ፍቅር ! ሰላም ! ለሀገረ ኢትዮጵያ!!! ሀገርን መውደድ አንድ ነገር ባላገር መሆን ግን አንድም ሁለትም ሶስትም ከዝያም በላይ ....የራስን መውደድ መልካም, ነገር ግን የሌላን ማክበር ለማወቅ መማር እና ማወቅ ደግሞ ባላገርነት ነው!!
#አቤል_ባለሀገር_ነኝ
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia

❤6
#ቦንቡን_ማን_ሰራላቸው ???
ይህ ጒፈሬያም አርበኛ ልጅ መክብብ ወልቀባ የፊትአውራሪ ወልቀባ
ረጋሳ ልጅ ነው::
...በየካቲት 12 1929 አብረሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስግዶም ግራዚያኒ ላይ
የወረወሩትን ፈንጂ (Home Made) ባሩድ ፈጭቶ ቀላጭ ቀጥቅጦ
ከወዳደቁ ቁሳቁሶች ሰርቶ የሰጣቸው ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው በዛን
ዘመን የገዳም ሰፈር ልጅ (የሸገሩ)'ና የ20 ዓመቱ ጥበበኛ ልጅ መክብብ
ወልቀባ ነው::
... (ኢራቆች) "አሊ-ኬሚካል" (በኩርድ የዘር ማጥፋት ቢወቀሱም)
የሚሏቸውና የሚኮሩባቸው የፈንጅ ጠበብት ነበሯቸው::
እኛም ልጅ መክብብ ወልቀባ'ን የመሰሉ ለጭቆና እምቢ ያሉ "ኬሚስቶች"
አሉን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

❤10👍4
◎ጳጉሜ ማለት ምን ማለት ነው?◎
◈◉◈◉◈◉◈◉◈◉◈◉◈◈◉◈◉◈◉◈
በኢትዬጵያ አቆጣጠር ከነሀሴ በኃላ ጳጉሜ አምስት /ስድስት ቀን አለች ።ወር እንዳትባል አቅም ያንሳታል ሳምንት እንዳትበል አምስት ቀን ብቻ ሆናለች ።
ጳጉሜን የሚለው ስያሜ ግን "ኤጳጉሜን" ከሚለው የግረክ ቃል የወጣ መሆኑን በአበው ቃል ተነግሯል "ኤጳጉሜን " ማለት ጭማሪ ማለት ነው ። በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው ። ተውሳክ ማለት ጨመረ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው።
በሌላ አገላለጽ የጳጉሜን፦ ዓመቱ በዕለት ሲለካ የተረሳ የተረፈ ማለት ነው፣
ጳጉሜን ለምን እንፆማለን??
በቅድስት ቤተ ክርስትያን ካሉ ሁለት ፈቃደ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃደ ፆም ነው። ይህም ፆመ ዮዲት በመባል ይታወቃል ይህ ግን እንደ አንደኛው የፍቃድ ፆም (ጽጌ ፆም) በብዙሀኑ ዘንድ የታወቀ አደለም የዮዲት ፆም የሚባለውም እርስዋ ስለፆመችው ነው ። እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስትያን ትምህርት ላይ በጥፋት ስራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን ።
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከፈጣሪዋ ኃይል በማግኘቷ ነው፡፡እኛም ጠላታችን ሰይጣንንና ፈቃደ ሥጋን ድል ለማድረግ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መታጠቅ አለብን ሲሉ ምእመናን ይጾማሉ፡፡
ጳጉሜን ለምን እንጠመቃለን?
ጳጉሜን የምንጠመቅበት ዋናው ምክንያት ከሊቀ መላአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ገር የተያያዘ ነው ።
በዚህ በጳጉሜ ወር በዓለም ላይ ውቂያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች ፣ኩሬዎች ጸበሎች በአጠቃላይ ውሃዎች ሰማይ ተከፍቶ ፣በመላእክት የሚባረኩበት ሰለሆነ፣
ጳጉሜን የቻልን ፀበል ቦታ ሄደን ወይም በአካባቢያች ጸበል ካለ ሄደን እዛም መሄድ ካልቻልነን ቤታችን ውስጥ ባለው ውሃ ብንጠመቅ እንባረክበታለን
በጳጉሜ ፀበል እንኳን የሰው በሽታ፣ በሽታ ያለው እህል በሽታው ይለቃዋል። ገበሬው ከጳጉሜ ወዲያ ነው የሚጠፋውን እና የሚለማውን እህል የሚለየው በተለይ ዛንጋዳ ጳጉሜ ላይ ነው በደንብ የሚለየው/የሚያስታውቅ
በአባባልም ዛንጋዳና ቡዳ ከመስከረም ወዲያ ነው የሚያስታውቀው ይባላል የሚገርመው አባቶቻችን ጳጉሜ ሶስት ሌሊት ስድስት ስአት በተለይ ፏፏቴ ያለው ወንዝ ፤ ውሃው ሲቆምቀድሞ አባቾቻችን ይህንን ተአምር ለማየት ጳጉሜ ሦስት ሌሊት በተለይ ፏፏቴ ያለበት ትልቅ ወንዝ ዳር ሄደው ያድሩ ነበር
በጳጉሜን ተለይም ጳጉሜ ሦስት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዚህ ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልውሆችን የሚባርክበት እና ለሰው ልጅች በፈጣሪው ፀጋ ድህንነት እና ስ የሚያሰጥበት ቀን ሰለሆነ ብንጠመቅ ከበሽታው እንድናለን።
ከዝክረ ቅዱሳን የተወሰደ

❤11
#መልካም_አዲስ_ዓመት
በአዲሱ ዓመት ስለ ሰላም ፣ ስለ ፍቅር ፣ ስለ አንድነት
የምንሰማበት ዘመን እንዲሆን እየተመኘሁ . ኢትዮጵያ ላይ
ያጠላው የጦርነት ፣ የስደት ፣ የበሽታ ጥላ በእግዚአብሔር
ቸርነት ተወግዶልን የሰላም አየር ለመተንፈስ እንዲያበቃን ፣
እንዲሁም መሪዎቻችን ከአስመሳይነት ፣ ከተንኮል ፣ ከእብሪት
እና ከዕልዕ ወጥተው ስለ ሰላም እና ፍቅር ለሚመሯት ኢትዮጵያ
ሀገራችን መልካሙን ሁሉ በቅንነት እንዲያደርጉ ልባዊ
ምኞቴን እገልጻለሁ
ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ !!
