Meba Microfinance Institution S.C (መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ)
1.41K subscribers
353 photos
33 videos
21 files
235 links
ይህ ገጽ የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ መልዕክቶች እና መረጃዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው::
Download Telegram
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የመጀመሪያ የሆነውን ቅርንጫፍ በመክፈት በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡

መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የመጀመሪያ የሆነውን ቅድስተ ማርያም ቅርንጫፍ የተቋሙ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች እና የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ ሐምሌ 29/ 2016 ዓ.ም በመክፈት በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡

በቅርንጫፍ መክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የዳሪከተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌትነት ኃይሌ ተቋሙ ሥራ መጀመሩን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ከብዙ ጥረትና ድካም በኋላ ሥራ መጀመሩን የገለጹ ሲሆን ለባለአክሲዮኖችና ለተቋሙ አጋር አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ አክለውም ሀገራችን በኢትዮጵያ በድህነት ውስጥ ያሉ በርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ እነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎችን የፋይናንስ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ ዓላማውን ማሳካት እንዲችል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ለመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች፣ ለባለ አክሲዮኖች እና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የመጀምሪያ የሆንውን ቅርንጭፍ በአዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ ቅድስት ማርያም ቅርንጫፍ በሚል ስያሜ ሥራ የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ግዜያት በአዲስ አበባ እና በክፍለ ሀገር ተጨማሪ ቅርንጫፎች እንደሚከፈቱ ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
👏17👍4🏆4❤1
መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ከደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ጋር መሥራት በሚያስችለው ተግባር ላይ የስምምነት ውል ተፈራረመ፡፡

መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም የተመሠረተበትን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ አስቻይ ከሆኑት አማራጮች አንዱ ከደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎትና መሰል ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት መሆኑን እንደሚያምን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ ማሞ በፊርማ ሥነ ሥረዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎችን የፋይናንስ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱአምላክ ይበልጣል በበኩላቸው ተቋሙ በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የተሠማራ መሆኑን ገልጸው ድርጅቱ ነባር የሀጋራችን እውቀትና ምርምርን መሠረት አድርጎ የተቋቋመ እና በዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማበርከት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ የፊርማ ስምምነቱ በመባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ ማሞ እና በደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱአምላክ ይበልጣል በኩል ተከናውኗል፡፡
👍19🔥2❤1👏1
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የሚሰጣቸው የቁጠባ አይነቶች

Follow Us

LinkedIn: http://www.linkedin.com/in/meba-microfinance-mfi
Twitter(X): https://x.com/MebaMfi1221
TikTok: https://www.tiktok.com/@mebamfi?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61563911902938
Telegram Group: https://t.me/mebamf
Telegram Channel: https://t.me/mebamfisc
👍13👏5❤1