ሊያና ኬር Liyana Care 7755
5.74K subscribers
327 photos
4 videos
1 file
213 links
➮ የጤና ምክሮች 👨‍⚕️
➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755
➮ ቴሌሜዲስን 💉
➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲
Download Telegram
🚨 የማርበርግ ቫይረስ (MVD)

🦠 መርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከስት የደም መፍሰስ እና ትኩሣት ህመም (hemorrhagic fever)ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንሰሳት ላያ ይከሰታል

⚠️ ምልክቶች

👉ከአፍ፣ከአፍንጫ፣ወይም ከቆዳ ስር የደም መፍሰስ ።
👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት።
👉የጡቻ እና የጀርባ ህመም ።
👉ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ።
👉ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ ጐልቶ የሚታየይ ሽፍታ ።

‼️የመተላለፊያ መንገዶች

👉ከበሽተኛው ደም፣ ሽንት፣እንባ እና ሌሎች ፈሣሾች ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ።

👉በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሣሽ የተበከሉ ቁሶች ፣እንደ ልብስ ፣አልጋ ልብስ ፣መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚኖር ንክኪ።

👉በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የለሊት ወፎች ውድ ሰዎች ይተላለፋል።

🛡 የመከላከያ መንገዶች

🔘ከታመመ ሰው ደም እና ፈሣሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ።
🔘ለይቶ ማቆየት (Isolate)፦ የቫይረሱ ምልክት ያለባቸውን ሰዎች በፍጥነት ለይቶ ማቆየት።
🔘ንጽህና፦ እጅን አዘውትሮ መታጠብ እና የመከላከያ ዩኒፎርም (PPE-ማስክና ጓንት) መጠቀም።
🔘ደህንነቱ የተጠበቀ ቀብር፦ በቫይረሱ የሞተን ሰው አስከሬን በባዶ እጅ አለመንካት፤ በሰለጠኑ ባለሙያዎች ብቻ እንዲቀበር ማድረግ።

💊 ሕክምና

❇️ድጋፍ ሰጪ ሕክምና፦ በሰውነት ውስጥ የጠፋውን ፈሳሽ መተካት (Rehydration) እና ምልክቶችን ማስታገስ።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
😴 የእንቅልፍ ማጣት (Insomnia)
የእንቅልፍ ማጣት (Insomnia) ችግር ቢያንስ ለሶስት ወራት ያህል በሳምንት ሦስት ሌሊት ወይም ከዚያ በላይ የሚከሰት፣ ዘላቂ የሆነ የእንቅልፍ መታወክ ነው።

⚠️ 3ቱ ዋና ዋና ምልክቶች (ቢያንስ ለ3 ወራት የሚቆዩ):
✔️ለመተኛት መቸገር (ከ30 ደቂቃ በላይ መውሰድ)
✔️ሌሊት ከእንቅልፍ መንቃት እና መልሶ ለመተኛት መቸገር:- ይህም በተደጋጋሚ መንቃት ወይም ከእንቅልፍ ከተነሱ በኋላ ወደ እንቅልፍ ለመመለስ ችግር መኖሩን ያመለክታል
✔️ጠዋት ቀድሞ መንቃት እና ወደ እንቅልፍ መመለስ አለመቻል (መቸገር) እና የእለት ተእለትተግባራት በማከናወን ላይ ድካም መሰማት

💊ሕክምና (Treatment)
የንግግር ሕክምና (Psychotherapy)
መድሃኒት (Medication)

🚫የእንቅልፍ ማጣት ችግርዎ ከወራት በላይ ከቆየ እና የዕለት ተዕለት ኑሮዎን እየነካ ከሆነ፣ የባለሙያ ድጋፍ (ሐኪም ወይም የሥነ-ልቦና ባለሙያ) ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🩸 ስለ ደም ማነስ (Anemia)🩸

ደም ማነስ ማለት ሰውነታችን በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎች (Red Blood Cells) ወይም በውስጣቸው የሚገኘው ኦክስጅን ተሸካሚው ሂሞግሎቢን (Hemoglobin) መጠን ሲቀንስ የሚከሰት የጤና ችግር ነው።


❓ ዋና ዋና ምልክቶች
👉ድካም
👉የገረጣ ቆዳ (Pale Skin)
👉የትንፋሽ ማጠር (Shortness of Breath)
👉የልብ ምት መጨመር
👉ራስ ምታት እና ማዞር
👉የእጅና እግር ቅዝቃዜ

