Nuha Islamic posts
43 subscribers
19 photos
2 videos
4 links
Nuha islamic post 😍

Our goal is to create a reader generation
"Come, let's have fun and learn."
Download Telegram
አስተማሪ የነቢዩላህ ዳውድ ታሪክ

✍
ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት መጥታ እንዲህ አለቻቸው፡
🧕 «ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት

🧕 «አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ። ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ። 🦅 ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በርሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
👳‍♀ «አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ።🚤 ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን። 😊

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።

ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት። 😍

<< አሏህ ለኛ የተሻለውን እንጂ አያደርግም!!>> ❤️

#መልካም_ውሎ
ሼር ማድረግ አትርሱ 👆

@Nuha_bint_Muhammed
ይቀላቀሉን 👆👆
አጂብ… ልብ የሚነካ ታሪክ
አደራ ካነበቡ በኋላ ሼር ማድረጉን አይርሱ!!!
የገንዘብ ደሀ እውቀትን ፈላጊና አላህን ፈሪ የሆነ ወጣት ነበር ።
አንድ ቀን በጣም ስለራበው ረሀቡን የሚያስታግስለት ነገር ፍለጋ ከቤቱ ወጣ።
ነገር ግን ምንም አላገኘም በመንዱ ላይ እያለ አንድ የአትክልት ቦታ አገኘ ቦታው በአፕል ፍሬዎች የተሞላ ነበር።
አንዷ ዛፍ ወደመንገዱ ወጣ ብላ ስለነበር አንዷን በልቶ ረሀቡን ማስታገስ ፈለገ።
አንድ አፕል ቆርጦ በላ ወደቤቱ ከተመለሰ በኃላ ግን ነፍሱ ትወቅሰው ጀመር።
ከነፍስም ራሷን የምትወቀስ ጥሩ ነፍስ አለችና፣ እንዴት የኔ ያለሆነን ሀቅ ወይም ባለቤቱን ሳላስፈቅድ እበላለሁ ? ሲል አሰበ። ተመልሶ የአትክልቱን ባለቤት ፈልጎ ካገኘው በኃላ "በጣም ራበኝና ከአትክልት ቦታህ ሳታውቅና ሳላስፈቅድህ አንድ አፕል በልቻለሁና አሁን ላስፈቅድህ ፣ ይቅር እንድትለኝ መጥቻለሁ" አለው ። ባለቤቱ ግን "ይቅርታ አላደርግልህም እንደውም የቂያማ ቀን እተሳሰበሀለው።" አለው ወጣቱ ያለቅስ ይቅርታ እንዲያደርግለትም ይማፀነው ጀመር፣ ባለቤቱ ጥሎት ሄደ።
ለዐስር ሰላት ሲወጣ አሁንም ወጣቱ እያለቀሰ ያገኘዋል እንዲህም አለው "ይቅርታ ካደረክልኝ የፈለከውን አደርጋለሁ ቀሪ እድሜየን ለአትክልት ቦታህ አገልጋይ ልሁንlehe..."
ባለቤቱም "ይቅርታ ላደርግልህ ዝግጁ ነኝ ግን በመስፈርት ነው" አለው።
"መስፈርቱም ልጄን ልታገባ ነው" ሲለው ወጣቱ ተደነቀ ባለቤቱ ቀጠለና " ልጄ ግን አታይም ፣ አትሰማም ፣ አትናገርም አትንቀሳቀስም እሷን ታገባለህ ! መስፈርቷን አምኖ የሚቀበልኝ ስፈልግ ጊዜያት አልፈዋል" አለው።
ወጣቱ እንዴት መኖር እንደሚችል አሰበ የአትክልቱ ባለቤቱም "ቀጠሮህ ሀሙስ ነው የመህር እና ለግብዣ የሚሆን ነገር በኔ ነው አታስብ" አለው።
የቀጠሮው ቀን ደርሶ ወደ ሙሽራዋ ገባ ••• "አሰላሙ ዐለይኩም ባሌ" ስትለው ወጣቱ በጣም ደነገጠ የሚያየውን ነገር ማመን ከበደው በጣም የተዋበች ናት፣ ወጣቷ ነገሩ ስለገባት አባቷ አስቀድሞ ለሱ የነገረውን እንዲህ አስረዳችው..
° አዎ ! አይኔ የታወረ ነው ሀራም አይቼ አላውቅም°
°ምላሴ ሀራምን አልተናገርም°
°ጀሮየም ሀራምን አልሰማም°
°እግሮቼም ወደ ሀራም ቦታ አልሄዱም °
°አባቴ ሷሊህ የሆነ ባል ፍለጋ አመታትን ቆይቷል ' በአንድ ፍሬ አፕል አላህን የሚፈራ ፣ በልጄም ላይ አላህን ይፈራል' ብሎ ነው የመረጠህ እንኳን ደስ አለህ !°
አለችው።
ከነዚህ ምርጥ ጥንዶች ምርጥና የታወቁት ኢማም ተወለዱ---ኢማም አቡ ሀኒፋ!!!
አስተማሪ ስለሆነ ሼር ያድርጉ👍

