Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
67.5K subscribers
9.33K photos
604 videos
130 files
1.38K links
The interest of this Channel is giving continuous information about

Housing Projects | Real Estate | Property | Construction | Home Services.

**This page is not a gov't page.**
Download Telegram
የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር የ70 ግራም ዳቦ ዋጋ ላይ ቅናሽ አደረገ።

በዚህ መሠረት አንድ 70 ግራም ዳቦ በሸገር ዳቦ 5 ብር ከ50 ሳንቲም፣ በብርሃን ዳቦ 5 ብር እንዲሁም በመንግስትና የግል አጋርነት የሚሠሩ ማምረቻዎች ላይ በ8 ብር መሸጡን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር በነፃ ገበያ የሚሸጥ የ70 ግራም ዳቦ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

ማህበሩ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ እንዳሳወቀው፣ ከክፍለ ከተሞች ዳቦ አምራች ማህበራት አመራሮች ጋር በዳቦ ዋጋ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ ቀደም ሲል በነፃ ገበያ 15 ብር ይሸጥ የነበረው 70 ግራም ዳቦ አሁን 13 ብር እንዲሸጥ ውሳኔ አሳልፏል።

እንደ አመራሮቹ ገለፃ የዋጋ ማስተካከያው የ70 ግራም ዳቦን ከ13 ብር በላይ የሚሸጡ የዳቦ አምራቾችን የሚመለከት ሲሆን ቀደም ብለው 70 ግራም ዳቦን ከ13 ብር በታች ሲሸጡ የነበሩ አምራቾች ን የማይመለከት መሆኑን አሳውቀዋል።

የዋጋ ማስተካከያው በነፃ ገበያው ዋጋቸውን በራሳቸው ወስነው ሲሸጡ የነበሩ የግል ዳቦ ቤቶችን ብቻ የሚመለከት መሆኑንም የማህበሩ አመራሮች ገልጸዋል። ቅናሹ የሸገር ዳቦን፣ የብርሃን ዳቦን እንዲሁም በመንግስትና የግል አጋርነት ዳቦ እያመረቱ የሚገኙትን 29 የዳቦ ፋብሪካዎችን እንደማይመለከት ገልጸዋል።
❤38👎24😁6🤔6👍3🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳያስቡት ሳይጨነቁ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ

ይህ ለነጋዴዎች እና ወደፊት ንግድ መጀመር ለምትፈልጉ ትልቅ ዜና ነው

ሀይሌ ጋርመንት ሱቆችን ባለፈው ሳምንት የተረከባችሁ ደንበንኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን አሁን ደግሞ

🚨 በ 600,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የንግድ ሱቅ ያውም ቀሪውን በወር 1% ብቻ እየከፈሉ የሱቅ ባለቤት የምትሆኑበት

በሳርቤት,በቡልጋሪያ እና በገላን

ከ10ካሬ ጀምሮ እስከ 861ካሬ በፈለጉት የካሬ አማራጭ

ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ባለባቸው ቦታዎች፣ ለሬስቶራንት፣ ካፌ እና የንግድ መደብሮች የተመቸ።

ከ 2.6 ሚሊየን ብር አጠቃላይ ክፍያ ጀምሮ ወይም በ25% ቅድመ ክፍያ የሱቅ ባለቤት መሆን ይችላሉ

ይህ እድል ለአጭር ጊዜ ስለሆነ ቀድመው ያናግሩን።

+251967770077

Telegram
http://t.me/Apartmentconsultant

Whatsapp
https://wa.me/251967770077
❤25👎3👏2👍1
ነባሩ መንጃ ፍቃድ ከአዲሱ መንጃ ፍቃድ በየትኛው ምድብ ውስጥ ይካተታል? ምን ምን ተሽከርካሪ ያስነዳል?
❤24👍10
Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
Photo
ጋዜጠኞችና ሚዲያዎች የ14 ዓመት የተመዝጋቢዎችን ስቃይ በወቅታዊው የሀገር የጸጥታ ጉዳይ ለመሸፈን መሞከራቸው ያሳዝናል። ሀገር ሰላምና ደህንነት ከሌላት ቤት ቢደርሰንም በሰላምና በደህንነት መኖር እንደማይቻል እንረዳለን፤ የሀገር ሰላም ለሁላችንም ይገባል። ነገር ግን የሰላም ጉዳይ የተመዝጋቢዎችን የ14 ዓመት ጥያቄ ለመሸፈን ምክንያት ሊሆን አይገባም። ሁለቱም ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

