ጳጉሜ 3 የ"ፅናት ቀን"
"አብሮነታችን ለፅናታችን፣ፅናታችን ለዘላቂ ሉዓላዊነታችን"
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ጳጉሜ 3 "የፅናት ቀን" አስመልክቶ አብሮነታችን ለፅናታችን፣ፅናታችን ለዘላቂ ሉዓላዊነታቸው በሚል መሪ ሀሳብ የወረዳው አመራሮች ፣ የፀጥታ አካላት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በርካታ ሁነቶች ተካሂደዋል።
በዕለቱ መርሃ-ግብር ላይ እንደተገለጸው፣ ባለፉት አበይት ዓመታት ማህበረሰቡ ያጋጠሙትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች በጽናት በመጋፈጥ ያስመዘገባቸው ድሎች ተነስተዋል። የወረዳው ስራዎች እና የልማት ስኬቶች የፅናት ውጤት መሆናቸው ተመላክቶ፣ ህብረተሰቡ ላሳየው ሁለንተናዊ ትዕግስት እና ትብብር ምስጋና ቀርቧል።
ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፣ ጳጉሜ 3 የፅናት ቀን መሆኑ ያለፉትን ውጣ ውረዶች እንድንረሳ ሳይሆን፣ ከታሪካችን ትምህርት ወስደን ለአዲሱ ዓመት አዲስ ጉልበት እና ተስፋ እንድንሰንቅ የሚያደርገን ልዩ ዕለት ነው ብለዋል።
ለሚ ኩራ ወረዳ 08 ኮሙንኬሽን 3/13/2018ዓ.ም