Prosperity Party A.A - ብልፅግና
11.1K subscribers
5.87K photos
371 videos
5 files
431 links
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት
Download Telegram
የመዲናችን ሁሉን አቀፍ ዕድገት የእሳቤ ጥራትና የተግባር ቁርጠኝነት ውጤት ነው!

አቅምን በደመረ፣ ፀጋዎችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ባዋለ፣ ነገን አሻግሮ በተመለከተ ግልፅ እሳቤ በገበታ ለሸገር ፕሮጀክት መሰረቱ የፀናው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ ውጥናችን ፍሬያማ በመሆኑ፣ መዲናችን ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ተምሳሌታዊነቷ ሰፍቷል፡፡

ግዙፉን የአድዋ ድል መታሰቢያ ጨምሮ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል፣ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት፣ ግዙፍ ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ በየክፍለ ከተማው የተገነቡ የፀጥታ ተቋማት፣ የውሃ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎችም ግዙፍ የልማት ነጠብጣቦች በመንገድ መሰረተ ልማቶች እየተሳሰሩ የከተማችንን አዲስ ገፅታ መግለጥ ችለዋል፡፡

ለከተማችን ፈጣን ዕድገት ማርሽ ቀያሪ ሆኖ የተከሰተውና ተሞክሮው በሁሉም የሀገራችን ከተሞች እየሰፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም የመዲናችንን የከፍታ ጉዞ እያፋጠነው ይገኛል፡፡

የመፍጠር እና የመፍጠን መርሀችን አካል የሆነው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም የነዋሪዎቻችንን ህይወት ከማሻሻል ባሻገር መዲናችንን ውብ ገፅታ በማላበስ የቱሪስት መዳረሻነቷን አሳድጓል፡፡

የከተማ መልሶ ግንባት ስራዎች በተለይም በውሃ፣ በመንገድ፣ በቴሌ፣ በመብራት እና በሌሎችም ተቋማት የቅንጅት ክፍተት ምክንያት ሲፈጠሩ የቆዩ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችንም እየቀረፉ እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል፡፡

አካባቢን የማልማት፣ ከተማን የመገንባት፣ ሀገርን የማሳደግ፣ ህዝብን ፍትሀዊ ተጠቃሚ የማድረግ የብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ እሳቤዎች ልቀው እንዲተገበሩ የመደመር መንግስት አበክሮ እየተጋ ሲሆን፣ ህዝባችንም ሁሉን አቀፍ ተሳትፎውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity
ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ሀብት አጠቃቀም፤ የመደመር መንግስት የከተማ ልማት አዲስ ምዕራፍ!

በአዲስ አበባ የተጀመረው ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተሸጋገሩ የከተማ አውቶቡሶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተራ የትራንስፖርት ለውጥ ብቻ አይደለም።

በመደመር መንግሥት የልማት ዕይታ ውስጥ ሲታይ፣ የሀገርን ሀብት ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም የመቀየር፣ የኢኮኖሚ ነፃነትን የማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግና ሰው ተኮር የከተማ ልማትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።

በጥቅምት 22 ቀን 2019 የመጀመሪያዎቹ 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተቀየሩ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ገብተዋል። 400 ተጨማሪ አዳዲስ የጋዝ አውቶቡሶችም እንደሚመጡ ተገልጿል። ይህ ለውጥ ከሚያመጣቸው የታሪፍ፣ የወጪና የአካባቢ ጥቅሞች ባሻገር ትልቅ የልማት ትርጉም አለው።

በመደመር መንግሥት ዕይታ ለከተማዋና ለሕዝቡ ያለውን ትርጉም ዋና ዋና ነጥቦች ስንመለከት:-

👉 የሀገርን የተፈጥሮ ፀጋዎችን ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም መቀየር!

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች ያሏት ሀገር ናት። ነገር ግን የሀብት መኖር ብቻውን ልማት አያመጣም፤ ዋናው ጉዳይ ያለንን ሀብት ወደ ምርታማነትና የሕዝብ ጥቅም መቀየር ነው።

በጎዴ የሚመረተውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ መዲናዋ በማምጣት፣ በከተማ ትራንስፖርት ውስጥ መጠቀም መቻሉ የዚህ ሀሳብ ተግባራዊ ማሳያ ነው።

ይህም ሀገራችን ከተፈጥሮ ፀጋዎቿ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን፣ ፀጋዎቿን በመጠቀም ለዜጎቿ የተሻለ ኑሮ መፍጠር እንደምትችል ያሳያል።

👉 የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስና የኢኮኖሚ ነፃነትን ማጠናከር!

