ኀጢአት ትሠራለህ...
ከዚያም በኋላ ሰላት ለመስገድ፣ ቁርአን ለመቅራት ወይም ዲናዊ ትምህርት ለማዳመጥ ታስባለህ፤
በዚህ ጊዜ ሸይጣን መጥቶ፦ «ኀጢኣት ሰርተህ ደግሞ አላህ ይቀበለኛል ብለህ ታስባለህ?» ይልሃል።
ሸይጣን ግልጽ የሆነ አሳሳች ጠላት ነው፤ ፈጽሞም ከልብህ አይወጣም! ስለዚህ ከእርሱ ይልቅ ብልጥ ሁን፤ ፈጽሞም እጅ አትስጥ!
ሁላችንም እናወንጃለን፣ ኀጢአትም እንሠራለን፤ ኀጢአት የሠራ ሁሉ ዒባዳ ትቶ ተስፋ ቢቆርጥ ኖሮ፣ በምድር ላይ አላህን የሚያመልክ ማንም ባልቀረ ነበር!
አንተ በሁለት መንገዶች ላይ ትታገላለህ፦ ታዛዥነቶችን ጠብቆ ለማቆየት፣ እና ከኀጢአቶች ለመራቅ።
እነዚህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ - እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ ቀን ድረስ - ልትጓዝባቸው የሚገቡ ሁለት መንገዶች ናቸው። ስለዚህ አላህ ጽናትንና ጉልበት እንዲለግስህ ለምነው፤ እርሱም ይረዳሃል።

👍26👌9
አንዳንድ የመልካም ሥራ ውጤቶች እና የሰዎችን ፍላጎት ማሟላት በምላስ ምስጋናና ውዳሴ መልክ ወደ አንተ አፀፋው ላይመለሱ ይችላሉ፤ ይልቁንም በልብህ ውስጥ ባለ ሰላም፣ በሲሳይህ በረከት፣ የቀልብ እፎይታ እና ካሰብከውና ከጠበቅከው ውጭ በሚመቻችልህ መልካም ነገር መልክ አፀፋው ይመለሱልሃል።
ስለዚህ, ሰዎች ላደረግከው ነገር ሁሉ ዋጋ እንዲሰጡህ አትጠብቅ፤ ሰዎች ዘንድም የበጎ አድራጎትህን አሻራ አትፈልግ፤ አላህ ዘንድ ያለው የተሻለና ጸንቶ የሚኖር ነውና፣ እርሱ - ጥራቱ ይገባውና - መልካም የሠሩትን ሰዎች ዋጋ በከንቱ አያስቀርም።
መልካምን ሥራ የአላህን ፊት ብቻ በመፈለግ (በቅንነት) ሥራው፤ ከዚያም በሙሉ ልብ መረጋጋት ፤ ምክንያቱም የበጎነትህን አሻራ ማየትህ፣ ወይም ወደ አንተ እንዴት አፀፋው እንደተመለሰ ማወቅህ ቅድመ ሁኔታ አይደለምና፤ አላህ ማወቁ ብቻ በቂ ነው።

❤16👍4
ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ኢብኑ አል-ሙንከዲር እንዲህ ብለዋል፦
«ከዱንያ ደስታ የተረፈ ነገር ቢኖር የወንድሞችን ሃጃ ማሳካት ብቻ ነው።» 📚[ሙኽተሠር ታሪክ ዲመሽቅ]
اللهم إنا نسألك فعلَ الخيرات وترك ، المنكرات وحب المساكين وأن تغفر لنا و ترحمنا و تتوبَ علينا .

👍13❤3
🌷ሰባሑል ኸይር!
የመንፈስ ዕረፍትና የቀልብ ንጽህና የሚጀምሩት የውስጥ ምስጢራትን መመርመርና ሐሳብን መተርጎም የ«ሩቁን ዐዋቂ» (የአለማቱ ጌታ) ብቻ መብቶች መሆናቸውን ስትገነዘብ ነው። ስለዚህ ጉዳዩን ለእርሱ አደራ ሰጥ፤ እርስህን በማስተካከል ላይ ተጠመድ።
« (አላህ)ዓይኖች በድብቅ የሚፈፅሙት ክህደትና(ሰርቀው የሚመለከቱን) ልቦችም የሚደብቁትን ያውቃል።»የሰዎችን ሐሳብ በመከታተል፣ ስውር የሆኑ የሰዎች ዓላማዎቻቸውን በማነፍነፍ፣ ወይም በጥርጣሬ በመመዘንና ቃላትንና ድርጊቶችን ያለ አግባብ በመተርጎም ጊዜህ ከማባከን ፈጽሞ ተቂጠብ። ቀልቦች የየአላህ ብቻ መሆናቸውንና እርሱም (ሱብሐነሁ ወተዓላ) በልቦች ውስጥ የሚሸሸገውን ሁሉ ዐዋቂ መሆኑን ሁልጊዜ አስታውስ።
የመንፈስ ዕረፍትና የቀልብ ንጽህና የሚጀምሩት የውስጥ ምስጢራትን መመርመርና ሐሳብን መተርጎም የ«ሩቁን ዐዋቂ» (የአለማቱ ጌታ) ብቻ መብቶች መሆናቸውን ስትገነዘብ ነው። ስለዚህ ጉዳዩን ለእርሱ አደራ ሰጥ፤ እርስህን በማስተካከል ላይ ተጠመድ።
❤12👍6💔1
#የዓፊያ_ዋጋ!
ጤና እያለን ስለብዙ ችግሮች እንጨነቃለን። ጤናችንን ስናጣ ግን ብቸኛው ምኞታችን ጤናችንን መመለስ ይሆናል።
اللهم إنا نسألك تمام العافية، ونسألك دوام العافية، ونسألك الشكر على العافية، ونسألك الغنى عن الناس.

