ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>>
34.6K subscribers
188 photos
1 file
23 links
<<ደስታን ምን እንደሚያካትት መፈለግህን ከቀጠልክ ፈጽሞ ደስተኛ አትሆንም..! የሕይወትን ትርጉም እየፈለግህ ከሆነ ፈጽሞ ሕይወትህን አትኖርም..! >>

አልበርት ካሙ

ለማስታወቂያ ሥራ➝ @Naolviva
Download Telegram
ጦርነት እየተካሄደ የሚያርስ ገበሬ "ለማን ነዉ?" ሲሉት "አላህ ለሰጠዉ ይሰጣል እኔ ከደረስኩበት እበላለሁ ካልሆነ ደሞ የሚመጡት ይበሉታል" አለ አርሶ ባዶ መሬት ከመተዉ ከዚህ በላይ ምን አሪፍ ሰዉ አለ

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
🔥9❤7
<<የዘመኑ ወጣት የአእምሮ በር የለውም። ቢኖረውም የሚያስወጣ እንጂ የሚያስገባ አይደለም። ከራሱ ዓለም ሐሳብ አውጥቶ >> ያልኩት ካልሆነ ይላል እንጂ የሌላውን ሐሳብ አይመዝንም። ሲወለድ ጀምሮ ሁሉን አውቆ የተፈጠረ ይመስለዋል። <<ያለ ብዙ ችግር ያገኘውን እውቀቱን ተፎካካሪ የሌለው ኃይል ያደርጋል። በትንሽ እውቀት ብዙ ነገር ፈታትቶ የሚገጣጥም ይመስለዋል።>>

(ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ)

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
❤19💯3
ተስፋ

ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው።ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው ወይም የሚገፋው መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋው ነው።ቢሆንም ግን ህይወት ተከታታይ መሆኗን መገንዘብ ይጠቅማል።ዛሬ የምኖረው በትናንት ምክንያት ነው።

📓አለመኖር


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
❤11🔥9
መዝሙረ ሄላም...
💯8❤4🥰4
"በድሮ ጊዜ ቀስት ሲሰራ ቂጡ ላይ ለሚዛን ላባ ይገባለታል፡፡ እና አንድ ጭልፊት ጎኑን በቀስት ተመቶ ከሰማይ ላይ እየወደቀ እያለ ዞር ብሎ የተወጋበትን ቀስት ሲያይ፤ የራሱን ዐይነት ላባ ተሰክቶበት አየ፡፡ ገባህ? በወገንህ እጅ እንደ መጥፋት ቀላልና ከባድ ነገር የለም ማለት ነው፡፡"

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
❤9😢7😁2🙏2
አስቄአቸው የማላውቅ እኔ ነኝ። ሲያወሩልኝ መስማት ብቻ። የሚወዱኝም በዚህ ነው። "እሱ ሰው ሲናገር ማቋረጥ አይወድም" እባልና። እኔ ግን ማውራት ስለሚደክመኝ ነው አፍ ፣ጥርስ፣ምላስ፣አገጭ፣ ጠቅላላ የፊት ጡንቻ፣ዐይኖች፣ግንባር፣እጅ ወዘተ....እነኝህን ሁሉ በአንድ ጊዜ አነቃንቄ ከእኔ ወደ ሌላ ሰው መረጃ ማስተላለፍ አድካሚ ነገር ይሆንብኛል። ያለማውራቴ ምክንያት ግን በተለያዩ ሰወች የተለያየ ትርጉም ይሰጠዋል:-

አክስቴ: "መልኬ በቃኝ ብሎ ነው"እያለች ታሽሟጥጠኛለች። የወጣልኝ አጎዶ።
አባባ: "ጨዋ ጨዋነት ነው" ይላሉ
ጋሸ: "ትዕቢት ፤ ትዕቢት ነው" ይላል
ጓደኛዬ: "መደበር ይወዳል ፣ ደባሪ ነው"ይላል
የጓደኛዬ ሴት ጓደኛ : ኩራት። ኩራት ነው። ሲበጣጠስ" ትላለች
የጋሸ ሚስት: ፍርሐት ፣ ፍርሐቱ ነው" ትላለች
ብቻ ሺህ ትርጉም ይሰጠዋል።

   (ህማማትና በገና)