🛡️ ዋና ዋናዎቹ የደም ማነስ አይነቶች

👉የብረት እጥረት ደም ማነስ (Iron-Deficiency Anemia):
👉የቫይታሚን እጥረት ደም ማነስ (Vitamin-Deficiency Anemia):
👉የደም መፍሰስ (Anemia due to Blood Loss)
👉ሥር የሰደደ በሽታ ደም ማነስ (Anemia of Chronic Disease)

✅ መፍትሔው
👉ምልክቶቹን ካዩ፣ ሐኪም ማማከር
👉የደም ምርመራ
👉የአመጋገብ ለውጥ
👉ማሟያ (Supplements): በሀኪም ትዕዛዝ የብረት ወይም የቫይታሚን ክኒኖችን መውሰድ።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
😴 ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ (Hypersomnolence Disorder)

💤በቂ እንቅልፍ (ከ7 ሰዓት በላይ) ቢተኛም ቀኑን ሙሉ ከፍተኛ እንቅልፍ እና ድካም የሚታይበት የእንቅልፍ መታወክ ነው።

ዋና ዋና ምልክቶች (Key Symptoms)

🥱የቀን እንቅልፍ: በቀን ውስጥ ተደጋጋሚ እንቅልፍ መውሰድ ወይም ማንቀላፋት።
😴የረጅም ጊዜ እንቅልፍ: በአንድ ሌሊት ከ9 ሰዓት በላይ መተኛት እና እንቅልፍ ሳይጠግቡ መነሳት።
🛌የእንቅልፍ ስንፈት (Sleep Inertia): ከእንቅልፍ ከተነሱ በኋላ ወዲያውኑ ሙሉ በሙሉ መንቃት መቸገር ወይም ዝለት መስማት።

የሕክምና  (Treatment)

✔️የንግግር ሕክምና (Psychotherapy)
✔️መድሃኒት (Medication)
የሚያነቃቁ መድሃኒቶች (Stimulants): ብዙውን ጊዜ በቀን ውስጥ ንቁ         ሆነው ለመቆየት የሚያግዙ መድሃኒቶች በሀኪም ትዕዛዝ ሊሰጡ ይችላሉ።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
✨የማህፀን ዕጢዎች (fibroids )✨

የማህፀን ፋይብሮይድስ በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚበቅሉ ካንሰር ያልሆኑ (Benign) ዕጢዎች ናቸው። መጠናቸው ከጥቃቅን ዘር
እስከ ትልቅ ኳስ ሊለያይ ይችላል።

⚡️ የአደጋ መንስኤዎች (Risk Factors)
👉ዘር (Race)
👉 በልጅ የመውለድ ዕድሜ (Reproductive Age) ውስጥ መሆን።
👉እናት ወይም እህት ፋይብሮይድስ ካለባቸው።
👉 ከመጠን ያለፈ ውፍረት።

⚠️ ምልክቶች
👉ከባድ የወር አበባ
👉 የዳሌ ህመም
👉ተደጋጋሚ ሽንት
👉የሆድ ድርቀት
👉መካንነት (Infertility) ወይም የፅንስ መቋረጥ

💊 ሕክምና
👉 የመድሃኒት ሕክምና
👉ቀዶ ጥገና
👉 ሌሎች አማራጮች (Uterine Fibroid Embolization)
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
📦📚🏠ሆርዲንግ ዲስኦርደር (Hoarding Disorder)

ይህ  አንድ ሰው ምንም ጥቅም የሌላቸውን ወይም ሌሎች እንደማይረቡ የሚቆጥሯቸውን ነገሮች ከመጠን በላይ የመሰብሰብ እና ለማስወገድ (ለመጣል) ከፍተኛ ጭንቀት የሚሰማበት የአእምሮ ጤና ሁኔታ ነው።

ይህ ሁኔታ ከጊዜ ብዛት ቤትን ወይም የመኖሪያ አካባቢን ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ እስከማድረግ ይደርሳል።

⏺️ምልክቶች

🧮ዋነኛው መለያ ምልክት ዕቃዎችን የማስቀመጥ ከፍተኛ ፍላጎት (ምንም ዋጋ ባይኖራቸውም) እና እነዛን ዕቃዎች ለመጣል ወይም ለማስወገድ በሚሞከርበት ጊዜ የሚሰማ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ስቃይ/ጭንቀት ነው።

