ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
20.1K subscribers
1.41K photos
103 videos
272 files
3.87K links
እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ!
በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ!
ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ!
ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን
Download Telegram
الرد_المبين_،_على_ابن_حامي_الدين١.pdf
192.6 KB
አዲስ Pdf
عنوان :- الرد المبين على محمد حامي الدين
في ثنائه على رئيس الإخوان وقائدهم سيد قطب وأمثاله
✍ للشيخ محمد بن حيات الولوي حفظه الله

ሙሀመድ ሃሚዲን የኢኽኑ'ል ሙስሊሚን መሪ የነበረውን ሰይድቁጥብን ባወደሰበት ንግግሩ ላይ የተሰጠ ግልፅ ምላሽ

https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara

✅ جزاكم الله خيرا وبارك فيكم ورفع قدركم في الدنيا والآخرة فقد اطلعت على البحث فوجدته نافعا وجامعا لانحرافات المردود عليه وزيادة على ما في  الفيدو الأخير . والراد على أهل البدع مجاهد فكتب الله أجركم وسددكم وثبتكم على التوحيد والسنة حتى الممات.
✍🏻الشيخ الدكتور حسين السلطي حفظه الله
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
الرد_المبين_،_على_ابن_حامي_الدين١.pdf
✅ جزاكم الله خيرا وبارك فيكم ورفع قدركم في الدنيا والآخرة فقد اطلعت على البحث فوجدته نافعا وجامعا لانحرافات المردود عليه وزيادة على ما في  الفيدو الأخير . والراد على أهل البدع مجاهد فكتب الله أجركم وسددكم وثبتكم على التوحيد والسنة حتى الممات.
✍🏻الشيخ الكتور حسين السلطي حفظه الله
Forwarded from Jemal Mohammed
♻️ ለኸይር ስራ ረፍዶ አያውቅም‼️
​የ21 ዓመቱን የኪራይ ታሪክ ለመዝጋት÷ መስጊዱ የእርስዎን እጅ እየጠበቀ ነው:-
      ➡️ አንድ ካሬ 12 ሺህ ብር ብቻ‼️
          ✅️ በራስዎ
           ✅️ በባለቤትዎ
           ✅️ በልጆችዎ
           ✅️  ወደ አኼራ በሄዱ ወገኖችዎ ስም ይለግሱ‼️
♻️ የአላህን ቤት ዕዳ ሙሉ በሙሉ ዘግተን  መስጅዱን እናስረክብ‼️
​የባንክ ሂሳቦች፦
💰ንግድ ባንክ፦ 1000-742-45-45-45
💰አቢሲንያ ባንክ፦ 245-566-778
💰ሂጅራ ባንክ፦ 100-927-373-0001
​📲 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/bilalmesji
ሰለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?1706372650618
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ለኢብኑ ሙነወር የተሰጠ ምላሽ

ርእስ:- ሠለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ጥር 17/2016 የተደረገ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ጠያቂ:- የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን?

መልስ:- ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
🔷 ክፍል 1⃣
➥ የሙነወር ልጅ ከጠንካራው የሠለፎች መንገድ ተዘንብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የተካተተበትን ነጥብ ለጠየቀ ሰው የተሰጠ መልስ።
እወቅ! አላህ ይዘንልህና ደጋግ ቀደምቶች ቢድዓንና ባለቤቶቹን በመጥላትና ከእነርሱም በመራቅ ላይ በእርግጥ ተስማምተዋል።
ኢማሙ ሷቡኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- "…ደጋግ ቀደምቶች የቢድዐህ ባለቤቶች ላይ የበላይ በመሆንና እነሱን በማዋረድ፣ ከእነርሱም በመራቅ፣ እነሱን ባልደረባ አድርጎ ከመያዝና አብሯቸው ከመኗኗር በመራራቅ፣ ተስማምተዋል። እነርሱን በመራቅና በመዝጋት ተግባርም ወደ አላህ በመቃረብ ላይ ተስማምተዋል።" [ዐቂደቱ ሰለፍ ሊሷቡኒይ]

