National ID Program - Ethiopia
✔
103K subscribers
927 photos
189 videos
406 links
Identity is the new collateral!
መታወቅ ለመተማመን።
የፋይዳ ቁጥር ለማግኘት ወደ *9779# ይደውሉ።
ሁሉን አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ከአፕ ስቶር (https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp) ወይም https://apps.apple.com/app/fayda-i) ያውርዱ።
Download Telegram
የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ መታወቅ ከልጅነት

በኦሮሚያ ክልል ሐረማያ ወረዳ በተካሄደ የመታወቂያ ምዝገባ ሱፐርቪዥን ወቅት የተወሰደ

@ICS_Ethiopia #ፋይዳለኢትዮጵያ
❤33🤩8👍2🔥2🤯1
Request for Expression of Interest: Finance Officer (Accountant)

The National ID Program invites qualified professionals to apply for the Finance Officer (Accountant) position in its Program Management Unit (PMU).

The role supports financial planning, reporting, payroll, reconciliations, and audit processes for Ethiopia’s Digital ID program.

Details to apply: https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00475679
❤25👏4👍3👌1
የቀሩት 20 ቀናት ብቻ ናቸው!

ወደ ባንክ ቤት በአካል መሄድ ሳይጠበቅብዎ ባሉበት ሆነው ፣ ወደ ድረ-ገጻችን id.et/connect በመግባት ብቻ የሁሉም ባንኮች ማስተሳሰሪያ ሊንኮች ያገኛሉ።

📅 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የባንክ ሂሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ።
❤26👍9🔥1
Partner Spotlight: @Addis_Bike

Making urban mobility smarter, simpler, and more accessible! Addis Bike is transforming urban mobility through convenient, technology-driven bike sharing. By integrating with Fayda, Addis Bike leverages digital identity to enable more efficient user verification and seamless service access, bringing greater trust and convenience to everyday mobility.

Driving Real Impact Together:
31,581+ registered users
100 eco-friendly bikes
14 strategic stations, starting in Bole Sub-City and Meskel Square, with plans to expand across Addis Ababa.

This partnership demonstrates how Fayda integration connects digital identity with everyday services, helping enterprises enhance user experiences and build a more connected digital ecosystem.

Integrate your system with Fayda and unlock smarter, more trusted digital services! ID.ET/API

#digitaltransformation
❤37👌3🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መታወቂያ ኮፒ ማድረግ ቀረ!

አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞቻችሁ ለማንነት ማረጋገጫ የሚያቀርቡትን የፋይዳ ካርድ ትክክለኛነት እንዴት እያረጋገጣችሁ ነው?

የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ትክክለኛ የግለሰቡ መሆኑን "FaydaPass" ሞባይል መተግበሪያን በማውረድ ኢንተርኔት ሳያስፈልግዎ "Offline" ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ማረጋገጥ ይችላሉ።

ፋይዳፓስ ለአንድሮይድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp

ፋይዳፓስ ለአይፎን (iOS)፦
https://apps.apple.com/app/id6740314990

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤49👍16👏3
Forwarded from FaydaPass Wallet
140,000 Credentials in 2 Months!

With FaydaPass, managing your digital ID credentials and other service credentials has never been easier.

Get access to your Fayda ID, scan and verify #Fayda card, order card print, update demographic data, and take full control of other verified service credentials all from one convenient app.

Download FaydaPass NOW:

FaydaPass Android፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp

FaydaPass iOS ፦
https://apps.apple.com/app/id6740314990
❤37❤‍🔥5👍3👏1🤔1🤯1
የልደት ቀን በምዝገባ ወቅት ከተሳሳተ ለማስተካከል ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?

በድረገጽ id.et/update ወይም በአካል በምዝገባ ጣቢያዎች መረጃዎን ማስተካከል ሲፈልጉ እነዚህን ዋና ዋና ነጥቦች ያስተውሉ።

❓ማሻሻያ ወይስ እርማት❓

📌 ማሻሻያ (በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚከናወን)፦ በልደት ምስክር ወረቀት፣ ፓስፖርት ወይም ቀበሌ መታወቂያ ካለው የተለየ አዲስ ሕጋዊ ዕድሜ (የትውልድ ቀን) ማስመዝገብ ሲፈልጉ።

📌 እርማት (በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት የሚከናወን)፦ የፋይዳ መረጃዎ ከማንነት ማረጋገጫ ሰነድዎ ወይም ከፈቃደኝነት ቅጽ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ወይም የተሳሳተ/የተለየ የትውልድ ዘመን ሲይዝ የሚደረግ ማስተካከያ ነው።

📌 ልብ ይበሉ፦ የፍርድ ቤት አቤቱታ ሲያቀርቡ እንደ “የፋይዳ ስህተት” ያሉ አገላለጾችን አለመጠቀም እና ፋይዳን በማስረጃ ዝርዝር ውስጥ አለማካተት

📌 ያስተውሉ፡ ትክክለኛ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቀረበ ማመልከቻ ተቀባይነት ስለማይኖረው ማመልከቻው ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።

📌 ለልደት ቀን ማሻሻያ ወይም እርማት በሚጠይቁበት ጊዜ ማቅረብ ስለሚገባዎ እና ማድረግ ስለሚጠበቅብዎት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረገጻችንን፡ id.et/resources ይመልከቱ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤36👍14👌6🔥3
Ethiopia’s digital finance ecosystem is experiencing rapid growth, driven largely by the Fayda digital ID. By streamlining eKYC and secure banking access, Fayda has facilitated over $148 billion in digital transactions in just nine months.