የነዳጅ ግዢ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ከሚያስከትሉ ዘርፎች አንዱ ነው። የከተማ አውቶቡሶች በአገር ውስጥ በሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ መንቀሳቀሳቸው ከውጭ የሚገባ ነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ያግዛል።

ይህም ማለት፦
- ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ፤
- የሀገር ውስጥ ሀብትን ለምርታማ ዘርፎች ማዋል፤
- በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ ምክንያት የሚፈጠርን የኢኮኖሚ ጫና መቋቋም፤
- የሀገርን የኢኮኖሚ መቋቋም አቅም ማጠናከር ማለት ነው።

ይህም እንደ ሀገር የተጀመሩ የራሳችንን ሀብት ተጠቅመን የራሳችንን የኢኮኖሚ ጫና የመቀነስ ጉዞ የሚያጠናክር ነው።

👉 በዜጎች ላይ ሊደርክ የሚችል ተፈጥሮዋዊና ሰው ሰራሽ ጫናዎችን መቀነስ!

የትራንስፖርት ወጪ የከተማ ነዋሪዎችን ዕለታዊ የኑሮ ወጪ ከሚወስኑ ነገሮች አንዱ ነው።

የአውቶቡስ የሥራ ማስኬጃ ወጪ ሲቀንስ ይህ በትክክል ወደ ተጠቃሚው ከተላለፈ፣ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።

የከተማ ልማት ማለት መንገድ፣ ሕንፃና ድልድይ መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በንጹህ አየር፣ በጤናማ አካባቢና በተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ማስቻልም ነው።
ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር የተሽከርካሪዎችን የተወሰኑ የአየር ብክለት አመንጪ ጋዞችና ቅንጣቶች ለመቀነስ ያግዛል።

በዚህም፦
- የአየር ብክለትን መቀነስ፤
- ለከተማ ነዋሪዎች ጤናማ አካባቢ መፍጠር፤
- የአረንጓዴ ከተማ ግንባታን ማጠናከር፤ እና
- የከተማን የአካባቢ ዘላቂነት ማሳደግ ማለት ነው።

እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር ወደ ዘላቂ የኃይል አጠቃቀም የሚወስድ ጠቃሚ የሽግግር እርምጃ ነው።

👉 የሀገር ውስጥ አቅምን፣ ቴክኖሎጂንና እውቀትን ማሳደግ!

ከዚህ ፕሮጀክት ትልቅ ትምህርት የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝን ማምረት ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊ ጥቅም ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂና አቅም መገንባት መቻልን ነው።

ጋዙን ከማምረቻ ቦታው ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን መገንባት፣ አውቶቡሶችን ማስተካከልና በሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ሥራውን ማከናወን አዲስ የእውቀትና የቴክኖሎጂ አቅም ይፈጥራል። ይህም በሀገራችን ልጆች ሆኖ ታይቷል፤ ትልቅ ስኬትም ነው።

ይህ በቀጣይ ለሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችም የሚስፋፋ አቅም ነው። የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማብቃት፣ የቴክኒክ እውቀትን ማስፋፋት፣ የጥገናና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪን ማጠናከር ያስችላል።

👉 የመደመር መንግሥት የልማት ጉዞን በተግባር ማሳየት!

የመደመር ዋና መርህ ያሉንን ሀብቶች፣ አቅሞች፣ እውቀቶችና የልማት እድሎች አቀናጅቶ ለጋራ ዓላማ ማዋል ነው።
ይህ ፕሮጀክትም በዚሁ ዕይታ ሲታይ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ አቅሞችን አቀናጅቶ ውጤት የማምጣት ተግባራዊ ማሳያ ነው።

- የኢነርጂ ዘርፍ የሚያመነጨው ሀብት፤
- የትራንስፖርት ዘርፍ የሚያቀርበው አገልግሎት፤
- የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያመነጨው መፍትሔ፤
- የሰው ኃይል የሚያበረክተው እውቀት፤
- የመንግሥት ተቋማት የሚያደርጉት ቅንጅት።

እነዚህ ሲዋሃዱ የአንድ ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን የሀገር አጠቃላይ የልማት አቅም ይጠናከራል።

👉 አዲስ አበባን አለም አቀፍ ተወዳዳሪና ዘመናዊና ከተማ ማድረግ!

አዲስ አበባ የሀገሪቱ መዲና ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከል ናት። ስለዚህ የከተማዋ የትራንስፖርት ሥርዓት ዘመናዊ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ ቀልጣፋና አካባቢን የሚጠብቅ መሆን አለበት። ይህንንም ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።

የተፈጥሮ ጋዝ አውቶቡሶች መግባት ከኤሌክትሪክ አውቶቡሶች፣ ከቀላል ባቡር፣ ከዘመናዊ የአውቶቡስ መስመሮችና ከእግረኛ ተስማሚ የከተማ መሠረተ ልማቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ ሲዳብር አዲስ አበባን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ያላት ከተማ ያደርጋታል።

አዲስ አበባን የብልፅግና ማሳያ ከተማ የማድረጉ ሂደት ከዚህም በላይ ጎልቶ ይቀጥላል።
#aa_prosperity
የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደር፡ አብሮ የማደግ፣ አብሮ የመለወጥ ተምሳሌት!