ይህ ጥያቄ ከ14 ዓመታት በላይ ሲነሳ የኖረ ነው። ጥያቄያችንን ለአዲስ አበባ ቤቶች ልማት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አቅርበናል፤ በማህበራዊ ሚዲያም ደጋግመን አንስተናል፤ በምክር ቤትም ጥያቄው ከረጅም ጊዜ በፊት ተነስቷል። በመሆኑም ይህ ጥያቄ ፖለቲካዊ አይደለም፤ የዜጎች መሠረታዊ የቤት መብት ነው።

የአስተዳደሩ ጥረት፣ የተከፈለ ዕዳ እና የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ የልማት ስራዎች መኖራቸው ተገቢና የሚደነቅ መሆኑ እሙን ነው::ለ14 ዓመታት የታገሰውን ተመዝጋቢ ህጋዊ ጥያቄ ሆነ ተብሎ ከፖለቲካ ጋር እንዲያያዝ መደረጉ የተመዝጋቢዎች እውነተኛ ብሶት ከህጋዊ ውልና ከልማት ማዕቀፍ ለማስወጣት፣ በተመዝጋቢዎች ና በመንግስት መካከል ያለውን እምነት ለማሸርሸርና ተመዝጋቢውን ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ለማናከስ ታስቦ የተፈበረከ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ነው።
አሁን ያለው አስተዳደር ከቀድሞው ስርዓት የተረከበውን ቢሊዮኖች የሚቆጠር ዕዳ እየከፈለ መሆኑ ቢገለጽም፣ ለ14 ዓመታት ያለመታከት የቆጠበው ተመዝጋቢ ህዝብም ከቀድሞው ስርዓት የተረከበውን የኪራይ እንግልት፣ የዋጋ ንረትና የብር የመግዛት አቅም መውረድ ተሸክሞ እስከዛሬ ይገኛል። ተመዝጋቢው የቆጠበው ገንዘብ በወቅቱ የነበረው የመግዛት አቅም ለአዲስ ግንባታ ውሎ ቢሆን ኖሮ የቤት አቅርቦት ጥያቄዎችን በበርካታ እጥፍ ማቀለል ይቻል ነበር።

የቤት ጥያቄ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን የፍትህ፣ የታማኝነትና የህጋዊ ውል ጥያቄ ነው። ድምፃችንን ሆን ብለው ወደ ፖለቲካዊና የጸጥታ አጀንዳ የሚቀይሩ አካላት ሊረዱት የሚገባው፤ የሀገር ሰላም ለኛ ቅድሚያ ቢሆንም፣ የ14 ዓመታት የቤት ጥያቄያችን ግን ፍትህ እስኪያገኝ ድረስ ህጋዊና መሠረታዊ ጥያቄ ሆኖ እንደሚቀጥል ነው።

የቤት ጥያቄዎች በአንድ ቀን የሚፈቱ ባይሆኑም፣ ተመዝጋቢው የህይወት ዘመን ቁጠባውን ለአስራ አራት ዓመታት መታገሱ ሊካድ አይገባም። በመሆኑም አስተዳደሩ የ2005 ተመዝጋቢዎችን ህጋዊ የፍትህ ጥያቄ ከፖለቲካዊና ከውሸት ስም ማጥፋቶች ለይቶ ማየት እና ከእውነተኛው የህዝብ ብሶት ጎን መቆም ይገባዋል::

የቤት ልማት ራሱ የመንግሥት ቀዳሚ ዕቅድ ነው። ስለዚህ የቤት ጥያቄ ማቅረብ መንግሥትን መቃወም ሳይሆን፣ መንግሥት የያዘው ዕቅድ እንዲሳካ መጠየቅና መደገፍ ነው።

via=የ2005 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች
❤99👍55🥰3
እጅግ የተጎሳቆሉ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ንፁህና ውብ መንደር የቀየረው ''የበጎነት መንደር"

