National ID Program - Ethiopia
✔
103K subscribers
929 photos
191 videos
409 links
Identity is the new collateral!
መታወቅ ለመተማመን።
የፋይዳ ቁጥር ለማግኘት ወደ *9779# ይደውሉ።
ሁሉን አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ከአፕ ስቶር (https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp) ወይም https://apps.apple.com/app/fayda-i) ያውርዱ።
Download Telegram
Live stream finished (11 minutes)
Forwarded from telebirr
ደረጃዎን በፋይዳ ያሳድጉ!

የቴሌብር አካውንትዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ በማስተሳሰር ደረጃዎን ያሳድጉ።

ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ደረጃችን ከፍ ሲል እንዲህ ነን!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
❤12🤔2🤩2
ጥቅምት 30 ደረሰ!

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የማስተሳሰር ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ብቻ ቀሩት።

እርስዎ ወይም ወዳጅዎ የባንክ ሂሳብ ከፋይዳ ጋር እስካሁን ካላስተሳሰሩ በቀላሉ በዲጂታል አማራጭ id.et/connect ላይ ይግቡ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ያስተሳስሩ ፤ አዳዲስ አገልግሎቶች እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ። ከተጠቀሰው ጊዜ በፊት በማስተሳሰር የባንክ ሂሳብዎ ከወጪ እንቅስቃሴ እንዳይታደግ ማድረግ ይችላሉ።

ያስተውሉ፡ ቀነ-ገደቡ በመጠናቀቁ የባንክ ሂሳብዎ ወጪ ማድረግ ከተከለከለ፣ ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር እንዳስተሳሰሩ ወዲያውኑ የሚስተካከል ይሆናል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤16
በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት፦ የመረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» ልዩነታቸውን ያውቃሉ?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ ሙሉ ስምዎ (የእርስዎ፣ የአባትዎ እና የአያትዎ ስም) እና የትውልድ ዘመንዎ ተቀባይነት ካላቸው ሰነዶች (እንደ ነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ) ጋር ተመሳሳይነቱ ተረጋግጦ ይመዘገባል።

ሆኖም ከተመዘገቡ በኋላ መረጃዎን ማረም ወይም ማሻሻል ሊያስፈልግዎ ይችላል። ታዲያ ልዩነታቸው ምንድነው?

1. የመረጃ እርማት (Correction)
በምዝገባ ወቅት የተፈጠረ የፊደል ግድፈት፣ የፊደላት መለዋወጥ ወይም የመዝጋቢ ባለሙያ ስህተትን በማስተካከል መረጃዎን ካቀረቡት ሰነድ ጋር ማጣጣም ነው።
ምሳሌ፦ በስህተት የተጻፈን ስም በትክክለኛ ፊደላት ማስተካከል (የስም ለውጥ የማይኖረው ከሆነ ብቻ)

2. የመረጃ ማሻሻያ (Update)
ቀድሞ የተመዘገበን መረጃ በአዲስ ማስተካከል ወይም መተካት ማለት ነው። ይህ ሂደት ለምሳሌ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የስም ለውጥ ማድረግን፣ እንዲሁም ከቀረበው የልደት፣ የፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ሰነድ ላይ የተለየ የትውልድ ዘመን ወይንም አድራሻን ቀይሮ ማስመዝገብን ያጠቃልላል።

ምሳሌ፦ በምዝገባ ወቅት የነበረው ስልክ ቁጥር የሌላ ሰው ከነበረ ወይም በአዲስ ስልክ ቁጥር መለወጥ ስያስፈልግ

📌 ጠቃሚ ማስታወሻዎች፦
• የመረጃ እርማት እንዲሁም ማሻሻያ በድረገጽ id.et/update ላይ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በቀላሉ መጠየቅ ይችላሉ።
• አንዳንድ መረጃ ማሻሻል ሲፈልጉ እንደ ስም እና የልደት ቀን ለውጥ ሲኖር የፍርድ ቤት ውሳኔ እና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ይዘው መቅረብ ያስፈልጋል። የበለጠ መረጃ id.et/resources ላይ ያገኛሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤44👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአንድ ስልክ ቁጥር ከአንድ በላይ ሰው ተመዝግበው የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ ተቸግረዋል?

