የሸይኽ ዐብዱረዛቅ ኢብኑ ዐብዲልሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር (አላህ ይጠብቃቸው) የሕይወት ታሪክ
ታላቁ ዓሊም፣ ወሪዕ(ጥንቁቁ ፈቂህ)፣ የመልካም ስብዕና እና የከፍተኛ ስነ-ምግባር ባለቤት የሆኑት ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ኢብኑ ዐብዲልሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር (አላህ ይጠብቃቸው)።
እሳቸው ጥልቅ እውቀትን፣ መልካም ስነ-ምግባርን፣ ከፍተኛ ትጋትን እንዲሁም በማስተማርና በዳዕዋ ስራ ላይ ዘወትር በማስተማር በአንድ ላይ ካዋሃዱ ታላላቅ ዑለማኦች (ሊቃውንት) አንዱ ናቸው። በለስላሳነታቸውና በርህራሄያቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ ከጭቅጭቅ የራቁና ሰዎችን ከማንቋሸሽና ሁከት ከመፍጠር የጠሩ ናቸው። ስለ ማንም ሰው መጥፎ ሲናገሩ አይሰማም፤ ይልቁንም መመሪያቸው ስህተትን መሸፈን፣ መምከርና በትክክለኛው መንገድ መምራት ነው።
የዒልም እድገታቸውና መሻይኾቻቸው፦
እሳቸው (አላህ ይጠብቃቸው) ያደጉት በዒልም እና በዲን በታነጸ ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በታላቁ የመዲና የሐዲሥ ሊቅ በሆኑት በአባታቸው በሸይኽ ዐብደልሙሕሲን አል-ዐባድ ጥላ ስር ነው ያደጉት። ይህም ለስብዕናቸው መገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። በመቀጠልም የዘመኑ ታላላቅ ዑለማኦች እውቀትን ቀስመዋል፤ ከእነዚህም መካከል፦
ሸይኽ ዐብደልዐዚዝ ኢብን ባዝ
ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን
ሸይኽ ዐብደላህ አል-ጉደያን
ሸይኽ ዐብደላህ አል-ጉነይማን
ሸይኽ ዐሊ ናሲር ፈቂሂ እና ሌሎችም።
በዚህም የኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ (መዲና) እውቅ መምህር እና በመዲና መስጂደ ነበዊ ከሚያቀሩ ታዋቂ የዲን ሊቃውንት አንዱ ለመሆን በቅተዋል።
የቅርብም የሩቅም ሰው ለመልካም ስነ-ምግባራቸው፣ በማስተማር ክህሎትና ብቃታቸውና ንግግራቸው ግልጽነት መስክሮላቸዋል። እንዲያውም ሸይኽ ሷሊሕ አስ-ሱሐይሚ ስለ እሳቸው ሲናገሩ፦
ታዋቂ ማብራሪያዎቻቸውና ትምህርቶቻቸው (ሸርሆች)
ሸርሕ አል-ቀዋዒድ አል-ሙሥላ (شرح القواعد المثلى)
ሸርሕ አል-ከሊም አጥ-ጦይብ (شرح الكلم الطيب)
ሸርሕ ቀዋዒድ አል-አስማእ አል-ሑስና (شرح قواعد الأسماء الحسنى)
ሸርሕ ሐሺየት ኢብን አቢ ዳውድ (شرح حاشية ابن أبي داود)
የዋሲጢያህ፣ የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ፣ የመሳኢል አል-ጃሂሊያህ እና የሌሎች ሰለፎች የዐቂዳ ኪታቦች ማብራሪያ።
