Hasen Injamo
15.1K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
391 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
Live stream started
Live stream finished (52 minutes)
ላይቭ አብቅቷል
👏21
መ-ገንዘብ መጽሐፍ ጃእፈር ሳይኖር አይቀርም
+251 91 112 5324
❤1
የ Alex Abraham ስቶሪ ማግኘት መታደል ነው:: አሌክሶ ወደ ውይይት እንሂድበት:: ያሻህን እዘዘኝ::
👍42
እንደ ሀገር የድህነታችን ዋነኛ ምንጭ የተፈጥሮ ሀብት ማነስም መብዛትም ... መጥፎ መንግሥት መኖር አለመኖር ... ሥራ መጥላታችን አለመጥላታችን ብቻ አይደለም:: ከዚህ የሚከፋና ለመቀየር ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል የፋይናንስ ፒራሚድ አለ::

ብዙ ቡና እና ወርቅ አመረትን እንበል:: ከዚያ የተሻለ ማሽን ብንፈልግ በምን እንገዛዋለን?
-> በአሜሪካን ዶላር::
እኛ ልናትመውም ልንቆጣጠረውም አንችልም:: ስለዚህ ሳንወድ በግድ አሜሪካንን እንለማመጣለን:: መንግሥታችንን ያለ እነርሱ ውክልና መምረጥ አይታሰብም:: የተመረጠውም ውልፍት ካለ .. አያድርም:: ካደረም አይውልም:: ልክ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት በዶክተር ዐብይ ላይ ቢተብት ማለት ነው::

Well, የትግ^ራዩ የደፂ ትእቢት በዓብይ ላይ እና የዓብይ ትእቢት በአሜሪካ ላይ ይለያያሉ:: ደፂና ዐብይ ሊሸናነፉ ይችላሉ:: ያው አለቃ-አሜሪካ ነች የምታጫውታቸው:: አሜሪካንን ግን ማን ያጫውታል ቢሉ ያው ፈጣሪ ብቻ ነው::

እኛ እንደ ሀገርም እንደ ግለሰብም ይህንን ሲስተም እና አቅማችንን ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ ነው ማድረግ ያለብን:: (ለዚህም መ-ገንዘብ ፎርሙላዎችን propose አድርጓል)::
❤63
ከላይኩ ኮሜንቱ በለጠ::
😁48
አንዳንዴም ቲክ እና ቶክ ላይ መከሰት ያስፈልጋል በሚለው
👇🏼👇🏼

https://vt.tiktok.com/ZSbppgv4m/
❤16
ደስ የሚል ዜና ነው::
ኢትዮጵያ ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ገንብታለች::
ትኩረቴም መጽሓፎቼም ወርቁ ላይ ናቸው:: 1944 ላይ አሜሪካ ዓለምን ያቸነፈችው በወርቅ ክምች ነበር:: 1971 ላይ ካ^ደች:: ብዙ ሀገራት ከአሜሪካን ዶላር ተጽእኖ ለማገገም የቻሉት በወርቅ ነው:: ዓለም ሁሉ ወርቅ ወርቅ እያለ ነው:: ለ BRICS መገበያያ ወርቅን እንደ ደጋፊ ሀብት ቀርቧል:: ለዚህም ብሔራዊ ባንክ ወደ CBDC እየሄደ ነው:: ስለ CBDC በመ-ገንዘብ ላይ በስፋት ቢብራራም በድምጽ ማብራራት ይፈልጋልና ወይ ቴሌግራም ወይ ቲክቶክ ላይ እንገናኛለን::
👍98
መሪ ስትሆን ሕዝቡን አንድ የሚያደርግ ባለሥልጣን ስታገኝ አባርረው:: በጥሩ ቀርቶ በመጥፎ ካስተባበረ ጠላ-ትህ ነው:: የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ምእመኑን በአንድ የተቃውሞ አጀንዳ ሲያሰልፍ ነው የቆየው:: ምሳሌ:- ታርጋ ሁሉንም ሾፌር ይመለከታል:: ስለዚህ የማይተባበር የለም:: So divide and mis-rule (ቸርችረህ ሽጠው) ነው የሚተገበረው:: ቅድሚያ የቤት መኪና ብቻ ቢል ... ምእመኑ በብሔ^ር ማለቴ በታርጋ ተከፋፍሎ አይተባበርም ነበር:: ከዚያ ዓመት ጠብቆ ታክሲ ብቻ ይቀይር ይላል:: ጫጫታ ሲነሳ ነዳጅ ተደጎመ ብሎ 80 ሳንቲም ይቀንሳል:: ወር ጠብቆ 60 ሳንቲም ይቀንስና ከሁለት ወር በሗላ 4 ብር ጨምሮ ያካክሳል:: ሾፌር ሁሉ ይሰልጥን ብሎ ሁሉም ተባብሮ አከሸፈው:: ምእመኑ መተባበርን ተማረ::
❤40
አሚርነት መጣሁልሽ
😁50
ብዙ ቢዝነስማኖች እና ውማኖች የተዝረከረከ ድርጅታቸውን ሲስተም እንዳሲዝላቸው ይጠይቁኛል::

