M.O.R East Addis Ababa Branch
25.3K subscribers
6.52K photos
18 videos
631 files
390 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት ግብር አሳውቆ መክፈያ ወቅት በመሆኑ ቅስቀሳ ማድረግ ጀመረ
……….
የ2018 በጀት ዓመት ግብር አሳውቆ መክፈያ ወቅት ከሃምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 መሆኑ ይታወቃል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቦሌ ክፍለ ከተማና በለሚ ኩራ ክፈለ ከተማ ከሚገኙ ግብር ከፋዮች ግብርን የሚሰበስብ ሲሆን ጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በክፍለ ከተሞቹ በመዘዋወር ቅስቀሳ ማድረግ ጀምሯል ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል ላይ መኆኑና ሌሎች ግብር ከፋዮችም ጥቅምት 30 ከመድረሱ በፊትም በቀሩት ጥቂት ቀናት ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉም ጥሪውን አስተላፏል
❤9🙏1
ተቀናሽ  የሚደረጉ  ወጪዎች
ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለመወሰን የሚከተሉት ከጠቅላላ ገቢ ላይ ይቀነሳሉ
በገቢ ግብር አዋጅ የተመለከቱ ገደቦች እንደተጠበቁ ሆኖ በንግድ ስራ ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ ለንግዱ ስራ ዋስትና ለመስጠትና የንግድ ስራውን ለማስቀጠል በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የተደረጉ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች፣
Ø በግብር ዓመቱ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ (trading stock) የወጣ ወጪ፣
Ø በንግድ ስራው ላይ ሲውሉ ዋጋቸው የሚቀንስ የንግድ ስራ ሃብቶችና ግዙፋዊ ህልወት ለሌላቸው የንግድ ስራ ሃብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣
Ø የንግድ ዕቃን ሳይጨምር ግብር ከፋዩ በዓመቱ ውስጥ የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የገጠመው ኪሣራ፡፡
Ø በሠራተኛው የጤና ዕቅድ መሰረት ቀጣሪ በተቀጣሪ ስም የሚከፍለውን የጤናመድን አርቦን ጨምሮ ለሠራተኛው የሕክምና አገልግሎት የሚያወጣው ወጪ ሲሆኑ በታክስ ህጉ የተፈቀዱ ሌሎች ዝርዝር ተቀናሽ ወጪዎች በመመሪያ ቁጥር 5/2011 ይመልከቱ  ፡፡
❤10👍5
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የደንበኞች አያያዝ ስልጠና ሰጠ
ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም. (የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጸሐፊዎች እና ለመልዕክት ሰራተኞች የደንበኞች አያያዝ ስልጠና ሰጠ። ስልጠናው የተዘጋጀው በሰው ሀብት ልማት አስተባባሪነት ሲሆን፣ የተሰጠውም በተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን ክፍል አማካኝነት ነው።
ስልጠናውን በማስጀመር መልዕክት ያስተላለፉት የሰው ኃይል ሙሌትና ሥራ ምዘና ቡድን አስተባባሪ አቶ ደሱ ነጋሽ፤ የጸሐፊነትም ሆነ የመልዕክት ስራ ሚስጥር ጠባቂነትን፣ የጊዜ አጠቃቀምን እና የተግባቦት ክሂልን በይበልጥ የሚጠይቅ ስራ መሆኑን ገልጸው፣ ሰራተኞች እነዚህን ክህሎቶች በስራቸው ላይ ማዳበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ወላንሳ ወጋየሁ በበኩላቸው፤ በጸሐፊነትና በመልዕክት አገልግሎት የሚሰጥ ሰራተኛ ሊኖረው የሚገባውን የሥራ ዲሲፕሊን ጠቁመዋል። በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተዋረድ የሚተላለፍ መልዕክት ትክክለኛ ይዘቱን ይዞ እንዲሄድ የሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ፣ ተግባቦቶች መደበኛ ስልቶችን በመጠቀም መተላለፍ እንዳለባቸው እና ይህም ለተቋሙ ገጽታ ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል።
የተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አዲሱ በበኩላቸው፤ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ (Customer Service Delivery) ስልጠና ሰጥተዋል። በስልጠናቸውም የጸሐፊ እና የመልዕክት ሠራተኞች በተቋሙ ውስጥ የሥራ ሂደት እንዲሳለጥ፣ መረጃ በትክክል እንዲተላለፍና የድርጅቱ የቀን ተቀን እንቅስቃሴ እንዲሳካ አስፈላጊ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። ሰራተኞቹም ለደንበኞች ቅድሚያ በመስጠት ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ማከናወን፣ ወደ ቅ/ጽ/ቤቱ የሚመጡ አካላትን በትህትና እና በቅንነት ማስተናገድ፣ እንዲሁም በኃላፊዎች የተሰጡ ውሳኔዎችን በቅልጥፍና ለፈጻሚ አካላት በወቅቱ ማድረስ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
❤5🤯1