= የደጋግ ቀደምቶችን የጋራ ስምምነት የተፃረረ፣ አለያም ለቢድዐህ ባለ ቤቶች የተከላከለ ሰው፣ አለያም የቢድዐህን ባለ ቤት ያወደሰ ሰው እርሱን ከቢድዐህ ባለቤቶች ያስጠጉታል ክብር የለውም። ይልቁንም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር የሚቀማመጥ ሰው ስለ ቢድዐህ ባለቤቶች ግልፅ ካልሆነለት ይብራራለታል፣ ተብራርቶለትም መቀማመጡን ከቀጠለ ወደዚያው ይካተታል(እሱም ከቢድዐህ ሰዎች ይመደባል)፣ደጋግ ቀደምቶች በዚህ መልኩ ነው የተጓዙት። በእርግጥም አምላካችን አላህ ወንጀል (ኃጢያት) የሚሰራና ሳይሰራ አብሮት የሚቀማመጥን ሰው እኩኩል አድርጓቸዋል፣ እስካልራቃቸው ድረስ ብይኑ ተመሳሳይ ነው። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا

«በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሀዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡» አን'ኒሳእ 140

አል ኢማም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- "ለዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ኸምር (አስካሪ መጠጥ) የሚጠጡ የነበሩ ሰዎችን ይዘው አመጡለት፣ እንዲገረፉም አዘዘ፣ ከእነሱ ውስጥ ፆመኛ ሰው አለ ተባለ፣ ከፆመኛው ጀምሩ አለ፣ አላህ እንዲህ ማለቱን አልሰማችሁም እንዴ?

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا

«በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሀዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡» አን'ኒሳእ 140

ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ሰው የተወገዘ ተግባር ከሚሰራ ሰው ጋር መገኘቱ በራሱ ሰውዬው ባይሰራም እንኳ አላህ  ልክ እንደሰሪው እንዳደረገው ግልፅ አድርጓል። [መጅሙዕ አል ፈታዋ 28/221]

አል ኢማም ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ: የቢድዐህ ባለቤቶችን የሚያወድስና የሚያሞግስ ሰው የነሱን ብይን ይዛል (ከቢድዐህ ባለበፀቶች ይሆናል?)

መልስ:- አዎን ጥርጣሬም የለውም!። እነሱን ያወደሳቸውና ያሞገሳቸው ሰው የነሱ ተጣሪ ነው፣ አላህ ይጠብቀንና ሰዎችን ወደነሱ ጠርቶላቸዋል። [ሸርህ ፈድሉ'ል ኢስላም]

በእርግጥ የሙነወር ልጅና ሌሎችም ሙመይዓዎች በሁለት ነጥቦች ተፈትነዋል:- የመጀመሪያው የተብዲዕ ነጥብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጀርህና ተዕዲል ነጥብ ነው። የሙነወር ልጅና ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎች በዒልመል ሀዲስ (በሀዲስ እውቀት)፣ በጀርህና ተዕዲል ላይ ጥግ የደረሱ መሀይሞች ናቸው። የሙነወር ልጅ የተመረቀው በታሪክ ጥናት ነው፣ ሸሪዓዊ በሆነ እውቀት ላይ ግንኙነት የለውም፣ ከመሻይኾቹም ከአህሉሱንና የሆኑ መሻይኾችን አናውቅለትም። በሱንና ዑለማዎች ላይ ባልተማረ ሰው መማሩ ደግሞ አይፈቀደም!። ሰለፎች እንዲህ ብለዋል:- "ይህ እውቀት ዲን ነው፣ ዲናችሁን ከማን እንደምትይዙ ተመልከቱ።"
በእርግጥም የሙነወር ልጅ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ በመከላከልና የሱንና ዑለማእዎችን በመተቸት ላይ እራሱን አጋልጧል (አንገቱን) ቀና አድርጓል፣ የቅርቡም የሩቁም ሁሉ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ከመንሀጀ'ሰለፍ ወጥተው ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መጠቃለላቸውንና ሠለፊዮችን በሁሉም ቦታ የሚዋጉ መሆናቸውን በእርግጠኝነት አውቋል። ይህ ተግባራቸው ደግሞ ንፁህ አዕምሮ ላለውና ሚዛናዊ ለሆነ ሠለፊይ ሁሉ ግልፅ ነገር ነው፣ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች አይከላከልም ከእነሱ የሆነ ቢሆን እንጂ።

