ፓን አፍሪካኒዝም! በአዳዲስ እሳቤዎች በፓን አፍሪካ አዳራሽ!
አፍሪካ በአንዳንዶች ዘንድ ‹‹ጨለማው አህጉር›› በመባል በምትገለፅበት፣ አፍሪካዊያንም በተመሳሳይ ‹‹ያልሰለጠኑ ህዝቦች›› በመባል በሚጠሩበት ዘመን፣ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ የህይወት መስዋዕትነት በከፈሉ አያቶቻችን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ቀንዲልነቷን አስጠብቃ ኖራለች፡፡
የኢትዮጵያውያን አይደፈሬነት በአድዋ ጦርነት ወቅት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ተዳፍሮ የገባውን ፋሽስታዊ ወራሪ ሀይል ድል በማድረግ ከተራራ የገዘፈ ህያው ታሪክ ፅፎ አልፏል፡፡
በአድዋ ጦርነት የተመዘገበው ድል ለአፍሪካ አህጉር እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ብርሀን የለኮሰ የፓን አፍሪካኒዝም ሞተር መሆኑን ታሪክ ይነግረናል፡፡ የበፊቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባን መቀመጫው ያደረገበት አንዱ ምክንያትም ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ወንድም እህቶች በለኮሱት የተስፋ ብርሃን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ኢትዮጵያ በተምሳሌታዊነት ጉዞዋን አፍሪካውያን ለጋራ እድገት እንዲነሱ ዛሬም እንደ ትናንቱ የድርሻዋን እያበረከተች ትገኛለች፡፡
አፍሪካዊያን እና መላው ፍትህና ነፃነት ወዳድ ህዝብ ሁሉ የሚኮራበትን የአድዋ ድል መታሰቢያ እውን ያደረገችው መዲናችን ፓን አፍሪካን የሚል ስያሜ በያዘው ግዙፉ አዳራሽ 2ኛውን የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ እያካሄደች ትገኛለች፡፡
የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን እውን በማድረግ የተሟላ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለው ዘርፈ ብዙ ርብርብም የአፍሪካዊያንን አብሮነት፣ ነፃነትና እና የጋራ ዕድገት ከፍ ለሚያደርገው የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ትልቅ አቅም ነው፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity

ጉባኤው የአፍሪካ ገዢም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢኮኖሚ ለውጥ እና ለዜጎች ህይወት መሻሻል ከፍ አድርገው እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው።
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር
#aa_prosperity
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር
#aa_prosperity
“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ። የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው።
በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው። ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል።
በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች።
ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጉባኤው ለመዲናችን ተምሳሌታዊ ጉዞ ማንሰራራት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል!
ብልፅግና ፓርቲ የጠራ እሳቤ ያለው፣ ቃሉን በተግባር የመተርጎም ልምድ ያካበተ፣ የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ያበሰረ ግዙፍ ፓርቲ ነው፡፡
የዴሞክራሲ ባህልን በጠንካራ መሰረቶች ላይ እየገነባ የሚገኘው ፓርቲያችን ለሀሳብ የበላይነት፣ ለሁሉን አቀፍ ልማት፣ ለአካታች ዕድገት እንዲሁም ለብሔራዊነት የወል ትርክት ግንባት ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡
በአዳዲስ ፈጠራዎች እና በመፍጠን መርሆቹ፣ በዳበረ የስራ ባህል፣ ቃሉን በተግባር እየተረጎመ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ በሁለንተናዊ አቅሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ላይ ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፓርቲዎች ተርታ መጠቀስ የቻለ ተራማጅ ፓርቲ ነው፡፡
ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ሀገራዊ ራዕይውን በተስፋ ሰጪ ድሎች እያሳካ የሚገኘው ፓርቲያችን አህጉራዊ አሻራውን ለማሳረፍም ብርቱ ጥረቶችን እያሳረፈ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፤ የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤዎች ተግባር ላይ በመዋላቸው የተመዘገቡ ስኬቶችን ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን በማካፈል የጋራ ዕድገትን ለማፋጠት ጉባኤው የጎላ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ በከተማ ውበትና ፅዳት በተለይም በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማት እንዲሁም በሌሎች የከተማ መልሶ ግንባታ ተግባራት በመዲናችን የተመዘገቡ ስኬቶች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለመጡ ፖሊሲ አውጪዎች እና የሀሳብ ፖለቲካ አራማጆች ጉልህ አበርክቶ ይኖራቸዋል፡፡
አዲስ አበባን ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት፣ ወጣቶች የነገ ህይወታቸውን ዛሬ የሚገነቡባት፣ ሴቶች እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባት፣ የሀገር ባለውለታ አረጋውያን ተገቢውን ክብርና እንክብካቤ የሚያገኙባት ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረጉ ሰው ተኮር ተግባራት በሌሎች ሀገራትም እንዲሰፉ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በመዲናችን መካሄዱ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
አህጉር አቀፍ ጉባኤው ለመዲናችንም ለተሞክሮ የሚበቁ ልምዶቿን ከማካፈል ባሻገር፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የሀሳብ ፖለቲካ አራማጆች የሚሰጧቸውን ገንቢ አስተያየቶች የዕቅድ አካል በማድረግ የላቀ ድል ለማስመዝገብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥርላታል፡፡