Join us 👉@Nuha_bint_Muhammed
Ashura😃😍

ከፊታችን እየመጣ ያለ ታላቅ የፆም ሳምንት እንዳያልፋችሁ ..!!

የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ ከረመዳን ወር በመቀጠል ፆም በላጭ የሚሆንበት ወር የሙሀረም ወር ነው።

📒📔📕 ሶሒሁ ሙስሊም (1163)
_

✋ እናም እንደምታውቁት ይህ አሁን ያለንበት ወር የሙሀረም ወር ከመሆኑ ጋር ከፊትለፊታችን ታላላቅ የፆም ቀናቶች አሉ ስለነዚያ በዝርዝር እንተዋወስ፡

● ጁምዓ (ከአሹራ በፊት ያለው ዘጠነኛው ቀን ነውና ይሄን ቀን መፆም ይወደዳል ፁሙት)፣
● ቅዳሜ (አሹራ ነውና ፁሙት የአንድ አመት ወንጀል ያስምርላችኋል)፣
● እሁድ (አሹራን አስከትለህ እሱንም መፆም ይወደዳልና ፁሙት)፣
● ሰኞ (አሁንም ይህ ቀን ስራችን ከአላህ ዘንድ የሚቀረብበት ቀን ስለሆነ ፁሙት)፣
● ማክሰኞ (የአያመል ቢይድ አንደኛው ቀን ነውና ፁሙት)፣
● እሮብ (የአያመል ቢይድ ሁለተኛው ቀን ነው)፣
● ሀሙስ (የአያመል ቢይድ ሶስተኛው ቀን ነው)።

✋ አደራ በተቻለን አቅም ለመፆም እንሞክር ምንዳቸው በጣም ትልቅ ነው፣ ከረመዳን ፆም በመቀጠል ትልቅ ምንዳን የሚያስገኙ የፆም ቀናቶች ናቸው።

ሌሎች ይደርሳቸው ዘንድ ሼር አድርግ ምናልባትም አንተ ሼር አድርገህ የማያውቁ ሰወች አንብበውት ቢፆሙ የነሱን እኩል ምንዳ ታገኛለህ።

የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ ሌሎች ሰወችን ወደ መልካም ስራ ያመላከተ ልክ እርሱም ያን ስራ እንደሰራው ተደርጎ ይያዝለታል።
ዝም አንበል

