የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.58K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
.قال رسول الله ﷺ  :
🌱🌹🌱
•مَنْ أصبَحَ منكمْ آمنًا في سِربِهِ معافًى  فِي جَسَدِهِ، عندَهُ قوتُ يومِهِ، فكأنَّما حِيزَتْ لَهُ الدنيـــا بحذافِيرِها•
🌱🌹🌱
صحيح الجامع (٦٠٤٢)
حسن

🌴የአላህ መልዕክተኛ ﷺ  እንዲህ ብለዋል፡-
🟤«አንድ ሰው በቀዬው ላይ ሰላምን በአካሉ ላይ ጤናን እና የእለት ጉርሱን ካገኘ፤ ምድራዊ ፀጋ በሙሉ እጁ እንደገባለት ይቆጠራል።»
📚ቲርሚዚ ዘግበውታል።

አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላምም ካንተ ነው፤
ሀገራችንን አማን ህዝቦቿን ሰላም አድርግልን!
ኣሚን!

https://telegram.me/sultan_54
❤8👍2
ሰባሑል ኸይር ያ ሸባብ!

አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾
«እናንተ ምእመናን ሆይ! (ትድኑ) ትሳኩ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ ተውበት አድርጉ (ተመለሱ)።» [1][2]

ተውበት የስኬት መንገድ እና የአንድ ባሪያ የመዳን ሰበብ ነው…
ስለዚህ ተውበትህን አታዘግይ፣ ወንጀልህንም ቸል አትበል፤ በፈጸምከው ጥፋት ተጸጽተህና ተመልሰህ ወደ አላህ ተመለስ።

ስህተት ላይ ብትወድቅም እንኳ ተመለስ፤ ሁለተኛም ሦስተኛም ሞክር [6][7]። ነፍስህን ታገል፣ የአላህ ባሪያ ሆይ! አላህ እንዳዘዘህም ቀጥ በል።

አላህ ሆይ! እውነተኛና ንጹሕ የሆነን ተውበት ለግሰን፤ አንተን እስክንገናኝም ድረስ በታዛዥነትህ ላይ አጽናን።
❤17👌2😱1
በዒባዳህ ላይ ያጋጠመህ ግድየለሽነት ወይም ጉድለት ምንም ያህል ቢበዛ፣ ጥሩ ሥነ-ምግባርን(አኽላቅ) ከመጠበቅ በጭራሽ ቸል አትበል፤ ወደ ከፍተኛዋ ጀነት መግቢያ ቁልፍህ ሊሆን ይችላልና። ደጋግ  ሰዎች ምንም ዓይነት ወንጀል የለባቸውም ብለህ ታስባለህን?! እነሱ እኮ፦ (በጥፋታቸው) ተሸፈኑ እንጂ በግልጽ(በአደባባይ አላመፁም፣ ምህረትን ጠየቁ እንጂ (በወንጀል ላይ) አልጸኑም፣ (ጥፋታቸውን) አመኑ እንጂ ነውራቸውን ለመሸፋፈን ኡዝር አላቀረቡም፣ እንዲሁም ካበላሹ በኋላ አበጁ (መልካም ሠሩ)።
ከቀደሙት ሰለፎች ለአንዱ፦ 'አንተና ዲንህ እንዴት ናችሁ?' ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም፦ 'ወንጀሎች ይበጣጥሱታል፤ እኔ ደግሞ በኢስቲግፋር እጠግነዋለሁ' ሲል መለሰ።
ጥያቄው ምንኛ ጥልቅ ነው! መልሱንስ ምን ያህል የጠለቀ ነው!!
👍23❤13
ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታቸውን እያየዙ ሊሆን ይችላል፤ ተስፋ አትቁረጥ!
በአንድ ጉዳይ ላይ ወደ አላህ አብዝተህና አጥብቀህ ዱዓ አድርገህ ... ከዚያ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ወደ ተቃራኒው ሲቀየር ብታይ፣ ዱአዬ አልተቀበለኝም ብለህ እንዳታስብ! አላህ መልካሙን ነገር አንተ ልትረዳው በማትችለው መንገድ እየመራው ይሆናል፤ በክስተቶችም የምስክርነትህንና የእምነትህን ጥንካሬ ይፈትናል። የእምነትህ ፅናት ሳይናወጥ የጸና ሆኖ ካገኘው ደግሞ ባልጠበቅኸው ስጦታ ያስገርምሃል.. አላህ በእርሱ በሚተማመኑት ባሮቹ ጥርጣሬና ግምት ልክ ነው!♥️
1❤35👌7👍3
የአንድ ተናጋሪ መልካም ንግግር (አቀራረብ)፦
– ጊዜን በጥንቃቄ መምረጥ፣
– ቃላትን መርጦ መጠቀም፣
– ረጋ ማለት (አለመቸኮል)፣
– ግልጽ በሆነ መንገድ ማስረዳት።
የአዳማጭ መልካም አረዳድ፦
– በጥሞና ማድመጥ፣
– ብዥታ ወይም ያልተገባ ነገር ሲኖር መጠየቅ፣
– በቀደሙ ቅሬታዎች ወይም አሉታዊ ሃሳቦች ላይ አለመመስረት።
👍27❤6
የዘመናችን ታላቅ ዓሊም ሙሐመድ ተቂዩዲን አል ሂላሊ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
​"በትዳር ሕይወት ውስጥ የትዳር አጋሮች መስተጋብር መሠረቱ ፍቅርና የጽኑ መተማመን መንፈስ ሊሆን ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን በሁለቱ መካከል ያለው የፍቅር ትስስር እየላላ በመሄድ፤ አንዱ ለሌላው የስቃይና የሰቀቀን መሣሪያ እንዲሁም የቅጣት አለንጋ የሚሆንበት መራራ እውነታ ይፈጠራል።"