"እንቁ" "ጣጣሽ" ሀገሬ ሆይ "እንቁሽን" አብዝቶ; "ጣጣሽን' ያጥፋልሽ::
#አቤል_ባለሀገር

❤10
ክርስቲያን ታደለ እንኳን ለቤተሰብህ አበቃህ። ሌሎች የቀሩ እስረኞችም በዚህ አዲስ አመት ለቤተሰቦቻቸው እንዲበቁ እመኛለሁ። ልዩነቶቻችንን በመነጋገር የምንፈታበት አመት ያድርግልን። በቃችሁ ይበለን 🙏
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
🔥8🤝4❤1🕊1
የዛሬ 52 አመት ደርግ የተባለ የወታደሮች ስብስብ የኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት የዘውድ ስርዓትን በዚህ መንገድ አወረደ። ደርግ ለውጦችን አልሞ ተነሳ። ግን ተሳካ?
@Historical_Ethiopia
@Historical_Ethiopia
❤4😭1
ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ—ቴዲ አፍሮ ዘብሔረ ኢትዮጵያ፦
አባይ ለዘዴው በአፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት እንዴት ያማል?
እያለ ነው።
ወርቅ ያበደረው ደርሶት አለት
እንዴት ይችላል ዝም ማለት...?
ብሎም እየጠየቀ ነው።
እኒህ መራራ ሥንኞች «ዳስስስስስ ጣልልልልል!» በተሰኘው እና «ኢቶሪካ» ውስጥ በሚገኘው ፍጹም አነጋጋሪ ሙዚቃ ውስጥ የተሻጡ ናቸው።
የጥላዬ አራጌ ልጅ ይህን ባለ በደቂቃዎች ልዩነት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የትዝታ ወልዴን ልጅ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድን፦
"የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ በደም መሠረት ላይ የቆመ በመሆኑ፣ ትናንሽ አጀንዳዎችና ጩኸቶች ሊያናውጡት አይችሉም፤"
የሚል ንግግር አቆነጃጅቶ አቅርቧል።
ቴዲሻ በአንፃሩ በዚህ በምሬት በተሞላ ሙዚቃው ውስጥ እንደ ጎንደር እና ጎጃም ገበሬ ያቅራራል።ተቀባዩ እንደ ጮቄ ጀግና ይፎክራል።በአጭሩ የካሣሁን ገርማሞ ልጅ በጥበብ ሰገባ አራት ኪሎ ገብቷል።
በፍቅር ጠርተው
ከዳር እስከ ዳር
መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር
ብሎ ዐቢይ አሕመድ ዐሊን ይተቻል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥምንት ዓመት በፊት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓመተ ምኅረት በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መላ የኢትዮጵያ ልጆች ተሰባስበው አገራቸውን አብረው እንዲገነቡ መጠየቃቸው ይታወሳል።
ያንን ጥሪ ሰምተው ወደ ውዷ አገራቸው የገቡት ጃል መሮ ዲሪባ እና ዘመነ ካሤ ባውቄ ዛሬ በወለጋ እና በጎጃም ጫካ ተበትነዋል።ቴዲ እንዲህ ያለውን ነገር፦
በፍቅር ጠርተው
ከዳር እስከ ዳር
መሀል ገቡና አቆሙን ከዳር
ሲል ይገልጸዋል።በዝነኛው 888 የተለቀቀው ኢቶሪካ በአጠቃላይ እዚህ «ዳስ ጣል» የተባለ ትራክ ውስጥ የታጨቀ ይመሥላል።ምክኒያቱም የጥላዬ አራጌ ልጅ፦
"ዳስ ጣል ልቤ ለውስጤ ሀዘን...ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ፣
አለ—ጊዜ፣
ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልኩት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ
እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት
የት ያለቅሳል ሄዶ...?"
እያለ ይቀጥላል።
ቴዲ እዚህ ሙዚቃ ውስጥ በጣም ሲቆጣ፦
"ወይድ አንተ
አትንገረኝ ማንነቷን፤
ምጥ አታስተምርም
ልጅ እናቷን።
ወይድ አንተ
አታስቆጥረኝ ደም አጥንቴን፣
እኔ አውቀው የለም ወይ
ማንነቴን።
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራዬን፣
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማዬን።
ባንዲራዬን አንሳው
ባንዲራዬን አንሳው
ባንዲራዋን አንሳው
ዓላማዋን አንሳው
በል አንሳው
ወደ ላይ አንሳው!"
እያለ ሥሜታችንን ይሰቅለዋል።
ቴዲ ይቀጥላል እንደገና በቁጭት፦
ምሶሶው ዘመመ፣ ጣራውም ያፈሳል
አገር የሞተበት፣ የት ሄዶ ያለቅሳል?
ባሳደገኝ ቀዬ፣ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሆኛለሁ፣ እንደሌለው አገር።
ያቆምኳትን ሰንደቅ፣ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ፣ ባንዲራዬን ላንሳት?
ባንዲራዬን ላንሳት?
እያለ ይቃጠላል።ደጋግሞ፣ደጋግሞ«ዳስ ጣል—አንሳው» ይላል።ዳስ ጣል—ማለቱ አገር ልትሞት እየቃተተች መሆኑን መግለጹ ይመሥላል።አንሳው—ሲል ደግሞ ተመልሳ ትነሳለች የሚል ተስፋ ያጭራል።እንደገና በሥሜት ረመጥ ይንተገተግ'ና፦
#የኢትዮጵያ_አርበኞች፣ እነ አናብስቱ፤
ሲረገጥ ባንዲራው፣ ገና አሁን ሞቱ።
ብሎ ይበሳጫል።ካሣን፣አብዲሳ አጋን፣አባ መቻልን፣አባ ነፍሶን፣በላይ ዘለቀ ላቀውን እያሰበ—የዛሬው ትውልድ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ትቶ በሰፈሩ በመሸጎጡ ንዴት የገባው ይመሥላል።
አራዶቹ—ቴዳ የሚሉት አጭር ግን ልበ ተራራ ኢትዮጵያዊ ይቀጥላል፦
ካለቦታው ሲሆን፣ወርቅ አይደለም ዝምታ ለበግም አልበጃት፤
አስራ ሁለት ሆና፣ አንድ ነብር ፈጃት።
በማለትም ትውልዱን ለአንድ አስፈሪ ጥሪ ይቀሰቅሳል።ይህን ጥሪውን ይበልጥ ለማጉላትም፦
ከዚህ በላይ ሀዘን፣
ከዚህ በላይ መርዶ፣
ከወዴት ይመጣል?
ፍቅርን ብየ እንጂ፣
እኔስ መታገሴ፤
መች ከሀገር ይበልጣል፣
እኔስ አንድ ነፍሴ?
