Lucrative Business Ideas
152 subscribers
21 photos
3 files
5 links
YOU CAN'T GO BACK AND CHANGE THE BEGINNING, BUT YOU CAN START WHERE ARE NOW AND CHANGE THE ENDING"!
Download Telegram
🖍ሲጋራ ማጨስ ለማቆም ቢዝነስ መጀመር


በ25 አመቴ የኮሌጅ ትምህርቴን በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ቢዝነስ አስተዳደር ጨርሼ ኒውዮርክ ውስጥ የገቢ ማሰባሰብ ስራ የሚሰራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ እሰራ ነበር ትላለች ግሬስ ስሚዝ፡፡
___________________________

ስራው ውጥረት እና ጭንቀት የሚበዛበት ነበር፡፡ በዛ ላይ ወጣትም ስለነበርኩ ከስራ መልስ ያለውን ጊዜ ፈታ ለማለት በሚል ሁል ጊዜ ማታ ማታ በመጠጣት፤ ሲጋራ በማጨስ፤ ከጓደኞቼ ጋር በመጨፈር ነበር የማሳልፈው፡፡
___________________________
ይሄ ሁሌ የድካም ስሜት እንዲሰማኝ እና ድብርት እንዲጫጫነኝ አደረገ፡፡ ሳስበው ሳስበው ጤነኛ የሆነ ህይወት መምራት እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡

___________________________
ስለዚህ መጠጥ መጠጣት እና ጭፈራ ቤት መሄዱን አቆምኩ፡፡ ነገር ግን ሲጋራ ማጨስ ለማቆም በጣም አስቸጋሪ ሆነብኝ፡፡ ማስቲካ ማኘክ፤ ከረሜላ መምጠጥ፤ ውሃ መጠጣት እና መሰል ነገሮችን ብሞክርም ሲጋራ ማጨስ ማቆም በጣም ከበደኝ፡፡
___________________________

ይሄንን የተረዳች አንድ ጓደኛዬ ሂፕኖሲሰ እንድሞክር መከረችኝ፡፡ ነገሩን ብዙም አልፈለኩትም ነበር፡፡
___________________________

ዝም ብለው ብሬን በልተው እንደሚያታልሉኝ ተሰማኝ፡፡ ቢሆንም ለአንድ ቀን ለአንድ ሰአት በባለሙያ የሂፕኖሲሰ ህክምናን ለመሞከር ተስማማሁ፡፡
___________________________

(ሂፕኖሲስ ማለት በባለሙያ የሚደረግ ሲሆን አንድ ሰው በእንቅልፍ እና በመንቃት መካከል እንዲሆን ማድረግ እና ድብቁ አእምሮውን (Subconscious) መክፈት ነው፡፡

___________________________

በዚህ ጊዜ ሰዎች ትውስታቸው፤ ትኩረታቸው እና ሃሳብ የመቀበል ችሎታቸው በእጅጉ ይጨምራል)፡፡

___________________________

ግሬስ እንደምትለው ከሆነ በአንድ ቀን ቀጠሮ በሂፕኖሲስ ከሲጋራ ጋር ያላት ግንኙነት ተቋረጠ፡፡

___________________________

በዚህ ምክንያት ግሬስ የሂፕኖቴራፒ ባለሙያ ለመሆን እና ሌሎችን ሰዎች ለመርዳት ቆርጣ ተነሳች፡፡
___________________________

አስፈላጊ የሆነውን ትምህርት እና ለ250 ሰአታት ከወሰደች በኋላ እና የሙያ ፈቃድ ከገኘች በኋላ በኦንላይን ይሄንን አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በስሟ ከፈተች፡፡


___________________________

ዛሬ የግሬስ ሂፕኖሲሰ ድርጅት ከሁለት መቶ ሃምሳ ሺ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይሄንን አገልግሎት በኦንላይን ይሰጣል፡፡

___________________________

ከደንበኞቿ ውስጥ ታዋቂ አትሌቶች፤ አርቲስቶች እና የትልልቅ ድርጅት መሪዎች ይገኙበታል፡፡

___________________________

በተጨማሪም ግሬስ ከሂፕኖሲስ ጋር የተገናኙ ሁለት መፅሃፍትን ፅፋ ለንባብ አብቅታለች፡፡

ግሬስ ለአዲስ ቢዝነስ ፈጣሪዎች የምትመክረው✅

✅ህልም ካላችሁ ጠንክሮ ለመስራት ተዘጋጁ፡-

እኔ የሙሉ ጊዜ ስራዬን እየሰራሁ ነው ማታ ማታ ሂፕኖቴራፒ የተማርኩት፡፡
___________________________

ስራዬን ባቆም የቤት ኪራይ የምከፍልበት፤ የምበላበት እና ለትምህርቱ የምከፍልበት ገንዘብ አይኖረኝም ነበር፡፡
___________________________
የሂፕኖቴራፒ ትምህርት ደግሞ ብዙ ማንበብ እና ማጥናት የሚፈልግ ስለሆነ ይደክመኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንክሬ በመስራት እዚህ ደርሻለሁ፡፡

___________________________

✅ ሪስክ መውሰድ ይኖርባችሁዋል፡-

ቋሚ ስራ እና ቋሚ ደመወዝ ትቶ ቢዝነስ መጀመር በጣም ያስፈራል፡፡ ያስጨንቃልም፡፡

___________________________
ነገር ግን በራሴ ላይ እና በቢዝነሱ ላይ ስለተማመንኩ ሊያውም በውዷ ከተማ ኒውዮርክ ውስጥ ሆኜ ስራዬን አቆምኩ፡፡ በጣም ትንሽ ቢሮ ተከራይቼ ቢዝነሱን ጀመርኩ፡፡

___________________________

✅ ለለውጥ መዘጋጀት፡- በኦንላይን ሂፕኖቴራፒ መስጠት የእኔ ሃሳብ አይደለም፡፡ ነገር ግን ደንበኞቼ ለስራ እና ለእረፍት ከከተማ ሲወጡ ወደ ቢሯችን መጥተው መገልገል አልቻሉም፡፡

___________________________
ነገር ግን ቴራፒው እንዲቋረጥም አልፈልጉም፡፡ ስለዚህ በኦንላይን መጠቀሙን እነሱ ነበሩ የመከሩኝ፡፡
___________________________
ደንበኞቼን ሰምቼ የአገልግሎት አሰጣጤን ለመለወጥ ፈቃደኛ ሆንኩኝ፡፡
___________________________
በርግጥ በሰአቱ የቴክኖሎጂ እቃዎችን ለመግዛት ብዙ ወጪ ቢያስወጣኝም አሁን ግን ትርፋማ አድረጎናል፡፡

__________________________

'' #ግሎባል-ጤና እና #አስደናቂ እውነታዎች

#join us👇 & #SHARE { #ሼር }

✨🇪🇹 @global_Health1
✨🇪🇹 @global_Health1bot