العشرة الحسنة بين الأزواج..

قال العلامة محمد تقي الدين الهلالي رحمه الله تعالى :

فأساس العشرة الحسنة
المحبة والثقة بين الزوجين
فإذا فقدتا فقد انقطع الحبل بينهما وصار كل واحد منهما عذاباً و وبالاً على صاحبه.

📚أحكام الخلع في الإسلام | 34

​📖 አሕካም አል ኹሉዕ ፊል ኢስላም (34)
🔗 https://t.me/sultan_54
👍8❤6
« أَكْثَرُ مَنْ يَمُوتُ مِنْ أُمَّتِي بَعْدَ كِتَابِ اللهِ وَقَضَائِهِ وَقَدَرِهِ بِالأَنْفُسِ »
« أَكْثَرُ مَنْ يَمُوتُ مِنْ أُمَّتِي بَعْدَ قَضَاءِ اللهِ وَقَدَرِهِ بِالْعَيْنِ »
«ከአላህ ውሳኔ፣ ፍርድና ቀደር በመቀጠል ከኡመቴ አብዛኛው (ሰው) የሚሞተው በዐይን (በሰው ዐይን/በቡዳ) ነው።»
💔10👍5😱1
⚠️ ለወንዶች ጤና እጅግ ጠቃሚ መረጃ!
የነርቭ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሙሐመድ አል-መህዲ ስለ ወንድ ልጅ ጾታዊ ጥንካሬ እና ጤና ያብራሩትን ወሳኝ እውነታዎች እነሆ፦
❌ የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እውነታዎች
ጾታዊ ጥንካሬን ለማሻሻል እንደ ለውዝ፣ ማር እና አቮካዶ የመሳሰሉ ምግቦችን ብቻ መመገብ ብቸኛ መፍትሄ ተደርጎ ይታሰባል። ይሁን እንጂ እነዚህ ጊዜያዊ መፍትሄዎች ብቻ ናቸው። በማስታወቂያ ቪዲዮዎች ላይ የሚታዩት "አስማታዊ መጠጦችም" ለቀናት ወይም ለወራት የሚቆሙ የጊዜ ገደብ ያላቸው መፍትሄዎች ናቸው።
🔋 ጠንካራ ጾታዊ ኃይልን የሚያመጡ 3 ዋና ዋና ነገሮች፡
የአእምሮ ሰላም: ከጭንቀት ነፃ የሆነ እና የተረጋጋ አእምሮ መኖር።
ጾም: ሰው ሲጾም የወንድ ሆርሞን (ቴስቶስትሮን) ከ 130% በላይ ከፍ ስለሚል የጾታ ጉልበት እና ኃይል ይሰጣል። (በረመዳን ወር የሚታየው ከፍተኛ ጉልበት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው)።
የልብ ጥንካሬ እና የደም ዝውውር: ልብ ደምን ወደ ጾታዊ አካል በበቂ ሁኔታ ማድረስ መቻሉ እጅግ ወሳኝ ነው።
🛑 ለችግሩ ቀጥተኛ ምክንያቶች
እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል፣ ማጨስ እና አልኮል መጠጣት ያሉ ነገሮች ለጾታ ድክመት በቀጥታ ይዳርጋሉ።
✅ ዘላቂው መፍትሄ ምንድን ነው?
ትክክለኛው እና ዘላቂው መፍትሄ የአእምሮ ሰላም፣ ጾም እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሲሆን፣ እነዚህ ለልብ እና ለጤናችን ጥንካሬን በመስጠት አስተማማኝ ውጤት ያስገኛሉ።
🔗 ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ! 📲 [https://t.me/sultan_54]
❤28💔3
ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) በ«ረውደቱል ሙሒቢን» መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ፦፦