የሪያዱ አስ-ሷሊሒን፣ የተጅሪድ አስ-ሶሪሕ፣ የሙኽተሰር ሶሒሕ ሙስሊም እና የአርበዒን አል-ነወዊያህ ማብራሪያ።
በስነ-ምግባርና በባህሪ ዙሪያ ጠቃሚ ትምህርቶች አሏቸው፤ ከእነዚህም፦ የአድ– ዳእ ወድ-ደዋእ ፣ የአኽላቅ ሐመለቲል ቁርዓን እና የዋቢል አስ-ሰዪብ ማብራሪያዎች።
ታዋቂ መጽሐፎቻቸው ፦
ፊቅህ አል-አድዒያህ ወል-አዝካር (فقه الأدعية والأذكار)
አል-ሐጅ ወተህዚብ አን-ኑፉስ (الحج وتهذيب النفوس)
ተዝኪረቱል ሙእተሲ ሸርሕ ዐቂዳህ ዐብደልገኒ አል-መቅዲሲ (تذكرة المؤتسي)
ዲራሰቱ አሠር አል-ኢማም ማሊክ ፊ ባብ አል-ኢስቲዋእ (دراسة أثر الإمام مالك)
ተዕዚም አስ-ሶላት (تعظيم الصلاة)
በሐዲስ፣ በፊቅህ፣ በዐቂዳና በስነ-ምግባር ዙሪያ የተሰሩ ምርምሮችና ጥናቶች።
ፊቅህ አል-አስማእ አል-ሑስና (فقه الأسماء الحسنى)
እነዚህና ሌሎች ጠቃሚ መጽሐፎች ያሏቸው ሲሆን፣ በቅርቡ መጽሐፎቻቸውና መልዕክቶቻቸው በሙሉ በአንድ ጠቃሚ ጥራዝ ተሰብስበው ታትመዋል።
ማጠቃለያ፦ እሳቸው አላህ እውቀትንና ተግባርን፣ ማስረጃንና ርህራሄን፣ ሱናንና መልካም ስነ-ምግባርን በአንድ ላይ የሰበሰበላቸው ሸይኽ ናቸው። በመሆኑም ለአስተማሪ ዳዒና መካሪ ዓሊም ምርጥ ምሳሌ ናቸው። የእውቀት ፈላጊዎች ወደ መጽሐፎቻቸው እንዲዞሩ፣ ትምህርቶቻቸውን እንዲያዳምጡ እና ዐቂዳን በማረጋገጥ፣ ነፍስን በማጥራትና በመልካም አስተዳደግ ረገድ ካላቸው ጠንካራ አካሄድ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
አላህ ሸይኹን ይጠብቃቸው፣ በእድሜያቸውና በእውቀታቸው ላይ በረከትን ያድርግላቸው፣ እስልምናንና ሙስሊሞችንም በእሳቸው ይጠቅም ዘንድ እንለምነዋለን።

"ዐብዱረዛቅ አል-በድር አባቱ ሸይኼ ነው፣ እሱ ደግሞ ተማሪዬ ነው፤ ዛሬ ግን እሱ ከእኔ ይበልጣል" ብለዋል።የሕይወት ታሪካቸውንና ትምህርቶቻቸውን ያስተዋለ ሰው አላህ የሰጣቸውን የብስለት አእምሮ፣ ጥበብና ቀጥተኛ አካሄድ በግልጽ ይመለከታል። እውቀትን ከተግባር፣ ዐቂዳን ደግሞ ነፍስን ከማጥራት(ተዝኪየቱ አን ነፍስ) ጋር ለማገናኘት ያላቸው ልዩ ትኩረት ይታያል፤ በዚህም የተነሳ የትምህርት መጃሊሶቻቸው በትህትና እና በሰኪና (በመረጋጋት) የተሞሉ ናቸው። በዒልማቸው በሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በርካታ ሕዝብ ተጠቃሚ ሆኗል።
ታዋቂ ማብራሪያዎቻቸውና ትምህርቶቻቸው (ሸርሆች)
ሸርሕ አል-ቀዋዒድ አል-ሙሥላ (شرح القواعد المثلى)
ሸርሕ አል-ከሊም አጥ-ጦይብ (شرح الكلم الطيب)
ሸርሕ ቀዋዒድ አል-አስማእ አል-ሑስና (شرح قواعد الأسماء الحسنى)
ሸርሕ ሐሺየት ኢብን አቢ ዳውድ (شرح حاشية ابن أبي داود)
