Lucrative Business Ideas
152 subscribers
21 photos
3 files
5 links
YOU CAN'T GO BACK AND CHANGE THE BEGINNING, BUT YOU CAN START WHERE ARE NOW AND CHANGE THE ENDING"!
Download Telegram
If you don't like the direction you're life is headed, change it. Life isn't about finding yourself, it's about creating yourself.
As we know, a lot of businesses, events have changed incredibly due to COVID-19. So what does this mean, It's a time to pivot, not pause. This is your opportunity to become a digital leader and master the art of mobile technology businesses.
Make Money with your Smart Phone; Achieve the Life You've always Dreamed Of.
Registration: @lemabbot or @lmmbr or 0913942808
If you want to change you have to be willing to do things you've never done. Stretch yourself and be uncomfortable until the new level of change becomes a normal and natural part of you.
Make Money with your Smart Phone; Achieve the Life You've always Dreamed Of.
Registration: @lemabbot or @lmmbr or 0913942808
እዉነት እኔ የራሴን ቢዝነስ ሰርቼ ሃብታም መሆን እችላለሁ?

ብዙ ሰዎች አሁን ካላቸዉ ኑሮ የተሻለ ህይወት ለመኖር ይመኛሉ፡፡ ምኞት ብቻዉን ግን በቂ አይደለም፡፡ ብዙዉን ጊዜ ምኞት በስራና በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልታገዘ የሚያልሙትን ህይወት ማግኘት ከህልምነት አያልፍም፡፡ በምኞት ብቻ የሚዋልሉ አቋራጭ ፍለጋ ላይ ያተኩራሉ፡ ሎተሪ መቁረጥ፣ ሃብታም ባል ወይንም ሚስት ፍለጋ መባዘን፣ ስራ ላይ በሚከሰት አደጋ ጠቀም ያለ ካሳ ለማግኘት ማለም፣ ዉርስ መጠበቅ፣ ሙስና፣ ወዘተ፡፡ ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች አቋራጮች አልፎ አልፎ ቢሳኩም አብዛኛዉን ጊዜ ግን መና ሆነዉ ሲቀሩ ይታያል፡፡

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ደግሞ በተቃራኒዉ ገና በጠዋቱ እጅ ሰጥተዉ ያለ ህልም ወይንም ራእይ እድሜያቸዉን ይገፋሉ፡፡ በህሊናቸዉ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ እና የተሳካ ህይወት የነርሱ ሊሆን እንደማይችል ራሳቸዉን አሳምነዉ ተቀምጠዋል፡፡ እኔማ ተምሬ ዲግሪ አልይዝም፣ የራሴን ቤት ሰርቼ ከኪራይ ልወጣ የማይታሰብ ነዉ፣ክብደትማ በፍፁም መቀነስ አልችልም፣ ወዘተ እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ብዙዎችን ሳይሞክሩ እጅ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡

በጣም በርካታ ሰዎች እድሜያቸዉን ሙሉ ለዚህ ወይንም ለዚያ ድርጅት ሲሰሩ አሳልፈዉ የጡረታ ጊዜ ሲቃረብ እንዴት እሆን ይሆን የሚለዉ ስጋት መምጣት ይጀምራል፡፡ እድሜ እየገፋ ሲሄድ አቅም ስለሚቀንስ ተሯሩጦ መስራት አማራጭ አይሆንም፡፡ ለጤና የሚደረገዉ ወጪም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የጡረታዉ ገቢም የሚያወላዳ አይደለም (በተለይም የዋጋ ግሽበት በቀጣይነት ሊኖር ስለሚችል) ፡፡

በደህና ጊዜ ልጆቹን ለቁምነገር ያበቃ የልጆቹን እጅ ማየት ሊኖርበት ነዉ፡፡ አሊያም ልጆቹን ያሳደገበትን ቤት ሸጦ ትንሽ ቤት ሰርቶ ወይ ገዝቶ ቀሪዉን እየበላ ኑሮዉን ይገፋል፡፡