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
😁12👍5❤2
- አንተ ሰው ከየት መጣህ?
- ከግብጥ
- ምን ይዘህ?
- ጭብጥ ጥጥ
- በምን አስረህ?
- በድጋይ ልጥ
- ይህስ ሰው ዋዘኛ ነው!
- ዋዘኛስ ክራር ነው
- ክራርስ ጥዝ ጥዝ ባይ ነው
- ጥዝ ጥዝ ባይስ ንብ ነው
- ንብስ ነዳፊ ነው
- ነዳፊስ ደጋን ነው
- ደጋንስ ጠማማ ነው
- ጠማማስ መንገድ ነው
- መንገድስ ወሳጅ ነው
- ወሳጅስ ውሃ ነው
- ውሃስ ብም ብም ባይ ነው
- ብም ብም ባይስ ጎሽ ነው
- ጎሽስ ዘላይ ነው
- ዘላይስ ፌቆ ናት
- ፌቆ ስትዘል አግኝቼ በልቼ መጣሁ
- ሰባች ጎፈየች?
- ሳትታረድ መጣሁ
- የሆነስ ሆነና ስምህ ማን ነው?
- ላገር አይመች
- ማን አወጣልህ?
- ጎረቤቶች
- የናትህ ስሟ ማን ነው?
- ሳልወለድ ሞተች
- የሆነስ ሆነና እግዚሀርን አይተኸዋል አላየኸውም?
- አዎን አይቸዋለሁ
- ቀይ ነው ጥቁር?
- ተከናንቦ ነበር
- ረጅም ነው አጭር?
- ቁጭ ብሎ ነበር


ስብሀት

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
👍14❤11🏆2
"ራስህን በትክክል የምትወድ ከሆነ ሌላን የምትጎዳ አይነት ሰው አትሆንም "
                          / ጉተማ ቡድሀ / ሰውን ለምን እንደሚጎዱ በሚጠየቁበት ሰአት #ሥለምወደው የሚል ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ስህተተኛ ብቻ ሳይሆን ሀሰተኛም ናቸው ። ሰውን ለመጉዳት የምንነሳው ስለምንወደው ሳይሆን የወደድነውን የራሳችን ብቻ ለማድረግ የሚገፋን ራስወዳድነት ሥለሚጫወትብን ነው።
፧
የወደድከው ነገር ሁሉ ያንተ ካልሆነ አጥፋው የሚል ስሜት ውስጥህ ካለ...ስሜትህ ውሸት ነበር ማለት ነው። ፍሬ ከናፍር እወደዋለሁ ያልከው ነገር ያንተነቱን እንጂ እሱነቱን አልወደድከውም ማለት ነው...። አንድን ነገር ስትወደው ተፈጥሮውን አድንቅለት...ነፃ አድርገው በቃ! ያንተ መሆን ያለመሆንን ምርጫ ለሱ ብቻ ተውለት...አንተ የመኖር መብት እንዳለህ ሁሉ የምትወደው ነገርም የመኖር መብት አለው...አንተ የመምረጥ መብት እንዳለህ ሁሉ የወደድከውም የመምረጥ መብት አለው...እዚህ መሀል ማስገደድ ካለ መውደድ የለም...!!
፧
የራስህን አስተሳሰብ ስርአት ባላስያዝክበት ሁኔታ ሌላ ላይ ጣትህን ለመጠቆም እንደማትበቃው ሁሉ ራስህን መውደድህን በትክክል ባላረጋገጥክበት ሁኔታም ሌላን ልትወድ አትችልም ። የፍቅርን ትርጉም የማያውቅ እና ራሱን አፍቅሮ የማያቅ ሰው...ሥላፈቀርኳት የሌላ ሆና ማየት ሥለማልሻ አጠፋኋት ሲል ባደባባይ ይዋሻል...ራስህን አትዋሽ...!!

በትክክል ራሱን የሚወድ ሌላን የሚጎዳ ስብዕና የለውም...!!