➡️ነገሮችን መጣል አለመቻል
➡️ከመጠን በላይ ማከማቸት
➡️የመጣል ፍርሃት
➡️ውሳኔ የመስጠት ችግር
➡️ሰዎች ወደ ቤት እንዳይመጡ መከልከል ወይም ማፈር።

⏺️ህክምናው
➡️የንግግር ህክምና
➡️የመድኃኒት ህክምና
➡️የቤተሰብ ድጋፍ
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🦵 ቫሪኮስ ቬን(Varicose Veins)

🔍 የደም ስር መሸበሸብ የሚከሰተው ደም ወደ ልብ እንዲመለስ የሚረዱት ትናንሽ ቫልቮች (Valves) ስራቸውን በትክክል ሳይወጡ ሲቀሩ ነው። በዚህም ምክንያት ደም ወደ ታች በመመለስ በደም ስሮቹ ውስጥ ይከማቻል፤ ይህም ስሮቹ እንዲያብጡና እንዲጠለፍለፉ ያደርጋቸዋል።

⚠️ ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች
👉እድሜ
👉ጾታ
👉ዘር (Genetics)
👉ከመጠን በላይ ውፍረት
👉 ለረጅም ሰዓት መቆም ወይም መቀመጥ

🚩 ምልክቶች
👉በእግር ላይ የሚታዩ ወይንጠጅ ወይም ሰማያዊ ያበጡ የደም ስሮች።
👉የእግር መክበድ
👉እግር ላይ የሚሰማ የማቃጠል፣ የመውረር ወይም የጡንቻ መኮማተር ስሜት።
👉ከረጅም ሰዓት ቆይታ በኋላ የሚከሰት የህመም ስሜት መጨመር።
👉በደም ስሮቹ አካባቢ የሚያሳክክ ስሜት

💊 የሕክምና
እንደ ህመሙ ደረጃ የተለያዩ መፍትሄዎች አሉ፦
👉የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ
👉 እግርን ከፍ አድርጎ መተኛት
👉 የመጭመቂያ ካልሲዎች (Compression Stockings)
👉 የሕክምና ሂደቶች፦ ህመሙ ከባድ ከሆነ እንደ Sclerotherapy (መርፌ) ወይም የሌዘር (Laser) ሕክምና በሃኪም ትዕዛዝ ሊከናወን ይችላል።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
📍ትሪኮቲሎሜኒያ (Trichotillomania)

ትሪኮቲሎሜኒያ  አንድ ሰው የራሱን ፀጉር (ከራስ ቅል፣ ከቅንድብ ወይም ከሽፋሽፍት) የመንጨት ከፍተኛ ፍላጎትና ድርጊቱን መቆጣጠር የማይችልበት የአእምሮ ጤና ሁኔታ ነው።

🔍 ምልክቶቹ
👉🏾በተደጋጋሚ ፀጉርን ነጭቶ በማውጣት በራስ ላይ የታወቀ መሳሳት   ወይም መመለጥ መፍጠር።
👉🏾ከመንጨቱ በፊት ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ውስጥ መሆን፤ ከነጩ በኋላ ደግሞ ጊዜያዊ እርካታ ወይም እፎይታ ያገኛሉ።
👉🏾ፀጉርን መጠቅለል፣ በእጅ ማሸት ወይም የተነጨውን ፀጉር መብላት (Trichophagia)
👉🏾በመመለጡ ምክንያት ማፈር፣ ቦታውን ለመደበቅ መሞከርና ከሰዎች መራቅ

⚠️ መንስኤዎቹ
👉🏾ከፍተኛ ጭንቀት ፣ ስትረስ፣ ድባቴ ወይም የቤተሰብ ግጭት
👉🏾በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ያለበት ሰው ካለ

💊 ህክምና
👉🏾የንግግር ህክምና (Therapy)
👉🏾የመድሃኒት ህክምና
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
👶 የህፃናት ሆድ ቁርጠት (Infantile Colic)

✨ አንድ ጤናማ ህፃን በቀን ከ3 ሰዓት በላይ፣ በሳምንት 3 ቀን እና ከዚያ በላይ ያለምንም የታወቀ ምክንያት ሲያለቅስ ማለት ነው።✨

ተጋላጭነት (Risk Factors):
👉የእናቶች በእርግዝና ወቅት ሲጋራ ማጨስ።
👉የህፃኑ የምግብ መፈጨት ሥርዓት አለመብሰል።

⚡️መንስኤ
👉የሆድ ጋዝ ወይም የምግብ አለመስማማት።
👉በዙሪያቸው ባሉ ድምፆችና ብርሃኖች መረበሽ።
👉የአንጀት ባክቴሪያ አለመመጣጠን።