ታዲያ ስኬትን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

ወደሃብት ጉዞ 

ቢዝነስ ለነጋዴ ልጅ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የንግድ ስራ በቤተሰብ የሚወረስ ብሎም ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የተተወ ይመስላቸዋል፡፡ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ቤተሰብ ዉስጥ መኖር ስለንግድ የተሻለ እዉቀት እንዲኖር ሊረዳ ቢችልም ሌላ ሰዉ ሊማረዉ አይችልም ማለት ግን አይደለም፡፡

ተነሳሽነቱ እና ቁርጠኝነቱ ካለ በየትኛዉም መስክ የሚፈለገዉን እዉቀት ማዳበር ይቻላል፡፡ መማር መመረቅ መቀጠር ከሚለዉ የተለመደ ወይንም ካደግንበት አስተሳሰብ ወጥተን ስራ ፈጠራን፣ የራስ ቢዝነስን ማደራጀት መሞከር ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ኑሯችን ወይ ከእጅ ወደአፍ ነዉ አሊያም ሰዉ የቆረጠልንን ደሞዝ እየጠበቅን የሌሎችን ስኬት ማፋጠን ብቻ ይሆናል የኛ ሚና እና መዳረሻ፡፡

መቼም ሁሉም ሰዉ የራሱን ቢዝነስ የሚሰራ ሆኖ የሚቀጠር ሰዉ አይኖርም ወይንም አይኑር ማለት አይደለም፡፡ ህይወቱን መቀየር እና ሃብታም መሆን የሚፈልግ ሰዉ ግን ጠዋት ገብቶ እስከ አስራ አንደ ሰአት ሰርቶ በወሩ መጨረሻ የሚሰጠዉን ደሞዝ ከመጠበቅ ወጥቶ የራሱ ጌታ ወደሚሆንበት አስተሳሰብ እና ተግባር መሸጋገር ይኖርበታል፡፡ ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም ግን ከልብ ካለቀሱ እንደሚባለዉ ነዉ ነገሩ….

ብዙዎች ስለኑሯቸዉ ና ህይዎታቸዉ ያማርራሉ ግን ደግሞ የለመዱትን ቢሮ ገብቶ መዉጣት አኗኗር ለመቀየር ቁርጠኝነት ይጎድላቸዋል፡፡ ስለሆነም ደስተኛም ባይሆኑ አዲስ ነገርን ፍራቻ ባሉበት መቆየትን ይመርጣሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ወሬያቸዉ ኑሮ ተወደደ፣ ኪራይ ጨመረ… ድሮ ጊዜዉ ጥሩ ነበር ወዘተ፡፡

በተቃራኒዉ ለለዉጥ ቀበቷቸዉን ያጠበቁት ደግሞ ምን እናድርግ፣ ምን ብንሰራ ያዋጣል፣ እያሉ መረጃ መለዋወጥ እቅድ ማዉጣት ይሆናል፡፡ ችግርን ደጋግመዉ ቢያወሩት ጊዜን ለማቃጠል ካልሆነ በራሱ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ባሉበት መርገጥ ነዉ መጨረሻዉ፡፡ ራስን በመቀየር ሁሌ ደሞዝ ጭማሪ ና እድገት ከመጠበቅ አዙሪት ወጥቶ የሚፈልጉትን ህይወት መምራት ይቻላል፡፡ ይህን በማድረግ (የገንዘብ ነፃነትን በማግኘት) ሌሎች እድሜያቸዉን ሙሉ ደሞዝን ስለማብቃቃት ሲያወሩ ስለሌላ አላማ እና ግብ ወይንም የሚወዱት ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይቻላል፡፡

@EthioBini @EthioBinibot
Make Money with your Smart Phone; Achieve the Life You've always Dreamed Of.
Registration: @lemabbot or @lmmbr or 0913942808
Emotional Intelligence is a critical trait in #Leadership and is equally important for the individuals who are their self Leaders.