Read this Biometric Update article to learn how foundational digital identity is expanding financial inclusion and advancing the 2030 Digital Ethiopia strategy: https://www.biometricupdate.com/202610/fayda-national-id-helps-drive-ethiopias-digital-finance-ecosystem
❤22
በፋይዳ ምዝገባ ወቅት ስምዎ ተሳስቷል ወይስ ከምዝገባ በኋላ ስም መቀየር ፈልገዋል? የፍርድ ቤት ውሳኔ የሚጠይቁት የትኞቹ ጉዳዮች ናቸው?

1️⃣ ማስተካከያ (በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም)
ሰነድዎና የፈቃደኝነት ቅጽዎ ትክክል ሆነው በሂደት ላይ ስህተት ሲፈጠር፦
• የምዝገባ ባለሙያ ስህተት፦ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ያመልክቱ።
• ትርጉም የማይቀይር የአጻጻፍ ስህተት፦ ትክክለኛውን አጻጻፍ የሚያረጋግጥ ሰነድ (የልደት ምስክር ወረቀት፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው) በማቅረብ ይስተካከላል።

2️⃣ ለውጥ (በፍርድ ቤት ውሳኔ)
• ከቀደመው የተለየ ስም ማስመዝገብ ሲፈልጉ
• ከምዝገባ በኋላ ስምዎን፣ የአባት ወይም የአያት ስምዎን ሲቀይሩ
የሚያስፈልግ ማስረጃ፦ የፍርድ ቤት የስም ለውጥ ውሳኔና ትዕዛዝ

📌 ያስተውሉ
• አቤቱታዎ “በፋይዳ ላይ ስሜ በስህተት ተመዝግቧል” ሳይሆን “የስም ለውጥ ጥያቄ አቀርባለሁ” የሚል መሆን አለበት።
• የአባትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ብቻውን የአባት ወይም የአያት ስም ለመቀየር በቂ አይደለም።
• የጉዲፈቻ ውሳኔ ስም የሚያስቀይረው ውሉ አዲሱን ስም ገልጾ በፍርድ ቤት ከጸደቀ ብቻ ነው።

❌ ሆን ብሎ ሀሰተኛ ስም ማስመዝገብ በወንጀል ያስጠይቃል።

ለበለጠ መረጃ፦ id.et/resources
❤46🙏6👏4👍1
የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ መንዝ ማማ ወረዳ የተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤31👏15🔥2
ነገ ከቀኑ 10፡00 በቲክቶክ ላይቭ እንገኛኝ!

በተደጋጋሚ በአስተያየት መስጫ እና በውስጥ መስመር ለምትጠይቁን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 24፣ 2019 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በቲክቶክ ላይቭ እንገናኝ፡

✅ ይፋዊ የቲክቶክ ቻናላችንን tiktok.com/@idethiopia ይከተሉ።

ጥያቄዎን ይዘው ነገ ይጠብቁን!

#ፋይዳለኢትዮጵያ
👍33❤28👏8
Live stream finished (1 minute)
Live stream finished (11 minutes)
Forwarded from telebirr
ደረጃዎን በፋይዳ ያሳድጉ!

የቴሌብር አካውንትዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ በማስተሳሰር ደረጃዎን ያሳድጉ።

ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ደረጃችን ከፍ ሲል እንዲህ ነን!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
❤9🤔2🤩2
ጥቅምት 30 ደረሰ!

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የማስተሳሰር ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ብቻ ቀሩት።

እርስዎ ወይም ወዳጅዎ የባንክ ሂሳብ ከፋይዳ ጋር እስካሁን ካላስተሳሰሩ በቀላሉ በዲጂታል አማራጭ id.et/connect ላይ ይግቡ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ያስተሳስሩ ፤ አዳዲስ አገልግሎቶች እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ። ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት በማስተሳሰር የባንክ ሂሳብዎ ከወጪ እንቅስቃሴ እንዳይታደግ ማድረግ ይችላሉ።

ያስተውሉ፡ ቀነ-ገደቡ በመጠናቀቁ የባንክ ሂሳብዎ ወጪ ማድረግ ከተከለከለ፣ ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር እንዳስተሳሰሩ ወዲያውኑ የሚስተካከል ይሆናል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤12
በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት፦ የመረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» ልዩነታቸውን ያውቃሉ?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ ሙሉ ስምዎ (የእርስዎ፣ የአባትዎ እና የአያትዎ ስም) እና የትውልድ ዘመንዎ ተቀባይነት ካላቸው ሰነዶች (እንደ ነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ) ጋር ተመሳሳይነቱ ተረጋግጦ ይመዘገባል።

ሆኖም ከተመዘገቡ በኋላ መረጃዎን ማረም ወይም ማሻሻል ሊያስፈልግዎ ይችላል። ታዲያ ልዩነታቸው ምንድነው?

