Pharmacy Rx plus
14.1K subscribers
1.79K photos
113 videos
466 files
603 links
➡️ This channel objects
✤ Pharmacy related books & reference
✤ Conversation of drugs
✤ talk about Coc Exam
⛎ For suggest and if you went serve/muckin contact me by @Sarfii & @D2555
Download Telegram
Live stream started
Info


ለቀጣዩ exam መዘጋጀት የምትፈልጉ ካላችሁ ምዝገባ ተጀምሯል የእናንተ ኪስ በማይጎዳ መልኩ መማር ትችላላችሁ ።

በዚህ ወር እስከ 26 ድረስ ብቻ መመዝገብ የሚቻለው እናም ከፈለጋችሁ በዚህ User 👉👉 @D2555 መነጋገር ትችላላችሁ ።

#Inbox 👉👉 @D2555
👍1👏1
#ExitExam

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚተገበረው አስገዳጅ መመሪያ ምን ይላል ?

(የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን)

" ከቀጣዩ ዓመት 2016 ዓ/ም ጀምሮ እያንዳንዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።

የግል ተቋማቱ 25 በመቶ ተፈታኞቻቸውን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት ፕሮግራሙ #ይሰረዛል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው። "

NB. ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት ያመጡት 12,422 ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

Credit : #FBC

@PharmacyRxplus
Live stream started
Info



ለቀጣዩ exam መዘጋጀት የምትፈልጉ ካላችሁ ምዝገባ ተጀምሯል የእናንተ ኪስ በማይጎዳ መልኩ መማር ትችላላችሁ ።

በዚህ ወር እስከ 26 ድረስ ብቻ መመዝገብ የሚቻለው እናም ከፈለጋችሁ በዚህ User  👉👉  @D2555  መነጋገር ትችላላችሁ ።

  #Inbox   👉👉 @D2555
Forwarded from Tarekegn Geresu
ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበር አስገዳጅ መመሪያ ተዘጋጀ
======      =======

 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎቻቸው ቢያንስ 25 በመቶዎቹን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት መስኮቻቸው እንዲታጠፉ የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልጿል።

በባለስልጣኑ የከፍተኛ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ክትትል እና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው አድነው ለፋና ብሮድካስቲንግ እንደተናገሩት፥ የመማር ማስተማር ስራው ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን አዲስ መመሪያ እና መስፈርት ተዘጋጅቷል።

የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የሚጠበቀውን ደረጃ እና ጥራት ማስጠበቅ ያስችላል የተባለው አዲስ መመሪያ እና መስፈርትም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።

በመመሪያው የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ በርካታ መለኪያዎች የተቀመጡ ሲሆን፥ አንዱ የመውጫ ፈተናን የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።

በዚህም እያንዳንዱ ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው በማንሳት ይህ ካልሆነ ግን የትምህርት ፕሮግራሙ ይሰረዛል ብለዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች ለባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት 50 እና ከዛ በላይ ያመጡት 12 ሺህ 422 ወይም 17 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸው ይታወቃል።

(ኤፍ ቢ ሲ፤ ሀምሌ 22/2015 ዓ.ም)
👍4