-> መጀመሪያ ረጅምምም የተዝረከረከ ሳቅ እስቃለሁ:: ፖለቲካውና የሕግ ሥርዓቱ ሥርዓት ባልያዘበት ሀገር እንደውም እብ^ድ የዘገነው በሶ ማስመሰል ነው እንጂ የምን ሲስተም መዘርጋት አመጣህ? ጨበጥ አድርገው:: ወንድሜ ከቻልክ አሮጌና አዲስ ሁለት ዓይነት መኪና ግዛ:: ትራፊኮችን ከፈራህ ገመቺሱን ይዘህ ውጣ:: መብራት ብትጥስ እንኳ አያስቆሙህም:: አሮጌ ከያዝክ እኮ ይቀምሉታል አይገልጸውም:: ዝንጀሮ እንኳ ልጇን እንዲህ አትቀምልም:: የሱሪ ቀበቶ አላሰርክም ብለው ሊከሱህ ይችላሉ::

Well, አጋቾችን ከፈራህ ደግሞ አሮጌውን ይዘህ ውጣ:: ኑሮ በዘዴ (ኢኮኖሚክስ) እንዲህ ነው:: ሐቀኛ ግብር ከፋይ ሁን:: ግን የሽልማት ቀን ተወካይ ወይም ጥበቃህን ላክ:: የከፈልከውን ታክስ ለዴሲማል 0.3 ሲያካፍሉት ሽያጭህ ጋር ይደርሳሉ:: ይህ እኮ ደረሰኝ የቆረጠለት ነው:: ያልቆረጠለት አምስት እጥፍ እንቅስቃሴ አለው ብለው አዋክበው በቀጣይ ዓመት አጭ^በርባሪ ተብለህ ልትቆለመም ትችላለህ::

ቢሆንም ቢሆንም ሥርዓት የያዘ ድርጅት ከፈለጋችሁ ሁለት ይኑራችሁ:: አንደኛው ዘመኑን እየዋጀ በመዋቅር ይሂድ:: ነባሩ እንደ ካራቺና ሌጎስ ባለበት ትቶ አቡጃና ኢስላማባድ መመሥረት ነው::
____
እንዲህ እንዲህ ያሉ የኑሮ በዘዴ ትምህርቶችን ከፈለጋችሁ AK ዓርባ ሰባት ላይ የዱዓ ይዛችሁ ብቅ በሉ::
❤53
ሆድህ ሲበዛ ጾታህ ይቀያየራል::
(ዋናው ፖስቱ ግን ይህ አይደለም)::
👍22
የግብርና ባንክ በሦስት ወራት ውስጥ ይጀመራል የሚል ዜና Capital መጽሔት ላይ አነበብኩ:: Congratulations 🎈🎉🍾
=========
የቻይና ግብርና ባንክ ባየሁ እና በተጠቀምሁ ቁጥር ሀገሬ ላይ እንደሚኖረን እመኝ ነበር:: ይልቅስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፔፐሬም በዚሁ ላይ ነው:: ፔፐሩም ከጋዜጠኛ አብርሃም ታደሰ ጋር በተከታታይነት አቅርበነዋል:: የባንኩ ሠራተኞች ዝግጅት በተመለከት ተጨማሪ ባለሙያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋብዤ በETV አቅርበነዋል:: በመጽሓፎቼም ርዕስ ሰጥቼ የዕድገታችን የመፍትኄ አካል አድርጌ ሠርቼዋለሁ:: ልዩ ትኩረት ከሰጠሗቸው ጉዳዮች ግብርና ባንክ ከበፊተኞቹ ነው:: መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ለመጀመር መድረሱ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም::

