የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.59K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
​🕌 እንግዶቹ ሄዱ... ቤተኞቹ ግን ቀሩ!
​ረመዳን ሲጠናቀቅ መስጂዶች ተቀዛቀዙ፣ የሰጋጅ ሰፎች ቀነሱ፣ ቁርኣኖችም ወደ መደርደሪያቸው ተመለሱ! ነገር ግን እዚያ ጋር
ህይወታቸውን ሙሉ ረመዳን ያደረጉ፣ ቁርኣናቸው አቧራ የማይበላው፣ ወደ መስጂድ እርምጃቸው የማይዝል ጥቂት ንጹህ ልቦች አሉ። ረመዳን ለእነርሱ ከጥንካሬ በላይ ጥንካሬን ሰጥቷቸዋል።

​"እንግዶቹ (የረመዳን ሰጋጆች) ሄዱ፤ ቤተኞቹ (ዘውታሪዎቹ) ግን ቀሩ!" የሚለው ትርጉም ይሄ ነው።
​🤲 አላህ ሆይ! ልቦችን የምትገለባብጥ ጌታ ሆይ! ልባችንን በዲንህና በታዛዥነትህ ላይ አጽና። አንተን እስክንገናኝ ድረስ እኛንም አጽናን፣ በእኛም ሌሎችን አጽና።
​✨ ከመስጂድ ቤተሰቦች ጋር የተያያዙ ነቢዩ ﷺ የተናገሯቸው ብስራቶች፦
​1️⃣ መስጂድ የጥንቁቁች ቤት ናት!
​"መስጂድ የእያንዳንዱ አላህን ፈሪ (ተቂይ) ቤት ናት። መስጂድን ቤቱ ላደረገ ሰው አላህ በመንፈስ ዕረፍት፣ በእዝነት፣ በሲራጥ ድልድይ ላይ አልፎ ወደ አላህ ውዴታና ወደ ጀነት ለመግባት ዋስትና ሰጥቶታል።"
(ሶሒሕ አት-ተርጊብ)

​2️⃣ የአላህ ጎረቤቶች እነማን ናቸው?
​"አላህ የቂያማ ቀን፦ 'ጎረቤቶቼ የት ናቸው? ጎረቤቶቼ የት ናቸው?' ብሎ ይጣራል። መላእክትም፦ 'ጌታችን ሆይ! አንተን ሊጎረብት የሚገባው ማነው?' ይላሉ። አላህም፦ 'የመስጂድ አዘውታሪዎች (አዘውታሪዎች) የት ናቸው?' ይላል።"
(አስ-ሲልሲላህ አስ-ሶሒሐህ)

​3️⃣ የመስጂድ ካስማዎች (አውታዶች)
​"ለ መስጂዶች 'አውታዶች ምሶሶች' (ቋሚ አዘውታሪዎች) አሏቸው፤ መላእክት የነርሱ የቅርብ ጓደኞች ናቸው። ቢጠፉ ይፈልጓቸዋል፣ ቢታመሙ ይጠይቋቸዋል፣ እርዳታ ቢፈልጉም ያግዟቸዋል።"
(ሶሒሕ አት-ተርጊብ)

​4️⃣ የአላህ አቀባበል
​"አንድ ሙስሊም ለሶላትና ለዚክር መስጂድን መኖሪያው (አዘውታሪ) ካደረገ፣ ልክ የጠፋባቸው ሰው ተመልሶ ሲመጣ ቤተሰቦቹ በደስታ እንደሚቀበሉት ሁሉ፣ እርሱም ከቤቱ ሲወጣ አላህ በደስታ ይቀበለዋል።"
(ሶሒሕ አል-ጃሚዕ)

