Ministry of Trade and Regional Integration-Ethiopia
22.2K subscribers
7.69K photos
36 videos
14 files
874 links
An Official Channel of Ministry of Trade and Regional Integration. ይህ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር ኦፊሴላዊ ቻናል ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር፡ የ8ኛውየሥራ ቡድን ስብሰባ ዝግጅት ተገመገ
(አዲስ አበባ ፡ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም)

ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ለሚካሄደው 8ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) የሥራ ቡድን ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን ያደረገውን ዝግጅት በዛሬው ዕለት ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ የድርድር ቡድኑ አባላት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር እና የዓለም ንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ ለድርድሩ የተደረገው ዝግጅት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሚኒስትሯ አክለውም የኢትዮጵያ ልዑክ በስብሰባው ላይ የተቀናጀና የተናበበ ድርድር ማካሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ተደራዳሪ ቡድኑ ከ7ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ያገኛቸውን ተሞክሮዎች በመገምገም ለስምንተኛው ምዕራፍ በቂ ዝግጅት ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ወደ ፍጻሜው እየቀረበ ያለውን የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት በእጅጉ ያፋጥነዋል ተብሎ ይጠበቃል።
❤13
ኢትዮጵያ በ9ኛው የቻይና ዓለም አቀፍ የገቢና ወጪ ንግድ  ኤክስፖ (CIIE) ላይ ምርቶቿን እያስተዋወቀች ነዉ
(ሻንጋይ ፡ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም) በቻይና በየዓመቱ የሚዘጋጀውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው የቻይና ዓለም አቀፍ የገቢና ወጪ ንግድ (CIIE) ኤክስፖ ከትላንትናው ዕለት ኅዳር 5 ቀን 2026 ጀምሮ በሻንጋይ ከተማ በድምቀት መካሄድ ጀምሯል።
እስከ ኅዳር 10 ቀን 2026 በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ ላይ ኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ እየተሳተፈች ትገኛለች።
በፔጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኤክስፖው ተሳታፊ ተወካዮች በተገኙበት በድምቀት በተከፈተው በዚህ ታላቅ የንግድ መድረክ ላይ በተለያዩ የኤክስፖርት ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ላኪዎች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።
 ኤክስፖው ላኪዎቻችን አዳዲስ የዓለም አቀፍ ገበያ አማራጮችን እንዲያገኙና ነባር የገበያ ትስስሮችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ዛሬ በሁለተኛው ዕለት በደመቀ ሁኔታ በቀጠለው በዚህ ኤክስፖ፤ በኢትዮጵያ የማሳያ ቦታ (ፓቪሊዮን) የተዘጋጀው የቡና ማስቀመስ መርሃ-ግብር እና አገር በቀል ባህላዊ ውዝዋዜዎች በርካታ ጎብኚዎችንና የንግድ ተወካዮችን እየሳበ ይገኛል።
 በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋሙንና የአገራችንን ገጽታ የሚያስተዋውቁ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ ለማሳያ ቦታው ተጨማሪ ድምቀት ሆኗል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አገራችን በኤክስፖው የምታደርገውን ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ በማስተባበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተሳታፊ ላኪዎች ውጤታማ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ፣ ምርቶቻቸውን ለአለም አቀፍ ገበያ እንዲያ አስተዋውቁ እና የንግድ ውሎችን እንዲያመቻቹ አስፈላጊውን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።
❤6