Maths Group11
5.02K subscribers
317 photos
3 videos
1.59K files
406 links
The main purposes of this channel are to:
1. 📝 Provide various Mathematics questions and exercises.
2. 📚 Share and publish different educational books.
3. 📖 Provide useful short notes and study materials.

For more, contact us through: @Fikiru_Asnake
Download Telegram
#ASTU/AASTU

Barattoota Yuunivarsiitii saayinsii fi teeknooloojiitti barachuuf galmooftan hundaaf,

Barattoota Yunivarsiitii Saayinsii fi Teeknooloojii Adaamaa fi Yuunivarsiitii Saayinsii fi Teeknooloojii Addis Ababaatti damee Applied Saayinsii fi Injinariingiitin bara barnootaa 2018tti barachuuf galmaa'aniif qormaanni seensaa kan kennamu Kibxata Fulbaana 20, 2018 ganama keessa sa'aatii 2:00 irratti akka gaggeeffamu isin beeksifna.

Yaadachiisa:-
➫ Dorgomtoonni galma'uu keessan kan agarsiisu website irratti galmooftan irra buusun print gochuun harkatti qabachuu qabdu.

➫ Dorgomtoonni sa'aatii qormaata dursanii eenyummaa isaanii kan ibsu waraqaa eenyummaa fi kaardii galmee(admission card) qabatanii wiirtuu qormaataa yeroo galmee filattan gahuu qabu.

➫ Dorgomtoonni bilbila harkaa fi sa'aatii ismaartii gara wiirtuu qormaataatti fiduun dhorkaadha.

Yuunivarsiitii Saayinsii fi Teeknooloojii Adaamaa fi Yuunivarsiitii Saayinsii fi Teeknooloojii Addis Ababa
❤2
#ASTU
#Result_Announcement

👉 በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈትናችሁ ፣ በ2018 ዓ.ም በሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ እና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው መመደባችሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ፣ አድሚሽን ቁጥራችሁን እና የመጀመሪያ ስማችሁን በማስገባት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲን መቀላቀላችሁን መመልከት ትችላላችሁ 👇

https://stuexam.astu.edu.et/
#ASTU

🎓 For anyone who wants to join ASTU!
Are you planning to join Adama Science and Technology University (ASTU)? This is for you! 🚀

@maths_group11
❤3🥰1
Maths Group11
#ASTU 🎓 For anyone who wants to join ASTU! Are you planning to join Adama Science and Technology University (ASTU)? This is for you! 🚀 @maths_group11
#ASTU_and_AASTU

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
===============================
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርት መስኮች፡-

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡
www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
❤4🔥2👍1🥰1
Maths Group11
#ASTU_and_AASTU የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ =============================== በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም…
#ASTU_and_AASTU!

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
===============================
በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች የመግቢያ ፈተና ለመፈተን  በኦንላይን (online) የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ስለሆነ በእለቱ  በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ መፈተን የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· ተፈታኞች በእለቱ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያዎች መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
· በፈተናው ዕለት የሞባይል ስልኮችን እና ማንኛውንም እሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
¡ ፈተናው የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ  መሆናቸዉን በድጋሜ እናሳስባለን፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
❤4
#ASTU!

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ማስታወቂያ

ዩኒቨርሲቲው ለ2019 ዓ.ም መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ አዲስና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናትን እንደሚከተለው አሳውቋል፡-
የምዝገባ ቀናት: መስከረም 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ገለጻ (Orientation): መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ።

የመጨረሻው የምዝገባ ቀን: መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም።

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን: መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ መያዝ የሚገባቸው ነገሮች፡-

የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒ፡-

1. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት።
2. ከ9-12 ክፍል የተማሩበት ትራንስክሪፕት።
3. 4 የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ።
4. አንሶላና ብርድ ልብስ።
5. የስፖርት ልብስና ጫማ።

👉ከተጠቀሱት ቀናት ውጭ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ: የክረምት ኢንተርንሺፕ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ለተጨማሪ መረጃ፡
www.astu.edu.et ይጎብኙ።
❤2