M.O.R East Addis Ababa Branch
25.8K subscribers
6.66K photos
18 videos
658 files
392 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
❤3🙏2
📋 በታክስ  áˆ›áˆťáˆťá‹Ť   á‹°áŠ•á‰Ľ ቁጥር597 /2019  áˆ˜áˆ°áˆ¨á‰ľ  ለደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች፡ የሩብ ዓመት ቅድመ ግብር ክፍያ እና የጊዜ ሰሌዳ

📢 ለደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች፡ የሩብ ዓመት ቅድመ ግብር ክፍያ እና የጊዜ ሰሌዳ
የንግድ ተቋምዎን የግብር ግዴታ በወቅቱ ለመወጣት እና ከአላስፈላጊ ቅጣት ለመዳን እነዚህን ሶስት ቁልፍ ነጥቦች ያስታውሱ፦
🗓 1. የክፍያ እና የሪፖርት ጊዜ ሰሌዳ
¡         የሂሳብ ዓመታቸው በሰኔ የሚያልቅ (እስከ ጥቅምት መጨረሻ ሪፖርት የሚያቀርቡ)፦
o    የቅድመ ግብር ወራት፦ ጥር፣ ሚያዝያ እና ሐምሌ
o    ዓመታዊ ጠቅላላ ክፍያ፦ እስከ ጥቅምት መጨረሻ (ከሐምሌ 1–30 አሳውቀው ጠቅልለው ከከፈሉ የሐምሌው ቅድመ ክፍያ አይመለከታቸውም)
¡         የሂሳብ ዓመታቸው በዲሴምበር የሚያልቅ (እስከ ኤፕሪል መጨረሻ ሪፖርት የሚያቀርቡ)፦
o    የቅድመ ግብር ወራት፦ ጁላይ፣ ኦክቶበር እና ጃንዋሪ
o    ዓመታዊ ጠቅላላ ክፍያ፦ እስከ ኤፕሪል መጨረሻ (እስከ ጃንዋሪ መጨረሻ አጠቃለው ከከፈሉ የጃንዋሪው ቅድመ ክፍያ አይመለከታቸውም)
¡         በሌላ የጊዜ አቆጣጠር የሚያቀርቡ፦
o    ሪፖርት ከቀረበበት ወር ቀጥሎ በሶስት ወር ልዩነት ይከፈላል (በመጀመሪያው ወር አሳውቀው ከከፈሉ የሶስተኛው ወር ቅድመ ክፍያ አይመለከታቸውም)።
🧮 2. የስሌት መሠረት
¡         በየሩብ ዓመቱ የሚከፈለው ግብር የሚሰላው ባለፈው የግብር ዓመት በተከፈለው ግብር ላይ ተመስርቶ ነው።
¡         ባለፈው ዓመት ኪሳራ ካጋጠመ ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ካልነበረ፣ መሠረቱ ግብር የተከፈለበት የመጨረሻው ዓመት ይሆናል።
¡         በታክስ ባለሥልጣኑ በልዩነት እንዲከፈል የተወሰነ ግብር ካለ ከዋናው ግብር ጋር ተደምሮ ይሰላል (ወለድና ቅጣትን ሳይጨምር)።
➖ 3. ተቀናሽ ሂሳብ
¡         ባለፈው ሩብ ዓመት ከተከፋይ ሂሳብ ተቀንሶ የቀረ ግብር (Withholding Tax) እና ወደ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተከፈለ የቅድሚያ ገቢ ግብር ከሩብ ዓመቱ ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።
¡         በዚያው ሩብ ዓመት ሳይቀነስ ቢቀር እንኳን በቀጣዮቹ ሩብ ዓመታት ወይም ዓመታዊ የሂሳብ መዝገብ ሲቀርብ ማቀናነስ ይቻላል።
📌 ማሳሰቢያ፡ የገቢዎች ሚኒስቴር የቅድመ ግብር የጊዜ ሰሌዳን የሚወስን መመሪያ ሊያወጣ ይችላል።ደቦችን በካላንደርዎ መመዝገብ እና የተቆረጡ/የተከፈሉ የቅድሚያ ግብር ደረሰኞችን በጥንቃቄ መያዝ የጥሬ ገንዘብ ፍሰትዎን (Cash Flow) ለማስተካከል እና ተጨማሪ ወጪዎችን ለማስቀረት ይረዳል።
❤10😁1
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ አመራሮች  ሰራተኞች በ26ኛው  የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር ተሳታፊ ሆኑ
……