“𝘌𝘮𝘰𝘵𝘪𝘰𝘯𝘢𝘭 𝘪𝘯𝘵𝘦𝘭𝘭𝘪𝘨𝘦𝘯𝘤𝘦 𝘪𝘴 𝘵𝘩𝘦 𝘢𝘣𝘪𝘭𝘪𝘵𝘺 𝘵𝘰 𝘴𝘦𝘯𝘴𝘦, 𝘶𝘯𝘥𝘦𝘳𝘴𝘵𝘢𝘯𝘥, 𝘢𝘯𝘥 𝘦𝘧𝘧𝘦𝘤𝘵𝘪𝘷𝘦𝘭𝘺 𝘢𝘱𝘱𝘭𝘺 𝘵𝘩𝘦 𝘱𝘰𝘸𝘦𝘳 𝘢𝘯𝘥 𝘢𝘤𝘶𝘮𝘦𝘯 𝘰𝘧 𝘦𝘮𝘰𝘵𝘪𝘰𝘯𝘴 𝘢𝘴 𝘢 𝘴𝘰𝘶𝘳𝘤𝘦 𝘰𝘧 𝘩𝘶𝘮𝘢𝘯 𝘦𝘯𝘦𝘳𝘨𝘺, 𝘪𝘯𝘧𝘰𝘳𝘮𝘢𝘵𝘪𝘰𝘯, 𝘤𝘰𝘯𝘯𝘦𝘤𝘵𝘪𝘰𝘯, 𝘢𝘯𝘥 𝘪𝘯𝘧𝘭𝘶𝘦𝘯𝘤𝘦.”
— 𝘙𝘰𝘣𝘦𝘳𝘵 𝘒. 𝘊𝘰𝘰𝘱𝘦𝘳. 𝘗𝘩.𝘋.
The break down of the 4 categories make it easier to understand the EQ concept,

✍ 𝕊𝕖𝕝𝕗-𝔸𝕨𝕒𝕣𝕖𝕟𝕖𝕤𝕤 - ability to know self emotions, conscious about the power and courage to steer such emotions in the positive directions. Knowledge of personal strength and the confidence in moving in the right direction strengthens the emotional intelligence which helps the other 3 categories.


✍ 𝕊𝕖𝕝𝕗-𝕄𝕒𝕟𝕒𝕘𝕖𝕞𝕖𝕟𝕥 - is reminding self to be in-control. What's coming and what needs to be addressed can only be manoeuvred when the Leader has the ability of self-control. This brings trust and provokes transparency.


✍ 𝕊𝕠𝕔𝕚𝕒𝕝 𝔸𝕨𝕒𝕣𝕖𝕟𝕖𝕤𝕤 - leads to the intrinsic skill of connecting with people, understanding their emotions and being empathetic. Servant Leaders care for the well being of their team which further builds the trust. What is being said is ensured being understood, brings success another step closer.


✍ ℝ𝕖𝕝𝕒𝕥𝕚𝕠𝕟𝕤𝕙𝕚𝕡 𝕄𝕒𝕟𝕒𝕘𝕖𝕞𝕖𝕟𝕥 - which is the heart of Leadership for a sustained success of the team and organization. Motivating the team, inspiring for a greater combined cause and influencing the outcome add up to better engagement.


Statistically, it is said that Leaders at the higher levels are to be equipped with 85% of soft skills, of which EQ is the top-most, so that they can be successful.


As 𝐋𝐞𝐚𝐝𝐞𝐫𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐌𝐚𝐧𝐚𝐠𝐞𝐫𝐬, what are your scores for EQ?
What makes you different in the market place?


#Leadership
Make Money with your Smart Phone; Achieve the Life You've always Dreamed Of.
Registration: @lemabbot or @lmmbr or 0913942808
"Most of us we wait for best time, good opportunity, right amount of capital to start. We live in what Brian Tracy call "someday island". We say things like, Someday I will start my own business etc. However,to achieve success we must have a crystal clear understanding of what we want and have a burning desire, a strong WHY which will inspire us. Let us be vigilant in seizing on opportunity. Don't wait for extraordinary opportunities-seize common occasions and make them great."
Have a joyful day!!
ሕይወት የትኛውንም ውጣ ውረድ ተጋፍጠን የምንሰራባት ናት፡፡

@EthioBini @EthioBinibot
ዘሩ ብቅ አላለም ብለህ ውሃ ማጠጣቱን አታቁም


አንዳንዴ ለፍተን ለፍተን ምንም ነገር ጠብ ሳይል ሲቀር ተስፋ መቁረጥ፤ ከተፍ ማልቱ አይቀርም። የምንለፋው ለምንድን ነው? ያሰኘናል።