የሙነወር ልጅ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች በመከላከል በርካታ የተለያዩ ፅሁፎችን ፅፏል፣ እንዲያውም ለኢልያስ አህመድ እየተከላከለ "የቢድዐህ ባለቤቶችን ያወደሰ ከሱንና አይወጣም" ብሏል፣ ይህን ለማጠናከርም በቀጣይ እንደሚቀርበው በበርካታ ዑለማዎች ላይ ቀጥፏል።
እንደሚከተለው የተወሰኑ የሙነወርን ልጅ የጥመት ሰበቦችን ማስታወስ ይቻላል:-
በቅድሚያ እንደማንቂያ:- ቀደም ሲል በነበሩ ጊዜዎች የሙነወር ልጅ በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ይናገር እንደነበር ማንም አይጠራጠርም። ጥፋታቸውን ግልፅ አድርጎ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር እየተጓዙ እንደሆነ ተናግሮ ሠለፊዮችም በዚህ ተግባሩ ተደስተው አመስግነውት ከጎኑ ቆመው እንደነበር ይሰመርበት።

1ኛ, ከዚያ በኋላ በመርከዙ ሰዎች ላይ ከመናገር፣ ከቀጠለውና እየበዛ ከመጣው ጥፋታቸው (ወደ ቢድዐህ) ማዘንበላቸው ምላሽ ከመስጠት ቆመ። ልቦች በአላህ እጅ ናቸው፣ የላቀው አላህ እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል፣ በዚህ ምክንያትም የሱንና መሻይኾች በኢብኑ መስዑ መርከዝ ሰዎች ላይ ያለውን ትክክለኛ አቋም ግልፅ እንዲያደርግ ጠየቁት።

2ኛ, ጭራሹኑ ለመርከዙ ሰዎች ምክንያት ይደረድርላቸው ጀመር፣ በተቃራኒው ደግሞ የሱንና መሻይኾችን መተቸት ጀመረ፣ ሸይኽ ዐ/ሐሚድንና ሸይኽ ሐሰን ገላውን ይመስል፣ ቆሻሻ በሆኖ ገለፃዎች ሁሉ ማጠልሸት ጀመረ፣ ወደ ሀዳዲይነትም አስጠጋቸው፣ ሰለፎች እንዳሉት ደግሞ ከቢድዐህ ባለቤቶች መገለጪያ አንዱ የሱንና ሰዎችን መተቸት ነው።
ይቀጥላል…
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
ጠያቂ:- የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን? መልስ:- ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) 🔷 ክፍል 1⃣ ➥ የሙነወር ልጅ ከጠንካራው የሠለፎች መንገድ ተዘንብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የተካተተበትን ነጥብ ለጠየቀ ሰው የተሰጠ መልስ። እወቅ! አላህ ይዘንልህና ደጋግ ቀደምቶች ቢድዓንና ባለቤቶቹን…
ጠያቂ:- የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን?
🔶 ክፍል ②
መልስ:- ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

ክፍል ① ለማግኘት ⤵️
https://t.me/IbnShifa/6004
ዐረቢኛውን ለማንበብ ⤵️
https://t.me/IbnShifa/6002