​📲 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
[https://t.me/sultan_54]
👍8👌1💔1
🌙 የረመዳን ቀዳ ሳያጠናቅቁ የሸዋልን ስድስት ቀናት መጾም ይቻላል?
ጥያቄ፦ የረመዳን ቀዳ (ያመለጡ ቀናት) ሳይከፈሉ የሸዋልን ስድስት ቀናት መጾም ይቻላል?
ምላሽ፦
የሸዋልን ስድስት ቀናት መጾም ለሚፈልግ ሰው ሱናው (የተመረጠው) በመጀመሪያ የረመዳን ቀዳውን በመጾም መጀመር ነው። ይህ መሆኑ "ረመዳንን ጾመ" የሚለው ንግግር በእርሱ ላይ እውነት እንዲሆን ያደርገዋል። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦
> "
ረመዳንን የጾመ፣ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ፤ ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል።"
(ሙስሊም)
>
ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የሐዲሡ ትርጉም፦ አንድ ሰው "ረመዳንን ጾሞ…" የሚባለው ያመለጡትን ቀናት ቀዳ አውጥቶ ሲያጠናቅቅ ብቻ ነው። ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ እንዲቆጠርለትም ይኸው ቅድመ ሁኔታ የግድ ይላል።
* የስነ-ልቦና ጥንካሬ፦ የሸዋል ስድስት ቀናት እንዲጾሙ መበረታታቱ፤ ሰውየው የረመዳንን ጾም አጠናቆ ነፍሱ ለዒባዳ ተዘጋጅታ፣ ጾም ሳይከብደውና በአላህ ስጦታ ተደስቶ በራሱ ፍላጎት ተጨማሪ ጾም እንዲጾም ለማሳየት ነው።
* ስለዚህ የሸዋልን ስድስት ቀናት መጾም የሚፈልግ ሰው መጀመሪያ ያለበትን የግዴታ (ዋጅብ) የረመዳን ዕዳ መክፈል አለበት፤ ከዚያም የሸዋልን ስድስት ቀናት ይጾማል።
📲 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
[https://t.me/sultan_54]
✍️ አቡ ሑዘይፋ ሱልጣን ኸድር
❤3👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የረመዳን ቀዷን እና የሸዋል ስድስት ቀናትን ጾም በአንድ ላይ የመጾም ብያኔ!
​ ሸይኽ ዐዚዝ ቢን ፋርሀን አል-ዒነዚይ እንዲህ ይላሉ፦
" ግለሰቡ ያለበትን የቀዷ ጾም እና የሸዋል ስድስት ቀናትን ጾም በአንድ ኒያ አጣምሮ መጾም እንደማይፈቀድ ገልጸዋል።
​ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶችን ጠቅሰዋል፦
​ዋጂብ ከሱና ይቀድማል፦ የቀዷ ጾም ግዴታ (ዋጂብ) ሲሆን፣ የሸዋል ጾም ደግሞ የውዴታ (ሱና) ነው። ስለዚህ ግዴታው ለብቻው መፈጸም አለበት።
​የተለያዩ አምልኮዎች መሆናቸው፦ ሁለቱም ጾሞች የየራሳቸው የተለየ ዓላማና ኒያ ስላላቸው በአንድ ላይ ሊጣመሩ አይችሉም።"
❤17
ሸይኽ ዐብዱ አር–ራሕማን ኢብን ናሰር አስ-ሲዕዲይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"
ከታላላቅ ትርፎችና እንቁ ከሆኑ ጥቅሞች መካከል፦
የመልካም ሰዎችን ወዳጅነት(ጓደኝነት) ማግኘት፣
እንዲሁም በህይወት እያለን ከሞትንም በኋላም የነርሱን ዱዓቸውን መጠቃቀም ነው።"
📚 መጅሙዕ አል-ፈዋኢድ
❤7👍5
🌙 ከሱረቱ አን-ነህል የተወሰደ ምክር(መውዒዛ)፦

የቀጥተኛው መንገድ ግልጽ ነውና አትዘንበል! 🌙


አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
> 《
ቀጥተኛውን መንገድ(ኢስላም እና የርሱን ወዴታ ማግኛ መንገዶችን) ማሳየት በአላህ ላይ ነው፤ ከእርሷም (ከመንገዶቹ) ጠማማ(የሚስት) አለ።》