በማለት የትግሉ አካል ለመሆን መዘጋጀቱን፣ለመሞትም መቁረጡን ይገልፃል።
ከዚህ ሙዚቃ መለቀቅ በፊት ኤርምያስ ለገሰ ዋቅጅራ እነ ልደቱ አያሌው ምኅረቱ—ቴዲ አፍሮን ወደ ካምፓቸው ሥበው «ሰላማዊ ትግል» ወደሚሉት እሳት ውስጥ ሊማግዱት ነው በማለት ሲያስጠነቅቀው ነበር።
ቴዲ ግን ምክር የሚሰማ ትንታግ መሆን አልቻለም።
እንደ ጥንቱ «ሞትም ይሙት፤የት አባቱ» ያለ ይመሥላል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለብልፅግና ፓርቲ ወግኖ ይጽፋል ተብሎ የሚታማው ናትናኤል መኮንን አልበሙ እየተደመጠ ባለበት አፍታ ብቅ ብሎ «የቴዲን አልበም ሙሉውን ሰማሁት። እጅግ ምርጥ ዘፈኖች የታጨቁበት ነው። ፖለቲካ እንዲዘፍንላቸው ለሚጠብቁ ወገኖቻችን ለማስተዛዘኛ “ዳስ ጣል” የሚል አንድ ዘፈን ሰጥቷቸዋል፤»ብሏል።
ግን ናቲዬ፦
"እምዬ ኢትዮጵያ አንቺ የፍቅር ሀገር
ምሶሶሽ ዘመመ ሆነሽ ያለማገር"
የሚለውን ቅኔ የዘለለው ይመሥላል።
ይሄ የቴዲ ቅኔ «ጀምበር» የተባለው ሙዚቃው ውስጥ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ምሰሶ ዘሟል።ማገር አጥታለች የሚል ትርጉም ይሰጣል።
የግርማዊነታቸው ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴን ድምጽ አስገብቶ ንግግር እንዲያደርጉ በፈቀደበት በዚህ «ጀምበር» የተሰኘ ትራክ መጨረሻ ላይ «አሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 11:00 ነው፤» ማለቱ ፖለቲካ ካልሆነ ምን ይባላል?
ንጋት 11:00 ማለት ቴዲ አፍሮ በሚወዳቸው የጥንት ኢትዮጵያዊያን ዘንድ «ሰማዩ የአሕያ ሆድ መሰለ» ተብሎ የሚገለጽ የድንግዝግዝ ጊዜ ነው።
ቀጥሎ ሰማዩ እየጠራ፤ንጋቱ እያሸነፈ ይመጣል።
ቴዲ—ጀምበሯ መምጣቷ አይቀሬ መሆኑን «አሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 11:00 ነው፤» በማለት ጠቁሟል።
በአጭሩ የኢትዮጵያ ጀንበር ይቅረብ ማለቱ ይመሥላል።
ከነገራችን ጋር ንጋት 11:00 ማለት አድናቂዎቹ «ንጉሡ» የሚሉት ቴዲ አፍሮ በፍቅራቸው የሚነድላቸው ቀኃሥ ለጸሎት የሚነሱበት የዘወትር ሰዓታቸው ነው።
ቴዲ አፍሮ ይሄንን ብዙ ቅኔ ያደራበትን «ጀምበር» የተባለ ሙዚቃ የሚጀምረው «ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ናት።ለምን ይገነጣጥሏታል ከኋላ እየመጡ!?» በሚሉ የወሎ እናቶች ነው።
ከኋላ እየመጡ የሚላቸው ዐቢይ አሕመድን ዐሊንም፣ዘመነ ካሴ ባውቄንም፣ጃል መሮ ድሪባንም፣ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤልንም፣ጃዋር ሲራጅ ሞሐመድንም ይመሥላል።
ቴዲ አፍሮ እዚች ሙዚቃ ውስጥ «ተነሳ ተራመድ፤ክንድህን አበርታ» የተሰኘውን በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጓዶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዘምረው እንደሰጡት የሚነገርለትን ውብ ዜማ'ም አካቶታል።
«ፀሐዬ ደመቀች» የተሰኘው የዚያው ዘመን ሥራም አልቀረውም።
በአጭሩ ቴዲ እሱ በሰዓት ዕላፊ ሥጋት በቤት ውስጥ ተወስኖ ያደገበትን፣አባቱ ካሣሁን ገርማሞ እና እናቱ ጥላዬ አራጌ ግን በተወዛዋዥነት ብሎም በመድረክ መሪነት በጋዜጠኝነትም ሆነ በጸሐፊነት ሥራ የተቋደሱበትን የመንጌ ዘመን «ጀምበር» ውስጥ ዘክሮታል።
ናትናኤል መኮንን ፖለቲካ መሆኑን የዘነጋው ወይም ሆን ብሎ የዘለለው ሌላኛው የ«ኢቶሪካ» አነጋጋሪ ትራክ«የአዞ እምባ» የተሰኘው ነው።
በሕዝባር «አይደለም» ተብሎበታል።
የአንተው የአዞ እምባ ነው—እኔ ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ የማነባው ግን ሃቅ ነው—ማለቱ እንደሆነ ተደርጎ ተተርጉሟል።
ቴዲም፦
በዋዛ መች ይቀራል ፈሶ
የአዞ እምባ ቢባል የኔ ለቅሶ!
