Hasen Injamo
ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ ቤተሰብ አለን:: ደስ ይላል:: ይህኛው ፎቶ ከትናንትና ወዲያ ሐሙስ የተጠናቀቀው የኢምፖርት ስልጠና ነው:: የኢምፖርት ይቀጥላል:: የትራንዚቱን በትራንዚተር ብቻ ሳይሆን ጉምሩክ በሠሩና በቂ ስልጠና ባላቸው…
''Finance for Non-Finance Managers''
ለ 3 ቀናት
ጥቅምት 10, 11 እና 12
ጠዋት
ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ
www.hab.et/register
ወይም
2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
3. 🤳 +251990555599
ለ 3 ቀናት
ጥቅምት 10, 11 እና 12
ጠዋት
ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ
www.hab.et/register
ወይም
2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
3. 🤳 +251990555599
www.hab.et
Register – HAB Management and Technologies
❤3
coffe_order_en_new.jpg
48 KB
📢 Advertising in this channel
You can place an ad via Telega․io. It takes just a few minutes.
Formats and current rates: View details

❤5
ለፋይናንስ ሲስተሙ ግማሽ መንገድ (50%) ለመጓዝ ቤት መግዛት ነው ተባብለናል:: ታዲያ ቤት ስትገዙ ሁለት ነገሮች መሟላታቸውን ከግምት አስገቡ:: አንደኛው ዲጂታል ካርታ መያዙን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካርታው የያዘው ማነው? የሚለው ነው:: ባለይዞታው አሁናዊ የትዳር ሁኔታው ወሳኝ ነው:: ተፋተው ወዲያው ያላገባ ሊያወጡ ይችላሉ:: የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከነአፈጻጸሙ ካልያዙ ዱዲ መክፈል አያስፈልግም:: እዚሁ ጋር የእዳ, ዋስትናና እግድ ጉዳዮች ይታያሉ:: ከእነዚህ ሁሉ ጽድት ያለ ካላገኘህ መክፈልህ ቤት አለኝ አያስብልህም:: ለሪል ኢስቴት ቀብድ ከከፈልክ ቤት ሳይሆን ኢንቨስትመንት ነው:: በአንዴ ከምከፍል እየሠራሁ ቤት ይኑረኝ ዐይነት ነገር ነው:: ታማኝ አልሚ ካገኘህ እድለኛ ነህ:: በሒደት ቤት ይኖርሃል:: ካላገኘህ ግን በርቶብሃል:: ሿሿ ላይ ነህ:: ውሱን ጥሩ አልሚዎች አሉ:: እነርሱም በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች ሊወላከፉ ይችላሉ:: ገንብተው ካርታ ለመበተን ቢያንስ የውስጥ ፓርቲሽን መጨረስ አለባቸው:: ለየቤቱ ስም ለማዞር በርና መስኮት ገጥመው የመጠቀሚያ ፈቃድ አውጥተው ከገቢዎች ክሊራንስ መጨረስ አለባቸው:: ምሳሌ:- አንድ ሕንጻ 60 ቤቶች ቢኖሩት 60 ሽንሽን ካርታ እና 60 የገቢዎች ክሊራንስ ይኖሩታል:: ክሊራንሱ የሚያገለግለው ለሦስት ወራት ብቻ ነው:: ባንኮች የሚሰሙህ ዲጂታል ካርታ ስትይዝ ብቻ ነው:: ቤቱ የሌላ ሰው ከሆነ የብድር ዋስ ሊሆንህ ይችላል:: እናልህ ካርታ የሌለው ስቴዲዮም አለኝ ከምትል ሰነዱ ጽድት ያለ ስቱዲዮ ይሻልሃል:: የሀብታምነት ጉዞ ላይ 50% ደርሰሃል:: ቀሪው ንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቢዝነስ መሥራት ነው:: (መ-ገንዘብ 2 እና 3 ይህንን ያስረዳሉ)::
