አካታች መሠረተ ልማት፤ ለሁሉም እኩል ዕድል፣ ለከተማዋ ዘላቂ እድገት!
አዲስ አበባ ሁሉንም ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ያደረገ አካታች መሠረተ ልማት በመገንባት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት እያሻሻለች ትገኛለች።
የልማት ሥራዎቿ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ በመከናወናቸው፣ ከተማዋ ለሁሉም የምትመች፣ የምትደረስና የምታገለግል እንድትሆን መሠረት እየጣለች ነው።
ለእግረኞች፣ ለአረጋውያን፣ ለሕፃናትና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆኑ መንገዶች፣ የእግረኛ መሄጃዎች፣ የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችና ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ማንም ከከተማዋ ዕድገት የማይገለልበትን አካባቢ እየፈጠረች ነው።
በተለይም የእግረኛ መንገዶችን ለእንቅስቃሴ ምቹ ማድረግ፣ የመሻገሪያ ሥፍራዎችን ማሻሻል፣ የሕዝብ መዝናኛና መሰብሰቢያ ስፍራዎችን ማስፋፋት ነዋሪዎች ያለ እንቅፋት በከተማቸው እንዲንቀሳቀሱና የከተማዋን ሀብቶች በእኩልነት እንዲጠቀሙ ዕድል ይፈጥራል።
ይህም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ ማኅበራዊ ፍትሐዊነትን፣ የኑሮ ጥራትን፣ የሕዝብ ተሳትፎንና የከተማ አገልግሎት ተደራሽነትን የሚያጠናክር ለውጥ ነው።
በጋራ እንጠቀም፣ በጋራ እንጠብቅ!
#aa_prosperity

2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የፓርላማ አባላትና ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ጉባኤው "እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው" በሚል መሪ ሀሳብ ለሦስት ቀናት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የዘንድሮውን አህጉራዊ መድረክ ብልፅግና ፓርቲ ከአፍሪካ የአስተዳደር ማዕከል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ሲሆን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአህጉሪቱ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ላይ ዋና ተዋናይ እና የኢኮኖሚ ሞተር እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
የፓርቲው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሁል ጉባኤውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ የመድረኩ ዋና ዓላማ ፓርቲዎች የሕዝብን ኑሮ ከማሻሻልና ከኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አንጻር ያላቸውን ኃላፊነት ማሳደግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጉባኤውን እንድታስተናግድ የተመረጠችው ብልፅግና ፓርቲ ሕዝቡን ከድህነት ለማውጣት የልማትና የእድገት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የተሻለ የኢኮኖሚ ሽግግር በማምጣት ረገድ ምሳሌ መሆን በመቻሉ ነው ብለዋል።
ሁነቱ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያሳየችው የኢኮኖሚ ስኬትና የወሰደቻቸው ደፋር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡
ጉባኤው በአህጉሪቱ የሴቶችን የመሪነት ሚና እንዲሁም ወጣቶች በፖለቲካው ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ በተመለከተ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው ላይ ከ20 በላይ የሀገራት መሪዎች፣ 80 የሚጠጉ ከፍተኛ የፓርላማ አባላትና ሚኒስትሮች እንዲሁም ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የፖለሪካ ፓርቲዎች ተወካዮችን ጨምሮ አጠቃላይ 1 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች ይታደማሉ።
ጉባኤው ሲጠናቀቅ "የአዲስ አበባ ስምምነት" እንደሚጸድቅ የሚጠበቅ ሲሆን፤ መድረኩ በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን የመደመር ፍልስፍና እና አተገባበር ለአፍሪካውያን ለማስተዋወቅ ዕድል እንደሚፈጥርም አመልክተዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝምና የዲጂታል ኢኮኖሚ ስኬቶች እንዲሁም 78 ከተሞችን ያካተተው የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተሞክሮነት ይቀርባሉ፡፡
በተጨማሪም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የነዳጅ፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን የመሳሰሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለአፍሪካ አጋሮች እንደሚቀርቡም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ258 በላይ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ያስተናገደች ሲሆን፤ በዚህ ጉባኤም የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን እንደምታጠናክር ይጠበቃል።