ወደ *9779# ሲደውሉ የአንደኛው ሰው የፋይዳ ቁጥር ብቻ እየመጣብዎት ከሆነ በቀላሉ:

1. ወደ ቴሌግራም ቦት @FaydaHelpBot ይግቡ።
2. ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ "የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ" የሚለውን ይምረጡ።
3. ባለ 29 አኃዝ የምዝገባ ቁጥርዎን (በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) የደረሰዎትን ወይም በምዝገባ ወቅት የተሰጥዎትን ወረቀት ላይ ያለውን) በጥንቃቄ ያስገቡ።

በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የፋይዳ ቁጥርዎ በስልክዎ ይደርስዎታል!
❤29👍11🤩3
የፋይዳ ቁጥርዎ አልደረሰዎትም? ወይስ በምዝገባ ወቅት መረጃዎ ተሳስቶ ደግመው ለመመዝገብ እያሰቡ ነው?

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበው ሲስተሙ ማንነትን በልዩ ሁኔታ አጣርቶ ሲጨርስ ከጥቂት ሰዓታት እስከ ተወሰኑ የስራ ቀናት ውስጥ የፋይዳ ቁጥር በተመዘገቡበት ስልክ ቁጥር እና በተጨማሪም በኢሜይል አድራሻ ይደርስዎታል።

በተጠቀሰው ጊዜ ካልደረስዎ ግን ደግመው መመዝገብ ሳይሆን እነዚህም አማራጮች ተጠቅመው የፋይዳ ቁጥርዎን ማስላክ ወይም ያለበትን ደረጃ ማጣራት ይኖርብዎታል።

📌 ወደ *9779# በመደወል በራስዎ ማስላክ
📌 በፋይዳ ቴሌግራም ቦት t.me/FaydaHelpBot መጠቀም
📌 የፋይዳ ፓስ (Fayda Pass) መተግበሪያን በመጠቀም ማስላክ (አንድሮይድ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
አይ ኦ ኤስ ፡ https://apps.apple.com/app/id6740314990)

በምዝገባ ወቅት መረጃዎ ቢሳሳት ወይም ቀድመው የሰጡትን መረጃ ማሻሻል ቢያስፈልግ ደግመው መመዝገብ አያስፈልግማ። id.et/update ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ወይም በአካል ወደ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ ማስተካከል ይችላሉ።

‼️ በድጋሚ መመዝገብ የሚያስፈልገው ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም “ደግመው ይመዝገቡ” የሚል አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሲመዘገቡ ባስገቡት ስልክ ቁጥር ሲደርስ ብቻ ነው።
❤34👍8👌2
የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ በአማራ ክልል፣ ባህር ዳር ከተማ የተማሪዎች ምዝገባ

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤22👍9🔥2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፋይዳ ከሰሞኑ: ዋና ዋና ክንውኖች በምስል

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ |  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ብሉስካይ | ዋትስአፕ | ኢንስታግራም
❤13👍8👌4
ለፋይዳ መታወቂያ ሲመዘገቡ የራስዎ ስልክ ቁጥር አልነበረዎትም? ወይስ በምዝገባ ወቅት ያስገቡት ስልክ ቁጥር ተሳስቷል?

እነዚህን ለማስተካከል ከሚከተሉት ትክክለኛ አማራጮች መካከል ይጠቀሙ ፡

1. ለፋይዳ ሲመዘገቡ በሌላ ሰው ስልክ ቁጥር ተመዝገበው ከነበረ እና አሁን ወደ ራስዎ ስልክ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ ድረገፅ id.et/update ላይ በመግባት በአካል መሄድ ሳያስፈልግዎ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በመሔድ መቀየር ይችላሉ። (ያስተውሉ፡ በዚህ ሂደት ወደ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል ወይም OTP ነባሩም አዲሱም ስልክ ስለሚላክ ሁለቱም ስልክ በእጅዎ ሊሆን ይገባል)

2. እንዲሁም በምዝገባ ወቅት የራስዎ ስልክ ቁጥር ሲሞላ የቁጥር ስህተት ካጋጠሞት ወይም ደግሞ ስልክ ቁጥሩ ከጠፋብዎ በአቅራቢያ በሚያገኟቸው የምዝገባ ጣቢያዎች በአካል በመሄድ መቀየር ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤26👍12🤯2🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዴሞግራፊክ መረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ያውቃሉ?

የመረጃ እርማት ወይም ለውጥ ሲያስፈልግዎ፣ በድረ-ገጻችን id.et/update በመግባት የትኞቹን መረጃዎች በቀላሉ ማስተካከል እንደሚችሉ እና የትኞቹ ደግሞ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያስፈልጋቸው ግራ ከተጋቡ ይህንን ቪዲዮ እስከ መጨረሻው ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ id.et/resources ይጎብኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ
❤16👍2