Pharmacy Rx plus
14.1K subscribers
1.79K photos
113 videos
466 files
600 links
➡️ This channel objects
✤ Pharmacy related books & reference
✤ Conversation of drugs
✤ talk about Coc Exam
⛎ For suggest and if you went serve/muckin contact me by @Sarfii & @D2555
Download Telegram
#OTC #VAT

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) አዋጅ መሠረት ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ መድሃኒቶች ወደ ታክስ መረቡ እንዲገቡ ተደርገዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የገቢዎች ሚኒስቴር ሰርኩላር በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 570/2017 አንቀፅ 58 መሠረት በቀድሞ አዋጅ ከታክሱ ነጻ የነበሩ አንዳንድ አቅርቦቶች ታክሱ እንደሚሰበሰብባቸው አመልክቷል።

ከነዚህም ውስጥ አንዱ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ መድሀኒቶች ነው።

አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ ተሰማርተው ግዴታቸውን ያልተወጡ አካላት ካሉ ተጣርቶ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ መደሃኒቶች ዝርዝር ከኢትዮጲያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እንዲላክ አድርጎ ለሚመለከታቸው ሁሉ ልኳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ደብዳቤ፤ የገቢዎች ሚኒስቴር የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ጀምሮ የሚጠበቀውን ግብር ለማስላት ያመቸው ዘንድ በሀኪም ትዕዛዝ እና ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በሽያጭ የሚተላለፉ መድሐኒቶችን የያዘ መረጃ ጠይቆት በዝርዝር እንደሰጠ ይገልጻል።

በመ/ቤቱ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የመድሐኒት ዓይነቶች OTC Medicines List ሰነድ ለገቢዎች ሚኒስቴር ልኳል።

(ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የመድሐኒት ዓይነቶች /OTC/ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@Pharmacyrxplus
@Pharmacyrxplus
❤5
❤11🤔2👍1🔥1