Pharmacy Rx plus
14.1K subscribers
1.79K photos
113 videos
466 files
600 links
➡️ This channel objects
✤ Pharmacy related books & reference
✤ Conversation of drugs
✤ talk about Coc Exam
⛎ For suggest and if you went serve/muckin contact me by @Sarfii & @D2555
Download Telegram
❤1
❤5
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ፥
___________

የጤና ሚኒስቴር የቀጣይ ዙር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥም ምዝገባ ይጀምራል። 

ለብቃት ምዘና ፈተና ለመመዝገብ የምትፈልጉ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሄድ የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ግዴታ የሚያስፈልግ ስለሆነ ከወዲሁ ዝግጁ እንድታደርጉ እያሳሰብን የምዝገባውን ፕሮግራም በቅርብ ቀን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

@Pharmacyrxplus
@Pharmacyrxplus
❤26👍2🥰2👏1
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ባሉበት
ጉዳዩ፦ 2018 ዓ.ም  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃን ይመለከታል፤
ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ጥራት ያለው ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ሰብስቦ በመተንተን የቁልፍ አፈጻጸም አመላካቾችን (KPI) በየጊዜው ለመከታተል፣ እንዲሁም በዘርፉ ያለውን የመረጃ አቅርቦትና ጥራት ችግር በዘላቂነት በመፍታት የሚተላለፉ ውሳኔዎች፣ የሚቀረጹ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫዎች እና የእቅድና ግቦች ተአማኒነት ባለው መረጃ ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ እየተሰራበት ይገኛል። በዚሁ መሠረት የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (Higher Education Management Information System) ተዘርግቶ ተቋማትም መረጃቸውን በሲስተም እንዲያስገቡ አካውንት በመፍጠር የአጠቃቀም ስልጠናዎች መስጠታችን ይታወሳል።

በትምህርት ሚኒስቴር እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር በነበረው ውይይት በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ አለባቸው። መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፌደራል መንግስት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ አቅጣጫ ተቀምጧል። ስለሆነም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ በhttp://hemis.ethernet.edu.et እንድታስገቡ እየጠየቅን ይህንንም ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ለኢፌድሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ኃላፊነት መሰጠቱን አሳውቃለሁ።

@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
❤14
Pharmacy_EHPLE Practice Test Booklet_2025.pdf
1.3 MB
መልካም ዜና

PharmacyRxplus ተቋርጦ የነበረው Tutorial ዳግም ሊጀምር ነው ።
ማጥናት ለምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ !!
በዚህ ➡️➡️ @D2555