ከክፍል አንድ የቀጠለው ፅሁፍ እነሆ…
3ኛ, ከዚያም የገባበትን የተምይዕ መንሀጅ ሊያጠናክርበትና ለእራሱ ለመከላከል ብሎ በጀርህና ተዕዲል ዙሪያ አዳዲስ የሆኑ የእነ ሀለቢንና የአቢል ሀሰን አል'መእሪቢይን መርሆዎችን ማሰራጨት ጀመረ።

4ኛ, በተለያዩ ሙሃዶራዎቹም ጀርህና ተዕዲል የኢጅቲሃድ ነጥብ እንደሆነ፣ ማንም ማንንም ሊያስገድድበት የሚችል ነጥብ እንዳልሆነ አስረግጦ ተናግሯል፣ ይህን ያደረገውም በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ግልፅና ትክክለኛ የሆነውን የሰለፊይ አቋም ግልፅ እንዲያደርግ በጠየቁት የሱንና መሻይኾች ላይ ምላሽ ለመስጠት ብሎ ነው።

5ኛ, ከንግግሮቹም:- አገሌ የሚባል ዓሊም አገሌን ሙብተዲእ ብሎት ሌላኛው ዓሊም ደግሞ ሙብተዲዕ አላለውም፣ ስለዚህ ያላለውን ዓሊም ሙብተዲዕ ብላችሁ ታስጠጉታላችሁን? በማለት በተብዲዕ ላይ የጋራ ስምምነት ግድ እንደሆነ አስመስሎ ልክ እንደ ሀለቢይ ይናገራል፣ በዚህ የሀለቢይ ንግግር ደግሞ የሱንና ሊቃውንት የተሳሳተ በመሆኑ ላይ ምላሽ ሰጥተውበታል።

6ኛ, የሙነወር ልጅ በመልክተኛው ﷺ ላይ ኸዋሪጆችን ጥፋታቸውን ከመናገራቸውም ጋር አወድሰዋል በማለት መዋሸቱ ነው፣ ይህም አዲስ ፈጠራ የሆነውን ከቢድዐህ ባለቤቶች ለመከላከል ብሎ የሙዋዘነህ መርህ ለማስቀመጥ የሄደበት ርቀት ነው። የአላህ መልክተኛ ﷺ ኸዋሪጆችን "ከዲን ሾልከው ይወጣሉ…" "የጀሀነም ውሾች ናቸው…" በማለት  ተናግሯቸው እያለ እንዲህ በድፍረት መዋሸቱ ልቡ እጅጉን ለተምይዕ ፊክራ የተመቻቸና ብዥታዎቹን ከልቡ የጠጣቸው እንደሆነ ያሳያል።

7ኛ, ሸይኽ ረቢዕ (ረሂመሁላህ) አሻዒራዎችን አወድሷል በማለትም በሸይኽ ረቢዕ ላይ ዋሽቷል፣ ይህን ውሸቱንም አጋልጠናል።

8ኛ, በኢማሙል አልባኒይ (ረሂመሁላህ) ላይም ኢኽዋን የሆነውን ሰይድ ሳቢቅን "ፊቅህ አስ-ሱነህ" ኪታቡን ተዕሊቅ ባደረገበት ወቅት ላይ አወድሶታል በማለት ዋሽቷል። በመሰረቱ ኢማሙል አልባኒይ ኪታቡን ራሱ ሶሂህና ዶዒፉን እንዲለዩ፣ የተለያዩ ሸሪዓን የሚጥሱ አስተሳሰቦችን እንዲያርሙ ተጠይቀው ነው ያረሙት።

9ኛ, በታላቁ ዓሊም በሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም አል ኢትዮጲ ላይ (ረሂመሁላህ) ከኢኽዋኑ ቀርዷዊ ኪታብ ላይ አንስተዋል በማለትም ዋሽቷል።

10ኛ, ልክ እንደ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን፣ ሱሩሪዮችና ሂዝቢዮች ሰለፊዮችን መዳኺላ በማለት ወርፏል።