👏32
በመደበኛ ባንክ እና በወለድ በነጻው ባንክ መሃል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ስጋትን (Risk)ን መጋራት ነው::
መደበኛውና ለዘመናት የምናውቀው ባንክ በተወሰነ መልኩ ስጋት (risk) ይጋራል:: ለቆጣቢ መጠነኛ የግሽበት ማካካሻ ይሰጣል:: ከተበዳሪም በኩል ያልሠሩበትን ዘመን ትርፍ አያስከፍልም:: ውሉም ግልጽ ነው::
ወለድ በነጻው ግን በፍጹም ስጋት (Risk) አይጋራም:: ቆጣቢ ብር በነጻ ያመጣል:: ተበዳሪም "የተሸጠ ዕቃ አይመለስም" በሚል አሠራር ያልሠራበትን ዘመን ትርፍ ይከፍላል:: ባንኩ ብር ማከራየቱን ባላየ ለማለፍ ሲሚንቶ ወይም ብረት ልግዛልህ ይላል:: ከደሃ ቆጣቢ ደግሞ ሲሚንቶ ቆጥቡ ... ብረት ቆጥቡ አይልም:: አታሎ በነጻ ይቀበልና በትርፍ ያበድራል:: ውሉ እጅግ የተቀሸበና ግልጽነት የጎደላቸው አናቅጽ አሉበት:: ብዙ ውሎች እጄ ላይ ስላሉ ነው:: የኢስላም ሕግጋትን በጽኑ ይጻረራሉ:: ባንኩ በመደበኛው አሠራር ሲጋራቸው የነበሩ ስጋቶችን (Risks) ከራሱ ላይ ሲያሸሽ ወለድ በነጻ ይሆናል:: በነገራችን ላይ ከቲዎሪው በተቃራኒው ነው:: ሙዷረባን እንዴት 180 ዲግሪ እንደገለበጡት ፊያት መገበያያና ወለድ መጽሓፍ ላይ በዝርዝር አለላችሁ::

👍19
<<በቤት ኪራይ ተሰቃየን:: መሄጃ አጣን:: እሺ መሬት ስጡን:: አዲሱ ትውልድ የት እንግባ>> እያለች ታለቅሳለች:: ይህ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው:: 1968 ላይ መሬት ላራሹ ተብሎ አዋጅ ታውጆ ትውልዱ መሬት አገኘ:: ከዚያ ወዲህ መሬት የሚባል ነገር አልተሰጠም:: መንግሥት መሬትን የሚያህል ሀብት አንቆ ይዞ ሊደባ^ደብ የሚሄደው የግለሰብ አከራዮች ጋር ነው:: መንግሥት ብር, መሬት, ቀረጥ, ሕግ ሁላ ይዞ ያልቻለውን መንግሥታዊ ሪል ኢስቴት ማለትም ኮንዶሚኒየም ሳይሰጥ... የግል አልሚዎች ካላሟላችሁ ይላል:: መንግሥት መሬትን በአግባቡ ማደል ሲገባው በሊዝ ያከራያል:: ትውልዱ ይሰቃያል:: ቢቸግራቸው ተሰደው ለፍተው መጥተው የወጠሩትንም ላስቲክ ያፈርሱባቸዋል:: መንግሥት መሬት ይስጥ, ኮንዶሚኒየም ይገንባ, የግሎችም የተረፈውን ይሸፍኑ:: በዋለ ባደረ ቁጥር ትውልዱ እየጨመረ የቤት ግንባታ ባለበት ቆሞ ወይም ቀንሶ እንዴት ሊጣጣም ይችላል? መጠለያ መሠረታዊ ፍላጎት ስለሆነ ወደድንም ጠላንም አብዮት ያስነሳል:: ምግብ መሠረታዊ ስለሆነ አብዮት ያስነሳል::
❤89
ሁሉንም ፈትኑ::
የተመቻችሁን ያዙ::
=====
1. ኤቲስት (Atheist - ኢ-አማኝ)
አመለካከት: "አምላክ ወይም ፈጣሪ የለም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ማንኛውንም የተፈጥሮ በላይ ኃይል ወይም አምላክ አይቀበልም። የዓለምን መፈጠር እና መንቀሳቀስ በተፈጥሮ ሕጎች እና በሳይንሳዊ መረጃዎች ብቻ ይረዳል::
2. ቴይስት (Theist - አምላክ አምላኪ / አማኝ)
