Meba Microfinance Institution S.C (መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ)
1.4K subscribers
352 photos
33 videos
21 files
234 links
ይህ ገጽ የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ መልዕክቶች እና መረጃዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው::
Download Telegram
መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ከደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ጋር መሥራት በሚያስችለው ተግባር ላይ የስምምነት ውል ተፈራረመ፡፡

መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም የተመሠረተበትን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ አስቻይ ከሆኑት አማራጮች አንዱ ከደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎትና መሰል ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት መሆኑን እንደሚያምን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ ማሞ በፊርማ ሥነ ሥረዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ መባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎችን የፋይናንስ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱአምላክ ይበልጣል በበኩላቸው ተቋሙ በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የተሠማራ መሆኑን ገልጸው ድርጅቱ ነባር የሀጋራችን እውቀትና ምርምርን መሠረት አድርጎ የተቋቋመ እና በዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማበርከት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ የፊርማ ስምምነቱ በመባዕ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ ማሞ እና በደሸት ትምህርትና ሥልጠና አገልግሎት አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱአምላክ ይበልጣል በኩል ተከናውኗል፡፡
👍19🔥2❤1👏1
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የሚሰጣቸው የቁጠባ አይነቶች

Follow Us

LinkedIn: http://www.linkedin.com/in/meba-microfinance-mfi
Twitter(X): https://x.com/MebaMfi1221
TikTok: https://www.tiktok.com/@mebamfi?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61563911902938
Telegram Group: https://t.me/mebamf
Telegram Channel: https://t.me/mebamfisc
👍13👏5❤1
Channel name was changed to «Meba Microfinance Institution S.C (መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ)»
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤ እና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን!
Follow Us

LinkedIn: http://www.linkedin.com/in/meba-microfinance-mfi
Twitter(X): https://x.com/MebaMfi1221
TikTok: https://www.tiktok.com/@mebamfi?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61563911902938
Telegram Group: https://t.me/mebamf
Telegram Channel: https://t.me/mebamfisc
🙏14❤5👍2
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ በይፋ ሥራ ጀመረ፣
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ በሁለት ቅርንጫፎች ሥራ በመጀመር የፋይናንስ ዘርፉን ተቀላቀለ። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ፈቃድ በማግኘት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል፡፡

የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጌትነት ኃይሌ በተቋሙ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ወቅት እንደተናገሩት በኢትዮጵያ አብዛኛው ማኅበረሰብ በበቂ ሁኔታ በፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ሳይሆኑ ቆይተዋል፡፡ አክለውም መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ በተደራሽነትና በአገልግሎት አሰጣጥ በኩል ያለውን ክፍተት በማሻሻል ሰፊ መሠረት ያለው የአነስተኛ ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የተቋቋመ መሆኑን ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

የቦርድ ሰብሳቢው የተቋሙ ምስረታ በስኬት እንዲጠናቅቅ ያገዙትን የአደራጅ ኮሚቴ አባላትን፣ ባለ አክሲዮኖች እንዲሁም ሌሎች ደጋፊ አካላትንም አመስግነዋል።

በመርሐ ግብር ላይ የተገኙት የአሐዱ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ በበኩላቸው አሁን በሀገራችን የሚታየውን የፋይናንስ አግለግሎት ክፍተት መፍታት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ይሄንን ችግር ለመፍታት የራሱን አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ያላቸውን ተስፋ ገልጸው በቀጣይ አሐዱ ባንክ ከመባዕ ጋር እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

በመጭረሻም መባዕ የጋራችን ተቋም እንደመሆኑ ተቋሙን በጋራ ማሳደግ እንደሚጠበቅ ያስረዱት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ ማሞ ሲሆኑ ለዚህ ደግሞ ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
👍33🔥7👏2