11ኛ, ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሓዲል መድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) ከዑምራ በኋላ ሸይኽ ረቢዕን የማይዘይር ሰለፊይነቱ ያጠራጥራል በማለቱ ተችቷል።

12ኛ, ከአህሉል ቢድዐህ ጋር ተባብሮ መስራት ይፈቀዳል ብሎ መናገሩና ኢትዮጵያ ውስጥም ሙስሊሞች ከመጅሊስ ጋር ይተባበራሉ ብሎ በመናገር "አላህን በመፍራትና በመልካም ነገር ላይ ተባበሩ" የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ከፍጡራን ሁሉ መተባበር ማለት ነው ብሎ አዙሮ ተርጉሟል።

13ኛ, የሙነወር ልጅ በከንቱ የተለያዩ ኺላፋቶችን በማውሳት የተሞላ ሰው ነው፣ ሁሌም ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ከሰይድ ቁጥብ ተከላክሏል፣ ሸይኽ ረቢዕ ደግሞ ሰይድ ቁጥብን ሙብተዲዕ ብለውታል በክር አቡ ዘይድ ወደ ሰይድ ቁጥብ ታስጠጉታላችሁ? ይህ ሰው (ኢብኑ ሙነወር) ሰለፊያን ያልተረዳ መሀይም ነው፣ ይህቺ አካሄድ  ለመርከዙ ሰዎች ለመከላከል የሱፊይነትና ሂዝቢይነት አካሄድ ናት። ግዴታ የነበረውማ የማስረጃን ባለቤት መከተል ነው፣ የሰይድ ቁጥብ ጥመት ከፀሃይ በላይ ግልፅ ነው፣ በርካታ ዑለማዎች ምላሽ ሰጥተውበታል፣ ስለዚህ የላቁ ንፁህ ሰለፊዮች ዘንድ የበክር አቡ ዘይድ ከሰይድ ቁጥብ መከላከል ዋጋ የለውም።

14ኛ, ሌላው ደግሞ ጀርህና ተዕዲል ማድረግ ሐበሻ ውስጥ ካሉ የሱንና ዑለማዎች አርቆ (ማድረግ አይችሉም) ብሎ ለራሱ ማፅደቁ ነው፣ ይህ የሚደንቅ መጣረስ ነው፣ የንግግር መጣረስ ከቢድዐህ ባለቤቶች መለያ ነው።

➣ እነዚህ ከፊል ወደ ቢድዐህ ባለቤቶች ሶፍ የተዘነበለባቸው ነጥቦች ናቸው፣ እሱም ያለ ምንም ጥርጥር ከቢድዐህ ባለቤቶች ነው። እነዚህ ከጥፋቶቹ በከፊሉ የተጠቀሱ ነጥቦች ከሱና ወጥቶ ወደ ቢድዐህ ለመጓዙ በቂ ምክንያቶች ሲሆኑ ሙሉ ጥፋቶቹና ጥመቶቹ ተሰብስበው ቢጠቀሱ እንዴት ሊሆን ነው?!።
አላህን እስክንሞት ጤናማነትንና በሱንና ላይ መፅናትን እንጠይቀዋለን!!
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
ዘመን መለወጫና ሙስሊም
—————
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በየትኛውም መንገድ ዘመን መለወጫ የሚባል ነገር አይመለከተውም!!።

ለዘመን መለወጫም ሆነ ለሌሎች ለከሀዲዎች በዓላቶቻቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት በእስልምና ሀይማኖት የማይፈቀድ (ሀራም) ነው!!