ያገባኘል እንበል ዝም ኣንበል ባካችሁ
ኣደባብሶ ማለፍ ተው ይቅርባችሁ
ትድረስ ከ ሟሟው ትውጣ ወደ ላይ
እሷ ይገባታል ከዚህም በላይ
እየቻለች መስራት ኣጉል ባህል ጎዳት
ባህል ወግ እያሉ ኣንሸራተው ጣሉዋት
እያየህ አትለፍ ከቻልክ አግዛት
ለሷ ደስታ እንጂ አትሁን እንቅፋት
ህልሟን ኣሳክታ ትይ ፍሬዋን
የትጋትዋን ውጤት ልፋት ድካምዋን
በጣም ስትጎዳ ሲሰበር ቅስሟ
ሁሉም እየመጣ ሲለክፋት በ ስሟ
ስሜቷ ተጎድቶ ተሟጦ ትግስቷ
በጣም አፈረች በእሷነቷ
ተመኘች ሞቷን እጅግ ተጎሳቁላ
ከ ጭንቁ ገላጋይ ኣንዳች ነገር መላ
አሁንም የለም ዞር ብሎ ሚያያት
ሁሉም ሲሽሹ ኣለሁልሽ ሚላት
ተዓምር ቢፈጠር ድንገት ከ ሆነበት
መንጭቆ የ ሚያወጣት ዐሁን ካለችበት
ትመኛለች በጣም ታደርጋለች ተስፋ x2
እሷ ተቀላቅላ ምድር እንድትሰፋ x2
ኣፍንጫ ተመቶ ዐይን ካላነባ
ስቃያችን ተጋብቶ ሆዳችን ካልባባ
ኢሄ ጭካኔ ነው የእውነት ውሸት የሌለበት
አዎ! ጭካኔ ነው የእውነት ውሸት የሌለበት
በደል ተንሰራፍቶ ስቃይና ጭቆና
የሚያጎላት ጠፍቶ የሚጨወት ሚና
ኣረ ዝም ዐንበል ዕንፍጠር ሰኪና
ተሰምቶን ሃዘኑ ያገባኛል እንበል
ሴቶች ሲበደሉ የ ዕውነት ያመኛል
ሲሰቃዩ ማየት በጣም ያስከፋኛል
ሁሌም ይደሰቱ ይድረሱ ካሰቡት
ህልማቸው ዕውን ሆኖ እስኪ ይመልከቱት
ከስኬት ጽዋ ሁሉም ይጎንጩ
በደስታ ጮቤ ሁሉም ይፈንጩ

ገጣሚ ፊርደውስ ዩሱፍ
ክብር ለ እናቶች
ክብር ለ ህቶች
ክብር ለ ሚስቶች
በባጠቃላይ ክብር ለ ሴቶቻችን!!!!
Forwarded from Deleted Account
✍አንድ ባልና ሚስት ነበሩ ✍

ሴትየዋ ሙያ ሚባል ነገር አልፈጠረባትም ሁልጊዜ ንፍሮ እየቀቀለች ነው ምታቀርበው እሱም በጣም ከመልመዱ የተነሳ እንግዳ እንኳን ሲመጣ “እስቲ ያን እጅ ሚያስቆረጥም ንፍሮ ቀቅይላቸው” ነው ሚለው።

አንድ ቀን ታድያ ይቺ ሙያ የሌላት ሚስቱ ጥላው ትሄዳለች ። እጅግ በጣም መጎዳቱን ያዩት ጎረቤቶቹ ሌላ ሚስት ያመጡለታል ። እሷንም ባገባ በመጀመርያው ቀን የተለያየ አይነት ምግብ ሠርታ ቡፌ ደርድራ ታቀርባለች።
ይሄ ምንድነው? ይላል በመደነቅ፤ እርሷም ምግብ ነዋ ትለዋለች። በጣም እየተገረመ “ለካ እንደዚህም አለ” እያለ እስኪጠግብ ከበላ በኋላ በሩን ዘግቶ በአለንጋ ይገርፋት ጀመር።

ጩኸቷን የሰሙ ጎረቤቶች ተሯሩጠው ይመጡና “ምን ሆነሃል? ሚስት እንድትሆንህ እንጂ እንድትደበድባት አይደለም’ኮ ያጋባንህ ! ይሉታል። እሱም “እስከዛሬ ድረስ በንፍሮ ስቀቀል የት ነበረች አለ ይባላል። ብዙዎቻችን አዲስ ለውጥ የሬት ያህል ይመረናል ።

💌:::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAFkWN5aOAqJHCsIEoQ
አጃኢብ!

አጃኢብ!