ፎቶ:- ቻይና ከ Agricultural Bank of China (ABC) ፊትለፊት
❤51
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ CBDC እጀምራለሁ ብሏል:: CBDC ምንድነው? ከንግድ ባንክ ዲጂታል መገበያያ በምን ይለያል? ይህንን ነጥብ ለታዳጊዎች በሚገባ ቋንቋ ሳይቀር ጽፌዋለሁ:: ለልጆች በሚገባ መልኩ መጻፍ ይከብድ ነበር:: ያው ግን ተወጥቼዋለሁ:: በአዋቂዎችም በታዳጊዎችም መጽሓፍ ውስጥ አለላችሁ:: የገዛችሁ ሰዎች መልሳችሁ ገርቡት:: BRICS ደግሞ እንደ መገበያያ ያስቀመጠው ወርቅ የደገፈው CBDC ነው:: ብሪክስ ግብይቱ ከንግድ ባንክ ይልቅ ብሔራዊ ባንክ ጋር ይሆናል:: ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ጋር ትስስር አለ:: ብሪክስም ከእኛ ጋር የምትዋዋሉት በባዶ ፊያት ሳይሆን ወርቅ ጋር የተደገፈ ሲቢዲሲ ይሁን ብለዋል:: እኛም ወርቅን ማንጠር ጀምረናል:: ብቻ ደስ የሚል ነገር ይታየኛል:: ያድርገው:: ስለግብርና ባንክ ስሰማ ደግሞ በደስታ እንባዬ ነው የመጣው:: በትክክል የሚተገበር ያድርገው::
❤55
የግብርና ባንክ በቅርቡ እንደሚቋቋም ሰምተናል:: በጣኣኣኣኣም ደስ ይላል:: እኔ ላቋቁመው ሳይሆን ላስቋቁመው ብዙ ወትውቻለሁ:: ምክንያቱም በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋም ተራ ባንክ አይደለም:: እጅግ በጣም ግዙፍ እና ሀብታም ባንክ ስለሆነ ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነው:: መንግሥት ቀድሞም አስቦበት ይሆናል አላውቅም:: እንደዚያ ነው ብለን እናስብ:: የእኔ አካሄድ የሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮዎች በአንክሮ እንዲመለከቱት ማድረግ በመሆኑ ቀዳማይ ታርጌቴ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የመንግሥት ሚዲያ አደረግሁ:: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስፈለገው ካሪኩለም እንዲያሻሽል ሲሆን የመንግሥት ሚዲያ ደግሞ ስለባንኩ ምንነት እንዲያስረዳ ነበር:: ለዚህም ETVን በተለይ ጋዜጠኛ አብርሃምና የዝግጅት ክፍሎችን አመሰግናለሁ:: ቀጣይ የነበረው የግብርና ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ባንክ ነበሩ:: ለዚህም Concept note አዘጋጅቼ ሞቅ ያለ ፕሮግራም ልናዘጋጅ ሰነዶቹን ልኬ ነበር:: ችግሩ ስሜን አልጽፍበትም:: ማንም ይጀምረው ማን ዋናው መጀመሩ ነው::

እኔ በሠራሁት ጥናት ግብርና ባንክ በጣም ሀብታም ባንክ ነው:: ምክንያቱም የሀብቱ ምንጭ ፊያት ሳይሆን ምርት ነው:: ማእድናትም ጭምር ስከሚያካልል ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚለምኑት ከግብርና ባንክ ነው:: ፔፐሩን ከፈለጋችሁ በኮሜንት አለላችሁ:: በመ-ገንዘብ መጽሓፍም ተዳሷል::

ሙሉ ፔፐር 👇🏼👇🏼👇🏼
https://etd.aau.edu.et/server/api/core/bitstreams/d2a9e377-3330-48ac-9ea5-b4b0593b8820/content