አመለካከት: "ዓለምን የፈጠረ እና አሁንም የሚመራ አምላክ አለ" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ከፍጥረቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው (ጸሎት ይሰማል፣ ተአምራትን ያደርጋል፣ ነቢያትን ይልካል) ብሎ ያምናል።
3. አግኖስቲክ (Agnostic - ተጠራጣሪ / ያልወሰነ)
አመለካከት: "የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ አእምሮ ሊታወቅ አይችልም" ይላል።
መግለጫ: አምላክ ለመኖሩም ሆነ ላለመኖሩ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ የለም ብሎ ስለሚያስብ "አምላክ አለ" ወይም "የለም" ብሎ እርግጠኛ ከመሆን ይቆጠባል።
4. ዲይስት (Deist - የተፈጥሮ አምላክ አማኝ)
አመለካከት: "አምላክ ዓለምን ፈጥሯል፤ ነገር ግን አሁን ጣልቃ አይገባም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ፈጣሪ ዓለምን እና የተፈጥሮ ሕጎችን ፈጥሮ እንደ ሰዓት ካስኬደ በኋላ ትቷታል። ጸሎት፣ ተአምራት ወይም ሃይማኖታዊ መጻሕፍት አያስፈልጉም ብሎ ያምናል።
5. ፓንቴይስት (Pantheist - ተፈጥሮ-አምላኪ)
አመለካከት: "ዓለም/ተፈጥሮ እና አምላክ አንድ ናቸው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ከዓለም ተለይቶ የሚኖር አካል ሳይሆን፣ አጽናፈ ዓለም (Universe) እና ተፈጥሮ በሙሉ እራሱ አምላክ ነው ብሎ ያምናል።
6. ሚሶቴይስት (Misotheist - አምላክ ጠሊ)
አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ክፉ/ጨካኝ ስለሆነ እጠላዋለሁ" ይላል።
መግለጫ: በአለም ላይ ያለውን መከራ እና ስቃይ በማየት አምላክ እንዳለ ቢያምንም፣ አምላክን እንደ አፍቃሪ ሳይሆን እንደ ጨካኝ ወይም ኢ-ፍትሐዊ አካል አድርጎ ይመለከተዋል፤ ስለዚህም ይጠላዋል።
7. ሄኖቴይስት (Henotheist - ከአንድ በላይ አማልክት ባሉበት አንዱን አብልጦ አምላኪ)
አመለካከት: "ብዙ አማልክት እንዳሉ ይቀበላል፤ ነገር ግን አንዱን ዋና አምላክ አድርጎ ያመልካል"።
መግለጫ: የሌሎችን አማልክት ህልውና ሳይክድ፣ ለእሱ ወይም ለወገኑ ግን አንዱን የተወሰነ አምላክ ብቻ የላቀ አድርጎ ያመልካል።
8. ፖሊቴይስት (Polytheist - ብዙ-አማልክት አምላኪ)
አመለካከት: "ከአንድ በላይ የሆኑ ብዙ አማልክት አሉ" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: እያንዳንዱ አምላክ የየራሱ የኃይል ወይም የተፈጥሮ ክፍል (የዝናብ፣ የፀሐይ፣ የጦርነት አምላክ...) አለው ብሎ ያምናል። (ለምሳሌ፦ የጥንታዊ ግሪክ እና ሮማውያን እምነት)።
9. ሞኖቴይስት (Monotheist - አንድ-አምላክ አምላኪ)
አመለካከት: "በእውነት ያለ እና የሚመለክ አምላክ አንድ ብቻ ነው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ከእሱ ውጭ ያሉ አማልክትን በሙሉ የሉም ወይም ሀሰተኛ ናቸው ብሎ ይኖራል።
10. ፓነንቴይስት (Panentheist - አምላክ በተፈጥሮ ውስጥ እና ከዚያም በላይ)