«አስተዋይ ሰው ይህን ይወቅ፦ በመጥፎ ስሜት ፍላጎቶች (ሸህዋ) የተለከፉ ሰዎች (በሂደት) ምንም ዓይነት እርካታና ጣዕም የማያገኙበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ፤ ያም ሆኖ ግን እንደ ልማድ (ሱስ) ስለሚሆንባቸው) እርሱን መተው አይችሉም።»
📚​(روضة المحبين 1/470)
❤18👍5
ገንዘባቸውን የሚመጸውቱ ባለሀብት የሆኑ ሰዎች አሉ። ይህም ፅድቅ ስራ ሲሆን ሰውን ወደ አላህ ያቃርባል። ነገር ግን ትልቁ አደጋና ጥፋት የሚመጣው፤ ግለሰቡ ከቅርብ ሰዎቹ ጋር ሆኖ “ለእገሌ እንዲህ ሰጠሁት፣ ለዚያኛው እንዲህ ለገስኩለት” እያለ  በራሱ በመኮፈስ ሲያወራ ነው። በዚህም ምክንያት በአላህ ዘንድም ሆነ በሰዎች ዘንድ ያለውን መልካም ዋጋ ያጣል፤ ምክንያቱም በጎ ስራውን የሰራው ለሚያልፈው የይዩልኝ ውዳሴና ለከንቱ ክብር ብሎ ስለሆነ።
"ሰደቃን በምትሰጡበት ጊዜ ቀኝ እጃችሁ የምትሰጠውን ግራ እጃችሁ እንዳታውቅ" አድርጉ የሚለውን አስታውሱ፤ እዚህ ላይ የተፈለገው ሚስጥራዊነት (ኢኽላስ) ነው፤ ምክንያቱም በስውር የሚመለከተው (አምላክ) በይፋ ምንዳችሁን ይከፍላችኋልና።
👍15❤9
« يَا مَعْشَرَ التُّجَّارِ، إِنَّ الْبَيْعَ يَحْضُرُهُ اللَّغْوُ وَالْحَلِفُ، فَشُوبُوهُ بِالصَّدَقَةِ »
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች
• ከንቱ ንግግር ፦ በንግድ እንቅስቃሴ ወቅት የሚደረጉ ጥቅም የሌላቸው ወሬዎች፣ ማጋነኖች ወይም ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን ያመለክታል]።
• መሃላ፦ ሸቀጡን ለማሻሻጥ ሲባል ወይም ደንበኛን ለማሳመን ሲባል የሚደረጉ አላስፈላጊ መሃላዎች ከባባድ ወንጀሎች ናቸው]።
• ሶደቃ ማውጣት፦ ነጋዴዎች በሚገበያዩበት ወቅት ከሚፈጠሩ ጥቃቅን ስህተቶች፣ ከንቱ ወሬዎችና አላስፈላጊ መሃላዎች ነፍሳቸውንና ሀብታቸውን ለማጽዳት ምጽዋት መስጠት እንዳለባቸው ይመክራል፤ ምክንያቱም መልካም ስራዎች ጥፋቶችን ያብሳሉና።
❤9🥰2
ትዳር ይሞታል!
—ትኩረትና እንክብካቤ ሲጎድል፤
ዝምታ የውይይት ቋንቋ ሲሆን፤ እልህና ድርቅና የመግባባትን ቦታ ሲይዝ፤ እንዲሁም ያማሩ ቃላት የማይረሳ ቁስል ሲሆኑ።
💔
በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ፣ በጣም አስፈላጊውን ነገር ልናጣ እንችላለን.. ገንዘብን ወይም ማዕረግን አይደለም የምናጣው፤ ይልቁንም ያንን የሚያሰባስበንን ሞቅ ያለ ፍቅርና ደስታችንን ይፈጥር የነበረውን ቀላልነት ነው የምናጣው..
ትዳር በሁለት ሰዎች መካከል ያለ ውል ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ቀጣይነት ያለው ትኩረት፣ እንክብካቤ እና ትዕግስት የሚያስፈልገው የፍቅር፣ የእንክብካቤና የመግባባት ጉዞ ነው::
🤍
👍22❤9
Audio
🔴 የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
الجنة ونعيمها

