አማራጭ አነስተኛ ግብርን ስለማቀናነስ (በተሻሻለዉ የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 597/2019 መሠረት)
፩/ ግብር ከፋዩ በአንድ የግብር አመት ከሁሉም የንግድ ስራ የገቢ ምንጮች ባገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ የከፈለው 2.5% (ሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) አማራጭ አነስተኛ ግብር ሊከፍል ከሚገባው ግብር በላይ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ሊከፍል ከሚገባው በላይ የከፈለው ግብር በሚቀጥለት አምስት አመታት ከሚከፈል ግብር ላይ ተቀናሽ ሊደረግ ይችላል።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት ተቀናሽ ሊደረግ የሚችለው የሚከተለት ሁኔታዎች ሲሟሉ ይሆናል፦
ሀ) ግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ የያዘ ከሆነ፤
ለ) አማራጭ አነስተኛ ግብር በተከፈለበት የግብር ዓመት ግብር ከፋዩ ሊከፍል የሚገባው ግብር ከአመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከ2.5 በመቶ (ሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) በታች ሊሆን እንደሚገባ በታክስ ባለስልጣኑ ሲረጋገጥ፤ እና
ሐ) ተቀናሽ በሚደረግበት የግብር ዓመት ግብር ከፋዩ የከፈለው ግብር ከ2.5 በመቶ (ሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) በላይ ሲሆን እና አማራጭ አነስተኛው ግብር እንደተጠበቀ ሆኖ ለተቀናሽ የሚውል ተከፋይ ግብር ያለ እንደሆነ፤
፫/ አማራጭ አነስተኛ ግብር ያለፉትን አመታት ኪሳራ ወደፊት በማሸጋገር ላይ የሚገኝ ግብር ከፋይ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። ስለሆነም ግብር ከፋዩ ካለፉት የግብር አመታት የተሸጋገረ ኪሳራ ያለው እንደሆነ ኪሳራው ሊካካስ የሚችለው በግብር ዓመቱ ሊከፈል ከሚገባው አማራጭ አነስተኛው ግብር በላይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ያለው በሚሆንበት ጊዜ ይሆናል።

❤13