በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ የሚወሰደው አዲሱ የኤችአይቪ መከላከያ መድኃኒት
**
የአሜሪካ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን (ኤፍዲኤ) በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመወጋት ከኤችአይቪ ቫይረስ የሚከላከለውን የሌናካፓቪር መድኃኒት አፀደቀ።
ይህ ውሳኔ በ120 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት መድኃኒቱ በቅናሽ ዋጋና በፍጥነት እንዲዳረስ ትልቅ መንገድ ከፍቷል።
መድኃኒቱ ለአንድ ሰው በዓመት 40 ዶላር ብቻ የሚያስወጣ ሲሆን ይህም በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ከሚዋጡት የመከላከያ ኪኒኖች ጋር ተመጣጣኝ ዋጋ ነው። ይሁን እንጂ በየቀኑ ኪኒን የመውሰድ አሰልቺ ሂደትን በማስቀረትና ቫይረሱን የመከላከል የላቀ ብቃት በማሳየቱ እጅግ ተመራጭ ያደርገዋል።
የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ተመጣጣኝ መድኃኒት ለ20 ሚሊዮን ተጋላጭ ሰዎች ተደራሽ መሆኑ በዓለም ዙሪያ አዳዲስ ስርጭቶችን እና ሞትን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የኤችአይቪ ወረርሽኝን ለማስቆም ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲል አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
@PharmacyRxplus

❤13👏4
❤8👍3👏1