የምጓዘው ጨለማ መቼ ነው የሚነጋው? የልፋቴን ዋጋ መቼ ነው የማገኘው? እያላችሁ ከሆነ ፤ ምላሽ የምታገኙበትን አንድ ድንቅ ታሪክ ላካፍላችሁ። እኔ በግሌ የምጠቀምበት ዘዴ ነው። አንድ ነገር ሞክሬ ለማቋረጥ ሳስብ ይህንን ታሪክ ምልሼ ለራሴ እነግረዋለው።


የቻይና ባምቡ ዛፍ አስተዳደጉ ከሌሎች ዛፎች በጣም ይለያል። ሌሎች ዛፎች ከተተከሉ ጀምሮ ማቆጥቆጥ ሲጀምሩ፤ ይህ የቻይና ባምቡ ዛፍ ግን፤ በቀን በቀን ውሃ ቢጠጣም እስከ አምስተኛው አመት ድረስ አፈሩን በርቅሶ አይወጣም። ያለማቋረጥ እለት ተእለት ውሃ መጠጣት አለበት፤ ነገር ግን አራት አመት ሙሉ ምንም አይነት እድገት አያሳይም።

በአምስተኛው አመት ግን በአምስት ሳምንት ወስጥ በአንዴ 90 ፊት ውይም 27 ሜትር ያድጋል። ታዲያ ይህ ዛፍ በአምስት ሳምንት ውስጥ ነው ያደገው? ወይስ በአምስት አመት?
መልሱ በአምስት አመት ነው።

ጽናት የሌለው ሰው ግን ቶሎ ብቅ ለማይል ዘር አምስት አመት ሙሉ ውሃ ማጠጣቱ አይዋጥለትም እናም ዛፉን በእንⶽጩ ይቀጨዋል። የእኛም ነገር እንዲህ ነው፤ ሃሳባችን ግቡን ባሰብነው ሰዓት ካልመታ፤ አላማችን በአቀድነው ቀን ካለተሳካ፤ ምኞታችን በእለቱ እውን ካልሆነ፤ የማይሳካ ይመስለናል። ለዚህ ነው ብዙዎቻችን ጉዞዋችንን የምናቋርጠው።


የእውነት አላማ በውስጥህ ካለ፤ ውሃ ማጠጣትክን እንዳትተው። ዛሬ ባይሳካ በጊዜው መሳካቱ አይቀርም። አንባቢ ባታገኝም መጻህፍህን አትተው፤ የሚጎበኝልህ ብታጣም መሳልህን አትተው፤ የሚሰማህ ብታጣም መዝፈንህን አታቋርጥ፤ አይዞህ የሚልህ ባታገኝ መማርህን አታቁም።

የብዙዏቻችን አላማ ልክ እንደ ቻይናው ባምቡ ዛፍ ነው፤ ሳናቋርጥ ውሃ ካጠጣነው እና ትዕግስት ካለን፤ ማቆጥቆጡ ብሎም ማደጉ አይቀርም።

ለሁሉም ጊዜ አለው ይል የለ መጽሃፉ………በጊዜው የተከልነው ችግኝ ሰማይ ማከሉ አይቀርም፤ እስከዛ ግን ማድረግ የሚገባህን ከማድረግ አትቆጠብ፤ ነፍስህ በቀን በቀን ውሃ አጠጣት።
🌀✅ የህይወት ዋጋ ምን ያህል ነው? ✅🌀

ልጁ አያቱን ይህንኑ ጥያቄ ጠየቀ። “አያቴ የህይወት ዋጋ ምን ያህል ነው?” አላቸው። አያቱም ያለ ምንም ማብራሪያ አንድ አንጸባራቂ ድንጋይ አወጡና ሰጡት።

እንካ ይህን ድንጋይ ሂድና የዚህን ድንጋይ ዋጋ ጠይቅና ና። ግን አደራ እንዳትሸጠው።” አሉት ልጁ ድንጋዩን ይዞ ወጣ። በመጀመሪያ ወደ አንድ የፍራፍሬ ነጋዴ ዘንድ ሄደና...“የዚህ ድንጋይ ዋጋ ምን ያህል ነው? አለው። ነጋዴውም አንጸባራቂውን ድንጋይ አተኩሮ እየተመለከተ “ከነዚህ አቮካዶዎች በርከት አድርጌ ልስጥህና ሽጥልኝ” አለው።
ልጁም “አያቴ እንዳትሸጠው ብሎኛል” አለውና ወጣ። ቀጥሎ ወደ አንድ አትክልት ነጋዴ ሄደና “የዚህ ድንጋይ ዋጋ ምን ያህል ነው?” አለው። ነጋዴውም “አንድ ጆኒያ ድንች ልስጥህና ሽጥልኝ” አለው።

