ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ጥቅምት 27/2019 //ምስራቅ አ/አ/አነ/ግለ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት//
የ2018 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ማስታወቂያ እና መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርቷል ። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም በቀሩት ቀናት ለማስታወቅና ለመክፈል ለሚመጡ ግብር ከፋዮች የአገልግሎት አሰጣጡ ሁኔታ ምን እንደሚመስል በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ፣ እንዲሁም ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የተቋማዊ ሥጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ከተመረጡ ኮሚቴዎች ጋር በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረጉ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በዚህ አጋጣሚ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር እስካሁን ያላሳወቃችሁና ያልከፈላችሁ ግብር ከፋዮች፣ በቀሩት ሁለት ቀናት ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ የታክስ ማሳወቂያ (e-Tax) ሥርዓት በመጠቀም ግዴታችሁን እንድትወጡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

❤1👏1