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
👏7❤3
🔊▫️▪️▫️ ሰባተኛ ፎቅ

ሰውየው ሰባተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆኖ ንፋስ ይቀበላል። አካባቢውን እየቃኘ እያለ አንድ ሰው
ምድር ላይ ሆኖ እጁን ሲያውለበልብለት ይመለከታል።
በድምፅ መደማመጥ ስላልቻሉ ምድር ያለው ሰውዬ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ያለውን ሰውዬ በምልክት 'ና' ይለዋል።
ሰባተኛ ፎቅ ላይ የነበረው ሰውዬ ስለሰውዬው ማንነትና ስለፈለገው ነገር እያሰበ ከፎቁ ይወርዳል። የምድሩ ሰውዬ ጋር እንደደረሰም: ፎቅ ላይ የነበረው: "አቤት ወንድሜ ምን ፈልገህ ነው?" ምድር ላይ ያለው: ፊቱን አሳዛኝ ካደረገ በኋላ "ይቅርታ ጌታዬ አለፋሁዎት አይደል? ለማኝ ነኝ። እስኪ ስለ እግዚአብሔር ብለው ያለዎትን ይመፅውቱኝ" ሲለው ሰውየው ከሰባት ፎቅ ድረስ በቁም ነገር ወርዶ በሰማው ነገር እጅግ ስለተበሳጨ
ለማኙን ካልገደልኩ ብሎ አስቸገረ።
ትርምሱ በአገላጋዮች ከረገበ በኋላ ለማኙ ላይ እየዛተ ወደነበረበት ፎቅ ይመለሳል።
እየተመለሰ እያለ ግን ለማኙ የምሩን ተቸግሮስ ቢሆን እያለ እያሰበ ነበር።
መጀመሪያ የነበረበት ሰባተኛ ፎቅ ላይ ደርሶ ወደታች ሲመለከት ለማኙ አሁንም አንጋጦ
ሲመለከተው ያያል።
ተስፋ ቆርጦ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ ያፏጭና ለማኙን ይጠራዋል።
ለማኙ በደስታ እየተፍነከነከና የሰውዬውን ልብ ያራራለትን አምላክ እያመሰገነ ሰባተኛ ፎቅ ከወጣ በኋላ:
ምድር የነበረው : እየተቅለሰለሰ "አቤት የኔ ጌታ?" ቢለው
ፎቅ ላይ ያለው (ተለማኝ): "እግዚአብሔር ይስጥልኝ😊!!!"


🗞🗞🗞🗞

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊
🤣11🥰7💔6👍5❤4
"በአእምሮህ ላይ ሙሉ ሥልጣን አለህ — ከውጭ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ ግን የለህም ይህንን እውነት ከተረዳህ፡ የማይበገር የውስጥ ጥንካሬ ታገኛለህ።"
— ማርከስ ኦሬሊየስ (ሜዲቴሽንስ)
 
 በቀላል አባባል ምን ማለት ነው?
በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮች በሁለት ይከፈላሉ፡
 
ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች፦  የአየር ጠባይ፣ የሌሎች ሰዎች አስተያየት ወይም ድንገት የሚፈጠሩ መጥፎ አጋጣሚዎች። 
 
 
በእኛ ቁጥጥር ሥር የሆኑ ነገሮች፦ ለነገሮች የምንሰጠው ምላሽ፣ አስተሳሰባችን፣ ትዕግስታችን እና ቀጣይ እርምጃችን እና ውሳኔዎቻቻን በኛ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ነገሮች ብቻ ናቸው ።
 
ማርከስ ኦሬሊየስ ሊነግረን የፈለገው፡ እውነታ ይህን ይመስላል  አብዛኛው ጭንቀታችን የሚመጣው ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮችን ለመለወጥ ስንታገል ነው። በዙሪያህ የሚፈጠረውን ነገር ሁልጊዜ መቆጣጠር አትችልም፤ አእምሮህ ውስጥ የሚፈጠረውን ስሜትና ምላሽ ግን ሁልጊዜ የመቆጣጠር ሙሉ መብት አለህ።
 
ይህን አስተሳሰብ ካዳበርክ በ እርግጥም ውስጣዊ ጥንካሬን ታገኛልህ ፣ የውጫዊው ጩኸት ውስጥህን አይረብሸውም።
 
🎯 ለዕለት ተዕለት ሕይወት እንዲህ አድርገህ መተግበር ይኖርብሃል
በአንድ ነገር ስትበሳጭ፣ ስትጨነቅ  ወይም ግራ ሲገባህ  አልፎም ህይወት ፈተናዎችዋን ስትልክብህ  ቆም በልና አእምሮህን ጠይቅ፡
· 
"ይህ ነገር በእኔ ቁጥጥር ሥር ነው?"
· 
መልሱ "አይደለም" ከሆነ፡ ነገሩን ለመቀየር በመጨነቅ ጉልበትህን አታባክን። ይልቁንም ትኩረትህን ምላሽህ ላይ አድርግ። እውነተኛ ጥንካሬና የውስጥ ሰላም የሚገኘው እዚያ ላይ ነው።
 
በ አንተ ቁጥጥር ስር ከሆነ  ግን ተነስተህ ፍታው !
 