የአዞ እንባ የአዞ እንባ
ግን አይደለም የኔ
ቢዘም እኮ ነው ማዕዘኔ
ቢከብድ እኮ ነው ሃዘኔ
እያለ ይቀጥላል።
ይሄን ግጥም ነገር ይገባናል ባይ ቡዳዎች ዐቢይ አሕመድ ዐሊ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ዕለት በደስታ ያነቡትን እምባ ሲሳለቅበት ነው—ብለው ተርጉመውታል።

❤7
አናብስት እና ዝሆን የሚወዱ፣በቤታቸው ያላመዱ፣ለአንበሳ ሥጋ በእጃቸው የሚያጎርሱ ነገሥታትን ታሪክ ፈልፍሎ ለትውልዱ የሚያስተምረው ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ «ቲንታጎ» በተሰኘው እና የጋሞ ቃላትን በብዛት ተጠቅሟል በተባለለት ሙዚቃ ውስጥ፦
ኦ ጋሞ ታኒ ጋሞና
አንበሳ ነኝ የአንበሳ ልጅ
ዳንጋርሳ ባቤናጋ
ዝሆን ነኝ የማልፈራ
ዳንጋርሳ ታኒ ጦኒያጋ
ዝሆን ነኝ አሸናፊ
ብሏል።
ከጥንት ጀምሮ «አልሔደ አለ፣'ሰው አርጊን እዚህ ተይ አገራችን'» እያለ የኢትዮጵያን ዲያሥጶራ ሰቆቃ ሲያዜም የኖረው ጠቢብ አሁንም በዚህ አልበም ውስጥ ራሣቸውን «የመዳም ቅመሞች» ብለው የሚጠሩ የአረብ አገር ሴት ኢትዮጵያዊያትን አልዘነጋቸውም።
«መሬማ» በምትባል የመን ውስጥ በምትኖር ተንከራታች ኢትዮጵያዊት ሴት ወክሏቸዋል።
ርዕሱንም “ አሳዘንሽኝ መሬማ “ ብሎታል።
'አሳዘንሽኝ መሬማ... ስንት አለ በሆድሽ መሬማ' እያለ ያልተዘመረላቸውን የኢትዮጵያ ስደተኞች ውጣ ውረድ በራሳቸው ጫማ ቆሞ አስረድቶናል።
በቃላት የማይገለጸውን የናፍቆትና የልፋት ጓዝ በሙዚቃ የቀመረበት ድንቅ ጥበብ ተብሎም ተወድሶለታል።
በዚሁ የቴዲ አፍሮ - Track 15 - ላይ ያለ መሬማ በሚለው ዘፈን ላይ "እንደ አፋር አፍሌታ" ንጉሡ ሲል ይደመጣል።
አፍሌታ ማለት በአፋር የመጠጥ ውሃ መያዣ ሲሆን የሚሰራው ከፍየል ቆዳ ነው!
አንድ የአፋር ተወላጅ « በነገራችን ላይ የአፍሌታ ውሃ ይጣፍጣል...! by the way ቴዲ አፍሮ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሚለቃቸው አልበሞች ውስጥ አፋርን ያነሳል...! Thank you (Gadda gey) ክቡር አርቲስት ዶ/ር Teddy Afro 🙏» ሲሉም አወድሰውታል።
«ኢትዮጵያ» በተሰኘው አልበሙ ውስጥ የነበረውን፦
ግመሌን ላጠጣት
እስኪ አፋር ተጉዠ
አንድ ገመድ አጣሁ
ልመልሳት ይዠ!
የሚል ቁጭቱ ያስታውሷል።
ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ «ጽዮን ሙሽራዬ» የሚልባት እዚሁ «ኢቶሪካ» ውስጥ ያለች ውብ ትራክ አስቀምጧል።
«የት ወለም ዘለም
ትላለህ
አምሳለ ጦቢትን
ሥንድር ዕያዬህ»
ብሎባታል።
ለቴዳ ኢትዮጵያ ሙሽራም ሆና ትታዬዋለች ማለት ነው።
ለዐቢይ አሕመድ ዐሊ እና ደጋፊዎቻቸው ይህ አገላለጹ መጠነኛ ተስፋ የሚሰጥ ነው።
ይህ ሁሉ መዓት የተሰማበት «ኢቶሪካ» ለአደባባይ ከበቃ በኋላ አስተያየቶች እንደ ጎርፍ እየወረዱ ነው።
ወጣቷ ድምፃዊት ለምለም ኃይለሚካኤል«ሙዚቃው የትዝታችን ማጀቢያ፣ ከልጅነት አውድማ እስከ ዛሬው የህይወታችን ማማ፤ የጥበብ ጥማታችንን ያለ ስስት ያረካ ነው ቴዲያችን!!! ይህ አዲስ አልበም ከዜማም በላይ ነው የጥልቅ ስሜት መነጸር፣ የጥበብ ከፍታ ማሳያ!! እናመሰግናለን ቴዲ🙏🏽❤️🙏🏽❤️»ብላለች።
ፋኑስ ብርሃን የተባሉ ጸሐፊ ደግሞ ቅኔውን በቅኔ ለመመለስ የወደዱ ይመሥላሉ።እንዲህ ሲሉ ሥንኞች ደርድረዋል፦
#ሀይለማርያም ስልጣን ሳይለቅ፤
አብይ አህመድ ሳይታወቅ፤
ጌታቸው ረዳ ሳይደበቅ፤
ህወሃት ሳይገረሰስ፤
ውጪ ሳይሞት መለስ፤
ዘረኝነት እንዲህ ሳይነግስ፤
ሁሉ እንደልቡ ሳይደነፋ፤
ፍቅር ተሰርቆ፣ አንድነት ሳይጠፋ፤
አንዳርጋቸው ፅጌ ሳይሸሽ፣ አብዲ ኢሌ ሳይታሰር፤
ነፃ-ውጪ ግንባር ሲፈረጥጥ፣ መሥርቶ ነፃ አውጪ ከንፈር፤
በአንደበቱ የታገለ፣ የጭቆናን ግዙፍ ቀንበር!
ይህ ሰው ነበር!!!
#አክቲቪስቶች እንደ አሸን፣ በሀገሪቱ ሳይፈሉ፤
ታጥቀው የሸሹ ታጋዮች፣ ትጥቅ አንፈታም ሳይሉ፤
ስናይፐርን ተማምነው፣ ጫላዎች ጩቤ ሳይጥሉ፤
እነ አበበ በጥጋብ፣ በሶ መብላትን ሳይጠሉ፤
ዛሬ ታጋይ ነን የሚሉ፣ ለትግል ሳይነሳሱ፤
ነፃአውጪዎች ሳይፀነሱ
#አንዳንዱ_ቄስ_ቀውስ_ሆኖ፣ ሳይዳፈር ክህነቱን፤
ለምድር ሀገር ፊንፊኔ፣ ሳይክዳት የሰማይ ቤቱን፤
እንደ ካህን ፍቅርን ሰብኮ፣ ቆቡን ሳይጭን የሚከበር፤
"ይፍታህ" ያለ ለትውልዱ፣ አባት ይፍቱኝ በሚል ሀገር፤
ይህ ሰው ነበር!!!
.
#ሀገር_በጭንቀት_ስታምጥ፣ ጭጭ ብሎ ጯሂ ሁላ፤
ከአብዮቱ ትምህርት ወስዳ፣ ለውጥ ልጆቿን ሳትበላ፤
ለውጡ ነውጥ በዝቶበት፣ ሳይቀይር መልክ ቀለሙን፤
መሪው ተሹሞ፣ ሳይቀምሰው የስልጣን ጣሙን፤
የድል አጥቢያ "አር"በኛዎች፣ ሲንሾካሹኩ በየቤቱ፤
ጀግና ነኝ ባይ በቅባቃዎች፣ ቀን አግኝተው ሳይበረቱ፤
ጨለማ ውስጥ ስለ ድፍረት፣ የተቀኘ በአንደበቱ፤
ይሄ ሰው ነው ነፃ አውጪው፣ ይሄ ሰው ነው አክቲቪስቱ!!!