አያቱ እንዳትሸጠው እንዳሉት ተናግሮ አመስግኖ ወጣ ልጁ ጉዞውን ቀጠለና ወደ አንድ ጌጣ ጌጥ ሰሪ ጋ ሄደ የድንጋዩ ዋጋም ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል ጠየቀው ጌጣ ጌጥ ሰሪውም ድንጋዩን ሲያይ ፈዘዘ
ንጹህ ጨርቅም አወጣና አንጥፎ ድንጋዩን አስቀመጠው። እየዞረ ድንጋዩን ተመለከተው። “ይህን አንጥረኛ ያልነካውን፣ ያልተቆረጠና ፍጹም ውድ የሆነ አልማዝ ከየት አገኘህ? ሱቄንና ንብረቴን ሁሉ ብሸጥ እንኳ ይህን ውድ አልማዝ ልገዛበት አልችልም…” አለው።
በዚህ ሁሉ ነገር ግራ የተጋባው ልጅ ወደ አያቱ ተመለሰና የገጠመውን ሁሉ ተናገረ።

💠 አያቱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት “ከፍራፍሬ ነጋዴው፣ ከባለ አትክልቱና ከጌጣጌጥ ሰራተኛው ያገኘሀቸው መልሶች ሁሉ ስለ ህይወታችን ዋጋ ይነግርሀል አንተ ምናልባት ዋጋህ ፍጹም ውድ የሆነ ድንጋይ ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ሰዎች የሚመዝኑህ እነሱ ባላቸው ችሎታ፣ እውቀትና አቅም አንጻር ነው ሰዎች አንተን የመዘኑበት መንገድ ስለ እነሱ እንጂ ስላንተ አይነግርህም እናም ህይወትህን ሊመዝን የሚገባው ሌላ ሰው ሳይሆን አንተው ራስህ ነህ።

✅ ራስህ ለራስህ ዋጋ ስጥ፣

✅ ራስህን አክብር፣

✅ ያንተን ህይወት ከሌሎች ጋር አታነጻጽር፣

✅ አንተን የመሰለ ሌላ ሰው በምድር ላይ እንደሌለና ፍጹም ልዩ ሰው መሆንህን እወቅ፣

✅ ይህ ነው የህይወት ዋጋው፣ አንተ የምትሰጠው ዋጋ!

✅ እውነተኛውን ዋጋህን አንተ ብቻ ነህ የምትመዝነው!!!

✅ ራስህን አክብረው→ያንተው ነውና፣

✅ ራስህን አትጣል→የሚያነሳይ የለምና ፤

✅ ራስህን ተከባከበው→ለራስህ ነውና፣

✅ ለራስህ ቦታ ስጥ→የሚደግፍህ የለምና፣

✅ አንተ መኖርህን ለማሳወቅ ብለህ አትጩህ→አንተን የሚፈልግ ስው ካለ በጨለማም ውስጥ ብትሆን ፈልጎ ያገኝሀልና።

✅ ጥንካሬህንና አቋምህን አስተካክል→በዙሪያህ ውድቀትህን የሚመኙ አይጠፉምና፣

✅ አንድ ቀን ከምትወደው ስው ጋር ጓደኝነታችሁ ካበቃ ፍቅሩን በልብህ ውስጥ አኑረው ታሪኩን ሚስጥሩን ደብቅለት ጓደኝነት ማለት መልካምነት ማለት ነው።
Make Money with your Smart Phone; Achieve the Life You've Always Dreamed Of. Be part of #1business opportunity!!
Registration: @lemabbot or @lmmbr or 0913942808
​እራስህን መለወጥ

እራስን ስለመለወጥ አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ በየትኛውም ህይወት ውሰጥ በየትኛውም የህይወት አቅጣጫ ውሰጥ ይጠቅምሃል። የተለያዩ 3 የሚሆኑ ነጥቦችን እንመልከት።