መቆጣጠር የማትችለውን ለመቆጣጠር ስትሞክር ብቻ ራስህን ስቃይ ውስጥ ድብርት ውስጥ እና ጭንቀት ውስጥ ትከታለህ ።
 
“ከማርከስ ኦሬልዬስ መዲቴሽን መጽሃፍ የተወሰደ “
 

ይህ መጽሃፍ በ አማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል ለመውሰድ በውስጥ አናግሩኝ
 
https://t.me/GREAT_ESKENDER
❤10👍6
Forwarded from ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>> (ESTIF 🀄️ዳማዊ 🫀)
በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።

  "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው  የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
😁18❤17🥰4🙏3
ለተሰበረ እግር ድጋፍ ቢፈጠርም
ምርኩዝን ተማምኖ እግር አይሰበርም
❤21🏆11👍1
...."ማንኛዉም ጠንካራ ሰው የጥንካሬዉ ምንጭ ያለፈበት የመከራ መንገድ ነው። ድሎት ዱለት እንጂ ጉልበት እና ጽናትን አያጠግብም። መከራ የጠንካራ ሰው አሻራ ነው። ክርስቶስን ማንም ሰው የሚያስታዉሰዉ በመስቀሉ እንጂ አሳ አበርክቶ በመቆለሉ አይደለም። ከታምራቱ ይልቅ ስቅላቱ አይረሴ አድርጎታል።
በምድር ላይ ጥልቅ ሃሳብ ይዘው እንደበጋ መብረቅ ምድርን ያናወጡ ፈላስፋወችማ ከክርስቶስ በፊት ስንት አዝማን ቀድመው ነበሩ። እነሶቅራጥስ እነቡድሃ... ሰዉን ሰዉ የሚአደርገው ቁመናው ሳይሆን ፈተናው ነው።"

ተልሚድ ይስማዕከ ወርቁ


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
👏12❤9🥰6🙏2👍1
💜ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩበት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ። ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።..."

"ዴርቶጋዳ"


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
❤15👍5😁1
ጠያቂ:- ጋሽ ስብሃት ደስታን እንዴት ነው ሚገልጹት?

ጋሽ ስብሃት:- ለምን እገልጸዋለሁ ተደስቼበት አልቋል!

ጠያቂ:- እኮ ደስታን እንዴት ይገልጹታል?

ጋሽ ስብሃት፡- ለምን እገልጸዋለሁ! ተደሰትኩ አይደለ ተመስገን ብዬ ጭጭ አልልም😂


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..😊
❤10😁2👏1
የምርጫ ቅስቀሳ

ባሻዬ! የአንዳንድ ሴቶች የገንዘብ መውደድ ያስገርመኛል። አንተ ተናደህ

"ሂጂ! ገሃነም ግቢ" ስትላት፣

"ገሃነብ የሚያደርስ የትራንሰፖርት ገንዘብ ስጠኝ" ትልሃለች።

ባሻዬ! ስለ ምርጫ ቅስቀሳ እጽፋለሁ ብዬ ስለ አንዳንድ ሴቶች የገንዘብ ፍቅር ማውራቴ ምን ይባላል? ወደ ምርጫ ቅስቀሳ እንግባ፣

የአንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወዳዳሪ የምርጫ ቅስቀሳ ሊያደርግ ወደ አንድ የገጠር ከተማ ገባና ቅስቀሳውን እንዲህ ሲል ጀመረ፣

"በቀጣዩ ምርጫ የኛን ፓርቲ ብትመርጡ ያሉባችሁን ችግሮች በአጭር ጊዜ እናስወግድላችኋለን" አለ። በዚህን ጊዜ አንድ ሽማግሌ ከመቀመጫቸው ተነስተው ጋቢአቸውን ካስተካከሉ በኋላ "እኛ ከተማ ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ችግሮች አሉብን። አንደኛው ችግራችን ክሊኒክ ቢኖረንም አንድም ዶክተር የለንም"

ፖለቲከኛው ንግግራቸውን አቋረጣቸውና ወዲያውኑ ሞባይሉን አውጥቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ በሞባይሉ ተነጋግሮ ስልኩን ዘጋና "በቃ ችግራችሁ ተወግዷል። ምርጫው እንዳለቀ አንድ ዶክተር ይመጣላችኋል። ሁለተኛው ችግራችሁ ምንድነው?"