ዩዴሞኒያ 6- ሊዚ
===========
እናቷን ያዋለዳት ሀኪም የተወለደችው ልጅ ሲያይ ደነገጠ። እንደዛ አይነት ልጅ አይቶ አያውቅም። እናቷ እንዳትደነግጥ ልጇን አላሳያትም። ፎቶ አንስቶ ሰጣት። እናቷ ግን ምንም አልመሰላትም። ልጇን ማቀፍ ነው የፈለገችው።

እናትና አባቷ ሊዚ የተለየች እንደሆነች እንዳይሰማት አድርገው ነው ያሳደጓት። ትምህርት ቤት ስትገባ ተማሪዎች ይጠቋቆሙባታል፣ ያንሾካሽካሉ፣ ይሸሿታል። ሆናም ሊዚ ተቋቁማ አለፈችው።

ሰባተኛ ክፍል ስትደርስ የቤት ስራ ተሰጥቷት ልትሰራ ኢንተርኔት ከፈተች። "በyou tube ትንሽ ዘና ብዬ የቤት ስራዬን እሰራለሁ።" ብላ Youtube ውስጥ ስትገባ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ያዩት ቪዲዮ ከላይ አለ። "የአለማችን እጅግ አስቀያሚዋ ሴት"The ugliest woman in the world ይላል። ስትከፍተው የእሷ ቪዲዮ ነው። ማን እንደቀረፃትና you tube ላይ እንደጫነው አላወቀችም። ለሊቱን ሙሉ ስታለቅስ አደረች።

ቆይታ ግን "እኔ ማለት ሰዎች የሚሉኝን አይደለሁም። ግሩም ድንቅ ነኝ። የሚሰድቡኝ፣ መጥፎ ነገር የሚናገሩኝ ሰዎች ማንነቴን እንዲወስኑ አልፈቅድላቸውም። ከድክመቴ ይልቅ ጥንካሬዬ ላይ ከጎደለኝ ይልቅ የተሰጠኝ ላይ አተኩሬ እሰራለሁ።" ብላ በተለቀቀው ቪዲዮ የተሸማቀቀችው ሊዚ ቪዲዮዎች እየሰራች ራሷ መልቀቅ ጀመረች። "ሰዎች ሲያዩኝ ምን ይላሉ?" ብላ በሀፍረት ቤት ትውል የነበረችው ሊዚ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ንግግር ማድረግ ጀመረች።

ሊዚ ቬላስኬዝ አሁን ታሪኳን በመናገር ለሚሊዮኖችን ተስፋ፣ ጥንካሬ እና ፅናትን እያስተማረች ነው። እንደሊዚ አይነት ህመም ያለባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ይሁኑ እንጂ ሁሉም ሰው ድክመትና ጉድለት እንዳለው ሁሉ ዩዴሞኒያም አለው። በአካባቢው ያሉ ሰው ሰዎች ድክመቱ ላይ እንዲያተኩር ቢገፋፉትም ግለሰቡ ግን ጥንካሬና እምቅ ችሎታው ላይ የማተኮር ምርጫ አለው።

ዩዴሞኒያ ለሁላችንም!