የዋሲጢያህ፣ የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ፣ የመሳኢል አል-ጃሂሊያህ እና የሌሎች ሰለፎች የዐቂዳ ኪታቦች ማብራሪያ።
የሪያዱ አስ-ሷሊሒን፣ የተጅሪድ አስ-ሶሪሕ፣ የሙኽተሰር ሶሒሕ ሙስሊም እና የአርበዒን አል-ነወዊያህ ማብራሪያ።
በስነ-ምግባርና በባህሪ ዙሪያ ጠቃሚ ትምህርቶች አሏቸው፤ ከእነዚህም፦ የአድ– ዳእ ወድ-ደዋእ ፣ የአኽላቅ ሐመለቲል ቁርዓን እና የዋቢል አስ-ሰዪብ ማብራሪያዎች።
ታዋቂ መጽሐፎቻቸው ፦
ፊቅህ አል-አድዒያህ ወል-አዝካር (فقه الأدعية والأذكار)
አል-ሐጅ ወተህዚብ አን-ኑፉስ (الحج وتهذيب النفوس)
ተዝኪረቱል ሙእተሲ ሸርሕ ዐቂዳህ ዐብደልገኒ አል-መቅዲሲ (تذكرة المؤتسي)
ዲራሰቱ አሠር አል-ኢማም ማሊክ ፊ ባብ አል-ኢስቲዋእ (دراسة أثر الإمام مالك)
ተዕዚም አስ-ሶላት (تعظيم الصلاة)
በሐዲስ፣ በፊቅህ፣ በዐቂዳና በስነ-ምግባር ዙሪያ የተሰሩ ምርምሮችና ጥናቶች።
ፊቅህ አል-አስማእ አል-ሑስና (فقه الأسماء الحسنى)
እነዚህና ሌሎች ጠቃሚ መጽሐፎች ያሏቸው ሲሆን፣ በቅርቡ መጽሐፎቻቸውና መልዕክቶቻቸው በሙሉ በአንድ ጠቃሚ ጥራዝ ተሰብስበው ታትመዋል።
ማጠቃለያ፦ እሳቸው አላህ እውቀትንና ተግባርን፣ ማስረጃንና ርህራሄን፣ ሱናንና መልካም ስነ-ምግባርን በአንድ ላይ የሰበሰበላቸው ሸይኽ ናቸው። በመሆኑም ለአስተማሪ ዳዒና መካሪ ዓሊም ምርጥ ምሳሌ ናቸው። የእውቀት ፈላጊዎች ወደ መጽሐፎቻቸው እንዲዞሩ፣ ትምህርቶቻቸውን እንዲያዳምጡ እና ዐቂዳን በማረጋገጥ፣ ነፍስን በማጥራትና በመልካም አስተዳደግ ረገድ ካላቸው ጠንካራ አካሄድ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
አላህ ሸይኹን ይጠብቃቸው፣ በእድሜያቸውና በእውቀታቸው ላይ በረከትን ያድርግላቸው፣ እስልምናንና ሙስሊሞችንም በእሳቸው ይጠቅም ዘንድ እንለምነዋለን።
❤30👍11🥰2
﴿إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا﴾
«በእርግጥ ከችግር ጋር ምቾት አለ።»
ቀናቶች ምንም ያህል ቢጠነክሩብህ ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ፤ ምክንያቱም ፈረጃው ባሪያው ባላሰበው መንገድ ይመጣል። አላህ በእርሱ ላይ መልካም የጠረጠረውን ሰው መቼም ቢሆን አያሳፍረውም።
አላህ ልባችሁን ደስታን እንዲሞላው፣ ነገሮቻችሁን እንዲያገራልችሁ እና ቁርአንን የልባችሁ ብርሃን እንዲያደርግላችሁ እለምነዋለሁ።

👍35❤12
ሪዝቅህ እንደ ዝናብ ነው! አላህ በሚወስነው ጊዜና ቦታ ይወርዳል። በሩ በፊትህ ቢዘጋብህ አትዘን፣ አንድ ሰው ቢርቅህም አትስጋ፤ ያንን በር በራህራሄው የዘጋው አላህ፣ ከሕልምህ በላይ እጅግ ሰፊና ውብ የሆኑ በሮችን ይከፍትልሃልና።
👍54❤29
ዑምራ፡ የመንፈስ ጉዞ ወይስ የዱንያ መዝናኛ?