✨ ጀነትና ፀጋዎቿ

⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️

🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ጁማደል አወል 06/1448 አ/ሂ

http://t.me/kalityhamzamesjid
❤14
«የሰዎች  ሃጃ ወደ እናንተ  መምጣት ከአላህ ለእናንተ የተሰጠ ጸጋ መሆኑን አታውቁምን?!»

— ፉደይል ኢብኑ ዒያድ (አላህ ይዘንላቸው)
❤25👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
​مَنْ أَصْبَحَ مِنْكُمْ آمِناً فِي سِرْبِهِ، مُعَافًى فِي جَسَدِهِ، عِنْدَهُ قُوتُ يَوْمِهِ، فَكَأَنَّمَا حِيزَتْ لَهُ الدُّنْيَا بحذافيرها
❤10👍3
«የታላቁ የዘመናችን ዓሊም ጥሪ!»
ፕሮፌሰር ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሲንዲይ ሀፊዘሁላህ

«ውድ የሐቅ ወዳጆችና ወንድሞች ሆይ! ሁሌም ልብ ልንለው የሚገባው አንድ መሠረታዊ እውነት አለ፣ እርሱም፦

በዒልም ፍለጋ ላይ ዘወትር መትጋትና መጽናት ብቁ ዓሊምን ያፈራል፤ ሸሪዓዊ ዕውቀትን ከላይ ከላይ ብቻ መቅመስ ግን ጥልቅ ያልሆነ አመለካከትን ይፈጥራል፤ አሊያም ምንም ፍሬ ሳያፈራ ባዶውን ያስቀራል።