[አን-ነህል፡ 9]
>
የአላህ ባሮች ሆይ! ይህች አንቀጽ ለአንድ አማኝ የጥልቅ አስተንትኖ በርን የምትከፍት ታላቅ አንቀጽ ናት። አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ)   በከንቱ አልተወንም፤ መንገዱንም ድንግዝግዝ አላደረገውም። ይልቁንም ቀጥተኛውን መንገድ አብራራልን፣ የቅኑን ጎዳና አሳየን፣ መልዕክተኞችን ላከ፣ መጽሐፍትንም አወረደ፣ ማስረጃንም አቋቋመ።
ነገር ግን መንገዱ ግልጽ ከመሆኑ ጋር፦ 《ከእርሷም ጠማማ(የሚስት) አለ》 ይላል።
ይህም ማለት፡- ብዙ የተሳሳቱ፣ ያሸበረቁና አታላይ የሆኑ መንገዶች አሉ። ሆኖም ግን እነዚህ መንገዶች መጨረሻቸው ጥፋት እንጂ ሌላ አይደሉም።
⚠️ ችግሩ የሐቁ መንገድ አለመታወቅ አይደለም፤ ይልቁንም የልቦች መዘናጋትና መሸሽ እንጂ!
ስንትና ስንት ሰው ሐቁን እያወቀ የማይከተለው አለ! ስንትና ስንት ባሪያ ቀጥተኛውን መንገድ እያየ ወደ ስሜታዊ ፍላጎቶች የሚያዘነብል አለ!
📌
ከረመዳን በኋላ ያለንን ሁኔታ እናስተውል፦
ለቁርኣን፣ ለሰላትና ለታዛዥነት ቅርብ ነበርን። ታዲያ አሁን እንጸናለን ወይስ የገነባነውን እናፈርሳለን?

አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ሲያስጠነቅቅ እንዲህ ይላል፦
> 《
እንደዚያችም ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ፍትፍት አድርጋ እንደበጠሰችው ሴት አትሁኑ።》

[አን-ነህል፡ 92]
>
💔 በትጋት አምላክህን ከተገዛህ በኋላ፤ በወንጀል ሁሉንም ነገር የምታፈርስ አትሁን! መንገዱን አውቀህ ከእርሱ ዞር የምትል አትሁን!
🌿 ቀጥተኛው መንገድ ግልጽ ነው፦
* ከክፉ የምትጠብቅህ ሰላት፣
* ወደ ቀጥተኛው ጎዳና የሚመራህ ቁርኣን፣
* ልብህን የሚያረጋጋው ዚክር፣
* ወደ ጌታህ የሚያቀርብህ ታዛዥነት።

🔥 ጠማማዎቹ መንገዶችም ግልጽ ናቸው፦
* ልብን የሚያበላሹ ስሜታዊ ፍላጎቶች፣
* ከአላህ የሚያርቅ ዝንጉነት(ገፍላህ)፣
* ልብን የሚያደነድኑ ወንጀሎች።

👉 እንግዲህ ለራስህ ምረጥ፦ የጀነትን መንገድ ወይስ የእሳትን መንገድ?
🤲 አላህ ሆይ! አንተ ልቦችን የምትገለባብጥ ጌታ ሆይ፤ ልቦቻችንን በዲንህ ላይ አጽናልን። አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ሙጥኝ ማለትን ወፍቀን፤ ቅኑን መንገድ ካሳየኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘንብልብን።
✍️ የጌታውን እዝነት ከጃይ የሆነው ወንድማችሁ፦ አቡ ሁዘይፋ ሱልጣን ኸድር
❤6
የሸዋል ኺትማ!