ዑምራ—የእስልምናን ቅዱሳት ስፍራዎች የመጎብኘት፣ ወንጀልን የማሰሪያ፣ ቀልብን ከዓለማዊ እና ቁሳዊ ሸክም አጥቦ ወደ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የመመለሻ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሚስተዋሉ አንዳንድ ልማዶችና የቱር አዘጋጆች ዘይቤ፣ የዚህን ታላቅ ዒባዳ ዋና ዓላማ እያሳቱት ይሆን? የሚል እውነተኛ ስጋት እያስነሳ ይገኛል።
1. የዓለማዊ ነገሮች መጎላትና የመንፈሳዊነቱ መቀጨጭ
በዑምራ ጉዞዎች ላይ አሁን አሁን ዋና ትኩረቱ ከዒባዳ ወደ መዝናናት ሲያደላ ይስተዋላል። ፈረስ ግልቢያ፣ የቀስት ውርወራ፣ የባህር ላይ የጀልባ ሽርሽር እና መሰል መዝናኛዎች የጉዞው ዋና ማእከል እየሆኑ መጥተዋል።
ከሁሉም በላይ ግን አሳዛኙ ነገር፡ በአል-ሐረመይን (በመካው መስጂደል ሐራም እና በነቢያችን መስጂድ) አንድ ሰላት መስገድ እስከ 100,000 ሰላት እጥፍ በነቢዩ መስጂድ ደግሞ አንድ ሺህ የሚደርስ ታላቅ ምንዳ (አጅር) እንዳለው እየታወቀ፣ ያንን ሁሉ እድል አግኝቶ በጨዋታና በመዝናናት ጊዜን በማሳለፍ በጀማዓ መስገድን ማስመለጥ ትልቅ ሂርማን (የአጅር ኪሳራ) ነው።
መዝናናት በራሱ የተከለከለ ባይሆንም፣ ቅዱስ ስፍራ ላይ ቆሞ ጊዜን በእንዲህ አይነት ነገሮች ማሳለፍ ግን የዑምራን ዋና መንፈሳዊ ጥቅም እና የልብ መረጋጋት እያመናመነው ይገኛል።
2. የሱህባ እና የሳሊሆች ሚና መዛባት
አንድ ሰው ለዑምራ ሲነሳ ከጎኑ የሚፈልገው አላህን የሚያስታውሱት፣ አምልኮቱን የሚያስተካክሉለት እና ወደ አኼራ የሚጠቁሙትን "ሩፍቀት አስ-ሳሊሃ" (መልካም ጓደኞችን) ነው። አሳዛኙ ነገር ግን፣ የቱር ኤጀንሲዎች ማስታወቂያዎቻቸው ላይ ሸሪዓዊ እውቀት ያላቸውን ረባኒይ መሻይኾች እና ዓሊሞችን መሪ ከማድረግ ይልቅ፣ የቲክቶክ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን (Activists) እንደ ዋና ሳቢ ማስታወቂያ ማቅረባቸው ነው።
መንፈሳዊ መሪዎችን በቲክቶክ አክቲቪስቶች መተካት የጉዞውን ሚዛን ያሳስታል። የዑምራ ጉዞ በቪዲዮ እይታና በፎቶ ብዛት ሳይሆን በዕንባ፣ በዱዓ እና በኢኽላስ የሚለካ ተግባር ነው።
የዑምራ አዘጋጆችም ሆኑ ተጓዦች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባል። ዑምራ የልብ ህክምና እንጂ የካሜራ ትርኢት ወይም የቱሪዝም ሽርሽር አይደለም። የዑምራ ጉዞ እውነተኛ ዓላማውን ሳይስት፣ የአላህን ፍራቻ እና የመንፈስ እድሳትን ማዕከል ያደረገ ይሆን ዘንድ አቀራረባችንን እና አስተሳሰባችንን ልንፈትሽ ይገባል።

❤25👍13👌6
ኢላሂ! ወደ መካ የሚያደርሰንን መንገድ የማይቋረጥ አድርግልን፤ ዱንያ ምንም ያህል ብትጠብብን በእሷ ውስጥ ሰፊ እፎይታ የሚያገኝ ልብንም ስጠን። ❤️
ኢላሂ! ደጋግሜ እንድጎበኛት የሚረዳኝን ሲሳይ (ሪዝቅ) ለግሰኝ...