አመለካከት: "ዓለም በአምላክ ተከቦ ይኖራል፤ ነገር ግን አምላክ ከዓለም ይበልጣል" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ተፈጥሮ የአምላክ አካል ቢሆንም፤ ግን አምላክ ከፍጡራኑ እና ከአጽናፈ ዓለም ወሰን በላይ የሆነ የራሱ ህልውና አለው ብሎ ያምናል። (ወሃb እዚህ ግድም ይመደባል)
11. ኦቶቴይስት (Autotheist - እራስ-አምላኪ)
አመለካከት: "እራሴ ወይም የሰው ልጅ እራሱ አምላክ ነው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ከውጭ የሚጠበቅ መንፈሳዊ ኃይል የለም፤ የሰው ልጅ የራሱ ህይወት፣ እጣ ፈንታ እና መንፈሳዊነት የበላይ ገዢ እራሱ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው።
12. ዲስቴይስት (Dystheist - አምላክ ሙሉ በሙሉ መልካም አይደለም)
አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ቸር/መልካም አይደለም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ፍጹም መልካም እንዳልሆነ እና አንዳንዴም ክፉ ወይም ግራ የሚያጋባ ባህሪ ሊኖረው እንደሚችል እንደ ፍልስፍናዊ እውነታ ይቀበላል።
13. ኢግኖስቲክ (Ignostic - የትርጉም ጥያቄ አቅራቢ)
አመለካከት: "'አምላክ' የሚለው ቃል ግልጽ የሆነ ትርጉም ስለሌለው ስለ እሱ መከራከር ትርጉም የለውም" ይላል።
መግለጫ: አምላክ አለ ወይም የለም ብሎ ከመከራከር በፊት "ለመሆኑ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው?" የሚለው ትርጉም በግልጽ ካልተበየነ በቀር ውይይቱ ፍሬ አልባ ነው ብሎ ያምናል።
14. አፓቴይስት (Apatheist - ደንታ-ቢስ)
አመለካከት: "አምላክ ቢኖርም ባይኖርም ለእኔ ምንም አያግደኝም/አያስጨንቀኝም" ይላል።
መግለጫ: የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ እለታዊ ህይወት ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎ ስለሚያስብ ስለ ጉዳዩ ማሰብም ሆነ መከራከር አይፈልግም።

😱10
ይልቃል ጌትነት በሰማያዊ ፓርቲ ይሁን በግራጫ ፓርቲ ምክንያት ታስሮ የረሃብ አድማ መታ:: ከዚያ ሊሞት ሲል ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በነፍሱ ደረሱና:-
ይልቅስ ይልቃል አሉት ... ድፍን ሀገሩ ረሃብተኛ በሆነበት ሀገር የረሃብ አድማ ብትመታ መሳቂያ ነው የምትሆነው:: ዜና እንድትሆን ከፈለግህ የጥጋብ አድማ መተህ ሰውነትህ መለስ ብሎልህ ስትወዛ እነተፈራ ዋልዋ እነደብረ ጽዮን እርሱ ይፈታና እኛን እሰሩን ብለው እጣ ይጣጣሉብሃል ብለውት መብላት ጀመረ ይባላል::
ብቻ ስጋ ያለመብላት አድማ የጠሩት የኤአይ በሬዎችና ጅቦች ይሆኑ እንዴ? ዛሬ በሄድኩበት ሁሉ ኤስ ኤች ዩ RO ሆነብኝ::

😁41