👉 @Nuha Islamic posts
😎😎Nuha Islamic posts😎😎
ሙስሊም ያልሆነ ወጣት አንድ ሸይኽ ጋር ይመጣና
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"እናንተ ሙስሊሞች ሴቶቻችሁን ለምንድን ነው ሒጃብና ኒቃብ የምታስለብሷቸው ? ፣ ለምንድነው ነፃ እንዳይሆኑ እየሸፋፈናችሁ የምትጨቁኗቸው?"
ብሎ ይጠይቃል።
ሸይኹም የዋዛ አልነበሩምና "ጥያቄህን ከመመለሴ በፊት ሁለት ከረሜላ ገዝተህ ይዘህልኝ ና!" ብለው ከኪሳቸው አንድ ብር አውጥተው ይሰጡታል።
ልጁም በፍጥነት ሁለት በላስቲክ የታሸጉ ጣፋጭ ከረሜላዎችን ይዞ ይመጣል።
ሸይኹ ከረሜላውን ተቀብለው አንዱን ሽፋኑን አንስተው ፣ ሌላኛውን ደግሞ ከነሽፋኑ አቧራ ላይ ጣሉት።
ወደ ልጁም ዘወር አሉና ከሁለቱ መርጠህ ውሰድ ብትባል የትኛውን ትወስድ ነበር?" ሲሉ ይጠይቁታል።
ልጁም "ይህማ ምን ጥርጥር አለው፣ ሽፋን ያለውን ነዋ የምመርጠው " ሲል ቆፍጠን ብሎ ይመልስላቸዋል።
ሸይኹም ፈገግ ብለው:- " አየህ የኛም ሴቶች እንደ ታሸገው ከረሜላ ናቸው። ራሳቸውን ስለሚጠብቁ ንፁህና ተፈላጊም ናቸው። " ሲሉ በጥበብ የተሞላ መልስ ሰጥተው አሰናበቱት።
*
ብዙ ሰዎች የሒጃብን ጥቅም ስለማይገነዘቡ መጨቆን ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ውድ ነገር ተሸፍኖ መገኘቱ ነው፣ መአድን በቀላሉ እንደማይገኘው ሁሉ የኛም ሴቶች በጣም ውድ ዋጋ ነው ያላቸው!
አንዳንድ የሙስሊም ጠላቶች ሒጃባችን ላይ ዘመቻ ከፍተውብናል። እኛም የሂጃብነ ክብር ማሳየትና ማስተማር አለብን እርሶም ሼር በማድረግ የበኩሎን ሃላፊነት ይወጡ!
Nuha Islamic posts
•••✿❒🌹ኡሙ አይመን (በረካ) ረዲየላሁ ዐንሃ ክፍል 1⃣🌹❒✿•••

" የጀነት ሴት ማግባት የሚሻ ኡሙ አይመንን (በረካን)ያግባ " (ረሱል ﷺ)

•••✿❒🌹❒✿•••

የሐበሻይቱ ኮረዳ በመካ እንዴት ለገበያ እንደቀረበች በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም። ትዉልድ ሐረጓ፥ አባትና እናቷ እነማን እንደሆኑና ስለዝርዮቿ የታወቀ መሰል አንዳችም ጭብጥ አይገኝም። በትዉልዳቸዉ ዐረብና ዐረብ ያልሆኑ እሷን መሰል ልጃገረዶችና ኮረዳዎች እየታደኑ በከተማይቱ የባሪያ ገበያ ላይ ለሽያጭ ይቀርቡ ነበር። እነዚያ በጨካኝ ጌቶችና እመቤቶች እጅ የገቡት ፀሐይ የጠለቀችባቸዉና ዕድለ ቢሶች ናቸዉ። ጉልበታቸዉ ያለ ርህራሄ ይመጠመጣል። ይዞታቸዉም ጉስቁልና የበዛበት ይሆናል። ሰብዓዊነት በጎደለዉ በዚያ ማኀበራዊ ሕይወት ዉስጥ ጥቂቶች ብቻ እድለኛ ሲሆኑ..

•••✿❒🌹❒✿•••

እነርሱም ርኀራኄ ከሚያደርጉላቸዉ መልካም ሰዎች ቁጥጥር ስር ይገባሉ። ወጣቷ የሐበሻ ኮረዳ፥ በረካም ረዲየሏሁ ዐንሀ፥ ከዕድለኞች አንዷ ስትሆን ርህሩህ በሆነዉ የአብዱል ሙጦሊብ ልጅ አብዱላህ (የረሱል ﷺ አባት) እጅ በመግባት ከጭቆናና ከግፍ ልትድን ችላለች። ብቸኛዋ የአብደላህ ቤት አገልጋይ ነበረች። አሚና የተባለች እመቤት እንዳገባም በአገልጋይነቷ ፀናች። በረካ (ረዲየሏሁ ዐንሀ) እንደተረከችልን፥ አብዱላህና አሚና በተጋቡ በሁለተኛው ሳምንት የአብዱላህ አባት ወደ ቤታቸዉ በመምጣትና ወደ ሶሪያ ከሚጓዙት የነጋዴዎች ቡድን ጋር አብሮ እንዲሄድ አዘዙት። ትዕዛዙ አሚናን በጣም ስላስከፋት ፦