አሚን አሚን አሚን #ያ_ረብ 🤍🤲🕊🕋❤️"

👍57❤37
አላህ ሆይ! በልብ ውስጥ ትርታ እስከ አለ፣ ነፍስም መናፈቋን እስከቀጠለች ድረስ መዲናን እንድንጎበኛት አድርገን፤ በነቢይህ ﷺ መስጂድ ውስጥ ሶላትን ስጠን፤ በውስጧም የማይጠፋ እፎይታንና በህይወትም ሆነ በሞት አጠገቧ መሆንን ለግሰን። 🤍🌿..
#የነቢዩ_መስጂድ (#المسجد_النبوي)
#የነቢዩ_መስጂድ (#المسجد_النبوي)
❤32👍17💔2
የዓለማቱ ጌታ (ረበል ዓለሚን) አልረሳህም፤ በደከምክበትና በሰብር ባሳለፍከው በእያንዳንዱ ቅጽበት ምትክ ይክስሃል። ተረጋጋ፣ እረፍት ይሰማህ፣ በዓለማቱም ጌታ ተማመን! ምክንያቱም የእሱ ካሣ እንደ ሰብርህ መጠን ነውና። የጠፋ ድካምም ሆነ መና ሆኖ የሚቀር ትዕግሥት የለም፤ ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ነው፤ ደስ ይልሃል፣ ልብህንም ደስ ያሰኘዋል። ፈጽሞ ተስፋ እንዳትቆርጥ፤ ምክንያቱም ቀኑ ቀርቧል...
ቀርቧል! የአላህም ካሣ ይመጣል።
ቀርቧል! የአላህም ካሣ ይመጣል።
❤38👍22
ይህንን ፔጅ ለሚከታተል እያንዳንዱ ሰው ልብ የተላከ መልእክት🤍..
ለእኛ የተጻፈልን ነገር የእኛ እንደሚሆን ጥልቅ እምነትና የቂን ሊኖረን ይገባል.. ስለዚህም ምስጋና ለአላህ ይሁንና.. አንድ ቀን እንረዘቃለን፣ እንደሰታለን፣ መከራን ሁሉ እናልፈዋለን፣ እንዲሁም በሚያምር ነገር ሁሉ እንካሳለን..
(«እኔ ባሪያዬ እኔ ባሰበኝ(በጠረጠረኛ)ዘንድ ነኝ») ብሏልና።
አላህ እንደሚሰማህና የልብህን ሰወር ቦታዎች እንደሚያውቅ ስታስታውስ የሚሰማህ ስሜት እጅግ ያረጋጋል.. ለማንም ያልተናገርካቸው ቃላትህ፣ ያላሳየኸው ሀዘንህ፣ እናም እርሱ በተባረከ እዝነቱ ከመጠየቅህ በፊት እንኳ የሚያቃልልልህ መሆኑ..
በአላህ መተማመን ምን ያህል ያምራል! አላህ እኛን ከነፈገን የሚበልጥ መልካም ስጦታዎች አሉት፤ ከመሆኑም ጋር ብዙ ለመስጠት ሲል ጥቂት ነገርን ይወስዳል..
መልካም ትዕግስት ይኑርህ፤ ሕይወት ያለ ትዕግስት ልናልፋቸው የማንችላቸው ፈተናዎች አሏትና..