በአዲስ አበባ ከተማ ከተከናወኑ ግዙፍ የልማት ስራዎች በተጨማሪ የላቀ ትርጉም ያለውና እጅግ የተጎሳቆሉ እና ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ንፁህ እና ውብ መንደር በመቀየር የብዙዎችን እንባ ያበሰ እና ከአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ያላቀቀ እንዲሁም ለሰው ክብር የሚመጥን አኗኗር ያጎናፀፈው ''በጎነት መንደር'' የላቀ ትርጉም ያለው ነው፡፡

''የበጎነት መንደር'' በተለይም የቤት እጥረት ችግርን በመቅረፍ በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ዜጎችን  በዘላቂነት በማቋቋም ምቹ መኖሪያ አካባቢ በመፍጠር የነዋሪውን ማህበራዊ ግንኙነት ያጠናከረ እና የመደጋገፍ ባህልን ያደሰ ነው ፡፡

ለሰው ክብር ቅድሚያ በመስጠት የመኖሪያ ቤት ችግር በዘላቂነት መፍታት ያስቻለው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በልደታ፣ በአራዳ፣ በኮልፌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በየካ:በለሚ ኩራና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ሌሎች የበጎነት መንደሮች በመገንባት የጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመቀየር ለኑሮ ምቹ የሆኑ፣ ንጽሕናቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች፣ የጋራ መገልገያዎች እና የጋራ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ዘመናዊ፣ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣  አረንጓዴ ሥፍራዎችና ሕፃናት ቦርቀው የሚጫወቱባቸው ምቹ  የስፖርት ሜዳዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡

አስተዳደሩ በመጠለያ እጥረት፣ በከፍተኛ የኪራይ ውድነት እና ለኑሮ ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና አቅመ ደካሞችን በዘላቂነት ለማቋቋም ያስችል ዘንድ በርካታ ብሎኮችንና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ለተጠቃሚው እያስተላለፈ ይገኛል፡፡
❤37👎26😁2
በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በጨረታ እንደሚሸጥ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በግልጽ ጨረታ ያቀረባቸውን ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ25/02/2019ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
❤48👎13👍4🥰3🔥2
🔥 ከአሁን በኋላ ኪራይ መክፈል ይብቃ! የራስዎ ሱቅ ይኑርዎት!

በአዲስ አበባ ተመራጭ በሆኑ የንግድ ቦታዎች ላይ የራስዎን ሱቅ በቀላሉ የሚያገኙበት ታላቅ እድል!

📍 ሳርቤት | ገላን | ቡልጋሪያ

💰 ከ2.5 ሚሊዮን ብር ጀምሮ
☑ 25% ቅድመ ክፍያ
☑ ቀሪውን በወር 1% የመክፈል እድል

የራስዎን ንግድ ያሳድጉ፣ የወደፊት ኢንቨስትመንትዎን ከዛሬ ይጀምሩ!

📞 0937405124

Temer Properties – የራስዎ ሱቅ፣ የስኬትዎ መሠረት!
Telegram
http://t.me/feyori

Whatsapp
https://wa.me/251937405124
❤13
ከ1997- 2007 ዓ/ም በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተስተዋሉ የግንባታ ጥራትና ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት በጥናት የተለዩ ሕንፃዎች ላይ የማስተካከያ ሥራ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የታዩ የግንባታ ጥራትና መሰል ችግሮችን ለመለየት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።

በጥናቱ የችግሮቹ ዓይነትና ደረጃ ተለይቶ ቅድሚያ የእርምት ርምጃ የሚያስፈልጋቸው ሕንፃዎች ተለይተዋል። በዚህም ከነዋሪዎች ጋር በመግባባት ፣ የሥራ ተቋራጮችን በመመደብና የማስተካከያ ሥራዎችን ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አመልክቷል።

በተጨማሪም በጥናቱ የተመለከቱ ጉድለቶችን በተመለከተ አስፈላጊውን የሰነድና የማስረጃ ዝግጅት በማድረግ፣ በውል ግዴታ መሠረት ተጠያቂነትን ለማስፈንና ተገቢውን የሕግና የውል እርምጃ ለመውሰድ እየተሠራ መሆኑን አሳውቋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል ::
❤50👎44😁17👍7
Ethiopia has become Africa's fifth-largest economy after rebasing its GDP to $210.7 billion for the 2025/26 fiscal year.

This statistical revision places Ethiopia among South Africa, Egypt, Nigeria, and Algeria as the continent’s leading economies.

The GDP rebasing increased Ethiopia's measured economic output by 59.2%, using updated methods and more comprehensive data sources.