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“በ(ከሃዲያን) ሰዎች የተመሳሰለ እርሱ ከእነሱ ጋር ነው።" [አቢዳውድ 4033 ላይ ዘግበውታል።]

የፈረንጆችንም ሆነ የማንንም ዘመን መለወጫ ማክበር በኢስላም በጥብቅ የተከለከለ ነው!!
በእስልምና ዘመን መለወጫ የሚባል ነገር የለም።

አንድ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው "እንኳን ለዚህ አበቃህ (አደረሰህ)" ተብሎ የደስታ መግለጫ እማይደረግለት ከሆነ፣ ከዚህ የከፋውን ተግባር በመፈፀም በአለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ "እንኳን በፈጣሪህ ክደህ ያሻህን ልታመልክና ልትሰራ አደረሰህ" ይባላልን?!

በበዓላቸው ልጆች እንዳይቦዝኑብኝ ብሎ ማረድም ሆነ ሌሎችን ከነሱ የሚያመሳስል ነገር መስራት አይፈቀድም!!። የሙስሊም ልጆችን የራሳችን የሙስሊም በዓል አለን ብሎ ማስተማር ነው!!።

እነሱ ለበዓላቸው የሰሩትን አምጥተው ቢሰጡ ተቀብሎ መብላትም አይፈቀደም!!

እነሱ ለራሳቸው ጊዜ ጥግ የደረሱ አክራሪዎች ሆነው የነሱን እምነትና ባህል የኛም እምነትና ባህል እንዲሆን ይተጋሉ!። እኛን ደግሞ የራሳችን ድንቅ ሀይማኖት አለን ብለን ቆፍጠን ስንል "አክራሪ፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ሰላም፣ ፀረ መቻቻል… ፀረ ፀረ ፀረ…" ይሉናል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖቱን እሴት አክብሮ ሊኖር ይገበዋል። ከከሀዲዎች ጋር የጋራ በዓልም ሆነ እምነት የለንም!!። ለኛ የራሳችን እምነትና በዓል አለን!!። የምናደምቀው የራሳችን እምነትና በዓል ነው። በነሱ በዓል ጊዜ ሙስሊሙ አብሮ ግርግር እንዲፈጥር የሚያደርገው ነገር የለም።

አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ ۝ لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ ۝ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ ۝ وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَّا عَبَدتُّمْ ۝ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ ۝ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ

«በላቸው፣ እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! "ያንን የምትግገዙትን አልግገዛም፡፡እናንተም እኔ የምግገዛውን ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ እኔም ያንን የተገዛችሁትን ተገዢ አይደለሁም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን (አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ!፡፡» አል-ካፊሩን 1-6

ይሄው ነው! እስልምናችን መጨመላለቅንና አጎብዳጅነትን አላስተማረንም!! ሀይማኖትህን ለማስከበር ቀድመህ አንተው መርሆቹን አክብር!!።

"ይሄ እኮ የጋራ በዓል ነው፣ የሀገራችን ዘመን መለወጫ እንጂ ሌላ ነገር የለውም" እያለ ሊያጃጅልህ ሲሞክር መጃጃልህን ትተህ አትተሻሽ "አይ! እምነቴ አይፈቅድልኝም!።" በለው። የሀገራችን የካላንደር አቆጣጠር ራሱ ከየት መጣና ነው? የራሳቸው የከሀዲያን አቆጣጠር ነው። እኛ የሚወክለን አቆጣጠር ኢስላማዊ (ሒጅሪይ) ነው፣ ለሱም ቢሆን እምነታችን ዘመን መለወጫ ብለን ማክበር አይፈቅድልንም። ዒዳችን ሁለት ዒዶች ናቸው፣ ዒዱል አድሃና ዒዱል ፊጥር፣ ከዚህ ውጭ ሳምንታዊ ጁምዐህ ነው፣ አበቃ። የትኛውም ዘመን መለወጫ የሚባል ኮተት ሙስሊሙን አይወክለውም!!።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
الرد_المبين_،_على_ابن_حامي_الدين١.pdf
191.1 KB
هذه النسخة أولى من النسخة الأولى

አዲስ Pdf
عنوان :- الرد المبين  على محمد حامي الدين
في ثنائه على رئيس الإخوان وقائدهم سيد قطب وأمثاله
✍ للشيخ محمد بن حيات الولوي حفظه الله

