Pharmacy Rx plus
14.1K subscribers
1.79K photos
113 videos
466 files
603 links
➡️ This channel objects
✤ Pharmacy related books & reference
✤ Conversation of drugs
✤ talk about Coc Exam
⛎ For suggest and if you went serve/muckin contact me by @Sarfii & @D2555
Download Telegram
Info

Mata 3:30 live stream ale

Zare model exam yewesedachu mereja mtlewawetubet seat ynorenal !!
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሜዲስን፤ ነርሲንግ፤ ጤና መኮንን፤ አንስቴዥያ፤ ፋርማሲ፤ ሜዲካል ላቦራቶሪ፤ ሚድዋይፈሪ፤ ዴንታል ሜዲስን፤ ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤ ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤ ሳይካትሪ ነርሲንግ፤ እና ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) ጋር በማቀናጀት የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን:-

1. የፈተናው አሰጣጥ ሂደት በኮምፒውተር ይሆናል።

2. የፈተናው መርሃግብር

- በ30/10/2015 ዓ.ም Nursing, Pharmacy, Public Health, Anesthesia, Medical Radiology Technology and Environmental Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Medicine, Dental Medicine, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing and Emergency and Critical Care Nursing

3. እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

4. የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን ለመስራት፤ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password እና የመፈተኛ ጣቢያ ለማወቅ የመረጣችሁብት ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ከፈተናው አንድ ቀን በፊት ማለትም ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በመገኘት ከጣቢያ አስተባባሪዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

5. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

6. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

7. ፈተናውን በድጋሚ ለምትወስዱ ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትመጡ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) QR code የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጋችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።

ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እያሳሰብን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936/952 መደወል ይቻላል፡፡

@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
ማሳሰቢያ
አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርትተቋማት
በአደረግንው ክትትል በዛሬው ዕለት እየተሰጠ በሚገኝው ሞዴል ፈተና ላይ አብዛኞቹ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁት በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳልተገኛችሁ እና ተማሪዎቻችሁ ሞዴል ፈተናውን እንዲወስዱ እንዳላደረጋችሁ ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የመጀመሪያ ዲግሪ የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲረዳ ቀደም ሲል ተለይተው በታወቁ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ለመውጫ ፈተና መውሰጃ በተዘጋጁ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችችሁን በመውሰድ በአስቸኳይ ሞዴል ፈተና እንዲወስዱ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
Live stream finished (1 hour)
#ይፋዊ

የትላንት የሬሜዲያ ፈተናዎች ተሰርዘዋል።

በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዎች አሳልፏል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።

2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ።

3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ይሰጣል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

NB. ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ትላንት ፈተናው መሰጠት ከተጀመረ በኃላ ተፈጥረዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር አላሳወቀም።

More : tikvahuniversity

@PharmacyRxplus