በአሁን ዘመን ያለው መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚሻው ጥልቅ ዕውቀት ያላቸውን ረባኒይ ዑለሞችን እንጂ፣ ጥራዝ–ነጠቅ ዕውቀት የሚመኩ ግለሰቦችን አይደለም። ምክንያቱም በዘመናችን የስህተትና የጥመት ሰባኪዎች፣ የጥርጣሬ ዘሪዎች እንዲሁም ዕውቀት የለሽ አዋቂ ነን ባዮች በዝተዋል።

ስለዚህ እናንተ የሐቅ ባለቤቶች ሆይ! በብርታት፣ በልፋትና በፅናት የዒልምን ጎዳናን አጥብቃችሁ ያዙ። በዕውቀት ፍለጋ ጉዞ ላይ «እዚህ ጋር ይበቃኛል።» ብላችሁ ገደብ አታበጁ። ታገሉ፣ ፅናት ይኑራችሁ፣ የዕውቀትን ጥልቀት ተቋደሱ፣ ጣፋጭ ቃናውን አጣጥሙት። በዒልም ጉዞ ውስጥ እያንዳንዱን ደረጃ በተሻገራችሁ ቁጥር ለእሱ ያላችሁ ፍቅር፣ ናፍቆት እና "ወረዐችሁ" (ጥንቁቅናታችሁ)እየጨመረ ይመጣል።

አላህ ለእኔም ለእናንተም ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ሥራን እንዲሁም በሁሉም ላይ ኢኽላስን ይወፍቀን! 🤲»

---ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሲንዲይ–
❤28👍10
የጥሩ ሚስት ሥነ-ምግባራት (አደቦች) መካከል በጥቂቱ፦
አል-ገዛሊይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦

• በቤቷ ውስጥ የምትረጋ፣ በስራዋ ላይ የምትበረታ፣ (ሰዎችን ለማየት ወይም ለመታየት) ወደ ውጭ መውጣትና ማየት የማታበዛ መሆንዋ ነው ።

• ከጎረቤቶቿ ጋር ንግግሯ አነስተኛ የሆነ፣ አስፈላጊ ሁኔታ ካላስገደዳት በቀር ወደ እነሱ ዘንድ የማትገባ መሆንዋ።

• ባሏ በሌለበት ክብሩን የምትጠብቅ፣ በጉዳዮቿ ሁሉ እርሱን ማስደሰትን የምትፈልግ፣ በራሷ ክብረ ንፅሀና ሆነ በገንዘቡ ላይ ክህደት የማትፈጽም መሆንዋ ።
• ያለ እርሱ ፈቃድ ከቤቷ የማትወጣ፣ በፈቃዱም ብትወጣ እንኳን ባልተጋነነ (ትኩረት በማይስብ) አለባበስ ተሸፋፍና የምትወጣ፣ ከዋና ዋና መንገዶችና ገበያዎች ይልቅ ሰው የማይበዛባቸውን ቦታዎች የምትመርጥ፣ ባዳ ሰው ድምጿን እንዳይሰማ ወይም በማንነቷ እንዳያውቃት እጅግ የምትጠነቀቅ መሆንዋ።

• ለሃጃዎቿ ስትል የባሏን ጓደኛ የማትቀርብ፣ ይልቁንም ያውቀኛል ወይም አውቀዋለሁ ብላ ከምትጠረጥረው ሰው የምትርቅ መሆንዋ።

• ዋነኛ ጭንቀቷና ትኩረቷ ጉዳዮቿን ማስተካከልና ቤቷን ማስተዳደር የሆነ።

•(በዒባዳዋ) በሶላቷና በጾሟ ላይ ትኩረት የምታደርግ።

• የባሏ ጓደኛ ደጃፍ ላይ ቆሞ ፍቃድ በጠየቀ ጊዜ ባሏ ከሌለ፣ ለራሷና ለባሏ ካላት ክብርና ጥንቃቄ የተነሳ ጥያቄ የማታበዛና  ተራ ወሬ የማታወራ መሆንዋ።