@PharmacyRxplus
@PharmacyRxplus
🔥8❤6🤔4
❤2
Pharmacy Rx plus
Photo
#ATTENTION🚨

‎" በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ከዛሬ ህዳር 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ሣምንት ትራንስፖርት ዝግ ይሆናል" - የዞኑ መንግስት
‎
‎በጂንካ ተከስቶ ለሰዎች ሞት ምክንያት እየሆነ ያለዉን የማርበርግ ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ ወደ በሽታዉ መነሻ የአሪ ዞን የሚገባም ሆነ የሚወጣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለ1 ሣምንት ዝግ እንዲሆን በአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ግብር ሃይል መወሰኑን የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምመላሽ አቦነህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
‎
‎የቫይረሱ ስርጭት ከዕለት እለት አስከፊ እየሆነ በመምጣቱ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር በአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ግብረሀይል ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊዉ እስካሁን በነበረው ሂደት ትምህርት ቤቶች የተዘጉና ፣ ሕዝብ የሚሰበሰብባቸዉ ጉዳዮች ላይ እቀባ የተጣለ ቢሆንም ስርጭቱን በሚፈለገዉ ልክ መግታት ባለመቻሉ የትራንስፖርት ዘርፉን ለ1 ሳምንት መዝጋት አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ህዳር 20/2018ዓም ጀምሮ ለ1 ሳምንት ዝግ እንዲሆን ግብረሀይሉ መወሰኑን ተናግረዋል።
‎
‎ጂንካ ከተማን ጨምሮ ለሁሉም መዋቅር የትራፊክ ፍሰት እና የፀጥታ ዘርፍ አስተባባሪዎች ይህ መልዕክት መተላለፉንም አቶ ደምመላሽ አስታዉቀዋል።
‎
‎በዚህ መሰረት ከክልል በወረደው አቅጣጫ መሰረት አገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ለ1 ሳምንት የታገደ ሲሆን በከተማ የሁለት እግር ተሽከርካሪዎችና የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ብሎም በዞኑ ውስጥ የሚኖሩ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በቀጣይ ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንደሚሰጥባቸው ገልፀዋል።
‎
‎ኃላፊው አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የማርበርግ በሽታ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ የተከሰተ ቢሆንም ጂንካ ለቅሶ መጥቶ የተመለሰ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በበሽታዉ  መሞቱን መስማታቸዉንና የስርጭት መጠኑን ለመቀነስ ብሎም ለመቆጣጠር ዉሳኔዉ መተላለፉን በመግለፅ በዞኑም ሆነ ከዞኑ ዉጪ ያለ ሕብረተሰብ ይህን ተግባራዊ እንዲያደርግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@PharmacyRxplus
❤16👍1
👍3😁1
❤11👍10🔥1🥰1
Pharmacy Rx plus
Photo
በወቅቱ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ (License) ያላሳደሱ ጤና ባለሙያዎች የቅጣት ይከፍላሉ
-------------------------
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሞያዎች የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ (license) በተለያየ ምክኒያት በወቅቱና በጊዜው ላይሰንስ የማያድሱ ጤና ባለሙያዎች የአገልግሎት ጊዜ ባለፈበት ከ31 ኛው ቀን ጀምሮ ከአገልግሎት ክፍያ በተጨማሪ የቅጣት ክፍያ ከፍለው የሚያድሱ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ላይሰንስ እድሳት ኦን ላይን አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ (license) የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው የጤና ባለሙያዎች ለማደስ የአገልግሎት እና የቅጣት ክፍያውን የሶፍትዌሩ ሲስተም የባለሙያዎችን ላይሰንስ የአገልግሎት ጊዜ ካበቃበት ቀን ጀምሮ በማስላት የቅጣቱን የገንዘብ መጠን የሚያስቀምጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከ31 እስከ 60 ቀናት የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ (license) ያላሳደሱ ባለሙያዎች የአገልግሎት 200 ብር ጨምሮ በድምሩ 600 ብር እንደሚቀጡ፣ ከ61ቀን እስከ 90 ቀናት ደግሞ ከአገልግሎት ክፍያ ጋር 1200 ብር፣ ከ91 ቀን እስከ 120 ቀን የአገልግሎት ክፍያና ቅጣት 1800 ብር እንደሆነ ፣ ከ121 እስከ 150 ቀናት ደግሞ የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ 2400 ብር፣ ከ151 እስከ 180 ቀናት ደግሞ የአገልግሎት ክፍያን በማካተት 3000 ብር የሚቀጡ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም እስከ 8 ዓመት እድሳት ያላከናወኑ ጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከአገልግሎት ክፍያ ጋር 4800 ብር፣ ከ 8 አመት እስከ 11 ዓመት 5400 ብር እንዲሁም ከ11 ዓመት እስከ 15 ዓመት 7200 ብር የአገልግሎት ክፍያን በማካተት ተቀጥተው የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ (license) የሚያድሱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ይህንን ስሌትም ኦንላይን ሲሞላ ራሱ የሚያስቀምጥ ተገልጿል

በመጨረሻም ጤና ባለሙያዎች የላይሰንስ እድሳት ጊዜው በተራዘመ ቁጥር ቅጣቱ እየጨመረ የሚሄድ መሆኑን በመገንዘብ በወቅቱና በጊዜው ላይሰንሳቸውን ማሳደስ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

@PharmacyRxplus
❤19