ሽማግሌው እዚያው እንደቆሙ "ሁለተኛው ችግራችን ደግሞ የሞባይል አገልግሎት እኛ ከተማ ገና አልተጀመረልንም። አንተ በሞባይልህ እንዴት እንዳወራህ ፈጣሪ ይወቀው" ብለው ቁጭ አሉ።

ባሻዬ! ነገሩ ከባድ ነው።

tesfaye hailemariam


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
❤7😁4
ሶሊያና


-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …

ኤፍሬም ስዩም✍

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
❤10👍3🕊2
•ጥያቄ፡- ዶሮዋ ለምን መንገዱን አቋረጠች?

-ዴካርት፦
“ወደ ሌላኛው የመንገዱ ጫፍ ለመድረስ።”

-ፕላቶ፡-
“ለእሷ እውነቱ በሌላኛው በኩል ነው።”

-አርስቶትል፦
“የዶሮ ተፈጥሮ ነው።”

-ካርል ማርክስ፦
“ቦታዎችን መቀየር አለብን ለውጥ የታሪክ ህግ ነው።”

ካርል ጁንግ፡-
“ዶሮዋ ገና ያልሄደችበትን ለመሄድ”

-ማርቲን ሉተር ኪንግ፦
“ዶሮዋ ለድርጊቷ ምክንያት የላት ይሆናል። መንገዱን የማቋረጥ ህልም ግን ነበራት።”

ሲዮራን፦
“ዶሮዋ መንገዱን አላቋረጠችም፤ እደግመዋለሁ ዶሮዋ መንገዱን አላቋረጥችም”

-ሶቅራጠስ፦
“ዋናው ነገር ዶሮዋ መንገዱን ማቋረጧ ነው። እና ለምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ አይደለም።”

-ቡድሃ፦
“ይህንን ጥያቄ መጠየቅ የዶሮዎችን ተፈጥሮ መካድ ነው።”

-ዲዮጋን፦
“ሰፈሯ ጠፍቷት”

-አንስታይን፡-
“መንገዱን ያቋረጠችው ዶሮዋ ትሆን ይሆናል። ወይም ከዶሮዋ እግር ስር መንገዱ ተንቀሳቅሶ ይሆናል። ይህ ከነገሮች አንጻራዊነት ጋር የተያያዘ ነው።

-በርናንድ ሾው፦
“እየሸሸች ይመስለኛል ላለመታረድ”

ጥያቄው ለምን ዶሮዋ መንገዱን አቋረጠች?😑



@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
🤔3❤2😁2🤯1🕊1
" እኔ ምልህ መሳይ?!"

ወዬ!

"ቅር ካላለህ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?"

ምንድነው ጠይቂኝ(ሰፍፍፍ ብዬ)

"ከዚች ከነጭዋ ሱሪ ውጭ ሌላ ሱሪ የለህም እንዴ?
ሁሌም ይቺን ብቻ ነው እጠቢልኝ እያልክ ምታመጣት"

ምን ማለት ሽ ነው?

"ከክፋት አትይብኝ እውነት ስላሳዘንከኝ ነው:: ሚገርምህ እስኪደርቅ ምትለብሰው አጥተህ እንዳትቸገር እያልኩ ወረፋ ቢኖር ራሱ በቻልኩት መጠን ያንተን ለማስቀደም እሞክራለሁ ሁሌም"

".....ካልሆነ ከተጣለ ሁለት ወር የሆነው ልብስ አለ ባለቤቱ ሚወስደው አይመስለኝም እሱን ልስጥህ እንዴ?"

አረ አንች ተይኝ በናትሽ😡
.....በመጀመሪያ አንድ ሱሪ ብቻ ስላለኝ ሳይሆን ሁለት ተመሳሳይ ነጭ ሱሪ ስላለኝ ነው:: ሲቀጥል ነጭ ስለሆነ ቶሎ ቶሎ መታጠብ ስላለበት ነው.....አሁን ገባሽ?