👍25❤12👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወርቃማ ምክር ከሸይኽ ሙሐመድ ረምዛን ሃጅሪይ ሀፊዘሁላህ
«ከአላህ ጋር ያለህን ምስጢር አድስ»
«ሰዎች ቢያወድሱህም፣ ቢያስታውሱህም፣ ላደረግከው መልካም ነገር ቢያመሰግኑህም... አንተ ከማንም በላይ የራስህን ሰወር ጥፋቶች ታውቃለህ።
የራስህን ምስጢር ታውቃለህ፣ ሌሊትህን ታውቃለህ፣ ቀንህን ታውቃለህ... ስልክህንና በእርሱ ውስጥ ያሉትን መልእክቶች፣ ያየሃቸውንና የሰማሃቸውን ነገሮች ሁሉ ታውቃለህ።
የሰዎችን ሙገሳና አድናቆት ተወው፤ አንተ ከአላህ ጋር ያለህን ምስጢር ከማንም በላይ አዋቂ ነህ።
ራስህን አስተካክል... ራስህን አክም! በውስጥህ ግድፈትና ጉድለት ካየህ፣ ያንነ አውቀህ አስተካክለው። የሰዎች ወሬና የአሞጋሾች ማወደስ አይሸንግልህ፤ አንተ ራስህን ከማንም በላይ ታውቃለህና ራስህን አርም!
ጥፋትህን ➔ አስተካክለው!
የልሳን ስህተት ➔ በዚክር (አላህን በማስታወስ) ለውጠው!
ሐሜት ➔ በመልካም ወሬ ለውጠው!
እግርህ ወደ ወንጀል አመራች? ➔ ወደ መስጂድ አቅናት!
ምላስህ ተንሸራተተች? ➔ ቁርዓን ወደ ማንበብ ቀይረው!
ዓይንህ? ➔ የአላህን መጽሐፍ ክፈት!
ጆሮህ? ➔ ቁርኣንን፣ ዚክርንና መልካም ነገርን ስማ!
ዝምድና መቁረጥ? ➔ ሂድና ያቋረጥከውን ሰው ቀጥል... አባትህ፣ እናትህ፣ አክስትህ፣ አጎትህ... እከሌ ቢሆን እንኳን ሂድና ይቅርታ ጠይቅ!
ወለድ? ➔ ተወው!
ወንጀል? የሙዚቃ/እያዩ የመስማት ነገሮች? ➔ ተጠንቀቅ፣ አስተካክለው!
«በእርግጥ መልካም ሥራዎች መጥፎ ሥራዎችን ያስወግዳሉ!»»

👍15❤11👌11💔6
የመልካም ጓደኝነት ውብ ከሆኑ ነገሮች አንዱ፡ በዚህች ዱንያ መጠናቀቅ የማይበቃ መሆኑ ነው፤ ይልቁንም እስከ ቂያማ የሚዘልቅ ሲሆን፣ ከአላህ ጥላ ውጭ ምንም ጥላ በሌለበት ቀን በአላህ ጥላ ስር አብረው ይጠለላሉ።
ورجلان تحابا في الله اجتمعا عليه وتفرقا عليه.

👍17❤8
እውነተኛ ጓደኝነት ለአላህ ብሎ ሲሆን… ✨
በዚህች ምድር ላይ ለአንድ አማኝ ከተሰጡት ትላልቅ ጸጋዎች አንዱ "መልካም ጓደኛ" ነው። ይህ ጓደኛ በገንዘብ፣ በዝና ወይም በጊዜያዊ ጥቅም ሳይሆን፣ ንጹህ በሆነው የአላህ ፍቅር ብቻ የተሳሰራችሁት ነው።
አብዛኛው የሰው ልጅ ግንኙነት በግላዊ ጥቅም ላይ በተመሰረተበት በዚህ ጊዜ፣ ለአላህ ተብሎ የሚመሰረት ውዴታ እጅግ ውድ ነው። ነቢዩ ሰለሏሁ አይሂ ወሰለም አላህ ዘንድ በልዩ ሁኔታ ስለሚጠለሉት ሰዎች ሲናገሩ፦ "ስለ አላህ ብለው የተዋደዱ፣ በእርሱ ላይ የተሰበሰቡና በእርሱ ላይ የተለያዩ..." ብለዋል።
ይህ ማለት ለአላህ ተብሎ የተገነባ የወንድማማችነት ፍቅር በሞት አያበቃም፤ ጠቀሜታውም ሆነ አማላጅነቱ ጀነት ድረስ የሚዘልቅ ዘላለማዊ ትስስር ነው!