• አላህ ባስገኘው የባሏ ሲሳይ ላይ የምትብቃቃ (ረክታ የምትኖር) መሆንዋ።

• የባሏን መብት ከራሷም ሆነ ከሌሎች ዘመዶቿ መብት ሁሉ የምታስቀድም ።

• ንፅህናዋን የጠበቀች፣ በፈለገው ጊዜ ሁሉ ባሏ እንዲደሰትባት በሁሉም ሁኔታዎች ዝግጁ የሆነች።

• ለልጆቿ አዛኝ የሆነች፣ ክብራቸውንና ምስጢራቸውን የምትጠብቅ።

• ልጆቿን ከመሳደብና ባሏን ከመነታረክ  ምላሷን የጠበቀች መሆንዋ ነው።

📚— ኢሕያእ ዑሉም አድ-ዲን (2/59) [1]
❤33👍11
📣 بشرى سارة للطالبات

مجالس علمية متميزة للنساء

✔️ تنبيه:- الدعوة خاصة بالنساء.

يسرُّ مركز ابن مسعود الإسلامي أن يدعو الأخوات الكريمات لحضور مجالس علمية وتربوية متميزة، تقدمها الأستاذة الفاضلة أم ليلى من المملكة العربية السعودية، وذلك وفق البرنامج الآتي:

📖  أولًا: شرح رسالة «معالم التوحيد»

الدرس الأول: أهمية التوحيد وخصائصه وأنواعه.

الدرس الثاني: تحقيق التوحيد، ونواقضه ونواقصه.

الدرس الثالث: مصدر التوحيد وفوائده وثماره.

📖 ثانيًا: دروس ومحاضرات متنوعة

- سنن قلَّ العمل بها.
- دور المرأة في الإصلاح وحماية المجتمع.
- التوبة وأهميتها في حياة المسلم.

📅 التاريخ: يومي الاثنين والثلثاء، ٢٦-٢٧ أكتوبر ٢٠٢٦م

⏳ وقت المحاضرة: العاشرة صباحا (الساعة الرابعة صباحا بالتوقيت المحلي)

📍 المكان: معهد دار الحديث بمركز ابن مسعود الإسلامي – حي ١٨، أديس أبابا

نسأل الله أن يجعل هذه المجالس مباركة نافعة، وأن يرزقنا جميعًا العلم النافع والعمل الصالح.

مركز ابن مسعود الإسلامي

____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna
❤1
📣 ዐረበኛ መስማት ለሚችሉ እህቶች ታላቅ የምሥራች!
ልዩ የሴቶች የዕውቀት ማዕድ
✔️ ማሳሰቢያ፡- ጥሪው ዐረበኛ መስማት ለሚችሉ ሴቶች ብቻ ነው።
የኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከሳዑዲ አረቢያ በመጡት የተከበሩሸይኻህ ኡሙ ለይላ የሚሰጡትን ግሩም የዒልም እና የተርቢያ መድረኮች እንዲከታተሉ በአክብሮት ይጋብዛል።
መርሃ ግብሩም በሚከተለው መልኩ ይከናወናል፡-
📖 الدرس الأول: أهمية التوحيد وخصائصه وأنواعه.

الدرس الثاني: تحقيق التوحيد، ونواقضه ونواقصه.

الدرس الثالث: مصدر التوحيد وفوائده وثماره.

📖 ثانيًا: دروس ومحاضرات متنوعة

- سنن قلَّ العمل بها.
- دور المرأة في الإصلاح وحماية المجتمع.
- التوبة وأهميتها في حياة المسلم.
📅 ቀን፡ ሰኞ እና ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16-17 ቀን 2019 ዓ.ል.
⏳ ሰዓት፡ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፡ ኢብኑ መስዑድ (ዳሩል ሀዲስ ) - 18 አደባባይ
አላህ እነዚህን መድረኮች የተባረኩና ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲያደርግልን፣ ሁላችንንም ጠቃሚ ዕውቀትና መልካም ስራን እንዲለግሰን እንለምነዋለን።
የኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
❤9👌9