1. አንብብ ፦ ጥሩ አንባቢ ሁን በአለም ላይ ያሉ ስኬታን የተጎናፀፉ ሰዎች ሁሉንም ስንመለከት አንባቢዎች ናቸው።

የነበራቸው ነገሮችን የማወቅ ጉጉታቸው ለማወቅ ያነባሉ...ያነባሉ... ያነባሉ።

አንባቢ ሁን ቀጣይ የማነሳቸውን ነገሮች ላትስማማባቸው ትችላለህ ግን ጥሩ ተማሪ ሁን እንጂ ተከታይ አትሁን። እኔ የምለው ህይወትህን ለመቀየር ማንበብ እንዳለብህ ነው።

አንተ ከራስህ የህይወት ተሞክሮ ልትማር ትችላለህ ወይንም ደግሞ ከሌሎች የሰዎች ተሞክሮ ልትማር ትችላለህ ግን እኔ የምልህ አንብብ ነው።

አንድ መፅሀፍ የአምስት አመት ልምድ በውስጡ ይዟል። ታውቃለህ? እንደዚህ ያሉ ብዙ መፅሀፎች አሉ " ጠንካራ እንዴት መሆን ይችላል?

" ፣ " ውሳኔ ላይ ጎበዝ እንድትሆን " ፣ " ስለግል መሻሻያ " ፣ " እንዴት መሪ መሆን እንደምችል?

" ሰዎች ላይ እንዴት ተፅዕኖ ማሳደር እንዳለብህ "

በእነዚህ ሁሉ መፅሀፍት አሉ። እና ደግሞ ሰዎች አያነቧቸውም!!! መቶ የሚሆኑ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች የህይወት ታሪካቸውን ፅፈዋል ነገርግን ሰዎች አያነቧቸውም!!! እንዴት ይህን የምታብራራው?

ብዙ ሰዎች እራሳቸውን አሳስረው ቁጭ ብለዋል። ቀን ከለሊት ቀን ከሌሊት ይሰራሉ ነገር ግን ማንበብ እንዳለባቸው ይዘነጉታል።

2. አዳምጥ ፦ ሌላው ደግሞ ስኬታማ ካልሆኑት መማር ትችላለህ። በዛ መሰረት ማስታወሻ ያዝ አዎንታዊ እና አሉታዊ ብለህ መድበው።

በአሉታዊ ምን መስራት እንደሌለብህ ታውቃለህ። ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለብህ እና ምን ማድረግ እንደሌለብህ ማወቅ አለብህ። ስለዚህ ከአዎንታዊ ብቻ

ሳይሆን ከአሉታዊውም ነገር ትማራለህ። ግን ከአውንታዊውም መማር ትችላለህ።

ስኬታማ ሰዎችን አግኝ እንዴት እንደሚሰሩ? እንዴት እንደሚናገሩ? ሁሌም በትኩረት አዳምጥ።

እኔ እንዳገኘሁት ከማንበብ ይልቅ ለማድመጥ መሞከር ከባድ እንደሆነ ነው።

ነገር ግን ማድመጥን ከተለማመድክ በቀን ውሰጥ አስገራሚ የሆኑ ሀሳቦች ታገኛለህ።

አንድ መርሳት የሌለብህ ደግሞ ካነበብከው እና ካአዳመጥከው ነገሮች ተነስተህ የራስህ የሆነ ማስታወሻ ይኑርህ።

3. መመልከት ፦ ሌላኛው ከስኬታማ ሰዎች የምታገኘው ትምህርት በመመልከት ነው።

ያ ሰው እንዴት ሰላምታ እንደሚሰጥ ተመልከት ያቺ ስኬታማ ሴት እንዴት ምላሽ እንደምትሰጥ ተመልከት። ብዙ ጊዜ ሰዎች አንድ ነገር ደግመው ደጋግመው ይሰራሉ።

አንተም ብልህ ከሆንክ እነኚህ ነገሮችን ታገኝበታለህ ህይወትህን ትቀይርበታለህ።

ሁለት እይታዎች አሉ አንድ በአይንህ የምታየው ነው ሁለት ደግሞ በአዕምሮህ የምትመለከተው እይታ ነው። ከዚህ ሌላ ትኩረት ማድረግ ነው። የትም ቦታ ሁን እዛ ቦታ ላይ ሁን።
Hi , Everyone!