"አይመስለኝም መሳይዬ! ምክንይቱም ሁለቱም ሱሪ ኪሶቹ ቀዳዳ ሊሆኑ አይችሉም ኣ!
አረ ቆይ....ደሞ በኪስህ ጩቤ ነው እንዴ ምትይዝበት?...እንዳለ ሶስቱም ኪስ ቀዳዳ ነውኮ"

"....ደሞ እዛው ቤትህ በማስታጠቢያ ነገር ለቅለቅ ብታረገው ችግር የለውም እኮ እዚህ ድረስ በ እንጀራ ፌስታል አንድ ሱሪ ዥውዥው እያደረክ ከምትመጣ:: ማለቴ ቤት ካለህ"

"ቅር አለህ እንዴ መሳይዬ አይንህ እንባ ቅርር አለውሳ?!"

Henok


@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
💔3🤣2❤1
ምክሩ
(በእውቀቱ ስዪም)
የሆነ ጊዜ ላይ ምኡዝ  ሰፈሩ  በሚገኘው  ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ በማኪያቶ ነፍሱን በማስደሰት ላይ  ነበር፤ ካጠገቡ  ሶስት ወጠምሻዎች አንዱን ጠረጴዛ ከበው ሻይ ቡና ይባባላሉ ፤ አንደኛው ሰውየ  የባጥ የፎቁን ያወራል፤ አፉን በከፈተ ቁጥር  ከውስጡ ከፍተኛ ጠረን እየተመዘዘ ይወጣና የእናት አገራችንን ንጹህ አየር ይበክለዋል፤
 
ምኡዝ  የሰውየው ጉዋደኞቹ በጠረኑ ተመርዘው አለመሞታቸው አስደነቀው፤  ማሽተት የተሳናቸው ሰዎች  መኖራቸውን አወቀ ፤ የኒህ ሰዎች አፍንጫ ዋና ጥቅም ፊታቸውን ለሁለት መግመስ እንደሆነ ገባው፤   ከራሱ ጋራ ትንሽ ሲሙዋገት ከቆየ በሁዋላ “ወንድሜ አንዴ ብቻህን  ላናግርህ “አለውና ወደ ጉዋሮ  ወሰደው፤

- “ይህንን ጉዳይ በጉዋደኞችህ ፊት  ልመክርህ  አልፈለግሁም፤ አፍህ መልካም ቃል እንጂ መልካም መአዛ ስለማያመነጭ መፍትሄ ፈልግለት ፤” አለው

“ ምን ማለት ነው ? “ አለ ሰውየው በንዴት፤

“ያፍህ ሽታ ልክ አይደለም፤ ከላይ ከላይ ከሆነ ቦርሸው፣ ከውስጥ  ከሆነ ታከመው”

“ሰውየ ታውቀኛለህ? ምናባህ  ነው የምትቀባጥረው?” አለ ሰውየው መዳፉ  ላይ ሀይል እያሰባሰበ፤

ምኡዝ በለዘበ ቃል ለማስረዳት ያደረገው ሙከራ ከንቱ አንደሆነ ሲሰማው ይለይለት ብሎ አንዲህ አለ፤

“ ያፍህ ጠረን በድንበር አካባቢ ቢነሰነሰ የውጭ ወራሪ አይደፍረንም ነበር”

ሰውየው እጁን ሰነዘረና ቢልቦርድ የሚያህል  አይበሉባውን ምኡዝ ፊት ላይ አሳረፈው፤  ከምኡዝ አፍንጫ  ደም ቡልቅ አለ
፤
“የሚገርመው መመታቴን ብዙ አልጠላሁትም፤   ሲነስረኝ አፍንጫየ ለጊዜው  ማሽተት አቆመ” ብሎ ትረካውን ደመደመ፤

ይህንን ሲነግረኝ ሆዴን እስኪያመኝ ሳቅሁና፤

” እዛው በጉዋደኖቹ ፊት ብትነግረው ይሻል   ነበር፤ ቢያንስ ገላጋይ አታጣም ነበር “ አልሁት፤

“ዝም በል ባክህ ! “  አለ ምኡዝ “ ሁሉም  ቡጢና አርግጫ ሊያዋጡ  ምን ይውጠኝ   ነበር! እንኩዋን በዚህ አለፈልኝ
!

@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹
@phylosophy_gora🇪🇹

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊
❤5👌2