የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ማወቅ የሚገቡዎት አዳዲስና የተሟሉ ሕጋዊ ነጥቦች! 📋📊
የታክስ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ፣ አጠቃቀም እና አዳዲስ ግዴታዎች ምን እንደሚመስሉ እነሆ፦
1. የታክስ ክሊራንስ ማመልከቻ እና የጊዜ ገደብ
ማንኛውም ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀቱ እንዲሰጠው ለባለሥልጣኑ ማመልከት ይችላል።
ባለሥልጣኑ ታክስ ከፋዩ ግዴታውን መወጣቱን ሲያረጋግጥ በ14 ቀናት ውስጥ መስጠት አለበት።
ለቀደሙት ዓመታት ያልተመዘገበ ታክስ ከፋይ ማመልከቻ ቢያስገባም፣ ምዝገባው ተጠናቆ በ14 ቀናት ውስጥ የምስክር ወረቀቱ ይሰጠዋል።
ባለሥልጣኑ ክሊራንሱን ላለመሰጠ ከወሰነ፣ ማመልከቻው በቀረበ በ14 ቀናት ውስጥ ያልተቀበለበትን ምክንያት የሚገልጽ የውሳኔ ማስታወቂያ ይሰጣል።
2. የታክስ ክሊራንስ አገልግሎት የሚሰጠው ለምንድን ነው? (ግዴታዎች)
የምስክር ወረቀቱ ከሌለ የሚከተሉትን ማከናወን አይቻልም፦
🛒 የንግድ ሥራ ወይም የሙያ ፈቃድ ለማደስ
🏛 በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ
🚗 ለተሽከርካሪዎች ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ /ክላውዶ/
🏦 የባንክ ብድር ለማግኘት
ማሳሰቢያ: ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ ማዘጋጃ ቤት ወይም ቢሮ የታክስ ክሊራንስ ካልቀረበ በስተቀር ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ ወይም በጨረታ ማሳተፍ አይችልም!
3. በሁኔታ ላይ የተመሠረተ (Conditional) የታክስ የምስክር ወረቀት
ያልተከፈለ የታክስ ዕዳ ቢኖርም በሚከተሉት ሁኔታዎች የምስክር ወረቀት ማግኘት ይቻላል፦
⚖️ የታክስ መቃወሚያ፣ ይግባኝ ወይም ክርክር የቀረበ ከሆነ
🤝 የሚፈለግብዎትን ዕዳ ለመክፈል ከባለሥልጣኑ ጋር የጸና የክፍያ ስምምነት የተፈጸመ ከሆነ
የጊዜ ገደብ እና መሻር፡ በአንቀጽ 72 መሠረት የሚሰጠው ይህ የምስክር ወረቀት ተፈጻሚ የሚሆነው ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪ

❤8
የታክስ ህጎች፣ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና መስጠቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል
............
ኅዳር 4/2019 //በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት //
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በታክስ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለግብር ከፋዮች በተከታታይ የሚሰጠውን “ሞጁላር” የተሰኘ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥላል ፤በዚህም የበጀት ዓመቱ የህዳር ወር የሞጁላር ስልጠና በትናትናው እለት መስጠት ጀምሯል፡፡
የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ የሺወርቅ ተጫነ የስልጠናውን መጀመር አስመልክተው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ታክስ ከፋዮች በቂ የታክስ ዕውቀት ኖሯቸው ግብራቸውን በሃላፊነት አዋጅ ፣ህግንና መመርያን ተከትለው መክፈል እንዲችሉ ታሰቦ ስለጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል ።አያይዘዉም ከሰልጣኞች የሚጠበቀው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ያገኙትን ስልጠና ተገባር ላይ እንዲውሉ አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም አቶ ውቡ ፈንታው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ በመጀመሪያ ሴምስተር ከሚሰጠው ስልጠና መሀከል ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚለውን ርአስ ለሰልጣኞቹ ማሰልጠን ጀምረዋል፡፡

❤10
Forwarded from Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
የግብር ሒሳብ መዝገብ አያያዝን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ
ሕዳር 4/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ሒሳብ መዝገብ አያያዝን ለማሻሻልና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ለማጣጣም በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከተለያዩ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ መድረክ ላይ ተገኝተው ውይይቱን ያስጀመሩት የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ታምራት በየነ፣ መመሪያዎች ጸድቀው ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት ጠቃሚ ግብዓቶችን ለማካተተ ይረዳል ያሉ ሲሆን በተለይም ግልጽነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተናግረወል።
በመድረኩ ረቂቅ መመሪያውን አሰመልክቶ ገለፃ ያደረጉት የሚኒስቴሩ የሕግ ዳይሬክተር አቶ አበረ አስፋው ፣ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያው በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የታዩ ለውጦችንና ወቅቱ የሚጠይቀውን የአሠራር ለውጥ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መመሪያውን የማሻሻል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አክለውም የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከወቅቱ የቢዝነስ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም፣ በአሠራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍና መመሪያው ግልጽ እንዲሆን በማሰብ ረቂቅ መመሪያው ተዘጋጅቶ በየደረጃው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ብለዋል።
ረቂቅ መመሪያውን በዝርዝር ያቀረቡት የሕግ ባለሙያ አቶ ቢኒያም ስዩም ሲሆኑ፣ በሰነዱ ላይ የተለያዩ የማሻሻያ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል።
በምክክር መድረኩ ከሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ዳይሬክተሮችና አማካሪዎች፣ ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተውጣጡ ፣ ሥራ አስኪያጆችና ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በታደሰ ኢብሳ
ፎቶ፡- ክፍሌ አዳፍሬ

❤11