፦ << ይገርማል! ይደንቃል!እንዴት የጫጉላ ጊዜያችንን ሳንጨርስ ባልተቤቴ ለንግድ ጉዳይ ወደ ሶሪያ ይሄዳል?>> በማለት አማረረች፦"ይገርማል! ይደንቃል!እንዴት የጫጉላ ጊዜያችንን ሳንጨርስ ባልተቤቴ ለንግድ ጉዳይ ወደ ሶሪያ ይሄዳል?>> በማለት አማረረች። የአብዱላህ ከእርሷ መለየት ልቧን ያደማ ክስተት ነበር። ከድንጋጤዋ የተነሳ አሚና ራሷን ሳተች። ከሄደ ከጥቂት ጊዜ በኀላም የነበረዉን ሁኔታ በረካ እንዲህ ስትል ገልፀዋለች፦ <<አሚና ራሷን ስታ ባየኋት ጊዜ በድንጋጤ እመቤቴ! በማለት ጮህኩ። በእምባ የተሸፈኑ አይኖቿን በመግለጥ ማንቋረሯን አቁማ ወደ እኔ እያስተዋለች፦

•••✿❒🌹❒✿•••

<<በረካ ወደ አልጋዬ ዉሰጅኝ>> ስትል ጠየቀችኝ። አሚና የአልጋ ቁራኛ ሆና ለረጅም ጊዜ ቆየች ከአዛዉንቱ ከአብደል ሙጦሊብ በስተቀር ጉብኝት የሚያደርጉላትን ሰወች አታናግርም።
አብደላህ ከተለያት ከሁለት ወራት በኀላ አንድ ቀን ጠዋት ወደርሷ ዘንድ ጠራችኝ። ፊቷም በደስታ ፈክቶ እንዲህ ስትል ነገረችኝ፦ "የመካን ተራሮች፣ ኮረብቶችና ሸለቆዎች ያጥለቀለቀ ብርሀን ከሆዴ ሲፈነጥቅ አየሁ "እርግዝና ስሜት ይሰማሻልን? ጥሩ ነገር ነዉ የእኔ እመቤት?" አልኳት። "አዎ በረካ! ግን ሌሎች እናቶችን እንደሚሰማቸዉ የሕመም ስሜት የለብኝም" ። ስትል መለሰችልኝ።

•••✿❒🌹❒✿•••

እኔም "መልካም ነገርን የሚያመጣ ቅዱስ ልጅ ትወልጃለሽ በማለት አበረታኋት።" አብደላህ ከተለያት ወዲያ አሚና መንፈሷ የተረበሸ ሴት ሆነች። በረካም ከርሷ ሳትርቅ የተለያዩ ታሪኮችን በማዉራት መንፈሷ እንዲታደስ ብዙ ጥረት አድርጋለች። በአንድ ወቅት አብደል ሙጦሊብ ወደርሷ በመምጣት ከተማዉን አብረሃ የተባለ የየመን ገዥ ሊወር ስለሆነ እርሷም እንደሌሎች የመካ ነዋሪዎች ሁሉ መኖሪያ ቤቷን ወደተራራዉ እንድታዛዉር ሲነግሯት አሚና ከቀድሞዉ የበለጠ እጅግ ተከፋች።

አሚና ሀዘን የጎዳት ሴት በመሆኗ ወደ ተራራው መሄድ እንደማትችልና አብረሀም በፈጣሪ የሚጠበቀውን መካን ዘልቆ ካዕባን ሊያፈርስ እንደማይችል አረጋገጠችላቸው። በሁኔታው አዛውንቱ እጅግ ተረበሹ። ነገር ግን በአሚና ፊት ላይ አንድም የፍርሀት ምልክት አላዩም። ከዕባ እንደማይጎዳ የነበራት እምነት ጥሩ መሰረት ያለው ነበር። እንደ እምነቷም ዝሆን ያስከተለው የአብርሀ ሰራዊት መካ ከመግባቱ በፊት አለቀ። ቀንም ሆነ ማታ በረካ ከአሚና ጎን አልጠፋችም። "አንድ ወቅት" አለች በረካ" ከአሚና ግርጌ ተኝቼ ሳለ በምሽት እያንቋረረች የተለያት ባልተቤቷን ስም ስትጠራ ሰማኋት። ከሐዘኗ እንድትላቀቅም ለማፅናናት ለማበረታታት ሞከርኩ።