©socialmedia(YT)

❤6🔥1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!
መስቀል ቤዛነ! እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።
የደመራ በዓልን በምናከብርበት በዚህ ቅዱስ ወቅት፣ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ግን ከደስታው ባሻገር በብዙ ፈተናዎች እና ስብራቶች የተሞላ ነው። ዛሬ ሀገራችን በገባችበት አስቸጋሪ ፖለቲካዊ ቀውስ እና መዋቅር አልባ አለመረጋጋት ምክንያት ንጹሐን ዜጎቻችን ያለ ወንጀላቸው በግፍ እየተገደሉ ይገኛሉ። የዜጎች ሕይወት ዋጋ አጥቶ ማህበራዊ ኑሮው ከባድ ፈተና ውስጥ ወድቋል።
በተለይም ሴቶች ፣ እናቶች እና ወጣቶች በአፈሳ እጅግ አስከፊ የሆኑ ጥቃቶች እያጋጠሟቸው ነው፤ ድምፃቸው የሚታፈንበትና ሰብአዊ መብታቸው የሚረገጥበት አሳዛኝ እውነታ ውስጥ እንገኛለን። ከዚህም ባለፈ የሰላም እና የመጠለያ ማዕድናት የሆኑት የቤተ እምነቶች መቃጠልና መደምሰስ የህዝባችንን መንፈሳዊ ቁስል ይበልጥ አባብሶታል።
ለሀገር ብርሃንና ተስፋ መሆን የሚገባቸው የሀገራችን ተማሪዎችም በደረሰባቸው ጫናና መፈናቀል ምክንያት ትምህርታቸውን በሰላም መከታተል እንዳልቻሉና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው በጨለማ ውስጥ እንዳለ ይገኛል። በዚህ በዓል ዕለት ልባችን ከፍ ቢልም፣ የህዝባችን ስቃይ እና የሀገራችን አጠቃላይ መዋቅራዊ ቀውስ ሊረሳ የሚገባው አይደለም። እውነተኛ ሰላም፣ ፍትሕ እና ዕርቅ በሀገራችን እንዲሰፍን የሁላችንም ጸሎትና ትግል አብሮ ሊቀጥል ይገባል።
መስቀሉ የሰላም፣ የፍቅርና የማስታረቂያ ምልክት እንደመሆኑ መጠን፣ አምላክ ለሀገራችን ምህረቱን ልኮ ቁስላችንን የሚጠግንበት እንዲሆንልን እመኛለሁ!

❤4
"ዓለም በየቀኑ ክርስቲያኖችን እየገደለች ነው...የንጹሐን ክርስቲያኖች ደም ክብር የሚያስኛቸው ቢሆንም ይህንን የሚፈጽመው አካል ግን በራሱ ላይ የማይወጣውን መርገም እንደሚያስከትልበት ጥያቄ የለውም።" ብለዋል።
ቅዱስነታቸው አክለውም "ይህ ከሚሆን ግን ከዚህ ድርጉት ብንቆጠብ ይሻላል።"ብለዋል
መስቀልን ለማሳደድ አጽራረ መስቀላውያን በሌለ ኃይላቸው ተጠምደው ብዙ ለፍተዋል ያሉት ቅዱስነታቸው ለዚህም ዛሬ የምናከብረው የመስቀል ደመራ በዓል ምስክር ነው።" ብለዋል።
መስቀልን ይታገሉታል እንጂ አያሸንፉትም ያሉት ቅዱስነታቸው አክለውም ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ዓለም የምታሴረው ሴራ አይሳካምና ብታስብበት እላለሁ።"ብለዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአባታዊ መልእክታቸው ፍቅርና ስምምነት፣ ሰላምና ፍቅርን ማስፈንና እኖደሚገባ አሳስዋል።
ቅዱስነታቸው አክለውም ለአንድነታችን እንቅፋት የሆኑትን በአርቆ አሳቢነት በማለፍ ለሀገራዊ አንድነት አበክረን እንድንሠራ ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
ቅዱስነታቸው አክለውም "ይህ ከሚሆን ግን ከዚህ ድርጉት ብንቆጠብ ይሻላል።"ብለዋል
መስቀልን ለማሳደድ አጽራረ መስቀላውያን በሌለ ኃይላቸው ተጠምደው ብዙ ለፍተዋል ያሉት ቅዱስነታቸው ለዚህም ዛሬ የምናከብረው የመስቀል ደመራ በዓል ምስክር ነው።" ብለዋል።
መስቀልን ይታገሉታል እንጂ አያሸንፉትም ያሉት ቅዱስነታቸው አክለውም ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ዓለም የምታሴረው ሴራ አይሳካምና ብታስብበት እላለሁ።"ብለዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በአባታዊ መልእክታቸው ፍቅርና ስምምነት፣ ሰላምና ፍቅርን ማስፈንና እኖደሚገባ አሳስዋል።
ቅዱስነታቸው አክለውም ለአንድነታችን እንቅፋት የሆኑትን በአርቆ አሳቢነት በማለፍ ለሀገራዊ አንድነት አበክረን እንድንሠራ ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
❤10
"...እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡"
ቅዱስ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ
#ሐምሌ 22 1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታላቅ የሀይማኖት አባት ሀገር ወዳዱ የነፃነት አርበኛ አቡነ ጴጥሮስ ሠማዕትነትን የተቀበሉበት ቀን ናት።
💚💛❤️
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
ቅዱስ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ
#ሐምሌ 22 1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታላቅ የሀይማኖት አባት ሀገር ወዳዱ የነፃነት አርበኛ አቡነ ጴጥሮስ ሠማዕትነትን የተቀበሉበት ቀን ናት።
💚💛❤️
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
❤7
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ
የኢትዮጵያ ቴአትር አባት
ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ
ዮፍታሔ ንጉሴ የተወለደው በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረ ኤልያስ በ1885 ዓ.ም ሲሆን በደብረ ኤልያስ ደብር የጥንቱን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትምህርት በሚገባ ተምሯል፡፡ ዮፍታሔ ፊደል ቆጥሮ ፣ ዳዊት ደግሞ ፣ ንባብ ተምሮ ከጨረሰ በኋላ እዚያው መሪጌታ አደላ ንጉሤ ጋር ዜማ ቀጠለ።
ከዚያም የቅኔን ትምህርቱን ሁለተኛውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስን ቅኔ እንዳስተማሯቸው በታሪክ ከሚነገረው የኔታ ገብረሥላሴ ዘንድ ቀጠለ፡፡ ምንምእንኳ ቅኔ ቤት ለመግባት በነበረው ልማድ ዕድሜው ገና ቢሆንም ፣ የዮፍታሔ ንቃትና ዕውቀት ይህንን ልማድ መስበር አስችሎታል።
በደብረ ኤልያስ ደብር የነበሩ መምህራን “ማህበረ ኤልያስ” በሚል ስም እግረ ኤልያስ ብለው ደቀመዛሙርት ተማሪዎቻቸውን ይጠራሉ፡፡ በዮፍታሔ የዜማና የቅኔ ችሎታ መምህሮቹ ከመደነቃቸው የተነሳ እግረ ኤልያስ (ቅኔ አዛዥ) የሚለውን ምርጥ ስም ሰጥተውት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት አገልግሎበታል ፡፡