🌙 የረመዳን አሻራ (ብርሃን) እንዲደበዝዝ አትፍቀድ! 🌙
ከረመዳን በኋላ የፅድቅ ምልክቶች ውስጥ ዋነኛው፦ በዕለት ተዕለት ውሎህ ውስጥ ለቁርኣን ቋሚ ቦታ እንዲኖረው ማድረግ ነው።
ሁልጊዜ ብዙ እንድታነብ አይጠበቅብህም፤ ነገር ግን የሚከፋውና የሚያሳዝነው በረመዳን በየቀኑ ሲቀሩ የነበሩት የቁርኣን ገጾች ተዘግተው ሲቀሩ (ሲተዉ) ማየት ነው።
አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
> 《ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ በጣም ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል።》 [አል-ኢስራእ፡ 9]
>
ነቢዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
> «አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ምንም እንኳን አነስተኛ ቢሆኑም ዘላቂነት ያላቸው (የማይቋረጡ) ናቸው።» (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
>
ስለዚህ ከቁርኣን ጋር የማይቋረጥ ቋሚ ግንኙነት (ዊርድ) ይኑርህ፤ መጠኑ አነስተኛ ቢሆን እንኳ... ዋናው ነገር ቋሚ መሆኑ ነው።
📅 የሸዋል ወር የቁርኣን (ኺትማ) ፕሮግራም
ቤተሰቦችህንና ጓደኞችህን አብረውህ እንዲበረቱ ጋብዛቸው!
ለሸዋል ወር የሚሆኑ 3 አማራጮች፦
* የጠንካሮች መንገድ (ሙሉ ኸትም)፦ በቀን 30 ደቂቃ ብቻ በመስጠት 1 ጁዝ (20 ገጽ) በማንበብ በወሩ መጨረሻ ሙሉ ቁርኣንን ማኽተም።
* የመካከለኛው መንገድ፦ በቀን 15 ደቂቃ ብቻ ከጊዜህ በመስጠት ግማሽ ጁዝ (10 ገጽ) በማንበብ በሁለት ወር አንዴ ማኸተም።
* የጽናት መንገድ (ዘላቂው)፦ በቀን ሩብ ጁዝ (5 ገጽ ወይም 2 ሉክ) በማንበብ ግንኙነትን አለማቋረጥ።
💡 ማሳሰቢያ፦ በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ ግሩፕ "ዛሬ የጀመርኩትን ቀርቻለሁ ✅" በመባባል እርስ በእርስ ተበረታቱ።
ይህ መልዕክት ለቤተሰብህና ለጓደኞችህ እንድታጋራው ሆኖ የተዘጋጀ ነው።
❤8👍4
ስለ ኒካሕ ማበረታቻ!
ኢብን አል-ቀዪም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
«ከጋብቻ [ኒካህ] ጥቅሞች መካከል፦ እይታን መስበር (ከሐራም መጠበቅ)፣ ነፍስን መቆጣጠር፣ ከእርም (ሐራም) የመታቀብ አቅምን ማግኘት እና ይህንኑ ጥበቃ ለሴቷም ማስገኘት ናቸው። ስለሆነም ጋብቻ ለሰውየው በዱንያውም ሆነ በአኺራው ይጠቅመዋል፤ ሴቷንም ይጠቅማል።»