🤲 ኢላሂ! ወደ አንተ የሚመሩንን፣ ስንዘናጋ የሚያስታውሱንን እና ትዕዛዝህን በመፈጸም ላይ የሚያግዙንን መልካም ጓደኞች ወፍቀን። ውዴታችንን ላንተ ብሎ ብቻ አድርግልን፤ በቂያማ ቀንም ምንም ጥላ በሌለበት ጊዜ በአርሽህ ጥላ ስር ከሚሰበሰቡት ባሮችህ አድርገን። አሚን! 🤍

👍24❤13
በሁሉም ነገር ውስጥ የአላህን ቸርነት እና ደግነት መፈለግን ለራሳችሁ ልማድ አድርጉ፤ ግራ በሚያጋቡ አጋጣሚዎች እና በጭንቀት/በመከራ ወቅትም እንኳ ቢሆን። ሁልጊዜም፦ «ምናልባት መልካም ይሆናል፤ ምናልባት አላህ የማላውቀውን ክፉ ነገር ከእኔ አርቆልኝ ይሆናል፤ ምናልባት ከዚህ በኋላ መላቀቅ፣ እረፍት እና ማቃለል ይመጣል» ማለትን ልማድ አድርጉ። ሁልጊዜም በአላህ ውሳኔ የመርካት (ቀደርን የመቀበል) መንፈስ ይኑራችሁ... ከዚያም በኋላ አላህ እንዴት እንደሚያስደስታችሁ እና እንዴት እንደሚበቃችሁ ታያላችሁ።
❤37👍12👌3
በሰላቱ ላይ የዘወተረ ሰው፣ በሁለት ሰላቶች መካከል ይሞታል፡ በሰገዳት እና በሚጠብቃት ሰላት መካከል፤ 🥹🌻🌸 አላህ ሆይ! ያማረ መጨረሻንና ከፍተኛዋን ጀነት (ፊርደውስን) እንለምንሃለን።
👍26❤15
Audio
🔴 የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
سلسلة أحداث يوم القيامة (الشفاعة)
✨ የቂያማ ቀን ክስተቶች (3)
ሸፈዓ (ምልጃ)
⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ሶፈር 25/1448 አ/ሂ
http://t.me/kalityhamzamesjid
🎙 خطبة الجمعة
سلسلة أحداث يوم القيامة (الشفاعة)
✨ የቂያማ ቀን ክስተቶች (3)
ሸፈዓ (ምልጃ)
⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ሶፈር 25/1448 አ/ሂ
http://t.me/kalityhamzamesjid
❤11
«ደካማ የሆነ ምላሽ(ረድ) ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ የሚያደርሰው ጉዳት ያመዝናል!