You've probably heard this advice – "put first things first"?


This is one of the key success principles taught in many success workshops and books. The idea is simple – to give priority to the things that matter most. This seems obvious, yet most of us fall into the trap of trying to do too much, including things that distract us from our true priorities.


So, how exactly can you put first things first and get the right things done? Here are 3 powerful tips - take your pick or do all 3!  

1) ASK THE FOCUSING QUESTION


In The ONE Thing, Gary Keller shares a really powerful question: "What’s the ONE Thing I can do such that by doing it, everything else will be easier or unnecessary?" Learn to ask this question in every aspect of your life, to identify the items can create a domino effect and multiply the impact of your efforts.

2. FOCUS ON WHAT’S IMPORTANT, NOT WHAT’S URGENT


In The 7 Habits of Highly Effective People, Stephen Covey suggests that you focus on the important activities, not just the urgent ones. To do that, you plan weekly and act daily, giving time to your priorities.  Use the time-management matrix.



Specifically, to ensure that you are preventing and not prioritizing crises, do your planning weekly, with 4 key activities :

a) Identify Roles: Write down the key roles in your life

b) Select Goals: Identify 2-3 key results to achieve for each role in the coming week, incorporating Quadrant II activities.

c) Schedule: Plan the week ahead and set aside time for these goals.

d) Adapt Daily: Adjust activities to manage unexpected developments.

3. ELIMINATE WHAT'S UNNECESSARY


As we add on priorities and to-do items, it’s equally important to eliminate what’s unnecessary.


In his book The Effective Executive, Peter Drucker recommends that you consciously ask yourself this question about you and your team's work: "if we did not already do this, would we go into it now?". Use this question as part of your weekly planning to identify activities that are no longer productive, eliminate them, and direct the resources to new opportunities.

GETTING STARTED

The 3 simple tips above can be applied immediately and used concurrently to help you sharpen your focus. Go ahead, try them and share your results and feedback with us!


Remember, the sooner you take action, the sooner you will see results!
በዚህ ዓመት ብርቱ ሰራተኛ ሁን!

“ሕልምና ራእይ ወደ እውነታ የሚመጣው በምትሃት አይደለም፡፡ በላብ፣ በቆራጥነትና ጠንክሮ በመስራት ነው” - Colin Powell

አንድ ቀን የምመኘውን አገኘዋለሁ” በማለት ቁጭ ብሎ የሚጠብቅ ሰው አንድ ቀን የሚመኘውን የማግኘቱ እድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡ ምናልባት እንኳ እንዴት እንደሆነ ባልገባን ሁኔታ አንድ ቀን የተመኘውን ቢያገኝም እንኳ፣ አንድ ቀን ደግሞ ያንን እንዲሁ በምኞትና ባጋጣሚ ያገኘውን ነገር ያጣዋል፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያቱት ቁጭ ብለን ያገኘነውን ነገር በዚህ ቁጭ ባለው ማንነታችን መጠበቅም ሆነ ማሻሻል ስለማንችል ነው፡፡

በላብ፣ በድካምና በብዙ ትጋት የመጣ ነገር በዚያ ድካም ምክንያት ባገኘነው የባህሪ ጽንአታችን ይቀጥላል፣ ይሻሻላል እንዲሁም ያድጋል፡፡ ስለዚህም ተቀምጦ አንድ ነገር ደጁ ድረስ እስኪመጣለት የሚጠብቅ ሰው ለብዙ ክስረት ራሱን ያጋልጣል፡፡ ከሁሉ የላቀው ክስረቱ ግን ተቀምጦ “እድል” ሲጠብቅ የኖረበት ዘመን የሚያባክንበት “ጊዜ” የተሰኘውን ሊመለስ የማይችል ውብ ሃብቱን ነው፡፡

ሕልምን ማለም ለሁሉ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ የታለመውን ሕልም ግን እውን ለማድረግ መንቀሳቀስ ጥቂቶች የሚለማመዱት ልምምድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በህልምና በራእይ ቢጀመርም የሚቀጥለው ግን በትጋትና በጠንካራነት ነው፡፡