•••✿❒🌹❒✿•••

" የመጀመሪያዉ ክፍል የንግድ ጉዞ ቡድን ከሶሪያ በሰላም ተመለሰ። የመካ ነጋዴዎች ቤተሰብም በደስታ ተቀብለዉታል። በረካ፥ የአብደላህን ሁኔታ ለማጣራት ከአሚና ተደብቃ ወደ አብደል ሙጦሊብ ቤት ሄደች።እሱን በተመለከተ ግን ምንም ወሬ የለም። አሚናን ሐሳብ ዉስጥ ላለመክተት ወደርሷ ስትመለስ ያየችዉን ሆነ የሰማችዉን ሳትነግራት ቀረች። በተከታታይ ቀናት የጉዞዉ ቡድን ወደ መካ ቢመለስም አብደላህ ግን አልነበረም። የአብደላህ የሞት መርዶ ከየስሪብ (መዲና)ሲመጣ በረካ በአብ
ዱል ሙጦሊብ ቤት ነበረች። የሞቱን ወሬ እንደሰማች የተሰማትን ሁኔታ እንዲህ በማለት ገልፃለች፦

<<የሞቱን ዜና እንደሰማሁ በድንጋጤ ጮኸሁ። ልቤን ስለነሳኝ፥ ከዚያ ወዲያ አደርግ የነበረዉን ነገር አላዉቅም። የማስታዉሰዉ፥ ዳግም ለማይመለሰዉ፥ ለረጅም ጊዜ በናፍቆት ስጠብቀዉ ለተለየን፣ ለመካዉ ለግላጋ፣ ዉብና ለቁረይሽ ኩራት-ለአብደላህ- እጅግ አዝኜ እየጮህኩ ወደ አሚና ቤት መሄዴን ብቻ ነበር። አሚናም ይህን አሰቃቂ ዜና እንደሰማች ራሷን ስታ በሞትና በሕይወት መሃል ሆነች።በዚያ ሐዘን በመታዉ ቤት ዉስጥ ከኔ በቀር ማንም አልነበረም። የአሚና መዉለጃ ጊዜ እየተቃረበ ነበር። የፈጣሪ ከዋክብት በብርሃናቸዉ ሰማዩን ባንቆጠቆጡባት ሌሊት...



ልጇን (ሙሐመድን)እስክትወልድ ካጠገቧ ሳልርቅ ሁኔታዋን ተከታትያለሁ።>> ትላለች በረካ። ረሱል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተወለደ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀፈቻቸዉ በረካ ነበረች። ከዚያም አያታቸዉ አብዱልሙጦሊብ ወደ ከዕባ ወስደዉ የዉልደቱን በዓል ከመካ ሰዎች ጋር አከበሩ። በዓረቦች ባህል ህፃናት እንደ ተወለደ ጠንክረዉ እንዲያድጉ በማሰብ በገጠር ለሚኖሩት ሞግዚት እናቶች ይሰጣሉ። በዚህ ባህል መሠረትም ሙሐመድ ሀሊማ ለተባለች ሞግዚት ተሰጡ። ከአምስት ዓመታት የሞግዚት ኑሮ በኀላም ሕፃኑ ሙሐመድ እናታቸዉ ዘንድ ተወሰዱ።

•••✿❒🌹❒✿•••

~~ እናታቸዉ አሚና እና በረካ ሙሐመድን የተቀበሉዋቸዉ በደስታ፣ በፍቅርና በአድናቆት ነበር። ሕፃኑ ሙሐመድ ስድስት ዓመት እንደሞ ላቸዉ አሚና የስሪብ የሚገኘዉን የባልተቤቷን የአብዱላህ ቀብር ከልጇ እና ከበረካ ጋር ሆና ለመጎብኘት ወሰነች። አብደል ሙጦሊብና በረካ ሐሳቧን እንድትቀይር ወተወቷት። ቢሆንም አሚና በዉሳኔዋ ፀናች። አንድ ቀን ጠዋት ወደ ሶሪያ ከሚጓዙት ነጋዴዎች ጋር ጉዟቸዉን ጀመሩ። አሚና ልጁ ጭንቀት ዉስጥ ይገባል በሚል ፍራቻ የአባቱን ቀብር ለመጎብኘት እንደምትሄድ አልነገረችዉም.........ይቀጥላል ...
ፈገግተኛው ጀናዛ
********