ሙሀመድ ሃሚዲን የኢኽኑ'ል ሙስሊሚን መሪ የነበረውን ሰይድቁጥብን ባወደሰበት ንግግሩ ላይ የተሰጠ ግልፅ ምላሽ

https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara

✅ جزاكم الله خيرا وبارك فيكم ورفع قدركم في الدنيا والآخرة فقد اطلعت على البحث فوجدته نافعا وجامعا لانحرافات المردود عليه وزيادة على ما في  الفيدو الأخير . والراد على أهل البدع مجاهد فكتب الله أجركم وسددكم وثبتكم على التوحيد والسنة حتى الممات.
✍🏻الشيخ الدكتور حسين السلطي حفظه الله
الفصل_المبين_في_دحض_شبهات_وتلبيسات_محمد_حامي_الدين.pdf
322.9 KB
👉 አዲስ pdf

عنوان:- الفصل المبين في دحض شبهات وتلبيسات محمد حامي الدين.

ርእስ:- ግልፅ የሆነ መለያ፣ የሙሀመድ ሃሚዲንን ብዥታና ማምታቻ በማጋለጥ ላይ…

📝
بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإثيوبي السلطي حفظه الله

📝 አዘጋጅ፦ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf  አውርዳችሁ አንብቡት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty

قد أجاد الشيخ الدكتور حسين ـ حفظه الله ـ وأفاد في ردّه على الشيخ محمد حامي الدين، فقد كتب رسالةً قيمةً نفيسةً، نافعةً لمن أيقظه الله تعالى من نوم الغفلة والهوى والتعصب والتقليد الأعمى، وأراد الحقَّ والإنصاف.
فجزى الله الشيخ خير الجزاء، وبارك في علمه وعمله، ونفع بجهوده، وزاده الله تعالى علمًا وبصيرةً وثباتًا على الحق والسنة.
✍🏻الشيخ محمد حيات الولوي حفظه الله
قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
Photo
🔷 ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ብን ሙሐመድ አስስልጢ - ሐፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :-

እወቅ - አሏህ ይምራህ :

"የፈጠራና የዝንባሌ ባለቤቶች የርዕዮተ አለም አራማጆቻቸውና የታላላቅ መሪዎቻቸውን የፈጠራና የሸሪዓ ጥሰቶች እንደቀላል ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ።

ታይቶ በቀላል የሚታለፍ - ማግለልን ፣ መተውን እና ከዚያ ነገር መራቅን የማያስከትል ተራ ስህተት አድርገው ይቆጥሩታል።

ሰይድ ቁጥብ ከኢስላም ከሚያስወጡ የሸሪዓ ጥሰቶችና በርካታ ፈጠራዎች ላይ የወደቀ ግለሰብ ነው። 

ይህ ከመሆኑ ጋር ቁጥብዮች ፣ ኢኽዋኖችና ሌሎች አንጃዎች እነዚህን ጥሰቶች  በከፍተኛ ደግነት እና ገርነት ሲያስተናግዷት ትመለከታለህ።

ለሰይድ ቁጥብ ቀዝቃዛ ይቅርታ ሲጠይቁ ፤ (እርሱን ለማዳን) ማንኛውንም አይነት ሰበብ ሲፈልጉ ፣ ከእርሱ ላይ  ሲከላከሉና ማህበረሰቡ እርሱን እንዲከተል ፣ በእርሱ ጎዳና  እንዲጓዝ ሲቀሰቅሱ ታስተውላለህ።

ሰይድ ቁጥብ ለኢስላምና ለህዝቦቹ ከሚከላከሉ የተሀድሶ አራማጆች መካከል አንዱ አድርገው ይቆጥሩታል። በእርግጥም ፍቅር ያውራል ፣ ያደነዝዛል።

አሏህ እንዲህ ብሏል:-

أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

"ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አሏህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን ፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን!? ታዲያ ከአሏህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?"

