Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
49.3K subscribers
8.78K photos
128 videos
19 files
1.27K links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የብሔራዊ የታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ የሶስት ወራት የገቢ አሰባሰብ እና የሪፎርም ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ገመገመ

ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ክቡር አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ ሰብሳቢ እና የታስክ ፎርስ አባለት በተገኙበት የ2019 በጀት ዓመት የ(3) የሶስት ወራት የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል።

በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ3(ሶስት) ወራት የገቢ አሰባሰብ እና የተቋማት የሪፎርም ስራዎች ሪፖርት ለብሔራዊ የታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ ቀርቧል፡፡

የታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ የቀረበውን ሪፖርት በጥልቀት የገመገመ ሲሆን የሶስት ወራቱ የገቢ አሰባሰብ እና ሪፎርም ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገምግሟል፡፡

በማያየዝም በሶስት ወራቱ የተመዘገቡ የገቢ አሰባሰብ እና የሪፎርም ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በበኃይሉ ሽመልስ
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ
ማስታወቂያ ለግብር ከፋዮች!

ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ያልተከፋፈለ ትርፍ

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

“ያልተከፋፈለ ትርፍ” ማለት የኩባንያው የሒሳብ ዓመት ካለቀ በኋላ ባሉት አስራ ሁለት (12) ወራት ውስጥ ለባለአክሲዮኖች ያልተከፋፈለ ወይም የኩባንያውን ካፒታል ለመጨመር ያልዋለ ወይም የኩባንያውን አክሲዮን ለመግዛት ያመለከቱ ባለአክሲዮኖችን የአክሲዮን ዋጋ ለመክፈል ያልዋለ የተጣራ ትርፍ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው በቋሚነት በሚሰራ ድርጅት አማካኝነት የንግድ ሥራ ለሚያካሂድ የውጭ አገር ኩባንያ ያልተላከ ትርፍን ያካትታል።

ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በአንድ የግብር ዓመት ግብር ከተከፈለ በኋላ ለአባላቱ ያልተከፋፈለ እና መልሶ ኢንቨስት ያልተደረገ የተጣራ የድርጅቱ ትርፍ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር ይከፈልበታል።
ግብር ከፋዩ በረቂቅ መመሪያዎች ላይ ምክክር ማድረጉ ግዴታውን በፍቃደኝነት እንዲወጣ የሚያበረታታ እና ለትግበራ ምቹ እንደሚያደርግ ተጠቆመ

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በረቂቅ የግብር ሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ፣ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ እና የታክስ ውሳኔ መሳወቂያና ስህተት የማስተካከያ አግባብ ለመወሰን በተዘጋጀ መመሪያ ላይ የግብዓት ማሰባሰብ ምክክር አያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በገቢዎች ሚኒስቴር የታከስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ እና የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ገዙ የታክስ አስተዳደሩን ለማጠናከር፣ ፍታዊነትን ለማረጋገጥ፣ ብሎም ግልፅና እና ውጤታማ የታክስ ስርዓት ለመፍጠር አዎጆችን፣ ደንቦችን አና መመሪያዎችን የማውጣት እና የማሻሻል ስራዎች በስፋት መሠራታቸውን ጠቁመዋል።

በማያያዝም በመድረኩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተው በረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት እንዲሰጡ ሲደረግ መመሪያዎች ከጸደቁ በኃላ በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስችል አስረድተዋል። በተጨማሪም ግብር ከፋዩ ግዴታውን በፍቃደኝነት እንዲወጣ የሚያበረታታ ነው ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ተሳታፊዎች ካላቸው ተግባራዊ ልምድና ዕውቀት አንጻር በረቂቅ መመሪያዎቹ ላይ ገንቢ የሆነ ግብዓት እንደሚሰጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በዚሁ የረቂቅ መመሪያዎች ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የዘርፍ ምክር ቤት አመራሮች፣ የሂሳብ አዋቂዎች፣ የተፈቀደላቸው ኦዲተሮች፣ የክልል ገቢዎች ቢሮ ተወካዮች እና የሚመለከታቸው የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ባለሞያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በበኃይሉ ሽመልስ
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ
Ministry of Revenues and IMF Strengthen Strategic Partnership to Enhance Tax Compliance in Ethiopia’s Construction Sector

November 6/2026 (Ministry of Revenues)

The Ministry of Revenues has held consultative discussion with a delegation from the International Monetary Fund (IMF).

The discussion has aimed to advance efforts at strengthening tax compliance, addressing revenue leakages, and enhancing domestic revenue mobilization in Ethiopia’s construction sector.

Speaking at the occasion, Mr Osman Mohammed, Director of Strategic partnership at the Ministry of Revenues, underscored Ethiopia’s commitment to implementing a range of strategic initiatives aimed at strengthening domestic revenue mobilization and improving the effectiveness of the national tax administration system.

He emphasized that achieving sustainable domestic revenue growth requires coordinated institutional efforts, evidence-based policy interventions, and strengthened international cooperation.

In this regard, he highlighted the significant contribution of international development partners, particularly the IMF, in providing technical expertise and institutional support. He also conveyed the Ministry’s appreciation for the IMF’s continued engagement and partnership.

As part of the discussion, IMF delegation expert Jonathan Leigh Pemberton delivered a presentation on Operationalizing the Construction Sector Compliance Improvement Plan (CIP).

By:- Shimelis Sisay