⚠️ምልክቶች
👉እንደ ህመም የሚሰማ ከፍተኛ ለቅሶ።
👉እጅን መጨበጥ እና እግርን ወደ ሆድ መጠቅለል።
👉የሆድ መነፋት

✅መፍትሄዎች
👉ማባበል
👉 የህፃኑን እግር እንደ ብስክሌት በማንቀሳቀስ ጋዝ እንዲወጣ መርዳት።
👉የአመጋገብ ለውጥ
👉ረጋ ያሉ ድምፆችን መጠቀም።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
"በርን አውት" (Burnout)📛🫩

"በርን አውት" (Burnout) ከከፍተኛ እና ለረጅም ጊዜ ከቆየ ስትረስ የተነሳ የሚመጣ የስሜት፣ የአካል እና የአእምሮ ዝለት (መዛል) ነው።😒

ይህ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው የምንሰራው ስራ ከአቅማችን በላይ ሲሆን፣ እረፍት ስናጣ ወይም ለሰራነው ስራ ተገቢው እውቅና ሳይሰጠን ሲቀር ነው።😒

⚠️ምልክቶቹ
አካላዊ ምልክቶች፡
👉🏾ሁልጊዜ የድካም ስሜት መሰማት (በቂ እንቅልፍ ቢተኙም እንኳ)
👉🏾ተደጋጋሚ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም
👉🏾የምግብ ፍላጎት መቀየር ወይም የእንቅልፍ መዛባት
👉🏾የመከላከል አቅም መቀነስ (ቶሎ በበሽታ መጠቃት)
ስሜታዊ ምልክቶች
👉🏾ተስፋ መቁረጥ እና የባዶነት ስሜት
👉🏾ለስራ የነበረን ፍላጎት እና ተነሳሽነት ማጣት
👉🏾ቶሎ ቶሎ መበሳጨት እና በራስ መተማመን መቀነስ
ባህሪያዊ ምልክቶች፡
👉🏾ስራን ማጓተት (Procrastination)
👉🏾ከማህበራዊ ግንኙነቶች ራስን ማግለል
👉🏾ለኃላፊነት ግድየለሽ መሆን
👉🏾ለመዝናናት ሲባል ጎጂ ነገሮችን (ለምሳሌ አልኮል) ማዘውተር

🔘መፍትሄዎች
👉🏾እረፍት መውሰድ (Resting)
👉🏾ወሰን ማበጀት (Setting Boundaries)
👉🏾አካላዊ እንቅስቃሴ
👉🏾ዲጂታል ዲቶክስ (Digital Detox)
👉🏾ባለሙያ ማማከር
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
✨የቅድመ ወሊድ ቫይታሚኖች (Prenatal Supplements) ✨
እነዚህ ቫይታሚኖች ነፍሰ ጡር እናቶች እና ለማርገዝ የሚያቅዱ ሴቶች፣ በምግብ ብቻ ላያገኙዋቸው የሚችሉትን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች እንዲያገኙ ተደርገው የተዘጋጁ የቫይታሚን እና የሚነራል ጥምረቶች ናቸው።

📅 መቼ መጀመር አለብን?
👉ከእርግዝና በፊት፦ ለማርገዝ እቅዱ ካለዎት ከ2-3 ወራት በፊት መጀመር ይመከራል።
👉በእርግዝና ወቅት፦ እርግዝናው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ እስከ መውለጃ ድረስ።
👉ከወሊድ በኋላ፦ ጡት በማጥባት ወቅትም መቀጠል ለእናቲቱ ጉልበት እና ለወተት ጥራት ይጠቅማል።

💊 ዋና ዋናዎቹ ይዘቶች ምን መሆን አለባቸው?
👉ፎሊክ አሲድ (Folic Acid)
👉አይረን / ብረት (Iron)
👉ካልሲየም (Calcium)
👉ቫይታሚን ዲ (Vitamin D)
👉አዮዲን (Iodine)

🔘 እንዴት መወሰድ አለበት?
👉በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት መውሰድ አይርሱ።
👉ቫይታሚኑን ከወሰዱ በኋላ የሆድ መረበሽ የሚሰማዎት ከሆነ፣ ከምግብ ጋር ወይም ከመተኛትዎ በፊት መውሰድ የተሻለ ነው።
👉በቂ ውሃ መጠጣትን አይዘንጉ።