* በዚህም ምክንያት ነቢዩ ﷺ ጋብቻን ይወዱ ነበር፤ ወደርሱም ቅስቀሳም ያደርጉ ነበር እንዲህም ይሉ ነበር፦
* ነቢዩ ﷺ ኡመታቸውን እንዲጋቡ ሲያበረታቱ፦ «ተጋቡ፤ እኔ በእናንተ በሌሎች ሕዝቦች (ኡመቶች) ፊት በብዛት እፎካከርባችኋለሁና (እኩራባችኋለሁና)።»ብለዋል
* ኢብን አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ብለዋል፦ «የዚህ ኡመት በላጩ (ሰው) ሚስቶቹ የበዙት ነው።»
* ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «እኔ ሴቶችን አገባለሁ፣ ሥጋ እበላለሁ፣ እተኛለሁ፣ (ለሶላት) እቆማለሁ፣ እጾማለሁ፣ አፈጥራለሁም፤ ከእኔ ፈለግ (ሱና) የራቀ ሰው ከእኔ አይደለም።»
* ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «እናንተ ወጣቶች ሆይ! ከእናንተ መካከል የጋብቻን ጣጣ (ወጪና አቅም) የቻለ ያግባ፤ እሱ እይታን ይበልጥ ሰባሪ፣ ብልትንም ይበልጥ(ከሐራም) ጠባቂ ነውና። ያልቻለ ግን ጾምን አጥብቆ ይያዝ፤ እሱ ለእርሱ መከላከያ (ስሜትን መስበሪያ) ነውና።»
* ጃቢር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ቀደም ሲል ባል አግብታ የፈታች(የሞተባት) (ሠዪብ) ሴት ባገባ ጊዜ ነቢዩ ﷺ እንዲህአሉት፦«የምታጫውታትና የምታጫውትህ ድንግል)አትሆንም ነበርን!»
*ዐብዱላህ ኢብን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ዱንያ መጣቀሚያ ናት፤ ከዱንያ መጣቀሚያዎች ሁሉ በላጩ ደግሞ መልካም (ሷሊህ) ሴት ናት።»
📚(ዛድ አል-ሚዓድ፡ 4 / 359 - 361)
👍12❤11🥰1
ደስታ ያለው የት ነው? – የጠፋውን ዕንቁ ፍለጋ!
​ብዙዎቻችን ደስታን የምንፈልገው በተሳሳተ ቦታ ነው። አንዳንዶች በሀብት፣ ሌሎች በዝና፣ አንዳንዶች ደግሞ በጊዜያዊ የስሜት እርካታ (ወንጀል) ውስጥ ያገኙት ይመስላቸዋል። ይሁን እንጂ፣ ይህ ደስታ ልክ እንደ ንጋት ጤዛ በቶሎ ይተናል፤ ከዚያም በምትኩ ብርቱ ጭንቀትና የጸጸት ስሜት ይተካል።
​አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) በቁርአኑ ውስጥ ለዚህ የሰው ልጅ ጥያቄ ቀጥተኛና የማይለወጥ መልስ ሰጥቷል፦
​«ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን ሥራ የሠራ ሰው በእርግጥ መልካም ኑሮን እናኖርዋለን።» (አን-ነሕል፡ 97)

​ይህ አንቀጽ (አያህ) እውነተኛውን የደስታ ቁልፍ ያሳየናል። እሱም እምነት (ኢማን) እና በጎ ሥራ (ዐመል ሷሊሕ) ነው።
​ሶላት ስንሰግድ የልባችንን ትክክለኛ ቦታ እናገኛለን።
​ዚክር ስናደርግ አዕምሯችን እረፍት ያገኛል።
​ለሰዎች መልካም ስናደርግ ደስታን እንሰጣለን፣ እኛም እርካታን እናገኛለን።
​ወንጀል ደግሞ እንደ መርዝ ነው። መጠኑ ትንሽ ቢመስልም መላ ሰውነታችንንና ነፍሳችንን ያቃውሳል። ሰላማችንን ያጠፋል።
​ስለዚህ፣

በወንጀል የምንፈልገው ጊዜያዊ “ደስታ” እውነተኛ ደስታ ሳይሆን፣ እውነተኛውን ደስታ የሚያስረሳን “ደብዛዛ ጥላ” ነው።
እውነተኛው ብርሃን ደግሞ ያለው ለአላህ በመታዘዝ ውስጥ ነው።
​ልባችን አሁኑኑ ይመለስ! ደስታ እጃችን ላይ ነው!
❤9👌3👍1
የዕለቱ መልክት!
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
​"ፍጥረታትን (ሰዎችን) በመኗኗር(መስተጋብር) ውስጥ እውነተኛውን ደስታ (ማግኘት ከፈለግክ)፦ ለአላህ ብለህ በመልካም መስተጋብር ልትኗኗራቸው ይገባል። በእነሱ ጉዳይ አላህን ተስፋ አድርግ፤ በአላህ ጉዳይ ግን እነሱን ተስፋ አታደርግ። በእነሱ ጉዳይ አላህን ፍራ፤ በአላህ ጉዳይ ግን እነሱን ልትፈራ አይገባም። ለእነሱ መልካም የምትውለው የአላህን ምንዳ ፈልገህ እንጂ እነሱ ብድሩን እንዲመልሱልህ ብለህ መሆን የለበትም። እነሱን ከመበደል የምትቆጠበውም አላህን በመፍራት እንጂ እነሱን በመፍራት ሊሆን አይገባም።"

​📚 [መጅሙዕ አል-ፈታዋ (1/51)]

​የመልዕክቱ ዋና ነጥቦች፦
​አላህን ብቻ ተስፋ ማድረግ፦ ለሰዎች መልካም ስትውል ምላሹን ከአላህ እንጂ ከሰዎች አትጠብቅ። ሰዎች ባይመሰግኑህ እንኳ አላህ ስለሚያውቅልህ ደስታህ አይቀንስም።
​አላህን ብቻ መፍራት፦ ሰዎችን የማትበድለው እነሱን ፈርተህ ሳይሆን አላህ ዘንድ መጠየቅን ፈርተህ ይሁን።
​ለአላህ ብሎ መኖር፦
ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ሁሉ አላህን ማዕከል ያደረገ ሲሆን፣ ሰዎች ቢቀየሩም ባይቀየሩም አንተ በአቋምህ ትጸናለህ፤ በዚህም ልብህ ዘላቂ ደስታን ያገኛል።
❤13
የ8000 ነውሮች(ጉድለቶች) መፍትሔ!
ኢማም አን-ነወዊ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
«በጥንት ዘመን የነበሩ ሁለት ጥበበኞች (ቀይስ ኢቢኑ ሳኢዳህ እና አክሠም ኢብኑ ሠይፍ) ተገናኝተው ሳለ፣ አንዱ ሌላኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "
በሰው ልጅ ላይ ስንት ጉድለቶችን (ነውሮችን) አገኘህ?"

ጥበበኛውም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ጉድለቶቹ ተቆጥረው አያልቁም፤
እኔ ግን 8000 (ስምንት ሺህ) ጉድለቶችን አግኝቻለሁ። ሆኖም ግን አንድ ባህሪ አለች፤ እሷን ከተጠቀምክ እነዚህን ስምንት ሺህ ጉድለቶች በሙሉ ትሸፍንልሃለች

።"
ያቺ ብቸኛ መፍትሔ ምንድናት? ተብሎ ሲጠየቅ፦ "ምላስን መቆጠብ (መጠበቅ)" በማለት መለሰ።»
* ዑመር ዐብዱል ዐዚዝ እንዲህ ይላሉ፦ «
ቀደምት ደጋግ ሰዎች (ሰለፎች) እውነተኛ (ዒባዳ) በጾምና በሰላት ብቻ እንደሆነ አያስቡም ነበር፤ ይልቁንም ትልቁ ዒባዳ የሰዎችን ክብር ከመንካት ምላስን መቆጠብ እንደሆነ ያምኑ ነበር።»

አንድ ሰው ቀኑን ቢጾም፣ ሌሊቱን ቆሞ ቢያድርም፤ ነገር ግን ምላሱን የማይጠብቅና ሰዎችን የሚሰድብ/የሚያማ ከሆነ፣ የቂያማ ዕለት የለፋበትን ምንዳ የሚያጣ "ከሳሪ" (ሙፍሊስ) ሆኖ ይመጣል።
👍23❤11
ነቢዩ ﷺ ለትዳር እንድንመርጣቸው ያበረታቱን የሴቶች ባህሪያት፦

ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ ﷺ ኡመታቸው ውብ፣ ድንግልና የዲን ባለቤት የሆኑ ሴቶችን እንዲያገቡ ያበረታቱ ነበር።"
1. ምርጥ የተባለችው ሴት፦
አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ ነቢዩ ﷺ "ከሴቶች ሁሉ በላጭ (ምርጥ) የተባለችዋ የትኛዋ ናት?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦
> "
ሲመለከታት ደስ የምታሰኘው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ በራሷም ሆነ በንብረቱ ላይ እሱ የማይፈልገውን ነገር የማታደርግ ናት።

" (ነሳኢ)
>
2. የዲን ባለቤትን መምረጥ፦
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
> "
አንዲት ሴት ለአራት ነገሮች ሲባል ትገባለች፦ ለሀብቷ፣ ለዘር ሐረጓ (ለክብሯ)፣ ለውበቷና ለዲኗ (ለሃይማኖቷ)። አንተ ግን የዲን (የሃይማኖት) ባለቤት የሆነችውን በመምረጥ ስኬትን ተቀዳጅ!"

(ቡኻሪና ሙስሊም)
>
3. አፍቃሪና ወላጅ ሴት፦
ነቢዩ ﷺ የሚወዱና የሚወልዱ ሴቶችን ማግባትን ያበረታቱ ነበር። በአቡ ዳውድ በተዘገበው ሐዲስ ላይ እንደተጠቀሰው፣ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ ﷺ መጥቶ "ቆንጆና የተከበረ ዘር ያላት ሴት አገኘሁ፤ ነገር ግን አትወልድም፣ ላግባት?" ብሎ ጠየቀ። ነቢዩም "አይሆንም" አሉት። ለሁለተኛና ለሦስተኛ ጊዜም ጠይቆ ከለከሉት። በመጨረሻም እንዲህ አሉት፦
> "
አፍቃሪና ወላድ (ብዙ የምትወልድ) የሆኑ ሴቶችን አግቡ፤ እኔ በቂያማ ቀን በእናንተ ብዛት ከሌሎች ህዝቦች ፊት እፎካከርባችኋለሁና (እኩራባችሁለውና!)"

>
❤15
​"ራስህን ከነዚህ አራት ጠንቆች ጠብቅ!" ⚠️
​🤐 አላስፈላጊ ንግግር፦ ቃላትህ ይመዘገባሉና ከመናገርህ በፊት አስብ።
​🍲 ከመጠን ያለፈ ምግብ፦ ለበሽታና ለስንፍና ይዳርጋል።
​😴 ትርፍ እንቅልፍ፦ ጊዜህንና በረከትህን ይበላዋል።
​👥 ከሰዎች ጋር በብዛት መቀላቀል፦ ልብህን ከፈጣሪህ ያርቃል።
​በረከቱ እንዲዛመት ለሌሎችም አጋራው! 🔄

​📲 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
[https://t.me/sultan_54]
👍7❤3
በዋትስኣፕ ለመከታተል፦👇
Follow the የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ(official) channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbC2qVH6hENvXGwN6U0c
❤3
አሁን መስመር ላይ ያለህ/ሽ... ✨

ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ በሚዛኑ ላይ የሚከብዱ፣ በአላህ (አር-ፈሕማን) ዘንድ የተወደዱ የሆኑ ሁለት ቃላት ከኔ ለመደጋገም ዝግጁ?
Anonymous Poll
96%
ሱብሓነሏሂ ወቢሐምዲሂ✨🤎🍁
89%
ሱብሓነላሂ አል ዐዚም✨🤎🍁
👍15❤10👌1
​«አሁን መስመር ላይ ያለህ/ሽ... ከጀነት ግምጃ ቤቶች (ሀብቶች) አንዱ የሆነውን ዚክር አብረኀኝ በል» ✨🤎
Anonymous Poll
95%
​• ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ 🍂🤎
85%
​• ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ 🍂🤎
👍19❤3