(ምን ብታይ ይሆን እንዲህ ፈገግ ያልከው)
ጌታዬ ሆይ! ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ
አድርግልኝ

መዲነቱል ሙነወራ ውስጥ ጀናዛ በማጠብ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ግለሠብ በሬሳ አጠባ ወቅት ከገጠሙት ድንቅ ነገሮች መካከል አንዱን እንዲህ ሲል ይተርክልን ይዟል…

"ተክለ ሰውነቱ ከሲታ ሲበዛ የቀጨጨ አካሉ በተበጫጨቀ ልብስ የተሸፈነ ካገኘ በልቶ ካጣም ባዶ ሆዱን የሚያድር የአላህ ባርያ። ለሊት ለተሀጁድ ቆሞ የጌታውን ቁርአን እያነበነበ የሚያነጋ። ከሰዎች አይቀላቀልም ብቸኝነት የህይወት ጌጡ ናት። በተበጫጨቀ ጨርቅ የተሸፈነ ጀናዛውን ወደ ማጠቢያ ክፍሉ ይዘነው ገባን በተዘረጋው የጀናዛ ማጠቢያ እንጨት ላይ አስተኝተን ልብሱን አወለቅንለት።

ጆሯችን መልካም ይሰማ ዘንድ በማሰብ ቁርአን በስፒከር ከፍ አድርገን ከፍተን ማጠብ ጀመርን።
ነፍሴ በእጄ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ጀናዛው የቁርአን አንቀፆቹን ሲሰማ ፈገግ አለ ከፈገግታው የተነሳ ጥርሶቹ ተከፍተው ድዶቹ ይታዩ ጀመር።
ቁርአኑን ስንዘጋው የተከፈቱት ነጫጭ ጥርሶቹ ይከደናሉ የቁርአኑን ድምፅ ከፍ ስናደርገው
ፈገግታና ሳቅ ከፊቱ ላይ ይታያል። በግርምት ተውጠን የሱን መልካም ኻቲማ እንዲወፍቀን አላህን እየተማፀንን አጥበን ጨረስን" ይሉናል
የታሪካችን አቅራቢ።

ገጠመኙን እንዲህ በማለት ቀጠሉት "ከተቀበረ ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ የመቃብሩ ስፍራ ለልማት ተፈለገና ተለዋጭ ቦታ ተሰጠን
በቅርብ ጊዜ የሞቱትን አፅማቸውን አውጥተን ወደ አዲሱ የመቃብር ስፍራ ወሰድን። ከቀናት በኋላ ተጠራንና ወደቦታው አቀናን ከአንድ ጉድጓድ አጠገብ ስራውን ያቆመ አንድ ዶዘር ወዳለበት አካባቢ ስንጠጋ ደስ የሚል ጠረን
ይሸተን ጀመር ወላሂ ከፈኑ እንኳ አልበሰበሰም ሰውነቱም አልተቀየረም ከሰአታት በፊት የተቀበረ
አዲስ ጀናዛ ነበር የሚመስለው አፈር አካሉን መብላትን እንቢ አለች ቁርአንን ታቅፎ የኖረን ሰውነት ለመብላት እንዴትስ ያስችላታል?! ከፈኑን
ስንገልጠው ያ ቁርአን ሲሰማ የሚንቀሳቀሰው ጀናዛ ነበር"

«የውመል ቂያማ ለቁርአን ባልደረባ አንብብ ደረጃውንም ከፍ ብለህ ውጣ ያንተ ማረፊያ የመጨረሻ አንቀፅ ቀርተህ በቆምክበት ስፍራ ላይ ነው ይባላል»

እውነተኛ ታሪክ እንጂ ልቦለድ አይደለም
አንብቦ ለሌላ ባካፈለ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈንበት


✨@Solualenebiiy ||★Islamic post★✨