አንዳንድ ሕግ አስከባሪ ለ50 ሰከንድ እንኳ አደብ የለውም:: በአደባባይ, ትራፊክ ፖሊስ ባለበት, በርካታ መኪናዎች ተደርድረው ለሕግ ተገዢ ሆነው በሚጠባበቁበት ወለል ባለ ሜዳ V8 የያዙ most likely ባለሥልጣናት ወይም ልጆቻቸው በጥቁር ስቲከር ተነቅበው በ2 ቁጥር ታርጋ .. መብራት ይጥሳሉ:: ዝም ብለን ስናሰላው ቢሮኣቸው ውስጥ ምን ጉድ እየሠሩ ይሆን? ትራፊክ ፖሊሱን እንኳ አያስፈቅዱም:: ትራፊክ ፖሊሶችም ይፈራሉ:: ዘወር ብለው አሮጌ መኪና, የራይድና የጭነት መኪኖችን ያሳድዳሉ:: ያመናጭቃሉ:: የበላይ ሕግ አስከባሪ የሚባሉት ለሰከንዶች መታገስ እያቃታቸው ሀያና ሠላሳ ዓመታት በችግር የታገሱ ሰዎች ግን መመሪያና ዱ^ላ ይበዛባቸዋል:: ምእመኑ ከማን ምን ይማር? በለውጡ ሰሞን ባለሥልጣናት ከእንግዲህ ላንድ ክሩዘር አይዙም ተብሎ አሁን ግን ጭራሽ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ መብራቱን እንዳሻቸው እየጣሱ ይረግጡታል:: ይህ ጥ^ጋብ መቸም ከላይ የወረደ እንዳልሆነ እንገምታለን:: ታዲያ የታችኞቹን ማስታገስ እንዴት ተሳነ? ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ቸኩለው ነው ካልክ ይብሳል:: ምክንያቱም ያለእቅድ ነው የሚጠዳደፉት ማለት ነው::
👌31
Ai ከመጠቀምህ በፊት ደ^ደደብ ከነበርክ Ai ድ^ድብናህን ያፈጥነዋል እንጂ ጎበዝ አትሆንም:: በ በኮምፒውተር ዘመን ሀብታም የነበሩት መሴጅ እንኳ መጻፍ የማይችሉት እንደነበሩ አትዘንጋ:: ስለዚህ Ai ፈጣን ደደ^ብ ቢያደርግህ ነው:: ስለዚህ እጅህ ላይ ያለውን መሳሪያ አፍጥነህ ተለወጥበት::
🙏28
መንግሥት መሬት ይስጠን ማለት ጀግንነት ነው:: መፍትሔው እዚያ ጋር ነው:: ቤት በርካሽ እና በተመጣጣኝ ኪራይ መከራየት አለበት ብሎ የሚያምን ሰው ... ቤት ሠርቶ በርካሽ እና በተመጣጣኝ የማከራየት መብት አለው:: ይህንን የምለው ችግሩ የግለሰብ ንብረት ላይ መጮኽ መፍትሔ ስለማያመጣ ነው:: ሀብታሞች ግቢያቸው ውስጥ ብዙ ባዶ ክፍሎች አሉዋቸው:: እነርሱን ማን ደፍሮ አከራዩ ብሎ ይጠይቃል? የፈረደበት ደሃውን ነው::
ማንም ቢመቸው ቤቱን ማከራየት አይፈልግም:: በዚያች በኪራይ ነው ልጆቹን የሚያስተዳድረው:: ማከራየትን እንደ ቢዝነስ የያዙን ትቼ ነው:: በግሌ ወላጆቼ በጊዜያቸው ያልያዙትን እና የሌላው አባት ለልጆቹ በያዘላቸው ሀብት ላይ መጮኽ አግባብ አይደለም:: ልጆቼም እኔ ባልያዝኩላቸው ንብረት ላይ መጮኽ የለባቸውም:: ለረጅም ዓመታት በኪራይ ኖሬያለሁ:: ጥሩም መጥፎም አከራይ ገጥሞኛል:: ተከራይነቴ የመጣው በአባትና በአያት ስህተት እንጂ በአከራዮቼ መጥፎነት አይደለም:: በገቢዬ አቅም ነው የምከራየው:: ምሳም የምበላው በኪሴ ልክ ነው:: የሸራተን አቅም ከሌለኝ ሸራ ተራ ሄጄ ጮርናቄ በሻይ ተፈውሼ ተፍ ተፍ ማለት እንጂ ሸራተን የምሳ ሒሳብ ይቀንስ ብሎ መጮኽ አግባብ አይደለም:: ተከራይ ሆኖ ኮተታ ኮተት የሚሰበስብ ሞልቷል:: አባቱ ቤት ሳይዙለት ያንኑ ስህተት በኪራይ ቤት የሚደግም ብዙ ሰው አለ:: በኪራይ ቤት ስምንት ልጅ ይደረድራል:: ግሽበት በሌለ ዘመን አስኪዷል:: አሁን እኮ ኑሮ ጦዟል:: በዚህ ዘመን ኑሮ ያላስታረቃቸው ባለትዳሮች ሽማግሌም ፍርድ ቤትም አያስታርቃቸውም::
ሲጠቃለል:- የቤት ልማት ፕሮግራም እና የመሬት ጉዳይ ትልቅ ለውጥ ይፈልጋል:: የትውልድ ቁጥር እየጨመረ, ምእመኑ መንታ መንታ እየወለደ ውሱን የግለሰብ ቤቶች ላይ ኪራይ ተመን ከተገባ ጭራሽ እጥረት ተፈጥሮ ... የሚከራይ ቤት ማግኘት ሎተሪ እንደመጠባበቅ ይሆናል::

👏42
ሀቻምና 57 ብር የነበረ ዶላር ዘንድሮ 163 ብር ገብቷል:: የጤፍ ወይም የስጋ ነጋዴ በሀቻምናው ዋጋ ይሽጥ እንዴ?