ለዮፍታሔ ገና በልጅነቱ የአባቶችን ማዕረግ ቀኝ ጌታ ሾመውታል። ቀኝጌታ ዮፍታሔ ከኤልያስ የወጣው ሁለት ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው በመልእክት ሲሆን መልእክቱን ድርሶ ተመልሷል። ሁለተኛው በራሱ ፈቃድ ሲሆን እንደወጣ ቀርቷል። በዚሁ በሁለተኛው ጊዜ በ1911 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደመጣ፣ ወዲያውኑ በአቦ ደብር በድብትርና አገልግሏል፡፡
ከጓደኛው መረስዔኅዘን ጋር በመሆን "ባያር" በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ለተወሰነ ጊዜ በ7 ብር ደሞዝ ሰርተዋል። ከቤተክርስቲያን አገልጋይነት ጎን ለጎን የባያር ኩባንያ ሲዘጋ በሊጋባ ወዳጆ ጽ/ቤት በዋስ አጋጅ (የተሰበሰበ ግብር ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር ማስገባት) ሥራ ለተወሰነ ጊዜ አገለገለ፡፡
በ1918 ዓ.ም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ በዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት በአማርኛ ፣ ግዕዝና ግብረገብ አስተማሪነት ተቀጠረ። እዚያም አያለ የተለያዩ ጽሑፎችን በጋዜጦች ማሳተም ጀመረ። በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ዮፍታሔ ንጉሤ ቀድሞ መልአኩ በጎሰው ተከትቶ ፣ ልዩ ልዩ መዝሙሮችን እየደረሱ ማስተማር ጀመሩ፡፡
በቀድሞ ጊዜ ዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ያስተምሩ የነበሩ መምህራን በየጊዜው በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ልዩ ልዩ ትያትሮች እየደረሱ ለተማሪዎች ያሳዩ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የመዝሙር መምህሩን ዮፍታሄን ከቴአትር ጋር አስተዋወቀው፡፡ ዮፍታሔም አዳዲስ ቴአትሮችን በተለየ አቅጣጫ መድረስ ጀመረ፡፡
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ከደረሳቸው በርከት ያሉ ቴአትሮች መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “የሆድ አምላኩ ቅጣት”፣ “የደንቆሮዎች ቴአትር”፣ “እርበተ ፀሐይ” እና “ጎበዝ አየን” ይጠቀሳሉ፡፡
ዮፍታሔ ንጉሤ በድርሰት ችሎታው ብዙ የተመሰገነ እና ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ብዙ ሽልማቶችን ያገኘ ነበር፡፡ ከጦርነቱ በፊት በመናገሻ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ሲባል ከነበረው ፣ከተፈሪ መኮንንና ከዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተመርጠው ልዩ ልዩ ትያትሮችን እያዘጋጁ ያበረክቱ ነበር፡፡
አንድ ጊዜ ጃንሆይ ዮፍታሔን ትያትር በመመልከት ላይ እያሉ በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ከልዑል አልጋ ወራሽ አንገት ወርቅ አውልቀው፤ ለዮፍታሔ አድርገውለታል፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ በርካታ የመድረክ ድርሰቶች አዘጋጅቶ አሳይቷል፡፡ ነገር ግን ድርሰቶቹ ባለመታተማቸው የተገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ “ጎበዝ አየን” የሚባለው ድርሰቱ የህትመት ብርሃን አይቷል፡፡
ለመድረክ ከቀረቡት ውስጥ የተመልካችን አድናቆት ያተረፈው “አፋጀሽኝ” የተባለው ድርሰቱ ነው፡፡ ይሄን ድርሰት ዮፍታሔ መጻፍ የጀመረው ከጣሊያን ወረራ በፊት ሲሆን ድርሰቱን የፈፀሙት ከወረራው በኋላ ነው፡፡
“አፋጀሽኝ” ድርሰት ምሳሌያዊ ሲሆን በወቅቱ የነበረውን የዓለም ፖለቲካዊ አዝማሚያ የሚጠቁም ከመሆኑም በላይ በድርሰቱ ውስጥ የተመሰለችው እናት ሀገር ኢትዮጵያ በሚከጅሏት ዘንድ የነበራትን የፖለቲካ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ “አፋጀሽኝ” ዋና ጭብጡ በጣሊያንና በኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት የሚያመለክት ነው፡፡ ይሄም የጊዜው አንገብጋቢ ፖለቲካዊ መልእክት ነበር፡፡ ድርሰቱ የዮፍታሔን ኪናዊ ችሎታ በቅጡ የሚያንፀባርቅ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡
በኢትዮጵያ የድራማ ታሪክ የመድረክ ተውኔቶችን ካቀጣጠሉት ፈር ቀዳጆች መካከል በቅድሚያ የሚጠቀሱት በጅሮንድ ተክለሀዋርያትና እና ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ናቸው፡፡ ዮፍታሔ የድራማ ሰው የነበሩትን ማትዮስ በቀለን አስተምረዋል፡፡ “ሙናዬ ሙናዬ” የተሰኘው ዘፈን የዮፍታሔ ግጥም ሲሆን ዜማው በአገር ፍቅር ማህበር ይገኛል፡፡
ቀኝጌታ ዮፍታሔ ከተውኔት ድርሰቱ በተጨማሪ መዝሙሮችንና ግጥሞችን ደርሷል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነትና የኅብረት መዝሙር የሚገልጽልንን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር (ተፈሪ ማርሽ)፣ ወላድ ኢትዮጵያ፣ አጥንቱን ልልቀመው፣ ድንግል አገሬ ሆይ የሚባሉ መዝሙሮች በጣም ታዋቂዎቹ ናቸው፡፡ አጥንቱን ልልቀመው የሚለው ግጥም አርበኞቹን የዶጋሊውን አሉላ አባ ነጋ እና ራስ ጎበናን በማነፃፀር የገጠመው ግጥም ሲሆን ድንግል ሀገሬ ሆይ የተሰኘውን ድርሰት የፃፈው በስደት ኢሊባቡር ሆነው በ1929 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ መዝሙር ከመጀመሪያ ረድፍ ከሚጠቀሱት ሥራቹ ቀዳሚው ነው፡፡
"ድንግል ሀገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ፣
ሕፃናቱ ታርደው ያንቺም ልብ ቆስሎ፣
ልጅሽ ተሰደደ አንቺን ተከትሎ ፣
የሕፃናቱን ደም አዘክሪ ኵሎ፡፡
(አዝማች)
አስጨነቀኝ ስደትሽ፣
እመቤቴ ተመለሺ እመቤቴ ተመለሺ "
..................................................