ጠንካራ ያልሆነ ምላሽ ሊመልሱ ወይም ማስረጃ የማይሆንን ነገር እንደ ማስረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ፤ ከዚያም በህዝቡ መካከል ሲበተኑት፣ በዚህ ጥርጣሬ (ሹብሃ) የተበከለው ሰው ምላሽህ ደካማ መሆኑን ሲያውቅ ያኔ ጥርጣሬው በልቡ ውስጥ የበለጠ ይስፋፋል።
አንተ የአህሉሱና ተወካይ ነህ፤ በዚህ ጃህል እይታ ውስጥ የአንተ ድክመት ማለት የሱና መንገድ (መዝሀብ) ድክመት ተደርጎ ይወሰዳል—ይህ ደግሞ ትልቅ ችግር ነው።
አንዳንዶች ምላሽ ለመስጠት በቅድመ-ግንባር ይሰለፋሉ፤ ነገር ግን ምላሾቻቸው ደካማና ተሰባሪ ናቸው፤ አስፈላጊው ዕውቀት፣ ጥንካሬና ጥልቀት የላቸውም።
በራስህ ውስጥ የዚህ መስክ ባለቤት አለመሆንህን ካወቅህ፣ አላህ ከአቅምህ በላይ አልጫነብህምና ጉዳዩን ለሌሎች ተወው። በህዝቡ መካከል 'ይህ የአህሉሱና መንገድ ነው' ብለህ እያሰራጨህ ምላሽህ ግን ያን ያህል ጠንካራ ካልሆነ፣በጣም አደገኛ ጉዳይ ነው።
ይህም ወደ ሌላ ነባራዊ ሁኔታ ትኩረት እንድስብ ያደርገኛል፤ እርሱም፦ ዛሬ ያሉ ወጣቶች በልቦቻቸው ውስጥ ጥርጣሬዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ጥርጣሬዎቹ ከቀደር ጋር የተያያዙ፣ ከአንዳንድ ሕግጋት ጋር የተያያዙ፣ ወይም ደግሞ ከፈጣሪ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ማንነት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ።
እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያና የኢንተርኔት መረቦች በዚህ ግልጽ በሆነ የጥመቶች ስብስብ የተሞሉ ናቸው፤ ስለዚህ ከእነዚህ ጥርጣሬዎች መካከል የሆነ ነገር በዚያ ወጣት ልብ ውስጥ ሊያድር ይችላል።
እናም አንተ በትምህርት ቤት ውስጥ ያለህ አስተማሪ፣ በ መስጂድ ውስጥ ያለህ ኢማም፣ ወይም ደግሞ እርሱ እንደ ሸይኽና እንደ ዓሊም (ዕውቀት ያለው ሰው) አድርጎ የሚያይህ ሰው ወደ አንተ መጥቶ ጥያቄውን ሲያቀርብልህ፤ እንዴት ምላሽ መስጠት አለብህ?
በአላህ መልካም ፈቃድ ጥርጣሬውን ከልቡ የሚያስወግድ፣ አጥጋቢና ትክክለኛ የሆነ ምላሽ ካልሰጠኸው፣ ማድረግ የሚገባህን አልሰራህም።
በዚያ ደካማ ምላሽ ምክንያት እርሱ ዝም ሊል ወይም በፊቱ አንገቱን ሊነቀንቅ ይችላል፤ ነገር ግን በእውነቱ በልቡ ውስጥ 'ጉዳዩ በእርግጥም አጠራጣሪ ነው፣ እረ እናንተ ሸይኾች ዘንድ ምንም ምላሽ የላችሁም' ብሎ ያምናል።
ይህንንም ከአንዳንዶቹ ሰምቼዋለሁ፤ ከእነዚህ ወጣቶች አንዱ ስላጋጠመው ጥርጣሬ ሲጠይቅ የተሰጠው ምላሽ፦ 'ይህን ንግግር ተወው!' የሚል ነበር።
'ይህን ንግግር ተወው' የሚለው ምላሽ በልቡ ውስጥ ያለውን ጥርጣሬ ያስወግደዋልን? አያስወግደውም! በተለይም የዛሬ ወጣቶች አሳማኝ ማስረጃ ያስፈልጋቸዋል፤ ልስላሴ ልታሳያቸው፣ በሚረዱትና በሚገባቸው ቋንቋ ልታበራራላቸው ይገባል።
ስለዚህ አንተ በቁጣ፣ ወይም 'ዝም በል' በማለት፣ ወይም ደግሞ በደካማ ምላሽ ካሰናበትከው፣ ጥርጣሬውን በልቡ ውስጥ የበለጠ ታጠናክራለህ።
ስለሆነም፦ ወይም አጥጋቢ ምላሽ ስጠው፣ ወይም ደግሞ መልካም ምላሽ መስጠት ወደሚችልና ወደሚያውቅ ሰው እጁን ይዘህ ውሰደው።"
ፕሮፌሰር ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሲንዲ

❤12👍8