ጤፍ ሲወደድ ገበሬው ወደ እርሻ ይገባል:: ክብሪት ሲወደድ ነጋዴው ወደ ማምረት ይገባል:: አቅርቦትና ፍላጎት ብዙ ጊዜ በራሳቸው እየተናበቡ ይሄዳሉ:: ለምርት እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች እንዲቀረፉ መሥራት ነው::

🤝31
የባንክ ወለድን ሀላል ለማድረግ ከተኬደባቸው መንገዶች አንዱ ስያሜን መቀየር ነው:: ኢንተረስት የሚባለውን ማርክአፕ ማለት, ብድር የሚባለውን ፋይናንሲንግ በማለት መቀየር ይቻላል የሚል አስቂኝ መከራከሪያ ይቀርባል:: ለዚህም በሬን በስመኣብ ብለህ ብታር^ደው ስጋው የክርስቲያን ሲሆን ቢስሚላህ ብለህ ብታር^ደው የሙስሊም ይሆናል የሚለውን ሎጂክ በማቅረብ::
ወለድ እንደ በሬ ሳይሆን እንደ አሳማ ነው:: አሳማን ቢስሚላሂ ብታርደ^ው ሀላል አይሆንም:: ቢራን ራህማ ወይም ዘምዘም ወይም መካ ብትለው ማስከሩን አይተውም::
ባንክ ብር ከማከራየት ውጭ በፍጹም እቃ ገዝቶ ሊሸጥ አይችልም:: ምክንያቱም የሕዝቡ ሁሉ ብር ባንክ ስለሚቀመጥ ባንክ እቃ ገዝቶ መሸጥ ውስጥ ከገባ ያልተገባ ውድድር ይፈጠራል:: ንግድ ይበጠበጣል:: መሸፋፈን አያስፈልግም:: ብድርን ንግድ ለማስመሰል መሄድ ፈጣሪን ልሸውድህ እንደማለት ነው:: መደበኛው የባንክ አሠራር ከወለድ በነጻው እጅግ በጣም የተሻለ ነው::

🤔42
የወረቀት መገበያያ በዓይን ይታይ ስለነበረ እንደውም ብልጭልጭ ቀለም ስለነበረው ... የድሮ ወርቅና ብርን ተክቷል የሚል አመለካከት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ:: አሁን ላይ በዓይን የማይታይ, በእጅ የማይዳሰስ, በምላስ የማይቀመስ, በሚዛን የማይመዘን, በኩባያ የማይሰፈር, በሬዲዮ ሞገድ እንኳ የማይለካ ቁጥር ሲሆን ምን ብለው ይሆን?
የሌለን ገንዘብ አትፈልጉ:: ሲስተሙ ሌላ ነው:: ንብረት ላይ አተኩሩ:: በተለይ የ Ai ዘመን ሀብት የ K ቅርጽ አስይዞታል:: ንብረት የያዘ ሲመነደግ ገንዘብ ያለ መስሎት የሚቆጥብ እንጦሮ-ጦስ ይሰምጣል::

🤔18
ሀብታም ስኬታማ መሆን ከፈለጋችሁ አይደለም ለሌላ ሰው ለራሳችሁም አትንገሩት:: ልክ ስታወሩት አዕምሮኣችሁ ይሸናዋል:: Done ይለውና ሌላ አዲስ ይፈልጋል:: ሰውም በፍጹም እንድትበልጡት አይፈልግም:: መንግሥት አይፈልግም:: ምክንያቱም ለሥልጣኑ ስጋት ትሆናላችሁ:: ምላሳችሁ በነጻ አውርቶ አውሬ ከምትሰበስቡ በጸጥታ ስሩና ስኬታችሁ ተከፍሎት ያውራ::
🔥71
ለመ-ገንዘብ ከፍላቺሁ ያልደረሳቺሁ የፖስታ ቤት መሴጅ አላነበባቺሁ ይሆናል:: እኔ ያላደረስኩ መስሏቺሁ ቅር እንዳይላቺሁ:: እኔም ልኬያለሁ ብዬ .. እናንተም ከዛሬ ነገ ይልክ ይሆናል ብላቺሁ በመሃል እንዳንተማማ ስልካቺሁን ቼክ አድርጉ:: መሴጁ RD ብሎ ዠምሮ ET ብሎ ያበቃል:: ከዚያ Ethio Post tracking የሚል ሳይት ትገቡና ስትሰርቹት የት እንዳለ ያሳያቺሗል:: ✔️ እንዳታደርጉት:: በተለያዩና ባልተለያዩ ምክኛቶች መሴጁ ካልገባላቺሁ ቁጥሩን ትወስዱ ዘንዳ በተለመደው ቴሌግራም አልደረሰኝም በሉኝ:: ሀጂ ደርሶኛል የሚለው መሴጅ በጣም ነው የምወደው:: መሴጁ ደርሷቺሁ ካልወሰዳቺሁ ወደ ዋናው ፖስታ ቤት ሊመልሱት ይችላሉ::
እዚህ መኮመት ስለማይጠቅም እዚያው ቴሌግራም ላይ ብቻ::
እዚህ መኮመት ስለማይጠቅም እዚያው ቴሌግራም ላይ ብቻ::
👍8