ህዳር 14/2019 ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
 
26ኛው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር እሑድ ህዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ህዳር 22/2026) በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በወንዶች ዘርፍ ይስማው ድሉ እንዲሁም በሴቶች ዘርፍ የኔዋ ንብረት አሸናፊ ሆነዋል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ ዓመራሮችና ተሳታፊዎች  ተሳታፊ ሲሆኑ ሜዳልያ   áŠ¨á‰°á‰ áˆ¨áŠ¨á‰°áˆ‹á‰¸á‹ ውስጥ  áŠ á‰ś ማቴዎስ አየለ  የታክስ ኦፕሬሽን  áˆ/ ሾል አስኪያጅ   áˆŠáŒŤá‹áŠ• ከመውዳደር  ከመጨረስ  áŒ‹áˆ­   የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን  የመቻልና  የመፈጸምን አቅም ምልክ ት መሆኑን  በሩጫ  በመግለጽ  á‹á‹ľá‹ľáˆŠ   áŠ áŒ áŠ“á‰€á‹‹áˆ  ፡፡
❤8
“የፌደራል የገቢ ግብር ደንብ (ማሻሻያ ) ቁጥር 597/2019”  áˆ˜áˆ°áˆ¨á‰ľ
የግብር ከፋዮች ደረጃ እንዴት ይወሰናል?  (አንቀጽ 52 እና 53)
የንግድዎን የግብር ከፋይ ደረጃ ማወቅ ለትክክለኛ የግብር አስተዳደር እና ሕጋዊ አሠራር ወሳኝ ነው። በደንቡ መሠረት ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፦
🔹 የደረጃ አወሳሰን መሠረት (አንቀጽ 52): የግብር ከፋይ ደረጃ የሚወሰነው ግብር ከፋዩ በተሰማራበት በሰንጠረዥ "ለ" እና "ሐ" የግብር ማስከፈያ ሰንጠረዦች ስር የሚወድቀውን ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ መሠረት በማድረግ ነው።
🔹 ዓመታዊ ምደባ እና ጽናቱ (አንቀጽ 53/1): ምደባው በእያንዳንዱ የግብር ዓመት በተናጠል ይከናወናል፤ ሳይለወጥም ለግብር ዓመቱ ሙሉ ያገለግላል።
🔹 የደረጃ "ሀ" ቋሚነት (አንቀጽ 53/2): በአንድ የግብር ዓመት የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ ሆኖ የተመደበ ግብር ከፋይ፣ ከዚያ በኋላ ባሉት የወደፊት ዓመታት ሁሉ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ ሆኖ ይቀጥላል።
🔹 የሚታሰበው ጠቅላላ ገቢ ምንድን ነው? (አንቀጽ 53/3እና 4):
¡         ለደረጃ "ሀ" ወይም "ለ" ምደባ የሚታሰበው ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ፣ በግብር ዓመቱ ከሰንጠረዥ "ለ" እና "ሐ" የተገኘ ጠቅላላ ገቢ ነው።
¡         ይህ ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ግብር የሚከፈልበትን ገቢም ሆነ ከግብር ነጻ የሆነ ገቢን ያካትታል።
🔹 ልዩ የደረጃ "ለ" አካታችነት  áˆľáˆˆ ደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ የተደነገገው ድንጋጌ፣ የአዋጁ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ (4) ተፈጻሚ የሚሆንባቸውን የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮችም ይጨምራል።
💡 ውድ ግብር ከፋዮቻችን  áŚ ትክክለኛ ስሌት በመያዝ እና የደረጃ ምደባ ሕጎችን በመረዳት ንግድዎን በሕጋዊ መንገድ ያምሩ።
❤10🙏1