ይሄ ግጥም ዮፍታሔ ንጉሤ ሕዝቡ በፋሺስት ወረራ የደረሰበትን ስደት የገለፀበት ስንኝ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእስራኤል ወደ ግብጽ ያደረገችውን ስደት እና በሔሮድስ ሕፃናት መቀላታቸውን ከኢትዮጵያ ስደት ጋር ያነፃፀሩበት ግጥምም ነው፡፡
የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ግጥሞች ትንቢታዊ ሲሆኑ በአንድ ስንኝ የሚጽፈወ ግጥም ተሰጥዖው የላቀ መሆኑን ያሳየናል።
የሰማይ አሞራ ልጠይቅሽ ወሬ፣
ተቃጥሏል መሰለኝ ሸተተኝ አገሬ፡፡
በጣሊያን ወረራ ወቅት ለፋሺስት ያገለገሉ ባንዳዎችን በማስመልከት የገጠሙት ምፀታዊ ግጥም እንዲህ ይላል፡-
ለጌሾ ወቀጣ ማንም ሰው አልመጣ፣
ለመጠጡ ጊዜ ከየጐሬው ወጣ፡፡
የግእዝ ብስለቱ ለቅኔያዊ አማርኛ ግጥሞቹና መዝሙሞቹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ማሽላና ስንዴ በአንድ አብረን ስንቆላ፤
እያረረ ሳቀ የባህር ማሽላ፡፡
ከሰል የሚሆኑ ብዙ እንጨቶች ሳሉ፤
ዝግባ ለምን ይሆን ይቆረጥ የሚሉ፡፡
ዮፍታሔ የአማርኛ ሥነጽሑፍን ለማሳደግ በተውኔት፣ በግጥም፣ በዘፈን እና በመዝሙር ባደረገው ጥረት በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የክብር ቦታ ያለው ነው፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ከጥቅምት 1935 ዓ.ም. አንስቶ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኖ ተሾመ ፡፡ ዮፍታሔ ባልተረጋገጠ ሕመም ምክንያት የሞቱ ሰሞን አካባቢ መርፌ ይወጋ ነበር። ሆኖም ሰኔ 30 ቀን 1939 ዓ.ም. የተለመደውን ሥራውን በቢሮው ውስጥ ሲሰሩ ውሎና አመሻሽቶ ወቤቱ መኪናውን እየነዳ ሲሄድ የተወጋው መርፌ ያደከመው መሆኑን እና ወደቤቱ እንዲያደርሱት ጠይቆ አደረሱት ።
ይቀጥላል ......

❤8
አምሽቶ በሰላም ከተኛ በኋላ ሌሊት አስር ሰዓት እየተነሳ ወደጽሕፈት ሥራው የሚሰማራው ባለቅኔ ነግቶም በአልጋው ሳይነቃ ቀረ:: የአሟሟቱ ጉዳይ አንግዳ በመሆኑ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ጉዳዩን አጣርቶ ይገልጠዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ቤተሰቦቹ ተመርዞ እንደሆን ሲጠረጥሩ በከሰል ጢስ ታፍኖ እንዳለፈ የሚጠያነሱም አሉ።
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ሐምሌ 1 ቀን 1939 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጸመ።
ከቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ታዋቂ የተውኔት ድርሰቶች መካከል ቀጥሉ የተዘረዘሩት ይገኛሉ።
1. ምስክር፣
2. ሙሽሪትና ሙሽራ፣
3. ጥቅም ያለበት ጨዋታ፣
4 የሆድ አምላኩ ቅጣት፣
5. የሕዝብ ፀፀት፣
6. ታላቁ ዳኛ፣
7. መሸ በከንቱ፣
8 አፋጀሽኝ፣
9. ዓለም አታላይ፣
10. እያዩ ማዘን
11.እርበተ ፀሐይ
12. ዳዲ ቱራ
13. እመት አታላይ
14. የደንቆሮዎች ቲያትር
15. መድኔ መድኔ
16. አትርሱኝ እዘኑ
17. ጠረፍ ይጠብቅ
18. ንጉሥና ዘውድ
19. አለቄጥሩ (ጎበዛዝት)
20. ስለአያ ከምሱ እና ስለአያ እነባንተ ይቀጡ
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ጽፎ ለመድረክ ካበቃቸው የመዝሙር ግጥሞች መካከል ቀጥሎ የተዘረዘሩት ይጠቀሳሉ።
1. መዝሙረ ሐዋዝ ዘምስለ መስንቆ፣
2. አብሪ ብርሃንሽን፣
3 ኢትዮጵያ ሆይ፣
4. የባህር ዳር ጨፌ፣
5 ተፈሪ ማርሽ፣
6. ድንግል አገሬ ሆይ፣
7. አጥንቱን ልልቀመው፣
8. ጐህ ፅባህ፣
9. ምጽዓተ-እስራኤል፣
10. ተጠማጅ አርበኛ
11.ደሙን ያፈሰሰ
12. አንተ ባለአጎዛ
13. በለስ ለመለመች
¤ ማስታወሻ : ባለታሪኮችን አንዱን በአንተ/አንቺ ሌላውን በአንቱታ ከመግለጽ ይልቅ ወጥ በሆነ መንገድ አንተ/ አንቺ እያሉ መጥራትን መርጠናል። ይህም አክብሮት ላለመስጠት ሳይሆን አድሎ ከመሰለ አገላለጽ ፣ ወይም የማራቅና ማቅረብ እንዳይመስል ከመፈለግ ነው።

❤3
ሰላም ዋሉልኝ
* አንድ ሰው ስልኩን ካላነሳልህ ከ 2 ጊዜ በላይ ደጋግመህ አትደውልለት።
* ገንዘብ ከተበደርከው ሰው ሳይጠይቅህ ገንዘቡን መልስለት።
* ጓደኛህ ወይም ቤተሰብህ የሆነ Restaurant ወስዶህ ምግብ ሲጋብዝህ ከሜኑው ላይ ውድ የሆነውን ምግብ አትዘዝ።
* ለሁሉም ሰው እኩል Respect ይኑርህ።
* አንድን ሰው በሰዎች ፊት አትገስፀው ፤ ወይም ስህተቱን በሰዎች ፊት አትንገረው። ስህተቱን ስትነግረው በሌሎች ሰዎች ፊት እንዲዋረድ አድርገህ ሳይሆን በግሉ ጠርተህ ለብቻው ንገረው።
* ታክሲ ውስጥ ወይም የሆነ አንድ የመገልገያ ስፍራ ውስጥ ጓደኛህ ሂሳብ ቢከፍል በሚቀጥለው ደግሞ አንተ ክፈል።
* የሁሉንም ሰው እይታ ወይም ሀሳብ አክብር።
* ሰዎች ሀሳባቸውን ሲገልፁ ወይም ሲያወሩ በመሀል አታቋርጣቸው።
* አንድን ሰው ለቀልድ ተርበኸው ወይም ቀልደህበት ከደበረውና ፊቱ ከተቀያየረ ወዲያው መቀለድህን አቁም።
* ሰዎች ሲተባበሩህ አመሰግናለሁ ወይም Thank you ማለትን ባህሪህ አድርገው።
* ቃል አትግባ ወይም የገባኸውን ቃል ፈፅመው።