1. የመረጃ እርማት (Correction)
በምዝገባ ወቅት የተፈጠረ የፊደል ግድፈት፣ የፊደላት መለዋወጥ ወይም የመዝጋቢ ባለሙያ ስህተትን በማስተካከል መረጃዎን ካቀረቡት ሰነድ ጋር ማጣጣም ነው።
ምሳሌ፦ በስህተት የተጻፈን ስም በትክክለኛ ፊደላት ማስተካከል (የስም ለውጥ የማይኖረው ከሆነ ብቻ)

2. የመረጃ ማሻሻያ (Update)
ቀድሞ የተመዘገበን መረጃ በአዲስ ማስተካከል ወይም መተካት ማለት ነው። ይህ ሂደት ለምሳሌ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የስም ለውጥ ማድረግን፣ እንዲሁም ከቀረበው የልደት፣ የፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ ላይ የተለየ የትውልድ ዘመን ወይንም አድራሻን ቀይሮ ማስመዝገብን ያጠቃልላል።

ምሳሌ፦ በምዝገባ ወቅት የነበረው ስልክ ቁጥር የሌላ ሰው ከነበረ ወይም በአዲስ ስልክ ቁጥር መለወጥ ስያስፈልግ

📌 ጠቃሚ ማስታወሻዎች፦
• የመረጃ እርማት እንዲሁም ማሻሻያ በድረገጽ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በቀላሉ መጠየቅ ይችላሉ።
• አንዳንድ መረጃ ማሻሻል ሲፈልጉ እንደ ስም እና የልደት ቀን ለውጥ ሲኖር የፍርድ ቤት ውሳኔ እና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ይዘው መቅረብ ያስፈልጋል። የበለጠ መረጃ id.et/resources ላይ ያገኛሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤38👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአንድ ስልክ ቁጥር ከአንድ በላይ ሰው ተመዝግበው የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ ተቸግረዋል?

ወደ *9779# ሲደውሉ የአንደኛው ሰው የፋይዳ ቁጥር ብቻ እየመጣብዎት ከሆነ በቀላሉ:

1. ወደ ቴሌግራም ቦት @FaydaHelpBot ይግቡ።
2. ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ "የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ" የሚለውን ይምረጡ።
3. ባለ 29 አኃዝ የምዝገባ ቁጥርዎን (በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) የደረሰዎትን ወይም በምዝገባ ወቅት የተሰጥዎትን ወረቀት ላይ ያለውን) በጥንቃቄ ያስገቡ።

በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የፋይዳ ቁጥርዎ በስልክዎ ይደርስዎታል!
❤23👍7🤩1
የፋይዳ ቁጥርዎ አልደረሰዎትም? ወይስ በምዝገባ ወቅት መረጃዎ ተሳስቶ ደግመው ለመመዝገብ እያሰቡ ነው?

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበው ሲስተሙ ማንነትን በልዩ ሁኔታ አጣርቶ ሲጨርስ ከጥቂት ሰዓታት እስከ ተወሰኑ የስራ ቀናት ውስጥ የፋይዳ ቁጥር በተመዘገቡበት ስልክ ቁጥር እና በተጨማሪም በኢሜይል አድራሻ ይደርስዎታል።

በተጠቀሰው ጊዜ ካልደረስዎ ግን ደግመው መመዝገብ ሳይሆን እነዚህም አማራጮች ተጠቅመው የፋይዳ ቁጥርዎን ማስላክ ወይም ያለበትን ደረጃ ማጣራት ይኖርብዎታል።

📌 ወደ *9779# በመደወል በራስዎ ማስላክ
📌 በፋይዳ ቴሌግራም ቦት t.me/FaydaHelpBot መጠቀም
📌 የፋይዳ ፓስ (Fayda Pass) መተግበሪያን በመጠቀም ማስላክ (አንድሮይድ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
አይ ኦ ኤስ ፡ https://apps.apple.com/app/id6740314990)

በምዝገባ ወቅት መረጃዎ ቢሳሳት ወይም ቀድመው የሰጡትን መረጃ ማሻሻል ቢያስፈልግ ደግመው መመዝገብ አያስፈልግማ። id.et/update ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ወይም በአካል ወደ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ማስተካከል ይችላሉ።

‼️ በድጋሚ መመዝገብ የሚያስፈልገው ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም “ደግመው ይመዝገቡ” የሚል አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሲመዘገቡ ባስገቡት ስልክ ቁጥር ሲደርስ ብቻ ነው።
❤18👍4