Prosperity Party A.A - ብልፅግና
11.1K subscribers
5.87K photos
371 videos
5 files
431 links
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት
Download Telegram
የመዲናችን ሽልማት የጋራ ጥረታችን እና ዘመን ተሻጋሪ አሻራችን ውጤት ነው!

የአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ለነዋሪዎቿ ብቻም ሳይሆን ከተማዋን በቅርብም በሩቅም ለሚያውቋት ሁሉ አስደማሚ ነው፡፡

ስራዎቻችን በአይን የሚታዩ ፣ በእጅ የሚዳሰሱ ፣ የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል የሚመዘኑ ናቸው።

ነገን ዛሬ በመገንባት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ርብርብ የዜጎቻችንን ህይወት አዘምኗል።

በመፍጠር እና በመፍጠን እየተገነቡ የሚገኙ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶቻችን ነዋሪዎችን ከጥልቅ ጉስቁልና በማውጣት የተሻለ ህይወት እንዲመሩ አስችለዋል።

ህፃናትን ፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያንን እና ሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ ፕሮጀከቶቻችን የልማታችንን አካታችነት ያረጋግጣሉ።

በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በኮሪደር ልማቱ የለሙ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የከተማችን ንፁህና ውብ መሆን አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የተመቸች፣ ለጎብኝዎችም ተመራጭ ማድረጋቸው የማይታበል ሀቅ ነው።

በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች የከተማችንን የቤት ፍላጎት እና አቅርቦት ያለመጣጣም ችግር በመሰረታዊነት ለመቅረፍ ከሚደረገው ርብርብ ባሻገር ባለፀጎችን እና ሌሎች በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ለአቅመ ደካሞች እየተገነቡ የሚገኙ ቤቶችም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን አሳድገዋል።

ዲጂታል የአንድ ሞሶብ አገልግሎትን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ በማድረግ የቴክኖሎጂን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እያቀለለ ይገኛል።

ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ከመገንባት ባሻገር የብዝሀ ትራንስፖርን በማስፋፋት፣ የተሽከርካሪ ፓርኪንግ እንዲሁም ተርሚናሎችን ተደራሽ በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትም የዜጎችን እንግልት ቀንሰዋል።

የከተማችን የደን ሽፋን ወደ 2 ነጥብ 8 በመቶ ወርዶ ከነበረበት ከ23 በመቶ በላይ መድረሱም ልምላሜዋን ከማሳደግ ባሻገር ብሩህ ተስፋዋን አፍክቷል።

አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት ለማሻሻል እያደረገችው ያለው ትጋት ተምሳሌት እንድትሆን አስችሏታል። የከተማችን ተምሳሌታዊ ጉዞ አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ እውቅና አስገኝቶላታል።

ተወዳዳሪነቷ በእጅጉ ስላደገ መዲናችን በርከት ያሉ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማሸነፏን አጠናክራ ቀጥላለች።

በተባበሩት መንግሥታት UN-Habitat በቻይና ያዘጋጀውን የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማትን በማሸነፍ አዲስ አበባ የከፍታ ጉዞዋን አስቀጥላለች።

በተደመረ አቅም ቀን ከሌት የምንተጋው ለህዝባችን ህይወት መሻሻል እንዲሁም ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ ነው። እየተገኙ ያሉ እውቅናዎች እና ሽልማቶችም በየደረጃው የሚገኘው አመራር እንዲሁም የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ዘመን ተሻጋሪ አሻራ ውጤት ናቸው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity
የከተማችን ፈጣን ዕድገት የስዕበት ማዕከልነቷን ከፍ ማድረግ ችሏል!

መዲናችን ተወዳዳሪ የሆኑ የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲኖሯት የተፈጥሮ ፀጋዎቿን በአግባቡ የማልማት ስኬታማ ርብርቡ በተለይም በኮሪደር ልማቱ፣ በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች እና በሌሎችም የከተማ መልሶ ግንባታ እንቅስቃሴዎች በጉልህ ተንፀባርቋል፡፡

የተፈጥሮ ውበት ከዘመናዊ የስነ-ህንፃ ጥበብ ጋር በማዋሀድ የተገነቡት ወዳጅነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ እና ሌሎች የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ ላይ ይገኛሉ።

አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጎብኝዎቿ ተመራጭ ለማድረግ በሚደረገው ብርቱ ጥረት የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶችም ጉልህ ሚና ማበርከት ጀምረዋል፡፡ አስታዋሽ አጥተው የቆሻሻ መጣያ ሆነው የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎች ፣ በተቀናጀ ሰው ተኮር ልማት፣ በፅዳትና በአረንጓዴ ልማት የከተማችንን ውብ ገፅታ መግለጥ ችለዋል፡፡

አልፎ ለመሄድ ጭምር አስቸጋሪ የነበሩ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ህፃናት የሚቦርቁባቸው፣ ወጣቶች ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚያዘወትሯቸው፣ አረጋውያንም የመንፈስ እረፍት የሚያገኙባቸው ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች በልዩ ደስታ የሚጎበኟቸው የስዕበት ማዕከላት ሆነዋል፡፡

የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን እና ሌሎችም ሜጋ ፕሮጀክቶችም አዲስ አበባን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ብርቱ ጥረት ወደ ፊት ያራመዱ የመደመር ትውልድ ግዙፍ አሻራዎች ናቸው፡፡

ብሔራዊ ቤተ መንግስትን ጨምሮ የከተማዋን ነባር ቅርሶች ዘመን ተሸጋሪ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት፣ አራዳ ፓርክን የመሳሰሉ ግዙፍ ፓርኮች፣ በየአካባቢው የለሙ የኮሪደር ልማቶች፣ በየአካባቢው ለወጣቶች የተገነቡ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የህፃናት መጫዎቻዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎችም ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን የስዕበት ማዕከልነት ከፍ አድርገዋል፡፡

በዳበረ የስራ ባህል ቀን ከሌት 7/24 በመትጋት እየተመዘገቡ የሚገኙት የከተማችን አንፀባራቂ ስኬቶች ለላቀ ድል ይበልጥ የሚያነሳሱ እንጅ የሚያዘናጉ አይደሉም፡፡ ፓርቲያችን ካስቀመጠው ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ግዙፍ ራዕይ አኳያ ይበልጥ በመትጋት፣ የላቀ ድል ማስመዝገብ እንደሚገባ በመረዳት ተቋማዊ አቅምን ማሳደግ ይገባል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity
የመደመር ዲፕሎማሲ ስኬት

ኢትዮጵያ ካለፉት የታሪክ ስብራቶች በመማርና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስቀደም፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት አዲስ የከፍታ ምዕራፍ ላይ አሸጋግራለች።

ባለፉት አመታት በብልፅግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግስት የመደመር እሳቤን የውጭ ግንኙነት መርሆ በማድረግ አገራዊ ክብርን፣ ሉዓላዊነትን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ ዉጤታማ የዲፕሎማሲ ስራን በተግባር አሳይቷል።

የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት ፕሮግራም "ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚለው መርህ የፓን-አፍሪካኒዝም መሪነቷን ያጠናከረ ሲሆን፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን ቀጣናዊ በማድረግ በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ መድረክ ላይ የላቀ ስምና ተቀባይነትን አትርፏል።

በሌላ በኩል የሀገሪቱን የመከላከያ አቅም በማዘመን ረገድም የተመዘገበው ወታደራዊ የዲፕሎማሲ ድል ሌላው ትልቅ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ ከሩሲያ መንግሥት ጋር ባደረገችው ዉጤታማ ስምምነት መሠረት፣ የዓለምን የአየር ኃይል የቴክኖሎጂ የበላይነት የያዙትን 12 (Su-35) ተዋጊ ጄቶች የመጀመሪያ ዙር በመረከብ ከሰሃራ በታች ይህንን የ4++ ትውልድ ቴክኖሎጂ የታጠቀች የመጀመሪያዋ ሀገር መሆን ችላለች።

በተጨማሪም (S-400) የረጅም ርቀት አየር መከላከያ ሲስተሞች ጋር ተዳምሮ፣ ሀገሪቱ የትኛውንም ዓይነት የአየር ላይ ጥቃትና ሚሳኤሎችን አስቀድማ የመቀልበስ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ፣ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ትንኮሳዎችን ቀድሞ ተዘጋጅቶ በመግታትና በቀጣናው ፍጹም የአየር ላይ የበላይነትን ለመጎናጸፍ ታላቅ ፋይዳ አለው።

በብልፅግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግስት በቀጣይም ሀገራዊ ክብርን እና ሀገራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ የውጭ ግንኙነት መርህ በማስቀጠል፣ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ተቋማትን በመገንባትና የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአለም መድረክ ክብሯ የተጠበቀ ታላቅ አፍሪካዊት ሀይል የማድረግ ራዕይን በተግባር ያሳያል።
#aa_prosperity