👇🏼👇🏼👇🏼ከጆርናል
www.ijmdrr.com/admin/downloads/070820234.pdf
❤36
መኖሪያ ቤት ከምትገዛ በብሩ ነግድበትና በትርፉ ቤት ትገዛለህ ይባል ነበር:: በወቅቱ ስህተት ላይሆን ይችላል:: ምክንያቱም ግሽበት ብዙም ስላልተስፋፋ የእቃ ይሁን የቤት ዋጋ ጭማሪ ብዙም አይራመድም ነበር:: አሁን ግን ተቃራኒው ነው ያለው:: ስለዚህ አሁን ደግሞ እጅህ ላይ ባለው ብር ቤት ትገዛና ቤቱን አስይዘህ በሞኝ የቁጠባ ብር ትነግዳለህ:: ይህ ሲባል ከሰው ሰው ይለያያል:: ሥራህ ፈጣን ትርፍ የሚያመጣበት ወቅት ላይ ከሆንክ ንግድህን አጧጡፍ:: ግን ቤት ለመግዛት አትዘግይ:: ምክንያቱም ከባንክ የመጀመሪያውን ብድር ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም:: ከዚያ ግን የሞባይል ካርድ መሙላት በለው:: ቤት ግዛ ስልህ ደግሞ አደራ:: ዲጂታል ካርታ የያዘና የባለቤትነት ችግር የሌለበት ማለትም ባለትዳሮች የተስማሙበት እና የውርስ ችግር የሌለበት ይሁን:: ይሄ ሪል ኢስቴት ላይ ቀብድ ከፍሎ ቁጭ ማለት ክሪፕቶከረንሲ ላይ የሆነ ብር ቀርቅረህ የሚሆነውን እንደመጠባበቅ ነው:: እርሱን ታማኝ ገንቢ ካገኘህ እና እንደ ኢንቨስትመንት ከቆጠርከው ጥሩ ሊሆን ይችላል:: ቀስ እያልክ ቤት ይኖርሃል:: ይህኛው ባንዴ መግዛት ለማይችል እና ባወጣው ያውጣው ለሚል ነው:: እርሱን አላልኩም:: እኔ እያወራሁ ያለሁት ስለፋይናንስ እና ታክስ አድቫንቴጅ ነው:: አስማት የሚመስለውን የእድገት ምሥጢርን ነው:: ጅብ ግልቢያ ሁሁይ የለውም:: Pure ማትስ ነው:: በራስህ ንጹሕ ብር ግንባታውም ሰነዱም የተጠናቀቀ ቤት ትገዛና ብሩን በንግድ ፈቃድህ በኩል ትስበዋለህ:: ይህንን multiply ✖️ ማድረግ ነው::

መኪና አስቀድሞ መሯሯጥ የሚመርጥ ይኖራል:: ይህም ስህተት ላይሆን ይችላል:: የፋይናንስ ሥርዓቱ መቆሚያ ሁለቱ እግሮች ኢንተረስና ታክስ ናቸው:: እነርሱን ነው የምታጫውተው::
❤62
መ-ገንዘብ መጽሓፍ ከፍሎ በወቅቱ አድራሻ በትክክል ጽፎ ያልተላከለት ያለ አይመስለኝም:: አንድም ሰው ከፍሎ ሳይደርሰው አይቀርም:: ለምን 100 ዓመት አይሆንም:: እስካሁን ያልደረሰው ምእመን

- ወይ ፖስታ ቤቶች ሲደውሉ ስልኩ ዝግ የሆነ
- ወይ ወትሮም አድራሻ ያልሞላና ዘግይቶ ሰጥቶን ፕሮሰስ ላይ ያለ
- ወይ ከነጥራሹኑ ያልሰጠን
- ወይ Bot ላይ ሲሞላ የሆነ ለተወሰነ ሰዓታት ክራሽ ያደረገ ወቅት ነበር:: ያኔ ሞልቶ ሳይደርሰን የቀረ::

ቢሆንም ቢሆንም 99% ፐርሰንት በላይ ለከፈለ አድርሻለሁ:: የቀረ ምእመን በክብር የማድረስ ውዴታ አለብኝ:: መጨረሻ ላይ አድራሻ ሰጥታችሁኝ ያልተላከ እጅግ few የሚባል ሰው አለ:: አጣራና በቅርቡ እልካለሁ:: ማጣሪያው ነው የሚያደክመው:: እንዳያመናጭቁዋችሁ እኔው እራሴው ነኝ የማስተናግደው::

ያልገዛ ግን ጃእፈር ጋር
👍8
ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ ቤተሰብ አለን:: ደስ ይላል:: ይህኛው ፎቶ ከትናንትና ወዲያ ሐሙስ የተጠናቀቀው የኢምፖርት ስልጠና ነው:: የኢምፖርት ይቀጥላል:: የትራንዚቱን በትራንዚተር ብቻ ሳይሆን ጉምሩክ በሠሩና በቂ ስልጠና ባላቸው አሰልጣኞች ... የውጭ ምንዛሪ ላይ ምርጥ በሚባሉ ባንኮች የ International Banking Divisions ባለሙያዎችን ... የ Single windowsም እንደዚያው በባለሙያ ... የቻይናውም ከቻይና Live እንገባለን:: ሌላውም በሚመለከተው ክፍል ነው የሚሰጠው:: ዳሸን ባንኮች ገራሚ ስልጠና ነው የሰጡልን:: አንድ እርምጃ የቀደመ ስልጠና::
_
Finance for non-financial managers የሚል ስልጠና የፊታችን
ማክሰኞ, ረቡዕና ሐሙስ
የሦስት ግማሽ ግማሽ ቀናት ስልጠና አለ::
ምዝገባ መጨረሻው ቀን ላይ ነን::
ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ
በአካል ብቻ
❤7