Forwarded from Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
የግብር ሒሳብ መዝገብ አያያዝን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ
ሕዳር 4/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ሒሳብ መዝገብ አያያዝን ለማሻሻልና ከወቅቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ለማጣጣም በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከተለያዩ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ መድረክ ላይ ተገኝተው ውይይቱን ያስጀመሩት የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ታምራት በየነ፣ መመሪያዎች ጸድቀው ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት ጠቃሚ ግብዓቶችን ለማካተተ ይረዳል ያሉ ሲሆን በተለይም ግልጽነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተናግረወል።
በመድረኩ ረቂቅ መመሪያውን አሰመልክቶ ገለፃ ያደረጉት የሚኒስቴሩ የሕግ ዳይሬክተር አቶ አበረ አስፋው ፣ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያው በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የታዩ ለውጦችንና ወቅቱ የሚጠይቀውን የአሠራር ለውጥ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መመሪያውን የማሻሻል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አክለውም የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከወቅቱ የቢዝነስ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም፣ በአሠራር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍና መመሪያው ግልጽ እንዲሆን በማሰብ ረቂቅ መመሪያው ተዘጋጅቶ በየደረጃው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ብለዋል።
ረቂቅ መመሪያውን በዝርዝር ያቀረቡት የሕግ ባለሙያ አቶ ቢኒያም ስዩም ሲሆኑ፣ በሰነዱ ላይ የተለያዩ የማሻሻያ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል።
በምክክር መድረኩ ከሚኒስቴሩ ዋና መሥሪያ ቤት ዳይሬክተሮችና አማካሪዎች፣ ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተውጣጡ ፣ ሥራ አስኪያጆችና ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በታደሰ ኢብሳ
ፎቶ፡- ክፍሌ አዳፍሬ

❤11
ስኬት በትክክለኛ አመራር በስትራቴቴጂካዊ አስተሳስብ ፣በትብብር ፣በተነሳሽነት በውጤታማ ውሳኔ ላይ ይመስርታል።’’ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራ አስኪያጅ
---------------------------------
ህዳር 7/2019 ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት ከወትሮ ለየት ባለመልኩ የማኔጅመንቱ አባላትን ከፍተኛ አመራሩር ፣የስራ ሂደት እንዲሁም ቡድኖችንና ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙዎችን ይዞ የ2019 የአራት ወር አፈጻጸም ለመገምገምና ለአመራሩ አቅም ግንባታ የሚሆን የግንዛብዬ ማስጭበጫ ስልጠና እንዲያገኝ በማለት በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ተገኝቷል።
ይሕንንም በማስመ ልከት ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታችው ስኬት በትክክልኛ አመራር በስትራቴቴጂካዊ አስተሳስብ ፣በትብብር ፣በተነሳሽነት በውጤታማ ውሳኔ ላይ ይመስርታል፣አመራር ማለትም ትእዛዝ ከመስጠት ባሻገር አቅጣጫ ማሳየት ለስራው ማነሳሳት ችግሮችን በአግባቡ በመፍታት የጋራ ወጤት ማምጣት ይጠይቃል ፣ከአመራሩም ይሕ ይጠብቃል ብለዋል ።
ጠንካራ ተቋም የሚገነባው በብቃት በተነሳሽነት ፣በትብብርና በቁርጠኝነት በሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች በመሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባብ እንዲሰልጥኑ በማሳስብ ሰልጠናወን በይፋ አስጀምረዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የአእምሮ ውቅር /Mindset / በሚል ርእስ በፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ አዘጋጅነት ተሰጥቷል።
በቀጣይ ሁለት ቀናት በዚህ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል ።

❤9👍1😁1