(ጃሲያ :23)


في رسالته : الفصل المبين في دحض شبهات وتلبيسات محمد حامي الدين  ص ١

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة
📢 አስደሳች የኮርስ ዜና 📢
ከዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🗓 የፊታችን ጁምዐህ ከመስከረም 1 እስከ እሁድ መስከረም 3 የሚቆይ ልዩ የኮርስ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ጁምዐህ ከ8:00 ጀምሮ
እሁድ ዙሁር ተሰግዶ ያበቃል

ኮርስ ሰጪ መሻይኾችና የሚሰጡባቸው ርእሶች…

بعنوان:- خمسون نصيحة ووسائل الوقاية من الوقوع في الفتن وتجنب تمزيق الصف السلفي.
للشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله تعالى.
ርእስ:- በፊትና ላለመውደቅና የሠለፊዮችን አንድነት (ሰፍ) ከመበጣጠስ ለመጠበቅ የሚጠቅሙ አምሳ ምክሮች!!
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

بعنوان:- فضل العلم وآداب طلبه...
للشيخ طه بن خضر الجمي حفظه الله تعالى.
ርእስ:- የእውቀት ደረጃውና የመማር ስርኣቱ…
በሸይኽ ጧሃ ቢን ኸድር (ሀፊዘሁላህ)

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
በተጨማሪም +251920908031
ሎኬሽን ⤵️⤵️
https://maps.app.goo.gl/qsBKATgS8jqrJMxw9

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
📢 አስደሳች የኮርስ ዜና 📢 ከዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🗓 የፊታችን ጁምዐህ ከመስከረም 1 እስከ እሁድ መስከረም 3 የሚቆይ ልዩ የኮርስ ዝግጅት ተሰናድቷል 🕰 ሰዓት:- ጁምዐህ ከ8:00 ጀምሮ እሁድ ዙሁር ተሰግዶ ያበቃል ኮርስ ሰጪ መሻይኾችና የሚሰጡባቸው ርእሶች… بعنوان:- خمسون نصيحة ووسائل الوقاية من الوقوع في الفتن وتجنب تمزيق الصف السلفي.…
خمسون نصيحة لطلاب العلم تعاونا على البر والتقوى وتواصيا بالحق والصبر والمرحمة . ففيها الحث على الاقتداء بالسلف عقيدة وسلوكا  والعمل بمقتضى العلم الشرعي الموروث عن النبي صلى الله عليه وسلم وفيها التحذير من الوقوع في البدع والفتن وفيها التنبيه على ما يشوه ويمزق صفوف السلفيين ويضر تآلفهم وتكاتفهم وتعاطفهم.  والله الموفق
✍الشيخ الدكتور حسين بن محمد حفظه الله
Live stream started
ሰይድ ቁጥብ እና መፅሀፉ
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
♦️| የዑለማዎች ገለፃ ስለ ሰይድ ቁጥብ እና መፀሀፉ

— ክፍል አንድ (1)

«
ቀደም ሲል ተቀርቶ ከተጠናቀቀው የ አጅዊበቱል ሙፊደህ ደርስ ቀጥር 𝟏𝟓 የተቀነጨበ »

🎙ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

|| የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
ሺዐቱ ሸይጧን 31
በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
አዲስ                 👉 ይደመጥ!!
🔷 ልዩ ተከታታይ ኮርስ

ርእስ:- ሺዐቱ ሸይጧን!!
በታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) የተዘጋጀ
Pdf↘️↘️
https://t.me/IbnShifa/6377

⏯ ክፍል 31

🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ (ሀፊዘሁላህ)

ኮርሱ የሚሰጠው በ t.me/ibnshifa ቴሌግራም ቻናል ዘውትር እሮብና ሀሙስ ከምሽቱ:- 4:00 ጀምሮ ነው፣ በሰኣቱ ቀጥታ ተከታተሉ

#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
Live stream started