የከተማችን አርሶ አደሮች በመሬታቸው ኢንቨስት በማድረግ ለከተማችን ፈጣን ዕድገትም የድርሻቸውን የሚያበረክቱበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ለጋራ ልማት ከይዞታቸው የሚነሱ አርሶ አደሮችም ህይወታቸውን በዘላቂነት የሚለውጡባቸው ዕድሎች በከተማ አስተዳደሩ እየተመቻቹላቸው ይገኛሉ፡፡

ተገቢውን ካሳ ሳያገኙ ከይዞታቸው ሲነሱ የቆዩ የከተማችን አርሶ አደሮች ከተማ መጣብን የሚል አስተሳሰብ እንዲይዙ ግድ ብሏቸው ቆይቷል፡፡ የአሰራር ማሻሻያ በማድረግ፣ የከተማችን አርሶ አደሮች በከተማችን ፈጣን ዕድገት ይበልጥ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ፣ ከተማ አስተዳደሩ ባከናወናቸው ተጨባጭ ስራዎች አሁን ላይ ከተማ መጣልን የሚል አስተሳሰብ እየተገነባ ይገኛል፡፡

ለከተማችን የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በማቅረብ ለገበያ መረጋጋቱም ጉልህ ሚና ሲያበረክቱ የቆዩት የከተማችን አርሶ አደሮች ውሀን ጨምሮ ተገቢው መሰረተ ልማቶች ሳይሟሉላቸው በውስብስብ ችግሮች ውስጥ ቆይተዋል፡፡

ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ የሚገኘው አስተዳደሩ የከተማችን አርሶ አደሮች ህይወት በዘላቂነት እንዲሻሻል አበረታች ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ለልማት የሚነሱ አርሶ አደሮች ከአካባቢያቸው ብዙም ሳይርቁ ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶች እንዲኖሯቸው በማድረግ፣ ኑሯቸውን በዘላቂነት መምራት በሚያስችሏቸው ዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች የሚሰማሩባቸው ዕድሎች እየተፈጠሩላቸው መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያ መፍጠርንና መፍጠንን ማዕከል ባደረገ መልኩ በቴክኖሎጂ ወደ ፊት ለመራመድ በመዲናችን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት ብርቱ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች፡፡ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ በሚባለው አካባቢ በግብርና ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ነዋሪዎችም ለዚህ ትውልድ ተሻጋሪ ሀገራዊ ልማት ከመሬታቸው በፈቃደኝነት በመነሳት በትውልድ የሚዘከሩበትን አብነታዊ ተግባር አከናውነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለልማት ተነሽዎች የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደርን በመገንባት የተሻለ ህይወት የሚመሩበትን ምቹ መኖሪያ ቤት እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ አበርክቷል፡፡

የተለያዩ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደር ለነዋሪዎች የስራ ዕድል የፈጠሩ የንግድ ሱቆች እንዲሁም የምርት ማከፋፈያ እና መሸጫ መጋዘን ተገንብተውለታል፡፡

በመኖሪያ መንደሩ የተገነቡ የከብት ሸዶች እና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያዎችም ነዋሪዎች የቤተሰብ የወተት ፍጆታን ከመሸፈን ባሻገር ምርቶቻቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበትን ዕድል ያሰፋሉ፡፡

በመኖሪያ መንደሩ የተገነቡ የህፃናት መጫዎቻዎች እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያዎችም ጤናማ እና አምራች ትውልድ ለማፍራት የሚደረገውን ብርቱ እንቅስቃሴ ተደራሽነቱን የሚያሳድጉ ናቸው፡፡

ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የሰው ተኮር ልማት ስትራቴጂ ሁሉንም የከተማችን ነዋሪ ፍትሀዊ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለልማት የሚነሱ ዜጎች እንደ ከተማ ነዋሪነታቸው ከከተማችን ፈጣን ዕድገት ከሚያገኙት በረከት ባሻገር ወቅቱን ያገናዘበ ምትክ ቦታ እና ተገቢውን ካሳ የሚያገኙበት፣ ከተማዋ ስትለወጥ ህይወታቸውም የሚሻሻልበት የአሰራር ስርዓት በቀጣይም ልቆ ይተገበራል፡፡


በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity