የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.58K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
በአቅራቢያዋ ሰላምና ስክነት አለ…🕊️
በአላህ መልእክተኛ ﷺ መስጂድ ቅጽር ግቢ ውስጥ ደግሞ ከምንም ነገር ጋር የማይመሳሰል የልብ እርጋታና እረፍት ይገኛል። 💚
❤37👍1
ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታቸውን እያየዙ ሊሆን ይችላል፤ ተስፋ አትቁረጥ!
በአንድ ጉዳይ ላይ ወደ አላህ አብዝተህና አጥብቀህ ዱዓ አድርገህ ... ከዚያ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ወደ ተቃራኒው ሲቀየር ብታይ፣ ዱአዬ አልተቀበለኝም ብለህ እንዳታስብ! አላህ መልካሙን ነገር አንተ ልትረዳው በማትችለው መንገድ እየመራው ይሆናል፤ በክስተቶችም የምስክርነትህንና የእምነትህን ጥንካሬ ይፈትናል። የእምነትህ ፅናት ሳይናወጥ የጸና ሆኖ ካገኘው ደግሞ ባልጠበቅኸው ስጦታ ያስገርምሃል.. አላህ በእርሱ በሚተማመኑት ባሮቹ ጥርጣሬና ግምት ልክ ነው!♥️
👍34❤27
اللهم ارزقنا عمرة و عودةً اليها لا تنقطع، ولقاءً يطمئن به القلب. 🕋✨
آمين آمين آمين
❤29👍5
اللهم مع شروق هذا اليوم، نسألك خيراً في كل أمر، ونوراً في كل درب، وراحة في البال، وتوفيقاً يرافق خطواتنا.
👍10❤4
አንድ ወጣት እንዲህ ይላል፦
"አንድ ቀን እኔና ጓደኛዬ የገንዘብ ቦርሳችንን (ዋሌታችንን) ተለዋወጥን። እኔ የእሱን ቦርሳ ስፈትሽ፣ እሱ ደግሞ የእኔን ቦርሳ ይፈትሽ ነበር። ቦርሳው ውስጥ የነበሩትን በርካታ የወረቀት ቁርጥራጮች እያነበብኩ ነበር። በአንዱ ወረቀት ላይ የተጻፈውን አነበብኩ ፊቴ በደስታና በግርምት ተሞላ።
'ይህ ምንድን ነው?' ብዬ ጠየቅኩት፤ – በስሜ የተቆረጠ የበጎ አድራጎት ድርጅት ደረሰኝ ነበር –
እሱም፡ 'የአንድ አባት የሌለው ልጅ (የየቲም) እርዳታ/ድጋፍ ነው' አለኝ።
እኔም፡ 'ግን ለምን በኔ ስም ሆነ!?' አልኩት።
እሱም፡ 'በአንተ ስም ነው የቲሙን የደገፍኩት' አለኝ።
እኔም፡ 'ከመቼ ጀምሮ ነው?' አልኩት።
እሱም፡ 'ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ' አለኝ።
እኔም፡ 'ለምን ይህንን አደረግክ!' ብዬ ጠየቅኩት።
እሱም፡ 'እሳት (ጀሃነም) እንዳይነካህ ስለፈራሁልህ ነው' ሲል መለሰልኝ።”
አላህ ሆይ! መልካም እና ደግ ጓደኛን ወፍቀን! 🥺
❤81👍26💔16
በሁኔታዎችህ (በስራህ) ምክንያት ከቁርኣን እንዳትራራቅ ተጠንቀቅ! በአላህ እምላለሁ! እነዚያን ሁኔታዎችህን እንድትወጣ ከቁርኣን ቲላዋ በረካ ውጭ ምንም የሚያግዝህ የለምና ..»
​ቃሪእ ሸዕባን ፋይዝ
❤24👍10
«ስለ ፂም መላጨት ከተነሳ፤ በአላህ ይሁንብኝ! በራሴ ላይ መጥፎ ድርጊትንና መጥፎ ንግግርን አላጣምርም። እኔ በተግባር የጣስኩት ቢሆንም እንኳ እውነትን አልሸሽግም። በአላህም ሆነ በሰዎች ላይ አልዋሽም። በዚህ ድርጊቴ ላይ ተሳስቼ የተገኘሁ መሆኔንም በራሴ ላይ አመምናለሁ።
ይህን ስህተት ለመተው ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን የነፍስ ፍላጎትና የልማድ ኃይል አሸነፈችኝ።
ፂሜን እስካሳድግ ድረስ አላህ በነፍሴ ላይ እንዲረዳኝ እጠይቀዋለሁ፤ እናንተም ይህንኑ አላህን እንዲለምንልኝ እጠይቃለሁ፤ የኢማን ወንድም ለወንድሙ በሩቅ የሚያደርገው ዱዓ በአላህ ፈቃድ ተቀባይነት አለው።»
✍ሸይኽ አሊ አጥ-ጠንጣዊ
👌19❤12👍4💘1
​"ዋናው ቁምነገር ሰው ማግባቱ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ትልቁ ቁልፉ ነጥብ፤ ማንኛዋን ያገባል?? የሚለው ነው።
​የዲን ባለቤት የሆነችዋን አግኝተህ ፤  ፈጥነህ አግባ፣ ይህን ካደረግህ (ዲነኛዋን ካገባህ) ታላቅ ሀብትን/ከንዝን አግኝተህ አሸንፈሃል፤ በረካም ተጎናጽፈሃል።
አሊያ  ግን እጆችህ አፈር ይፈሱ (የያዘከው ሀብት አይባረክ!)"

​ከታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቋቸው)
❤5👍3
በአንዳንድ ወጣቶች አእምሮ ውስጥ፣ አንዳንድ ጊዜ ከመጠን በላይ በሆነ እራስን የመተማመን ስሜት የታጀበ፣ ለስላሳ እና ሮማንቲክ የሆነ አስተሳሰብ ይሰረጻል፤ ይህም አንዳንዶቹ፡ «ዲኗን ያልጠበቀች ወይም የላቀ በጎ ምግባር የሌላትን ሴት አግብቼ በራሴ እጅ አርማታለሁ፤ ወይም እቀይራታለሁ ፣ ወደ ቅን መንገድም እመራታለሁ» ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል። ይህንንም የሚያስቡት በጥበባቸው፣ በጠንካራ ስብዕናቸው እና በሰዎች ላይ ባላቸው የማነፅ አቅም በመተማመን ነው።
​ይህ አስተሳሰብ፣ ውጫዊ ገጽታው በመልካም እሴት የተሸፈነ ቢመስልም፣ በውስጡ ግን ትልቅ ስህተትን እና ፍጹም ተገቢ ያልሆነ ዓይነ-ሥውር የሆነ በራስ የመተማመን ጥግ ነው።
نعوذ بالله من الحور بعد الكور!
👍14❤7
ዲንን ማቃለል እና በ«ዑለሞች መካከል ልዩነት/ኺላፍ አለ» በሚል ሽፋን ስሜትን መከተል
በዑለሞች መካከል ኺላፍ አለባቸው በሚል ምክንያት በርካታ ዲናዊ ጉዳዮችን ለማቃለል (ለማለስለስ) መሞከር፤ በልዩነቱም በመመካት ደካማ የአቋም ብያኔዎችን ለመከተል ሰበብ መፈለግ፤ እንዲሁም የተገለሉና አሻሚ አቅዋሎችን ማስተዋወቅ፣ ማሰራጨት እና በህዝቡ መካከል ማስፋፋት ሰዎች የተሳሳቱና አሻሚ አቋሞችን እንዲይዙ ማድረግ እጅግ አደገኛ መርዝ ነው።
ይህ ድርጊት ያለ ምንም ጥርጥር ዲንን ከማበላሸት የሚቆጠር ሲሆን፣ መጥፎ አላማ ላላቸውና በሽታ ያለባቸው ደካማ ነፍስ ለአስከፊ ተግባራቸው እንዲሁም ሸይጣኖቻቸው በዓለም ላይ እንዲያሰራጩ የሚጎተጉቷቸውን መጥፎ ሃሳቦች ለመተግበር በሩን ይከፍትላቸዋል።

ቃዲ አቡ በክር እብኑል አረቢ እንዲህ ብለዋል፡-
«የሚከሰቱትን ኺላፎች በሙሉ የምንከተልና የምንጠብቅ ቢሆን ኖሮ፣ ዲን በማንኛውም መሰረት ላይ ሊረጋገጥና ሊፀና ባልቻለ ነበር።»
❤8
ፊትን መሸፈን(ኒቃብ) ጉዳይን በተመለከተ፡ ዑለሞች ከሴት ልጅ ፊትና ሁለት መዳፎች ውጭ ያሉትን የሰውነት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ መሸፈን ግዴታ (ዋጅብ) መሆኑ ላይ በጋራ ተስማምተዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል)። ማለትም፡ ሁለት እግሮቿን፣ እጅን እስከ ክርን ቢሆን ማሳየት ይፈቀዳል የሚል አንድም የለም።
​ሁለተኛ፡ ዑለሞች ፊትንና ሁለት እጆችን መሸፈን ትልቅ ደረጃ ያለው፣ (በላጭ ነው) የታዘዘበት እና የተወደደ (ሙስተሃብ) ተግባር መሆኑ ላይ ተስማምተዋል። ፊትን ማሳየት ይፈቀዳል የሚሉት እንኳ መሸፈኑ የተወደደ ነው ይላሉ፤ ምክንያቱም እጅግ ዝቅተኛው ጥቅም እንኳ ከልዩነት (ኺላፍ) ለመውጣት ይረዳልና።
​ሦስተኛ፡ በውበቷ ምክንያት ፈተና ይፈጠራል ተብሎ የሚሰጋባት ቆንጆ ሴት ፊቷንና ሁለት እጆቿን መሸፈን ግዴታ (ዋጅብ) ይሆንባታል በሚለው ላይ ተስማምተዋል። እንዲሁም ማሳየት ይፈቀዳል የተባለው ፊት ምንም ዓይነት ሜካፕ (የፊት መኳኳያ) የሌለበት መሆን አለበት በሚለው ላይም ተስማምተዋል።
❤22👍17
በመጀለት አድ-ደዕዋ (ቁጥር 1591፣ በ9/1/1418 ሂ) ላይ «ፊ ዚላሊል ቁርኣን» በተሰኘው መጽሐፍ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢማም ኢብኑ ዑሠይሚን -ረሒመሁልላህ- ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፦
«ለሱረቱል ኢኽላስ የሰጡትን ተፍሲር አንብቤአለሁ፤ በእሷም ውስጥ ከአህሉሱና ወልጀማዐህ እምነት ያፈነገጠ ታላቅ (አደገኛ) ንግግር ተናግረዋል። ተፍሲራቸው የሚያመላክተው "ወሕደቱል ውጁድ" (ፍጡርና ፈጣሪ አንድ ናቸው) የሚለውን እምነት እንደሚቀበሉ ነው። እንዲሁም "ኢስቲዋእ" የሚለውን የኣላህ መገለጫ "በስልጣኑ ተቆጥጥረና በስልጣን የበላይነት" (ሀይመናህ ወሰይጠራህ) ብለው ፈስረውታል።»
👌15❤6👍5
Audio
وشهد شاهد من أهلها
ይህ እንግዲህ የዚህ ዘመን የኢኽዋን ዓሊምና ኢማም የሆኑት አል-ቀርዳዊ የሰይድ ቁጥብን የ‘ተ‘ክፊዐር አካሄድ (መንሃጅ) የሚያረጋግጡበት ምስክርነት ነው።
ዩሱፍ አል-ቀርዳዊ «አውላውያት አል-ሐረካህ አል-ኢስላሚያህ» በተሰኘወወ  መጽሐፋቸው፤(ገጽ 110) ላይ፦
"በዚህ ደረጃ ላይ የሸሂዱ የሰይድ ቁጥብ መጻሕፍት ብቅ አሉ፤ እነዚህም የመጨረሻውን የሐሳብ እድገት ደረጃውን የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ፡ ማህበረሰቡን በ‘ካ’ፊ’ር’ነት በመፈረጅ፣ ፊቅህን የማደስና የማሻሻል እንዲሁም ኢጅቲሃድን  (የማንቃት) ሐሳብን በመጠቀም ወደ ኢስላማዊ ስርዓት የሚደረገውን ጥሪ በማዘግየት፣ ከማህበረሰቡ የስሜት መገለልን (ዑዝላህ ሹዑሪያህ) ማድረግንና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥን ጥሪ የሚያደርጉ፣ ሁሉንም ሰዎችን የማጥቃት ጂሃድ ማወጅን እንዲነሳሱ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም የመቻቻልና የለዘብተኝነት ጥሪ አድራጊዎችን የሚያናንቁና በምዕራባውያን ሥልጣኔ ፊት በየዋህነትና በስነ-ልቦና ሽንፈት የሚከተሷቸው ናቸው።" የሚሉ ትችቶቹ የኋላ ኋላ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። ይህ አመለካከቱ «ፊ ዚላል አል-ቁርዓን» ሁለተኛው ዕትም ላይ እና «መዓሊም ፊጥ-ጠሪቅ» መጽሐፉ ላይ በጣም በግልጽ ጎልቶ ይታያል።»
❤18👍3
የዚህ ዘመን አብዛኞቹና ዋና ዋናዎቹ የኢማን መንሸራተት መንስኤዎች ወደ ሁለት ነገሮች ይመለሳሉ፦
የመብተኝነት (የይገባኛል) ስሜት የበላይነት፤ አላህ የሚሰጣቸውን ጸጋዎች እንደ መለኮታዊ ችሮታ አድርጎ ከመመልከት ይልቅ፣ በፈጸሙት ታዛዥነት ብቻ እንደተገቢነታቸውና እንደሚገባቸው አድርጎ መገመት።
የዱንያ በልብ ውስጥ ማዕከል መሆንና፤ የተቅዋና የታዛዥነት ዓላማ የዱንያን ጥቅም በመሻት ላይ ብቻ መወሰን። በዚህም ምክንያት የአኺራ ህልውና በልብ ውስጥ ይዳከማል፤ ዱንያ ግብ ይሆናል፤ ጊዜያዊውም ነገር ዘላቂ ተደርጎ ይወሰዳል።
በልብ ውስጥ ማንኛውም ጸጋ ከአላህ የሚገኝ ችሮታና ስጦታ መሆኑ፣ እንዲሁም ዋናው ግብ አኺራ እንደሆነ ቀልባችን ውስጥ ከሰረፀና ከጸና፤ መንገዱ ይቃናል፣ ከብዙዎቹም የኢማን መንሸራተት መንስኤዎች በአላህ ፈቃድ ይጠበቃል።
👍18❤11
በቤታችሁ ውስጥ ያለውን አላውቅም፤ ነገር ግን በውስጡ ያለውን ሁሉ የሚያውቀውን አላህን እንዲህ ስል እለምነዋለሁ🤍
በውስጡ ታማሚ ካለ እንዲፈውሰው፤ በውስጡ የተጨናቀ ካለ ጭንቀቱን እንዲገላግለው፤ በውስጡ ባለዕዳ ካለ ዕዳውን እንዲከፍልለት፤ በውስጡ የተፈተነ ካለ ጤና እና ሰላም እንዲሰጠው፤ በውስጡ በዓይን ናስ የተጎዳ ካለ የዓይኑን ጉዳት እንዲያጠፋለት፤ በውስጡ መካን ካለ መልካም ዘርን (ልጅን) እንዲለግሰው፤ የእኛንም ሆነ የእናንተን ሙታን በሙሉ እንዲምርልን እማፀነዋለሁ...
❤89👍24🥰5👌1💔1
አንዳንዶቹ  እጅግ ወሰን ያለፈ አድናቆት ለዘመናዊ ግለሰቦች ባላቸው ስሜታዊ ተፅዕኖ መሸነፍ የተነሳ፤ ከነቢዩ ﷺ ባልደረቦች (ሶሃቦች) ይልቅ ለኋለኞች የበለጠ እንዲያደሉ እና እንዲቆረቆሩ ያደርጋቸዋል።
👍31😱1
«ሱኒይ» (የሱና ተከታይ) ማለት ስሜታዊ ፍላጎቶች፣ ቢድዐዎችና የተለያዩ የጥመት አንጃዎች በተወሱ ጊዜ፤ ወደ አንዱም አያዘነብልም፣ ለማናቸውም ወገንተኝነትን (ተዐሱብን) አያሳይም፤ ይልቁንም በቁርኣንና በትክክለኛው የነቢዩ  ﷺ ሱና ላይ ብቻ ይጸናል።»
አቡበጀር ኢብኑ ዐያሽ
👍21❤2
قال الشيخ العلامة زيد المدخلي
رحمه الله

“وقهـــوةُ البُنِّ للأبــــدانِ مُنْعِشـــةٌ …
مذاقُهَـــا مُمتــعٌ كالبُرِ والعسلِ

رفيقــةُ العُمْرِ في الأسفـارِ مُؤنسةٌ …
كنفحةِ المِسْكِ إن فاحتْ بلَا جدلِ

وبُغْيةُ النَّفـسِ في الإصْبَاح مُبهجةٌ …
تَسُرُّ إلْفًا مَتَى جــاءَتْ على مَهَلِ

ِيـا حبَّذا الشِرْبَ إنْ صاغتهُ ماهِرةٌ …
لِتُكْرِمَ الضَّيْفَ مِـنْ آتٍ ومُرْتحِــل

في كُــلِّ بيتٍ لَهَــا ذِكْرٌ ومَنْقَبَــــةٌ …
تُضَاحِكُ الخِلَّ إينَاســاً بِـــلا خَطَـلِ

تقولُ مرحى وطول الوقتِ بَاسِمَةٌ …
تُعِيدُ مَرْحَى رَفيــعَ القَـــدْرِ والمُثُلِ

لا عيب فيهــا ومِنْ غَوْلٍ مُبَرَّأَةٌ …
فاشْربها صِرْفًا ولا تخشى من العِلَلِ”
___
■الشيخ العلامة زيد بن هادي المدخلي رحمه الله

■المنظومات الحسان(الديوان المليح) لزيد بن هادي المدخلي – ص 343 ط الأولى، دار الميراث النبوي.€___
የጤና ባለሙያዎች በአጠቃላይ በቀን እስከ 400 ሚሊግራም ካፌይን ወይም አራት ባለ 8 አውንስ ስኒ ቡና መጠጣት ምንም ጉዳት እንደሌለው ይናገራሉ።

ከዚህ በላይ መጠጣት ግን የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

✅ የቡና ጥቅሞች:

የአልዛይመር እና የፓርኪንሰን በሽታን ይከላከላል።

ለልብ እና ለጉበት ጤና ጠቃሚ ነው።

አንዳንድ የካንሰር አይነቶችን ተጋላጭነት ይቀንሳል።
👍18❤12
🔸ሸይኽ ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው፣ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!
"አህሉ ሱና ወልጀማኣ ሲባል (ሰለፍዬች፣አሽኣሪዬች እና ማቱሪዲዮች ናቸው።" የሚል ተሳስቷል።
ይህ ስሕተት ነው!!
ሁሉም አህሉ ሱናህ ሊባሉ ይችላልን?
ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም።
አንዱ ሌላኛው ላይ ምላሽ እየሰጠ እንዴት ሆኖ ሁሉም አሕሉ ሱና ሊሆኑ ይችላሉ?
ይህ ሊሆን ፈፅሞ አይቻልም፣ምናልባት ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ ከተቻለ እንጂ!!
ከነዚህ አንጃዎች አንዱ ብቻ ነው አህሉ ሱና ሊሆን የሚችለው።
እሱ ማነው?
አሽኣሪያ?
ወይስ ማቱሪዲያ?
ወይስ ሰለፊያ?
ሱናን የገጠመ እርሱ አሕሉ ሱና ነው፣ሱናን የተፃረረ እርሱ አሕሉል ቢድዓ ነው።
እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው ከሰለፊዮች ውጭ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!"

【"ሸርሑ ዐቂደቱ አልዋሲጢያ"(1/33_34)】

(የመክተበቱ ጠበሪያ ህትመት አንደኛ ዕትም)

https://telegram.me/sultan_54
👌9❤4
Audio
من هو سيد قطب
للشيخ إلياس أحمد
👍12❤4