👍19❤17👌5
🌷#ሰባሑል_ኸይር
እንዳዘዘህ ስገድ፤ በገባልህ ቃልም ተደሰት (ተስፋ አድርግ)
በተለያዩ ችግሮች ለደከመው ልብ ሁሉ የተሰጠ ማጽናኛ፦
﴿يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ﴾
«ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያስተናብራል…» (ሱረቱ አስ-ሰጅዳህ 32:5)
ነገሩን ሁሉ እርሱ(አላህ) እያስተናበረው ሳለ፣ ለምን ትጨነቃለህ?
- የደረሰብህ በሽታ፤ ፈውሱ እርሱ ዘንድ ነው…
- ያደከመህና ያስጨነቀህ እዳ፤ መክፈያው እርሱ ዘንድ ነው…
- የከበደህ ጭንቀትና ሀሳብ፤ መወገጃው እርሱ ዘንድ ነው…
- ያስከፋህና እንድትጨናነቅ ያደረገህ ችግር፤ መውጫውና ሰፊ እፎይታው እርሱ ዘንድ ነው… ስለዚህ በጌታህ ተማመን!
ለአላህ የምታደርጋቸው ሁለት ሰጅዳዎች የደከመህንና ያሳሰበህን ሁሉ በግልጽ ጉዳይህን ሁሉ ለአላህ የምትነግረው እና ምስጥርህን የምትናዘዝባቸው ናቸው፤ እርሱም እንደሚጠግንህና እንደሚያክምህ እርግጠኛ በመሆንህ ልብህ ይረጋጋል።

👍20❤8
አቡ እስሐቅ አል-ፈዛሪ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦
📚(ምንጭ፡ ሒልየቱል አውሊያእ፣ 8፥255)
«ከሰው ልጆች መካከል ውዳሴ የሚወዱ አሉ፤ ነገር ግን እነሱ አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ የምታህል ዋጋ የላቸውም።»
📚(ምንጭ፡ ሒልየቱል አውሊያእ፣ 8፥255)
👌6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
## የአሻኢራ (አሽዐሪይ) ዑለሞች የማላቅ አደጋ!
ሸይኽ ሳሊሕ አስ-ሰነዲ የአሽዐሪይ እንዲህ ይላሉ፦፦
“በአሽዐሪይ ዓሊም ላይ ከመጠን በላይ መልካም ግምት መያዝ ትልቅ ችግርና አደጋ አለው። ለዚህም እንደ ምሳሌ አቡ ዘር አል-ሀረዊን (የታወቁና የሰሒህ አል-ቡኻሪ ዘጋቢ) ቢሆኑም፣ በአሽዐሪይ አስተሳሰብ እንዲወድቁ ያደረጋቸው አንዱ ምክንያት ለአሸሪያ ኡለሞች የነበራቸው መልካም ግምት ነው።(ሑስን አዝ–ዘን) ነው።
አቡ ዘር አል-ሀረዊ ከአሽአሪያ መሻይኾች አንዱ የሆኑት ለአቡበከር አል-ባቂላኒ ትልቅ ክብር ነበራቸው። ይህም የሆነው የታላቁን የሐዲስ ሊቅ አድ-ዳረቁጥኒ ለባቂላኒ የነበራቸውን አክብሮትና ማላቅ በመመልከታቸው ነው። በዚህም ምክንያት ባቂላኒን መቅረብና የአሽዐሪይ አስተምህሮን መቀበል ጀመሩ።
አቡ ዘር አል-ሀረዊ ወደ መካ በመሄድ የአሽዐሪይ (ኩላቢይ) አስተምህሮን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚያ ያስፋፉ ሰው ሆነዋል።
ከሞሮኮና ከአንደሉስ (ስፔን) ወደ መካ ለትምህርት የሚመጡ ተማሪዎች አስተምህሮውን ከአቡ ዘር በመቅሰም ወደ ሀገራቸው ይዘውት ተመለሱ።
### ማጠቃለያ
ሸይኽ ሳሊሐ አስ-ሲንዲ እንደሚሉት፣ የአሽዐሪይ አስተሳሰብ በሰፊው ሊሰራጭ የቻለው ለአሽዓሪያ ዑለሞች በተሰጠው የተጋነነ ክብርና ለእነሱ በተያዘው (ሑስን አዝ–ዘን) መልካም ግምት ምክንያት ነው። ይህም ከአህለል ሱና ወል-ጀመዓ (ሰለፊያ) እምነት እንዲርቁ ምክንያት ሆኗል።