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ 5ኛ ደረጃን ያዘ

ብሉምበርግ እንደዘገበው፣ ኢትዮጵያ ባደረገችው የኢኮኖሚ ስሌት ማሻሻያ ምክንያት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ቀደም ሲል ከተገመተው በ60 በመቶ ገደማ አድጎ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነበራትን የኢኮኖሚ ደረጃ በአራት ደረጃዎች በማሻሻል ከ9ኛ ወደ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የገንዘብ ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በ2025/26 በጀት ዓመት 210.7 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በአዲሱ የ2024/25 መነሻ ዓመት ስሌት ደግሞ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ 201.4 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ማሻሻያ ኢትዮጵያን ከደቡብ አፍሪካ ($489 ቢሊዮን)፣ ከግብፅ ($443 ቢሊዮን)፣ ከናይጄሪያ ($387 ቢሊዮን) እና ከአልጄሪያ ($332 ቢሊዮን) ቀጥሎ በአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ ያደረጋት ሲሆን፤ ሞሮኮን (~$196 ቢሊዮን)፣ አንጎላን፣ ኬንያን እና ጋናን ለመብለጥ አስችሏታል።
❤49😁38👎8🤔3👍2🔥1👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏡🔥 የራስዎ ቤት ከ4.7 ሚሊዮን ብር ጀምሮ!

ከዚ በፊት የገዙ ደንበኞቻችን በኛ ደስተኞች ናቸዉ እናንተም የዚ እድል ተጠቃሚ ይሁኑ

📍 አዋሬ – መገናኛ CMC፣ Convention Center አቅራቢያ

ዘመናዊ አፓርታማ በሚመችዎ አከፋፈል!

🏢 ከStudio እስከ 3 መኝታ ቤቶች

💰 Studio ከ4.7 ሚሊዮን ብር ጀምሮ!

☑ 20% ቅድመ ክፍያ
☑ በወር 1% ክፍያ

✨ ለመኖሪያም ሆነ ለኢንቨስትመንት ትልቅ እድል!

⏳ ይህንን እድል እንዳያመልጥዎ!

ለበለጠ መረጃና ቦታ ለመያዝ አሁኑኑ ይደውሉ!
☎️ 0937405124

Temer Properties – የራስዎ ሱቅ፣ የስኬትዎ መሠረት!
Telegram
http://t.me/feyori

Whatsapp
https://wa.me/251937405124


🏠 ቤት መግዛት ህልም ብቻ አይደለም፤ ዛሬ መጀመር ነው!
❤19👎6
#መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፀም ትኩረት መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

ማንኛውም መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፅሙ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩/ በሁሉ አስቀድሞ ይዞታው ህጋዊ ካርታ (የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት) እና ህጋዊ ፕላን ያለው መሆን አለበት፡፡

፪/ በሻጭ እጅ ያሉ ሰነዶችና በክ/ከተማው በመዝገብ ቤት በሻጭ ስም ያለ የይዞታ ማህደር ጋር ሰነዶች በትዩዩ አንድ አይነት መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡ በተለይም በካርታው ላይ ያለው የካርታ ቁጥርና በክ/ከተማ መዝገብ ቤት ያለው ቀሪ ካርታ ቁጥር ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡

፫/ የይዞታ ማህደሩ ከእዳ፣እገዳና ሌሎች ክልከላዎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የሊዝ እዳ ገዥው እስከ እዳው መግዛት የሚፈልግ ከሆነ እዳውን ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

፬/ ትዳር ያለው ከሆነ ከወሳኝ ኩነት የትዳር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፡፡ ትዳር የሌለው ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡

፭/ ሕጋዊ የሽያጭ ውል በሰነዶች ምዝገባ/ውልና ማስረጃ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

፮/ በውክልና የሚሻሻጡ ከሆነ ውክልናው ህጋዊ መሆኑን ውክልና ከሰጠው የፍትህ ተቋም ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

፯/ በተጨማሪም በአካል ወደ ሚሸጠው ቤት ሂዶ ቤቱን በአካል ማየትና ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

‼️ ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ማለትም ይዞታው ወደ ፊት ለመኖሪያ ወይስ ወደ ንግድ መቀየር ይቻላል የሚለውን ሀሳብና ከግንባታ ከፍታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ማማከርና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
👍31❤28