* የሌሎችን Privacy አክብር። የሰዎችን የግል ህይወት ለራሳቸው ተውላቸው። ራሳቸው ካላነሱት በስተቀር በግል ህይወታቸው ዙሪያ Deep የሆነ ጥያቄ አትጠይቃቸው።
* ሰዎች ሲያወሩህ ሙሉ ትኩረት ስጣቸው። ስልክህን እየነካካህ ወይም የመሰላቸት አይነት ነገር እያሳየህ ማዳመጥ አክብሮት የሌለው ድርጊት ነው።
* የሰዎችን ስኬት አድንቅ። የጓደኛህ ወይም የሌላ ሰው ስኬት እና ደስታ ከልብህ ደስ ይበልህ።
* ሰዎች ሚስጥራቸውን ሲነግሩህ ብትጣሉ እንኳን ሚስጥራቸውን ጠብቅላቸው።

❤7👍3
🇪🇹🏆 ቴዲ አፍሮ በዚኮማ አዋርድ ለምርጥ የዓመቱ አልበም ተመረጠ!
#Ethiopia | የሀገራችን ኩራት የሆነው ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ «ኢቶሪካ» በተሰኘው አልበሙ በዚኮማ አዋርድ (Zikomo Awards) የምርጥ የዓመቱ አልበም ዘርፍ እጩ ሆኖ ቀርቧል።
ይህ ለቴዲ አፍሮ እና ለኢትዮጵያ ሙዚቃ አፍቃሪያን ትልቅ የኩራት ዜና ነው!
የምንወደውን አርቲስት እንደግፍ!
ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ለቴዲ አፍሮ እና ለ«ኢቶሪካ» አልበምዎ ድምፅዎን (VOTE) ይስጡ!
ድምፅ ለመስጠት፦ https://zikomoawards.com/polls/cms6q8s570034jfscvjm9hklq
የኢትዮጵያ ሙዚቃ ድምፅ በዓለም እንዲጎላ በአንድነት እንደግፍ!

የአጼ ቴዎድሮስ መድፍ ሴቫስቶፖል ሰሪ ባሻ ውድነህ ውቤ
ባሻ ውድነህ ውቤ በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን በጋፋት ታዋቂውን መድፍ በመሥራት የተሳተፉ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ጥበበኛና መድፍ ሰሪ ነበሩ።
ቁልፍ ታሪካዊ ነጥቦች
• የትውልድ ቦታ: ከትውልድ ስፍራቸው ጎጃም (ቢቡኝ) የመጡ ሲሆን፣ ከአፄ ቴዎድሮስ መስዋዕትነት በኋላ ወደዚያው ተመልሰዋል።
• የጥበብ ዝና: በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሥር ጋፋት ላይ መድፍ የመሥራት ጥበብ ከፈረንጆች ተምረዋል።
• ከአፄ ቴዎድሮስ በኋላ: ንጉሠ ነገሥቱ ከመስዋዕትነት በኋላ ወደ ጎጃም ሲመለሱ፣ የወቅቱ የጎጃም ገዥ የነበሩት ደጃዝማች አዳል ተሰማ (በኋላ ንጉሥ ተክለሃይማኖት) ቀጥረው መድፍ አሠርተዋቸዋል።
• ተኳሽነት እና ጀግንነት: ባሻ ውድነህ ውቤ መድፍ ሰሪ ብቻ ሳይሆኑ በጦር ሜዳ የሚፈሩ መድፍ ተኳሽም ነበሩ።
• የቤተሰብ ዝና: የታወቁት የዳሞት አርበኛ ደጃዝማች ኃይለእየሱስ ፍላቴ አያት (የልጅ ልጅ) ናቸው።
Abebe Haregewoin

🔥5❤1😁1
አበል_ባለሀገር:
🇪🇹 ለሀገራቸው የተሰውት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፳፰ ፤ ፭፡፲፭ ሰዓት ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሞአቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው
ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት ፡፡ እንዲቀመጡም ፈቀደላቸው ፡፡ በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኩዋቸው ፡፡ ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ የሆነ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር፡፡
የሀገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ ለመገደል ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይጎዳ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሔድ ከመካነ ፍትሑ ፲ ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ “ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?” ሲል ጠየቃቸው ፡፡ “ይህ የአንተ ሥራ ነው” ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ ፡፡ ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር
ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ ፡፡
ከዚያ በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ ርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ ፡፡ ወዲያው አዛዡ “ተኩስ” በማለት
ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው ፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ ፡፡ ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው ፡፡ ብፁዕነታቸው የተገደሉበት ቦታ መኻል አዲስ አበባ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ አካባቢ ነው፡፡ “የብፁዕነታቸው አስክሬን ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአዲስ አበባ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር እንዲቀበር ተደረገ ፡፡ በዚያች
ሌሊት በአዲስ አበባ ውስጥ በየቤቱ ልቅሶና ዋይታ ሆነ ፡፡”
#ሼር

❤12