👍9❤5
ዒልምን የመቅሰም እውነተኛ ዓላማ
ዕውቀትን ለመመራት (ለቅን መንገድ) በማሰብ ለመቅሰም ሞክር፤ የምትሰማውን ማንኛውንም አያት በጥንቃቄ አዳምጥ፣ በልብህ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ አስተውል፤ የሚደርስህን ማንኛውንም ሐዲስ በቀንህ ውስጥ እንዴት ልትጠቀምበት እንደሚገባህ ተመልከት።
ሸሪዓዊ እውቀት ለአንተ ጠቃሚ መሆኑን ከሚያሳዩ ምልክቶች እና የጥልቀ ግንዛቤ ጠንካራ ብርሃን ከሚሆኑባቸው ነገሮች አንዱና ዋናው፤ የዒልም ዋናው ዓላማ ተግባር ላይ ማዋል መሆኑን ከአእምሮ አለማጥፋቱና ሁልጊዜም ወደ አላህ የሚያቃርበውን ነገር ሁሉ አጥብቆ መሻቱ ነው።
ሙሳ (አለይሂ ሰላም) -ኸድርን(አለይሂ ሰላም)፦ (ከተማርከው እውቀት ቅን መንገድን (رشد) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህ?) እንዳለው ማለት ነው። ስለዚህ ለሸሪዓዊ ዕውቀት የሚደረግ ጥረት ከሁሉ በላይ ታላቁ ኒያ (ኢኽላስ) ቅን መሆናትንና መመራትን መፈለግ ነው።
የሸሪዓዊ ዕውቀት በረከት ሰዎች እንዲደነቁበት፣ አድናቆትን እንዲያትርፍና ምስጋና እንዲቸረው በሚል አላማ የተማረ፤ እውቀቱ ይወገዳል ወይም ይዳከማል፤ ለአላህ ብሎ ዕውቀትን የፈለገ ሰው ግን ትንሽም ዒልም እንኳ ይበቃዋል።
አላህ በዚህ መንገድ እንዲመራን፣ ባለመቻላችንና በቸልተኝነታችን ምክንያት እርሱ ዘንድ ካለው መልካም ነገር እንዳይከለክለን፣ ከዚህም ዕውቀት ያገኘነው ደርሻችንን ወሬና ጉራ ብቻ እንዳያደርግብን እንማጸነዋለን። ያ ረብ! ያ ረብ!
አላህ ሆይ! ቅን መንገድን አሳየን፣ ትክክለኛውንም ነገር ለግሰን፣ የነፍሳችንንም ክፋት ጠብቀን፣ ወደ አንተ ቅርበትና ፍርሃትን የሚጨምርልን ጠቃሚና የተባረከ ዕውቀት ስጠን።

❤19👍5🥰3💔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጎበኙት የነበረው ታዋቂው "የሸይኽ አቡ ሰሪዕ" መቃብር ሲከፈት የተገኘው አስደንጋጭ ምስጢር!
በግብፅ፣ በሱዌዝ ግዛት በዐይን ሱኽና ተራሮች አካባቢ "የሸይኽ አቡ ሰሪዕ" ዶሪሕ (መቃብር) በመባል የሚታወቅና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚጎበኝ ስፍራ ነበረ።
ይህ ቦታ በየዓመቱ በሳጥኑ ውስጥ የሚሰበሰበው የስለትና የስጦታ ገንዘብ ከፍተኛ ንብረትና ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ፣ በአካባቢው በሚገኙ ሁለት የገጠር አረብ ጎሳዎች መካከል የባለቤትነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥል ውስጥ ከቷቸው ቆይቷል።
ለረጅም ጊዜ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ሁለቱ ወገኖች በሽምግልና ተስማሙ፤ ስምምነቱም "መቃብሩን ወደ ሌላ ገለልተኛ ቦታ ማዛወር እና የሚሰበሰበውን ገንዘብ በእኩል መከፋፈል" የሚል ነበር።
ሆኖም መቃብሩን ለማንሳት ሲከፍቱት ትልቁ ድንገተኛ አደጋ ተፈጠረ! በውስጡ የሰው አፅምም ሆነ ዓይነት የ"ወሊይ" ቅሪት ሳይኖር፣ የተገኘው "የጥጃ ራስ" ብቻ መሆኑ ተደረሰበት።
ይህ አስደንጋጭ ግኝት በወቅቱ ሕዝቡንና ጎሳዎቹን ክፉኛ ያስገረመ ሲሆን፤ ውሸቱና ማጭበርበሩ በመጋለጡ መቃብሩ/ደሪሕ ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል።

👌21👍5❤4😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔴 ማለዳዎን በዚህ በሚማርክ ቲላዋ ይጀምሩና ቀንዎን ያስውቡ!
تلاوة عاطرة للشيخ محمد أيوب رحمه الله
تلاوة عاطرة للشيخ محمد أيوب رحمه الله
❤9👌4🥰3