ነው:: ሁለቱም ከሌሉህ በእንፉቅቅ ተራራ ከመውጣት ይብሳል:: እዚህ ጋር ነው በአምላክህም በጸሎትህም በመንግሥት በፀሓይም የምታማርረው:: ወደ ሁለቱም ግብአቶች (ትርፋማ ቢዝነስ) እና ኮላተራል መሄድ ዛሬውኑ መጀመር ነው:: ሲስተሙ በአቋራጭ ልግባ ብትል አያስገባህም:: ድሮ በዘመድ ነበር:: አሁን ኮምፒውተሮች ዘመድ አያውቁም:: Ai ዘመድ የለውም:: ለጊዜው ሰዎች ያጫውቱት ይሆናል:: ግን አቋራጩ እየጠበበ እየሄደ ነው::

ድሮ ኪስህ ውስጥ 500 ብር ኖሮህ የአምስት መቶ ሺህ ብር ፈቃድ አውጥተህ ትንቀሳቀስ ነበር:: አሁን የምትችለው በያዝከው 500 ብር ብቻ ነው:: ከዚያ እያንዳንዱ የገንዘብ እንቅስቃሴህ በባንክ ሰርቨሮች ላይ ይታያል::

ቀጣይ ሀብት ወደ ኮርፖሬት (ድርጅታዊ) አሠራር እየሄደ ነው:: ትናንሾቹ እየተዋጡ ይሄዳሉ:: ከላይ ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ ይፈጠራል:: የተለያዩ ንብብሮች አሉት:: በምንም አይነት ድሪል አትበሳውም:: ከስር ትርመሰመሳለህ:: አዋሽ ባንክ ወደ ታች መውረድ አይችልም:: አንተ ሀብታም መሆን የሚከብድህ ያህል ሀብታሙም ደሃ ለመሆን ይከብደዋል:: ፖለቲከኞች የሀብታም ዘበኛ ናቸው:: ለጀነራሉ ውጪ ሀገር አካውንቱ ላይ ያስገቡለታል:: ከዚያ አበቃ::
❤53
👍6
https://vt.tiktok.com/ZSbQDpQBv
መ-ገንዘብ በድምጥ
🌚3
ዛሬ ቴሌግራም Live ይኖረናል::

https://t.me/Haseniye/6479
❤18
🔨
😁69
Live stream scheduled for
👍4
❤10
❤7
Live stream started
Live stream finished (52 minutes)