⚠️ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች
✔️የሆድ ድርቀት (በብረት/አይረን ይዘት ምክንያት)።
✔️የመቅለሽለሽ ስሜት።
✔️የሽንት ቀለም መቀየር (ይህ የተለመደ ነው)።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
😴 ናርኮሌፕሲ (Narcolepsy)
ናርኮሌፕሲ አንጎል የእንቅልፍ እና የንቃት ሂደትን በአግባቡ መቆጣጠር ሲያቅተው የሚከሰት የእንቅልፍ ችግር ነው።
ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በቀን ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ከፍተኛ እንቅልፍ ሊጥላቸው ይችላል።

ምልክቶቹ 🚩
🔘ከፍተኛ የቀን እንቅልፍ፦ በማንኛውም ሁኔታ (በንግግር፣ በምግብ ወይም በሥራ ወቅት) ድንገት እንቅልፍ መውሰድ።
🔘ካታፕሌክሲ (Cataplexy)፦ በድንገተኛ ስሜት (ሳቅ፣ ንዴት) ምክንያት የጡንቻ ድንገት መዛል።
🔘የእንቅልፍ ሽባነት(sleep paralysis)፦ እንቅልፍ ሲወስደን ወይም ስንነቃ ለጥቂት ሰከንዶች መንቀሳቀስ አለመቻል።
🔘ቅዠት፦ እንቅልፍ ሲያሸልበን በጣም ግልጽ የሆኑና የሚያስፈሩ ሕልሞችን ማየት።

ሕክምናው 💊
መድኃኒቶች፦ ንቃትን የሚጨምሩ(Stimulants) እና እንቅልፍን የሚያስተካክሉ በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች
ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
በቀን ውስጥ አጫጭር (20 ደቂቃ) እንቅልፎችን መውሰድ
ቋሚ የእንቅልፍ ሰዓት:-በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት መተኛት እና መነሳት
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
✨የትልቁ አንጀት ካንሰር (Colon Cancer)✨

የአንጀት ካንሰር የሚጀምረው በትልቁ አንጀት የውስጠኛው ክፍል ላይ በሚበቅሉ ፖሊፕስ (Polyps) በሚባሉ ትናንሽ ስብስቦች ነው። እነዚህ ፖሊፕስ መጀመሪያ ላይ ካንሰር ባይሆኑም፣ በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰርነት ሊቀየሩ ይችላሉ።

‼️ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
👉የሰገራ ልማድ መለወጥ (ተቅማጥ ወይም ድርቀት ለረጅም ጊዜ መቆየት)
👉በሰገራ ላይ ደም መታየት
👉ያለ ምክንያት ክብደት መቀነስ
👉ሁልጊዜ የድካም ስሜት መሰማት
👉የሆድ ቁርጠት ወይም የሆድ መነፋት

❓ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
👉ዕድሜ
👉አመጋገብ፦ ብዙ ቀይ ሥጋ እና የተቀነባበሩ ምግቦችን (Processed foods) ማዘውተር።
👉የቤተሰብ ታሪክ
👉አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት።
👉ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል ማዘውተር።

🛡መከላከያ መንገዶች
👉ምርመራ (Screening)
👉ጤናማ አመጋገብ
👉አካል ብቃት እንቅስቃሴ
👉ክብደትን መቆጣጠር እና ሲጋራ አለማጨስ።

💊 የሕክምና አማራጮች
✔️ቀዶ ጥገና (Surgery)
✔️የጨረር ሕክምና (Radiation Therapy)
✔️ኪሞቴራፒ (Chemotherapy)
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
✨የአእምሮ ጤናዎን ይንከባከቡ!✨

ለአካላዊ ጤናችን እንደምንጨነቀው ሁሉ ለአእምሮ ጤናችን ትኩረት መስጠት ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል

❕የአእምሮ ጤናን ለመንከባከብ የሚረዱ መንገዶች

☑️ የውስጥ ሰላምዎን በመጠበቅ (Protecting Inner Peace)🕊
☑️አእምሮዎትን ማሳረፍ (Mental Rest)
☑️ የማቆም ጥበብ በመጠቀም(The "Pause" Technique)
🔘እረፍት መውሰድ ስንፍና ሳይሆን አስፈላጊ ነው። ጭንቀት በሚኖርበት ጊዜ ለ5 ደቂቃ ያህል ስራዎን አቁመው በጥልቀት ይተንፍሱ።🧘🏽‍♂️
☑️ ከቴክኖሎጂ በመራቅ (Digital Detox)
☑️ ለራስ ደግ መሆን (Kind Self-Talk)
🔘ለራስዎ የሚነግሩትን ቃል ይጥንቀቁ። ለምሳሌ "ተሸነፍኩ" የሚለውን በ "እየተማርኩ ነው" ይተኩት።😊
☑️ ትናንሽ ስኬቶች (Small Wins)
🔘ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለመለወጥ አትሞክር። ዛሬ በቂ ውሃ መጠጣትህ፣ አልጋህን ማንጠፍህ ወይም ለ10 ደቂቃ በእግር መጓዝህ ትልቅ ስኬት ነው።🥇
☑️ ስሜትን መግለጽ (Expressing Emotions)
☑️ እንቅስቃሴ ለጤና (Physical Movement as Medicine)💪🏼
☑️ አመስጋኝነት (Gratitude)🙏

መልካም ቀን😊
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
ድባቴ /Depression/😞
ድባቴ ምንድን ነው? 😔

የድባቴ (ዲፕሬሽን) ሕመም የስሜት መውረድን ብሎም የደስታ ስሜት ማጣትን ያሳያል፡፡ አንድ ሰው በድብርት ውስጥ ሲሆን በውስጣዊ ስሜቱ እና በውጫዊ ገጽታው ይንፀባረቃል÷ ይህም ደስታ ማጣት፣ መከፋት፣ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ውስጥ መሆን ናቸው፡፡🤐

ከድብርት ምልክቶች፦
የስሜት መዛባት፣ 😔🖤
በፊት ያስደስቱ በነበሩ ሁኔታዎች አለመደሰትና አለመፈለግ፣ 😢
የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መቀነስ ወይንም መጨመር፣🍚🚫
ምክንያቱ በግልጽ ያልታወቀ ከፍተኛ ድካም፣ 😔🌧
እራስን በከፍተኛ ሁኔታ አሳንሶ ማየት፣ 😞💔
እራስን በከፍተኛ ሁኔታ መውቀስ (የተጋነነ የጥፋተኝት ስሜት)፣ ሕይወትንና ኑሮን መጥላት፣ ሞትን መመኘት፣ 😞
እራስን ለማጥፋት ማሰብ ብሎም ለማጥፋት መሞከር

የድብርት ሕክምና

ሥነ-ልቦናዊ (ሳይኮ ቴራፒ)
የመድኃኒት ሕክምና
የሕመሙ ተጠቂዎች ሆስፒታል ተኝተው ሊታከሙ የሚችሉበት ሁኔታ አለ፡፡
ሕመሙ ሥር ሰዶ ምግብ መመገብ፣ መናገር ብሎም መድኃኒት ለመውሰድ ፈቃደኛ የማይሆኑበት ጊዜ ከደረሰ አንጎልን በኤሌክትሪክ የማነቃቃት ሕክምና ሊሰጥ ይችላል፡፡
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  7755 ይደውሉ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
✨የጡት ካንሰር(Breast cancer )✨

🔍 የጡት ካንሰር የሚከሰተው በጡት ውስጥ የሚገኙ ሴሎች ያለ ቁጥጥር ሲባዙና በዙሪያቸው ያሉ ጤናማ ቲሹዎችን (tissues) ሲወሩ ነው።

⚠️ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች
🔘ዕድሜ
🔘የቤተሰብ ታሪክ
🔘የአኗኗር ዘይቤ

🚩 ዋና ዋና ምልክቶች
☑️በጡት ወይም በብብት አካባቢ የሚሰማ አዲስ እብጠት።
☑️የጡት ቅርጽ ወይም መጠን ድንገት መቀየር።
☑️የጡት ቆዳ መቅላት ወይም እንደ ብርቱካን ልጣጭ መሸብሸብ።
☑️የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሰርጎድ ወይም ፈሳሽ መውጣት።

🛡 የቅድመ ምርመራ ዘዴዎች (Screening)
👉🏽የራስን ጡት በራስ መመርመር
👉🏽በጤና ባለሙያ የሚደረግ ምርመራ
👉🏽ማሞግራም (Mammogram)
👉🏽የኤክስሬይ (X-ray) ምርመራ

🏥 የሕክምና አማራጮች
➡️ቀዶ ጥገና (Surgery)
➡️የጨረር ሕክምና (Radiation)
➡️የኬሞቴራፒ ሕክምና (Chemotherapy)
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲

ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448